“እንኳን ቤትህ እንዲሸጥ ልረዳህ ሰው እንዳይገዛህ ጥሪ አቀርባለሁ” ለወያኔ ካድሬው የተሰጠ መልስ (አማረ አፈለ ብሻው)

ወያኔዎች የህዝብ ገንዘብ ዘርፈው የገነቡትን ቤትና ንብረት እየሸጡ መሆኑ ተሰማ ፤ ነገሮች እስከሚጠሩ ሕዝቡ ከነዚህ ዘራፊ ባለስልጣኖች ምንም አይነት ንብረት እንዳይገዛ ጥሪ ተደርጓል

በኢትዮጵያዊንቱ ይኮራ የነብረ ወዳጄ በወያኔ ቫይረስ ክርስትና ተነስቶ መጋባባት አቅቶን በስልክ መገናኘት ካቆምን ቆየን።

ዛሬ ስልክ ደውሎ “ወያኔ በመላው ኢትዮጵያ እንዲደፈር ያደረገን ደመቀን እንዴት ይፈታል” ሲለኝ “በድን ብአዴን ተገዶ እንጅ ወዶ አይደለም” ስለው “የጎንደር ሕዝብ ወጥቶ ሲቀበለውና ከቤቱ ሕዶ ሲጠይቀው እነደማየት የሚያናድድን ነገር የለም” አለኝ።

እኔም የጎንደር ሕዝብ ሐምሌ 24 ቀን 2008 ዓ.ም “ጠባችን ከወያኔ ጋር እንጅ ከትግራይ ሕዝብ ጋር አይደለም” ያለውና የኢትዮጵያ ሕዝብ ከግለሰቦች በቀር “ወያኔንና የትግራይን ሕዝብ ለይቶ ያያል” በእናንተ በካድሬዎቹ በኩል ግን እንደ ፍርሃት ቆጠራችሁት ወያኔ ያላችሁን ብቻ ይዛችሁ ሕዝብን ትጠላላችሁ፣ እናንተ ቤትና ንብረት ያካበታችሁ ልብ ግዙ” ስለው ቀዝቀዝ ብሎ “ቤት አዲስ አበባ አለኝ! ልሸጥ ፈልጌአለሁና ኮምሽን እከፍላለሁ እርዳኝ” አለኝ። እንኳን ቤትህ እንዲሸጥ ልረዳህ ሰው እንዳይገዛህ ጥሪ አቀርባለሁ ብየው ስልካችን ዘጋን።

ስለዚህ ቄሮና ፋኖ ዘርማ ነብሮ ወያኔዎችን ካድሬዎቻቸው በተለያዩ ከተማዎች ያሏቸውን ሱቅና ቤት ሕዝብ አንዳይግዛ ቅስቀሳ ልታደርጉ ይግባል።

ውጭ ያሉት ወያኔዎችን ካድሬዎቻቸው ቤታቸውን ለመሸጥ እንደዚህ ካሰቡ አገር ቤት ያሉትማ ጠቅልለዋል ማልት ነው።

በተለይ በአዲስ አበባ ዙሪያ ከ150 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ተፈናቅለው የተሰርውን ቤት የሚገዛ ይዋል ይደር እንጂ የሚጠየቅ ይሆናል።

ሌላው ዛሬ ወያኔ ጥቂት እስረኞችን ፈትቷል። ከቀበሌ ጀምሮ የታሰሩ በተለይ ሽሬ አውራጃ ውስጥ የታሰሩ በርካታ አማራዎችና ወያኔ የፈራቸው ኢትዮጵያውይን የትግራይ ልጆችም ጭምር ሊፈቱ የገባል።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
የካቲት 13 ቀን 2010 ዓ.ም
አማረ አፈለ ብሻው

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.