የበረከት ቅርሻ – ጥቅርሻ (ሥርጉተ ሥላሴ የሳተናው አምደኛ)

ከሥርጉተ – ሥላሴ 08.03.2018 (ከገዳማዊዋ ሐገር – ከሲዊዚዬ።)

„የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኮለኛ፤ እጅግም ክፉ ነው፤ ማንስ ያውቀዋል? እኔ እግዚአብሄር ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱ፤ እንደ ሥራው ፍሬ እሰጥ ዘንድ፤ ልብን እመረምራለሁ፤ ኩላሊትንም እፈትናለሁ።“

(ትንቢተ – ኤርምያስ ምዕራፍ ፲፮ ከቁጥር ፱ – ፲፩)

 • ትርታ በህቅታ እንደ መግቢያ …
በረከት

አገር ከቅል የተሠራ አይደለም። ህይወትም ከቅል የተሰራ አይደለም። መኖርም ከቅል የተሰራ አይደለም። ነፍስም ከቅል የተሠራ አይደለም። የሁሉ ነገር ጠቅላይ ማዕላዊ አዛዡ ህሊናም ከቅል የተሰራ አይደለም። ከተፈጥሮ ፈጣሪው በማይመረመር ርቁቅ ሥልጣነ – ክህሎቱ፤ ኪናዊ – ጥበቡ  የተፈጠሩ ናቸው – ሁሎችም። ኢትዮጵያዊነት የጽናት፤ የፍቅር፤ የሰላም፤ የድል፤ የጸጋ፤ የበረከት፤ የሃይማኖት፤ የጥበብ፤ የተመክሮ፤ የመሆን፤ የትውፊት፤ የወግ፤ የባህል፤ የቃል፤ የታማኝነት፤ የልሳን፤ የቋንቋ፤ የማዬት፤ የማድመጥ፤ የቃና ፤ የመቀበል ፤ የመመራመር፤ የመስጠት፤ የሙሉዑነት፤ የመፈጠሪያነት፤ የአብሮነት፤ የመቻቻል፤ የቅርስ፤ የውበት፤ የአትኩሮት፤ የህብርነት፤ የሥራ፤ የብልህነት፤ የማስተዋል፤ የህግነት፤ የጥቁርነት፤ የሀዘን – ተፍሰሃ ወዘተ ፍልስፍና ነው። ዝልቅ ማንነት ነው ኢትዮጵያዊነት። ይባቤ። ኢትዮጵያዊነት ነው ኢትዮጵያን የሰዬማት፤ የሾማት የሸለማት። ኢትዮጵያዊነት በግርግር አልተፈጠረም። በግርግርም አይጠፋም። የኢትዮጵያዊነት እና የኢትዮጵያ ጠባቂ መላዕክ አላቸው። ተግተው ይሠራሉ። አሁን ምን አለ? መንግሥት የላትም። ግን በጥበቡ አውሎ ያሳድራታል። ከአንድ ቀን የሚያልፍ የዕለት ጉርስ የሌላቸው ሚሊዮኖች ናቸው ግን ቆመው ይሄዳሉ። ምንም የሌላቸውም እንደ ሰማይ ወፎች ጉርስ፤ ከፈን፤ መጠለያ ያለገኙ ሚሊዮኖች ናቸው ግን አሉ። ይህን የሰማይ ጸጋ እዬመራሁት ነው የሚለው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥርዕወ መንግሥት ደግሞ እራሱን መምራት የተሳነው ግዑዝ ነው። የብረት ጤስ ጤዛ።

 • ንጽጽር።

ለወያኔ ሐርነት ሐገር ማለት የንግድ ተቋም ማለት ነው። ማንነትም ሸቀጥ፤ የሚሸጥ የሚለወጥ፤  የሚያተርፍ የሚያከስር። ለዚህ ነው ሐገርን ያህል ነገር በሸቀጥ የንግድ መደበር የሚደረደር የቁስ ዕለታዊ ግብይት አድርጎ የሚያው። አቶ ሞላ አስገዶም ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ የመጀመሪያም የመጨረሻም ዕድላቸው በሚዲያ መስኮት መምጣት ይህው ብቻ ነው። አይደገመም፤ አይሰለስም ብዬ ጽፌ ነበር። ስለምን? ክብሩ ልዕልናው ካለቦታው የተቆለለ ስለነበር። እስኪ 1.70 ሜትር ቁመት ያለውን ሰው 1.20 ሜትር ቁመት ያለውን ሰው ልብስ ይልበስና ይታይ። ወይንም 1.20 ሜትር ቁመት ያለው 1.70 ያለውን ይሞክረው። የወያኔ ሃርነት ትግራይ ኢትዮጵያን የመምራት የህሊና አቅሙ፤ ብስለቱ፤ ጥበቡ፤ ስልቱ፤ ምጣኔው በልክ ያልተሰፋ ሽብሽቦ ወይንም እጀጠባብ ነው ልክ እንደ ስደት ህይወት ወይንም ኑሮ።

 • ስለዝበት።

ለእኔ ዶር ደብረጽዮን ገብረሚኬኤል ማለት የደህሚቱ አቶ ሞላ አስገዶም ማለት ናቸው። ኢትዮጵያ የምትመራው በወያኔ ሃርነት ትግራይ የጭንቅላት ጥብቆ ልክ ነው። በአራት ማዕዘን የጣውላ ሳጥን ነፍስ ታግቶ እንደ ማለት። እማስበው እኔ የደህሚቱ የአቶ ሞላ አስገዶም ጭንቅላት ኢትዮጵያን እንደመራት ነው የተፈረደው። ምንም ልዩነት የላቸውም። ሁለቱም አድገው ያልጨረሱ አይደሉም። ለመብቀል ያልሞከሩ ቆባ ናቸው። ለማደግ ተስፋነት ቀርቶ። stagnant። እትዬ ትግራይም ፈርዶባት ነው ውክል አካሏ መከል ያልጀመረ መንፈስ አንዲወክላት ሲገመደልባት። የነገ መጻኢ ዕድል ወሳኝ ሆኖ በተስፋ ለአደጋ ጊዜ በቅልብ ላይ የሚገኘው ደምሂት ምን ዓይነት ጭንቅላት እንደገነባው፤ እንደመራውም ማዬት ይቻላል አቶ ሞላ ውስጣቸው ሲፈተሽ የህሊና አቅሙ። ያው ተስፈኞች ስላሉ አሁንም። … 27 ዓመት ሙሉ በአማተር የጫካ መከላከያ ሲታመስ ኖረ ሐገራዊው ቷቁሙ መከላከያ፤ አሁንም ይሄ ይጠበቅ ነው የሚለው – የአይዋ ሻብያ ህልመኛ አቶ ቅርሻ በጥቅርሻ።

https://www.youtube.com/watch?v=uESpF8bRdoE

አቶ ሞላ አስገዶም የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ

https://www.youtube.com/watch?v=NgKWbpdbaQc

Debretsion መብራት ሲነሳ ሲንተባተብ ጉደ በሉ

https://www.youtube.com/watch?v=FlIugQCubD0

Debretsion G/michael Opinion regarding EBC service Vs ETV Derg Regime

 • ተናቡር።

የኔ ውድ ቅኖች — ይህንን ካዳመጣችሁ በኋዋላ፤ ካለልኩ የተወጠረ ታንቡርን እሰቡት። ኢትዮጵያን ያህል ሀገር በአቶ ሞላ አስገዶም መንፈስ ተመጥና ስትመራ። ለእኔ ዶር ደብረጽዮን የመጀመሪያ ዕለት መግላጫ ሲሰጡ በአራትዮሹ የኢህአድግ ልሳን አቶ ሞላ አስገዶም ነበር የመጡብኝ። ጫካ ላይ በነበረበት ጊዜ በዓይነ ምድሩ „ማሌሊት ያሽነፋል“ ብሎ ይጽፍ ከነበረው ልቅና ዘንቦ ተባርቆ ልኩን ስለማውቅ ብዙም አልደነቀኝም። መግለጫውን ሳዳምጥ ሄሮድስ መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት ወረዳ መድበዋቸው እንደ ነበር ስምቼ ስለነበር የሟቹን ጠ/ሚር ልካቸውን ማዬት አስችሎኛል። ዕውነት ለመናገር ፍጥረተ ነገራቸው ለመሪነት ቀለመ-ቢስ ነው። ጸጋውም የላቸውም። ልኩ ካለልኩ ስለሆነ ከተፈለገው የነጥብ ጣሪያ አልደረሰም፤ ቢንጠራራም። ሞቱ ከዚህ ላይ ነው። የወያኔ ሃርነት ትግራይ ቁመናው የሚሠፈርበት ልኬታው በዚህ ሜትር ልክ ነው። ትግራይም ብሄራዊ መሪነቷ ልዕልና የምትመዘንበት በዚኸው ጭንቅላት ነው። መመካት በልክ አያያዝ መልካም ነገር ቢሆንም፤ የምትመካበት ነገር ግን በምንም ሊሆን አይገባም። ብናኝ ሰብዕና ቀርቶ እንደ አንድ የሥራ የክፍል ሃላፊ ለማዬት እጅግ ከባድ ነው። ይህ ወና መንፈስ ነው ሰሞኑን ለእጩነት የቀረበው። ለዛውም ጥምር ዕንቁ የሁለመና ውቅያኖስ የሆነችን ገናና ሐገር ውክልና ለመወስድ። የዓለም ጥቁሮች አብነት ናት ኢትዮጵያ – የመንፈስ ብቸኛ ጥጋቸው፤ የአፍሪካ ቀንዲል ናት ኢትዮጵያ – የአብነት አንባቸው። ስንት ምርኩዝ ሊዘጋጅ ይሆን? ሃሳቡን እራሱ ለማሰብ ምጥ ነው። ካለልኩ የተሳፍ ግብግብ። ለድርጅቱም ውርዴት ነው። ለታሪክም ውርዴ!

 • የግራጫ ጨለማ ወባራ!

የብቃቱን ነገር ለጥቁሩ ካባ ባለ ዶክትሬትነት የግዢና የሽያጭ ጉልት ትተን በጽሞና ቢሰላ፤ ከልብ ተሁኖ ቢደመጥ የግራጫ ጨለማ አልጋ ወራሽ የሆኑት አቶ በረከት ስምዖን ያሰሉት መንገድ እኮ የኢትዮጵያን ማንነት እጅግ ረግረግ ላይ የሚከት የቁርሾ አባዜ ነው። አቶ ደመቀ መኮነን ሆኑ ዶር. ገብረጽዮን ገብረሚኬኤል በስጋ ፈቃድ እጅግ የረከሰ ሰብዕና ያላቸው ናቸው። ግልሙትናው ያ ቆሻሻ ታሪክን ከነግማቱ ተሸክሞ እራስንም ሐገርንም ለማዋረድ መሰናዳት ህሊና የት ነህ ያስብላል? ግን ህሊና አለን? ከተገኘው ጋር፤ ከሆነው ጋር በምንትሶ ምንትስ ቅብጥርስ ተሁኖ? ህም!

በሌላ በኩል አቶ ሽፈራው ሽጉጤን አክሎ ዶር. ገብረጽዮን ገብረሚኬኤል በአማራ ዘር ጥፋት ተከሳሽ ሲሆኑ ቀን የሚጠብቅ የወንጀል የህሊና እስረኛ ናቸው። ደመነፍሱን ነው የሚወዛወዘው የንግሥና ሥርዓቱ ግጥግጥም። የሥነ – ልቦና አቅም ክፍተት አለበት። የራስ መተማመን ፍቀት አለበት። አንዳቸውም ዕዱሉን አግኝተው ውጪ ከዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ጋር የመሰብሰብ ሁኔታ ቢገጥማቸው የመሳቂያ መደበር ብቻ ሳይሆን የተኮፈሱበት ፉኛ ይፈነዳል። ምን አለን ብለው ይሆን ለዚህ ቦታ የሚሰናዱት? ከሰብዕና ሰብዕና፤ ከብቃት ብቃት፤ ከሰብዕዊነት ሰብዕዊነት ምኑ? የሌላቸውን ሊያመጡት ቢያምጡ ከዬት ይመጣል? የህሊና ጥሪት ፍልሰቱ ምክንቱ እኮ የአደባባይ ሚስጢር ነው። የሙሉ ስብዕና እርሾ እውቀት እና ጥበብ ያሰፈልጋል ለዬትኛውም የሃላፊነት ደረጃ። ለጭነቅት በሽታ ለመዳረግ ካልሆነ በስተቀር ይህ ቦታ ለእነሱ ሰማይን መኖሬያ ቤት ሰርቶ እንደ መቀመጥ ማለም ነው። ራሳቸውን ለመግለጽ አንዲት የምትደመጥ ትንሽ ነፍስ ከሚባለው ረቂቅ መንፈስ ጋር በጥጉ ሊቀመጥ የማይችል ጠረነቢስ ኳኳቴ ተሸክሞ ለዚህ ውድድር አለሁ እኔም ማለት ራስን አለመግዛት ነው – ለእኔ። መሪ እኮ ሊደመጥ የሚችለው በወንበሩ ሳይሆን፤ በውስጡ ባለው የንጥረ ነገር ጥራት እና ብቃት ልክ ነው። አልችለውም እኮ ይባላል። ምን ነውር አለው። „ልክን ማወቅ ከልክ“ ያደርሳል ይላሉ ጎንደሬዎች። ክብር ነው። በስንት ባላ ድጋፍ ባረገረገ አዬር ይሆን ህልሙ? ይሄ ለታሪክ ልግጫና ለትውልድ ርግጫ የታቀደ ነው። ገበርዲን አይችለው የለ – ሥጋን፤ ከረባትም አይችለው የለ። ይህን ተሸከም የተባለው የሰውነት ክፍል ሁሉ ጥሎበት። ይህም ሆኖ ለጉድነቱ በገመና ድውለት ለዓለም አደባባይ መሰናዳቱ ውልቅልቅን የሚያወጣ ስለመሆኑ ያሰቡበት አይመስልም። ክስምት!

ልብስ እኮ ገመናን ቢሸፍን እንጂ የግሎባልን ዲጅታል ፈተናን አያሳልፍም፤ „ነፍስ ካለ መነገዳገድ አይቀርም“  ሆኖ ነው እንጂ ሸሽጉኝ፤ ደብቁኝ የሚያሰኝ ጉድ እና ወንጀል ተሸክሞ አደባባይ ላይ መሰለፍ መካሪ የለንም ያሰኛል። ሐገር መምራት እኮ ቃታ መሳብ ሳይሆን ህሊናን መሰራት ነው። ይደገም የሰው ህሊናን መሥራት፤ መምራት ነው። ራሱ ያለተሰራለት ዕብን እንዴት የተሰራለትን ህሊና አዳብሮ መምራት ይቻለዋል? የሆነ ሆኖ ከሌለ ደግሞ ያልነበረው በአንድ ቀን አይፈጠርም። ጸጋም የሚባል ነገር አለ። ክህሎትም የሚባል ሌላ ኪናዊ ውጣ ውረድ አለ። ብን ብሎ የደረቀ ጉድ። ሽሁራር በበላው የሶሻሊዝም ቅሪት አካል በአቶ በረከት እንዳይባል እሳቸውንም ዘመን ጥሏቸዋል ከነዝገታቸው፤ ከነዝክንትላቸው ንቅዘት ሆነው ቀርተዋል። እኒህ ሰው በውርዘት የሚያንጎላቹበት ቀን ጠባቂ ናቸው።

 • የግልሙትና ቤት ባለመሰናዶ እጩዎች።

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከምትታወቅባቸው የፍጽምና ሞራላዊ መለያዎች ሁሉ እጅግ የከበረ ነው ይሄ ሥጋን የመግዛት፤ ከእንሳሳዊ ዓለም መለየት። የሚወዳደሩት እኮ ለከብት ተራ ገብያ አይደለም። ሰብዕናው ከከብትም ያለነሰ ነውና። ስሜትና መቋጣጠር አቅቶ የትም ቦታ የሚጋደም ጸያፍ ስብዕና ሊታፈርበት ይገባል። ለዛውም በብዙ ህብር ለተቀመረ ረቂቅ ማንነት ነው – ለኢትዮጵያዊነት። ጥፍጥፍ ይባል፤ ልሙጥ ይባል፤ ድንቡልቡል ይባል አይታወቅም – ልካቸው። ሥም የለሽ ከረባት እና ገበርዲን ከንቱነት የዳነሰበት ተፈጥሮ ብለው ይሻል ይመስለኛል። ዕውነትም እንደሚባለው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ መንፈስ የሚመራው የዲያቢሎስ መንፈስ ነው። ፈርኃ እግዚአብሄር ክው ብሎ የነጠፈበት። ውርዴት የተጠለፈበት።

የሴራው ቅርሻ ጥቅርሻ ትርፋቸው የኢትዮጵያዊነት ገናናነትን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ማሸማቀቅ፤ ማቅ ማልበስ፤ አፈር ማስጋጥ ነው። ይሄ እንደ ዜጋ ውስጥን፤ ክብርን የሚመረምር እና የሚፈትን ነው። ማህጸንንም በሃዘን ይፈልጣል። ስሜትን ይሰብራል። አቶ ደመቀ መኮነን ታዳጊ ወጣት አስገድደው ደፈረው ከዛው ገመናቸው ጋር ከትመዋል – ከነነውራቸው፤ አሁን ደግሞ ዓይናቸውን በጥሬጨው አጥበው ቤተ-መንግሥትን ቋምጠውለታል። እሳቸው ዕድሉ ባይሳካላቸው ሌላ መሰል ተተኪ ተዘጋጅቶላቸዋል። የጉግልን የግብረ ሰዶም ኪዮክስ ሲያሳድዱ ውለው የሚያድሩት ዶር. ደብረጽዮን ገ/ሚኬኤልን። መሸታ ቤቱ እስከ አልጋው፣ እስከ አንጣፊው፣ እስከ ባልኮኒው፣ እስከ አሳላፊው ዋንጫው 4 ኪሎ ላይ አና ሊል ነው። ውርዴት!

እራሱ በዚህ መንፈስ ውስጥ ኢትዮጵያ ስትታሰብ ይቀፋል፤ ያንገሸግሻል፤ ምጥ ያስይዛል። አዎን! ጥሪው የግራጫው ጨለማ ተልዕኮ ለዚህ ነው። ኢትዮጵያን መልምሎ ድራሿን ማጥፋት። ገዳይነቱ፤ ፋሽስትነቱን አቅደው እዬከወኑት ነው አንጡራ ባላንጣዋ የቅርሻ ጥቅርሻ አቶ በረከት ስምኦን። ይህን አረንቋዊ መከራ ተሸከሚ ተብላለች – ኢትዮጵያ። መከረኛ! የልጇ የጥቁር ለባሿ የጎንደር ላይበቃ። የገማናው ክርፋት አፍሪካን እንደ አህጉርም ያጥነገንጋል – ነገንም። የጥቁር ተምሳሌትም ስለሆነች በዓለም ዙሪያ ትምክህት ያላቸውን ወገኖቻችን ሁሉ መንፈስ እንኩቶ ያደርጋል – ከዛሬ ጀምሮ። ይህ ታቅዶ፤ ተሰልቶ ትናንት ከተፈጠሩትም ከእነ ኤርትራ፤ ከእነ ደቡብ ሱዳን በታች እንድትሆን በተንኮል አለባሶ የተሰፋ ሽርብ ሴራ ነው።

በማስተዋል ሆኖ ማድመጥን ለፈቀደ ኢትዮጵያዊነት „ምነው ፈጣሪ ኢትዮጵያን ረሳሃት“ ያሰኘዋል። ከአንዱ ገዳይ ወደ ሌላ፤ ከአንዱ ጸያፍ ሴሰኛ ወደ ሌላ። ሌትና ቀን ኢንተርኔት ላይ የሥጋ ፈቃድ ሱቅ በደረቴ ላይ ተተክሎ የሚውል ነፍስ፤ በዬሄደበት ሁሉ የሥጋ ገብያ ሲቃርም የሚገኘው ጥንዙል ነፍስ ሃፍረቱ የእሱ ብቻ ሳይሆን የሀገርም፤ የታሪክም ነው። የቅርስም የውርስም ነው። የገመናው ጥንባት አያስቀርብም – ይገፈትራል። እንዲህ ባለ እጅግ በወረደ ሰብዕና የዛገጠ ታሪክ ይዞ በዓለም አደባባይ ሲወጣ ለዛውም የኢትዮጵያ ውክል አካል ሆኖ ምነው ባልተፈጠርኩ፤ ጭንጋፍ ሆኜ ቀርቼ በነበረ ያሰኛል። ረመጡ ያርመጠምጣል። ማህጸንን በሰቀቀን ይጎምዳል።

ይህን እጅግ የደመነ ከእንሳሳም ያነሰ ሰብዕና አሽኮኮ ተደርጎ የአደባባይ ሰው ለመሆን ማሰቡ በራሱ ግብዝነት ነው። ይሄ የዝርፊያ፤ የስረቆት፤ የቅጥፈት ወዘተ ነውር ተከድኖም አይቻል። ቀዳዳው ብዙ ነው እና። ይህ እንሰሳዊ ሰብዕና የሚያሸማቅቅ እንጂ የሚያኮራ ሊሆን ከቶውንም አይገባውም። ስለምን? እኛ ከሊስት ወጣንም የሚያሰኝም አይደለም። የሚሰቀጥጥ እንጂ። ጎሽ¡ አበጀህ¡ የሚያሰኝ ሊሆን አይገባም፤ ተው እባክህ! ከነገመናህ ተከወንልን፤ ተሸሸግልን የሚያስኝ በሆነ ነበር ህሊና ቢኖር። ከሁሉም የሥነ – ምግባር ዓይነት ከእንሰሳ ያልተለዬ ሰብዕና እንኳንስ ለሀገር መሪነት ለጉርብትናም አይጣል ነው። እኛ ስናድግ ብቻ ሳይሆን ዛሬም ሙሉ ዕድሜ ላይ ሆነን መንገድ ላይ፤ ፊልም ላይ ተፈጥሯዊ የሆኑ ነገሮችን ማዬትን አንፈቅድም። የተሠራላቸው ቦታ እና የጊዜ ክፍል አለው። ልዩ ነው ኢትዮጵያዊነት። አደባባይ የማይወጡ ብዙ በፈቃዳችን በተዕቅቦ ያሉ የውበት ሥነ- ህይወት ህብራዊነቱ ረቂቅ ነው ኢትዮጵያዊነት። ሰው እንኳን ባይኖር ፈጣሪ/ አላህ ያዬናልም አለ።

 • አቅም።

አቶ ደመቀ መኮነን የኢህአዴግ መግለጫ ሥሙ ተብለን ሲሰዬሙ በቃ እኔ እንደ ሐውልት ነበር ያዬኋዋቸው። ምኑ ይደመጣል። ድርቆሽ የሆነ ጉድ። ሰንክሳር የሆነ – ጣፊያ። አዬ ያቺ ያልታደለች ሐገር እንዴት እና እንዴት ሆና ይሆን ይሄን ሁሉ ዘመን የተሻገረችው? 27 ዓመት እጅግ ብዙ እኮ ነው። ይህ የተሰለሰለ የአቅም ኪሳራ ተሸክሞ ለጠ/ሚር ደረጃ ውድድር? ለዛውም ዛሬ? እራስ እግሩ ቋያ በሆነበት፤ ስንት የዘመናት ፈተናዎች፤ ታምቀው የኖሩ ችግሮች አፍጠው በመጡበት ወቅት። ዕብንነትን ተሸክሞ ከንቱነትን ለማምረት ይሆን? አይታወቅም። ሥም – የለሽ ጠቀራ በቅርሻ ወበራ።

ወደ ዶር ደብረጽዮን ገብረሚኬኤል ሲመጣ ስም አይችለው የለ ያሰኛል። የንግግራቸው ምት ቁጣው እዬጨመረ ሲመጣ ተቀብሮ የኖረ አውሪያዊ የጭካኔው ቃናም አብሮ ነበር የመጣው። „እንጨርሳቸዋልን፤ እንፈጃቸዋልን እናሳያቸዋልን ድድድድድ።“ በዛ ላይ ቀደም ብዬ እንዳነሳሁት ምናቸውም የመሪነት ሰብዕና የለውም። ፍቅፍቅ። አጭርም ቢኮን፤ ቀጭንም ቢኮን የመሪነት ግርማ ሞገስ አለ። እንዲያውም ብዙ ታዋቂ ሰዎች አጭር እና ቀጫጫ ናቸው። አሁን ግርማዊ ቀዳማዊ ሃይለ ሥላሴ – ጃንሆይ አጭርና ቀጫጫ ነበሩ፤ ግን ግርማቸው ሞገሳቸው ከሰውነታቸው በላይ ግዙፍ እና ተፈሪ ነው። የእኒህ እኮ ለእኔ ቢጤ ተራ ወንበርም በፍጹም ሁኔታ ቅብዕ የሌለው፤ ክው ብሎ የደረቀ፤ ፍልስ የሆነ አመዳም ነገር ነው። … አልተሰጣቸውም። መሪ ለመሆን መሪ ሊያደርግ የሚችል ተፈጥሯዊ መሃባ አለ፤ ሥህን አለ፤ ሥነ – ደም አለ። ልዩ የሆነ የምትመሰጥበት ጣዕም አለ። ገና አንደበቱ ሲል ህሊናህን ከፍተህ የስንቅ ጎተራህን ቧ አድርገህ ሙላልኝ ብለህ ሰምተህ – አድምጠህ – የማትጠግበው፤ የምትጠብቀው ባለ ጸጋ ሰብል አለ። ልቅላቂው የላቸውም። ቀትረ ቀላል ይሉታ እንዲህ ያለውን ነፍስ ብልሆቹ። አቅላቸው ሆነ መንፈሳቸውም የተላጠ ነው ወይንም የተጋጋጠ። ፍርጃ!

 • ባለገጀራው የጠ/ሚር እጩ፤

ሌላው የሰብዕ ፍጡር አንጡራ ጠላት የሆኑት፤ በጥላቻ መንፈስ የሰመጡት አቶ ሽፈራው ሽጉጤም ቢሆኑ በወንጀለኝነት የሚጠዬቁበት ሁኔታ ጊዜ ቢጠበቅለትም፤ ቢያንስ ወንጀለኛን ለዚህ ታላቅ ቦታ ማጨት ከንቀት በላይ ነው። ሥነ – ልቦናው አይመጥንም። ሥነ – ልቦናው ደንጋጣ እና ባናኝ ነው። ለነገሩ ኢትዮጵያ እኮ ለቅጣቷ ነው እንዲህ ያለ የመከራ ዘመን ትገፋ ዘንድ ወያኔ ሃርነት ትግራይ የሚባል ጨፋጭፊ፤ ወራሪ እና ዘራፊ የተፈጠረባት፤ አቶ በረከት ስምዖን የሚባል የሴራ ቸረቸራ ጥቅርሻ የተጫነባት። ከቶ አቶ በረከት ስምዖን ቢያልፉ መቃብሩ በተለመደው ወይንስ ሬሳቸውን በታሪክ እንደሰማናው እንጦረጦስ ሲወርድ ይታይ ይሆን? የጎንደር የመከራ ቀንበር፤ የዕልቂትና የጉብጠት ኑሮ አስፈጻሚው መቼም በተለመደው አኳኋን ቀብራቸው አይጠናቀቅም? አንድ ታምር አርባ አራቱ ይፈጥር ይሆናል።

 • ገጀራ እና የበቀል ጥማቱ …

ከእንግዲህ ግን ገጀራው ለአማራ ብቻ አይሆንም። ወይንም የጎንደርን አከርካሪ ለማንከት ብቻ አይሆንም። ኦሮሞም የተሰላለት ሴራ አለ። ባለፈውም አይተናል ሰምተናል። በ600, 000 ወገኖቻችን የደረሰው የመፈናቀል ሰቆቃው፤ መቼስ ሞቱን ስለለመድነው እንጂ 600 ወጥተው የቀሩት የሬቻ ሰምዕታትም አሉ። አሁን ግን ከዛም የከፋ፤ በተለየ ስልትና የዕዝ ሰንሰለት የሚከወን፤ ተመስጥሮ የተያዘ አድማ አዲሱ የኤርትራ ማንፌስቶ አይማረኝ ላልምርህ ይሆናል። ኤርትራ ለአንዲትም ሰከንድ ለኦህዲድ ወጣት የለወጥ መብራቶች ከሴራ ትታቀባለች ተብሎ አይታሰብም። እራሳች ናቸው በበላይነት የሚመሩት። ሁለመናዋን ማጣቷ ስለሆነ የሞት የሽረቱ ትግል በጣምራ ኦህዲድ ላይ ታልሟል። ሰራዊትም አሰልፋለች። ዛሬ የግድ ኢትዮጵያ መሄድ አያስፈልግም። ምርኮኛውን መንፈስ በዶላሩ ፈጥሮ የልቡን ያሳካለታል – የኤርትራ መንግሥት። አንደበቱን ስሎ በተለያዬ ስልትና መንገድ የትውልድን ብክነት በመሪነት ያስኬደዋል።

ኦህዲድ በማንኛውም ሰዓትና ሁኔታ የቀጥታም ባይሆን በምግብ ብክለት ከሚደርስው ማንኛውም ጥቃት ራሱን መጠበቅ ይኖርበታል። መዘናጋት በፍጹም የለበትም። በጋራ እና በወል በሚደረጉ የሥራ ግዴታዎችም ላይ ይሄ የቡና የሻይ እረፍት፤ የወል የማዕድ ቤተኝነቱን በአስቸኳይ ሊነቃበት ይገባል። ማቆምም አለበት። አዘናግተው መበቀል ሻብያና ወያኔ የተመረቁበት መደበኛ የተግባር መርሃቸው ነው። በታሸገ ውሃ ውስጥ ሳይቀር ብክለቱ አይቀሬ ነው። ደም የቋጠረው የሻብያ ጥቃት ከዚህ የሴራ ድር ይታቀባል ተብሎ አይታሰብም። ኦህዲድ ዛሬ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ብቻ ሳይሆን ኤርትራ የተሰናዳችበት ቀዝቃዛ ጦርነት ላይ መሆኑን ልብ ሊለው ይገባል። ቅኖቹ ኢትዮጵውያን ለተስፋቸው ቀን በተጠንቀቅ ቁመው የሚችሉትን ሁሉ ማድረግ ይገባቸዋል። የተስፋ መንፈስ ናፍቆተኝነት፤ እውነተኝነት የሚረጋግጠው ሰበብ አስባብን አራግፎ ከእርበኞቹ ጎን ለመሰለፍ በመፍጠን መሆን አለባቸው። ይህ ዕድል የሰማይ ግርማ ሞገስ ነው። የበቃችሁ ቸር ዜና ደወል ነው። ዘመናይነቱም ይሁን ቅልጣኑንም መቀነስ ያስፈልጋል።

አሁን ኦህዲድ የሰላ የጥቃት ዘመቻው በጣምራ ተከፍቶበታል። አሁን የሚዶለተው ሁሉ ይሄው ነው ጠልፎ ለመጣል። አቅም ያነሰው ሁሉ እልሁን የሚወጣው በዚህ መሥመር ብቻ ነው። እንዲህ ኢትዮጵያ የልቤ የምትለው ብሄራዊ ጀግና፤ የአጥቢያ ኮከብ ከኦሮምያ ይወጣል ብሎ አልሞት አያውቅም አይዋ ኤርትራ። ናዳ ነው ለገደል ማሚቶ ህልመኛው ለኤርትራ መንግሥት ካቢኔ። ቀን ከሌት መላ ህሊናው ኦህዲድ ላይ ነው – የኤርትራ የስለላ መረብ። ስለምን? እንኳንስ ለኢህአዴግ ለራሷ ለኢትጵያ ምዕራፍ ከፋች የጸሐይ ዋዜማ ስለሆነ። ኢትዮጵያ በተሰናዳ፤ በታቀደ፤ በወጉ በተደራጀ አቅም እዬተመራች የአፍሪካ መሪ ስትሆን ከማዬት ሞት በስንት ጣዕሙ ነው ለኤርትራው ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ። የመንፈስ የቀብር ሰሞናታቸው ነው። ቢሆንለትማ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ሥር ወድቃ ወድቅድቅ ብላ ማዬት ነበር። ካልሆነም በእርስ በርስ የበቀል ማወራራጃ መሳቂያና መዳለቂያ እንድትሆን ነበር ምኞቱ። ድብልቅልቁ ወጥቶ፤ መሪ አልቦሹን ታንኳ እኔ በሰላም አስከባሪ ስም ለማለት ነበር ምኞቱ። በእሱው ኮማንድ ፖስት ሥር፤ የጦር አዝማችነት፤ መሪነት፤ የጸጥታ አስከባሪነት፤ የሰላም ተልዕኮ አጋፋሪነት ባለቀይ ምንጣፍ እሆናለሁ ብሎ ኤርትራ ሲያልም ኦህዲድ ወሽመጡን ቆረጠው። ህልሙ ወገቡ ከሁለት ተከፈለ። ሰቁ ተጎመደ። ስለዚህ ከቆዳ መልስ መስሎ የተቀላቀለውን ሰላዩን ያላ የሌለ ሃይሉን ተጠቅሞ ድፍርስ ያለች፤ የጎሽች ኢትዮጵያ፤ የደማነባት ኢትዮጵያ ትፈጠር ዘንድ ተግቶ እዬሠራበት ነው። የህዝቡ ብስጭት ጎልቶ አንድ ነገር ቢፈጠር የቆሼው ህልም ዓላማ ግብ መታ ነበር።

እሳት ነው የሚጠብቀው የኤርትራ መንግስት። ሌሎቹም አቅጣጫ የለሹ ድፍን ስሜትና ፍላጎት ይሄው ነው ምኞታቸው። ብጥብጡ መሪ አልባ ሲሆን ኤርትራ ገላጋይ ሆና ኢትዮጵያን የቅኝ ግዛት ለማድረግ ነው ህልሙ። በኢትዮጵውያን ደም እና አጥንት የኤርትራ የህልም እንጀራ ሊጎዘጎዝ ተቋምጧል። ለዚህም ነው ያልሆኑ መጠራቅቆች፤ ጊዜያቸውን ያልጠበቁ መጠይቆች፤ እጅግ የዘመኑ ቅድመ ሁኔታዎች ለኦህዲድ እዬቀረበለት ያለው። በዚህ ውጥረት ሃሳባቸውን በመክፈል፤ የውስጥ ሰላማቸውን በማባከን መንገድ ከፋች የሆኑ በሮች ክርችም ብለው እንዲዘጉ ግራ እዬመከሩ ግራ መንገድ እንዲመርጥ በአማላጅነት እዬኳተኑ ያሉት ግራጫው ጨላማ አቶ በረከት ስምዖን። የሞት የሽረቱ ትግል 4ኪሎን መስጥሮ ያለመው ሁሉ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ጦሩን ሰብቋል፤ ኦህዲድ የደከመበትንም መንፈስ ክፍተት ለመፍጠር በትጋት እዬተሰራበት ነው። ከዚህ ላይ ነው የብልህነት ወንፊቱም፤ ማንዘርዘሪያውም፤ ማጣሪያውም፤ ልኬታው የሚታወቀው። የማን ምንነቱ፤ የፖለቲካ ብስለቱ፤ የህሊና ክህሎታዊነቱ መስፈርቱ ይሄው ነው። ይንዘረዘራል፤ ይበጠራል፤ ይነፋል – ሁሉም በልኩ በሚያዋጣው ልክ።

 • ምን ይደርግ?

ወያኔ ሃርነት ትግራይ ከሳጥኑ ወጥቶ አይኑን ከፍቶ ያለችውን እንጥፍጣፊ እድል መጠቀም ይኖርበታል። ኢሠፓ በታሪክ ዘር አልባ ባክኖ የቀረ ድርጅት ነው። አቅሙ እንዲህ በጠላት እንደሚብጠለጠለው አይደለም። አቅሙ ልኩ ወደር አልነበረው። የተዘለሉ ነገሮች ጊዜ፣ ቦታ፣ እና ሁኔታን ማድመጥ ባለመቻሉ ነው አቅሙ መቅኖ አጥቶ፤ ታሪክም ወራሽም አልባ ብክን ብሎ ሾልኮ የቀረው። ጥሩ ነገር ኢሠፓ የዘረፋ፤ የወረራ ማነቆ ስላልነበረበት ጓዘ ቀላል ስለሆነ፤ ታሪክ ሲክደው በቀስታ ሹልክ አለ። ማቄን ጨርቄን አላለም። ሰነዱ ላይ የስም ዝርዝር በስተቀር ምንም ሊገኝ አልቻለም። ያ ሰንድ ደግሞ በአንድ ክብሪት እራት ማደረግ ቀላል ነበር ለጠላቱ ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ሠራዊት።

የወያኔ ሃርነት ትግራይ እና ተባባሪዎች ግን ጉድ አለባቸው። የተንሰራፋ፤ መሬት የያዘ፤ ከተጠያቂነት የማያስመልጥ፤ የተያያዘ በጥቅም የተሳሰረ፤ በዘር ሐረግ የተቆላለፈ የገመና ድፎ አለባቸው። ጨርቄን ማቄን ሳይል ሹልክ ማለት አይችልም ወያኔ ሃርነት ትግራይ – ተባባሪ ድርጅቶቹም። በተገኘው አጋጣሚ እና ሁኔታ መሠረቱን በሁሉም ቦታ ተክሏል። ያ ሁሉ ነፍስ አንድ ነገር ቢፈጠር ዋቢ አልባ ይሆናል። አብሶ ህጻናት፤ ነፍሰ ጡር ሴቶች፤ አዛውንታት፤ ህመምተኞች፤ አካላቸውን ማዘዝ የማይችሉ የአካል ጉዳተኞች፤ ተማሪዎች እንደ ወጡ መቅረት ይመጣል። ራሱን መከላከል የማይችል ለሌላው አጥር እና ቅጥር ሊሆን አይችልም – በጭንቅ ወቅት። ቀጣዩም ምን ይምጣ? ምን ይሁን አይታወቅም። ግራኝዝም፤ ጉዲቲዝም፤ ስታሊንዝም፤ ሻብያዊዝም … ሁሉም ክፍት ነው …

ስለሆነም ትዕቢተኛው ወያኔ እሱም ሆነ „ጌታዋን የተማመነች በቅሎ“ አድርጎ አሳብጦ ያሳደጋቸው መንፈሶችን ለማዳን ከተንጠራራበት ከፍታ ዝቅታን መምረጥ ግድ ይለዋል። ለራሱ ቢል፤ እሳት ሲነድ የሚመርጣው የለም። አሁን ያለው ጠበንጃ ጠባቂ መሆኑ ቀርቶ ራሱን ነጻ የሚያወጣ የነፃነት አርበኛ ነው የሚሆነው። ከራስ በላይ ነፋስ የለም እና። ወስጡም የጤሰ ነው። አድሎው፤ ግለቱ፤ ባይታወርነቱ፤ ጸያፍፉ ስድብ፤ ቁም ተሰቀል፤ ቁጭ ብድግ በልነቱ፤ ቁስለቱ ስንቱ ተዘርዝሮ ያልቃል። ያ ሁሉ ሂሳብ መወራራጃው አጭር ይሆናል።

ቂም ያረገዘው ብስጩው አዬርም እንደ ሰላማዊው ሽግግር ሩህሩህ አይሆንም። በፍጹም። የተገፋ ህዝብ ሲገነፍል ህግ አይሰራም። ሃይማኖትን አይሰራም። ጆሮ ይቀረቀራል። ብስጭት ሲያል „ሰው“ የሚያሰኘው መንፈስ ይለወጣል። „ሰው“ የሚያስፈራ የጫካ አውሬ ሊሆን ይችላል። ጸሐይ ራሷ አስፈሪ ትሆናለች። ስለዚህም ለራሱ ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ይህቺ ወቅት ሳትዘገይ፤ ሳታመልጥም ለሚሊዮኖች ለራሱ ደሞች ሲል፤ ለነገም ለሚፈጠሩትም ካለ እዳቸው ዕዳ ተሻካሚ ስለሚሆኑት የትግራይ ቀጣይ ትውልድ አባልተኞችም ሲል በክብር ቀድሞ ለባለ አቅሙ ከላምንም ግርግር ማስረከብ ይኖርበታል። እንደ አቅሙና እንደ ወርዱ በተገባው መጠን ልክ ለመኖርም ደፍሮ መወሰን እና ክለቡ መቁረጥም ይኖርበታል። ቀኑ አልቋል። የአንዲት ነፍስ ሃብት የለውም። ጥላው እራሱ መርዛም ነው። ኮቴው ጎምዛዛ ነው። አሳንጋላ!

 • የተገፋው „ዘመን“

የተገፋው „ዘመን“ እራሱን ለመግለጽ ቃል የለውም። ማጣት ይኖራል ብዙ ነገር፤ ግን ትውልድ ማትረፍ ከትርፍ በላይ ነው። አቶ ለማ መግርሳ እኮ አቅማቸው ላንሳ ሳልል እሱን ልተወው ብል በጭልፋ ስለማይችለው ብዕሬ፤ ግርማቸው፤ ለዛቸው፤ ርህርህናቸው፤ የውስጥ ጸጥታቸው አንድ ትውልድ ይገነባል፤ ግን ያደረጉት ነገር እግዚአብሄር ወርዶ የማዬት ያህል ነው። ከዚህ በላይ ታላቅ ተቋም ተምሳሌነትም የለም። ሊዚህ ትውልድ ራሱን እንዲሰራበት ህሊናን ያህል ዕንቁ የሸለሙ የሰማይ የምህርት አደባባይ ናቸው። ሥህነ – ውሳኔያቸው ከትንግርት በላይ ነው። በምን ቀን እንዴት አንደተፈጠሩ ራሱን የቻለ መጸሐፍ ብቻ ሳይሆን ሥነ – መዘክር ማዘጋጀትን ይጠይቃል። እንደ ዋልድባ አብረንታት ገዳም ትውፊት ቢሆን ታቦት ያስቀርጻል። ለዘመኑ፤ ለምዕቱ፤ ለሃይማኖቱ፤ ለተቋማቱ ሁሉ እንደ አንድ የትምህርት ሳብጀክት የሚማሩት የእዮር አብነት ነው። ይህ ቅዱስ መንፈስ በ100 ዓመትም አይታሰብም።

ለራሱ ለወያኔም ቢሆን እንዲድን የታለኩለት የምህረት ቃልኪዳን ናቸው። ከዚህም በላይ ያ ምንም ያልነበረው፤ ባዶ ርብራብ ላይ ተኮፍሶ ግንባሬ ሲል የነበረው የህሊና አቅሙ ጥሎት የሸፈተበት ኢህዴግም ቢሆን አውጥቶታል። አትርፎታል። ለመሆኑ እናንተን የመፍትሄ አካል ቀርቶ ፍርፋሬ አልባ ሽው እንድትሉ ነበር ስንታገላችሁ እኛ የኖርነው። ዛሬ ግን የለውጥ ሐዋርያ ሆኖ የወጣው ኦህዲድ የመንፈስ ዲታ ሆኗል። የገዱ መንፈስም አብሮት የቆመ የራሱ የሆነ የጸና መንፈስ አለው። ዕድል እኮ ነው። ልዩ እድል። አሁን እናንተን ቆዩልን ልትባሉ? ይህን ያደረገው ጸጋ ተመንፈስ ነው። ፈጣሪም ያልተዋት ሐገር ኢትዮጵያ ስለሆነች እንጂ እኛ እስከ ቅል ቋንቋራችሁ ከሥራችሁ እንድትነቀሉ ነበር ተገድሏችን። ጸሎታችን።

ስለዚህ ጊዜና ቦታ ወሳኝ ነገሮች ናቸውና የቀለጠ ወርቅ ይፈሳል፤ የፈሰሰ አይታፈስም። ይሄን ሁሉ በመሳሪያ ተመክቶ ከመወራጨት፤ ይህን የችግር ዘመን በበቃ አዲስ የለወጥ መንፈስና አቅም፤ በጠራ መስምር በጥሞና ሊመራ የሚችል ሙሉ ክህሎትና ቁመና ላለው አካል ለኦህዲድ መስጠት ግድ ይላል። ደግሞስ የእናንተው እኮ ነው – ማህበርተኛችሁ። እንዲያውም ይህን ያህል ተቀባይነት ሲያገኝ ደስ ሊል፤ ኩራታችን ተብሎ ሊከበር ይገባል። መወድስም ሊደረግለት፤ ሽልማትም ሊሰናዳለት ይገባል። ኢህድግ እኮ እንደ ኢሠፓ ዘርአልባ መሆን የነበረበት ድርጅት ነው። ኢሠፓ እኮ የነበረው ድርጅታዊ አቅም ጦርነቱ እርስ በእርስ ባይሆን ኖሮ „ዘመን“ ነበር። እናንተንም እኮ ለዚህ አቅም ያበቃችሁ የኢሠፓ የተደራጀ የህሊና ጥሪት እረሾ እንጂ ጫካ ላይ እያላችሁ እናውቃችሁአለን። ምን ነበራችሁ? ቀላሃ ብቻ። በመጣችሁበት ተምልሳችሁ የተነሳችሁበትን ቦታ እንኳን የማወቅ ብልሃት ያልነበራችሁ ምንም። ምን ነበራችሁ? በቆይታችሁስ ምንስ መልካም ነገር አላችሁ? ለዛውም ለ21ኛው ምዕተ ዓመት የሚመጥን ምን አቅም፤ ምን ጸጋ እና በረከት? ከሻገተው የሶሻሊዝም ለዛውም አልባንያዊ፤ እንደገናም ጎሳዊ ነው። በአንድ አናሳ ቡድን ብቻ የምትታመስ ሐገር ነው ያለችው። ውልቅልቋ የወጣ። በዚህ ዘመን እኮ መለኪያው ተፈጣሯዊነት እና ሰዋዊነት ብቻና ብቻ ነው። ብናኝ ነፍስ ከእናንተ ጋር መጠጋጋት የሚችል አላችሁን? ድርቅ የመታው ድርጅት ተሸክማችሁ ነው ያላችሁት። ደግሞም ፈርሷል። ሃብት የላችሁም የሥነ – ልቦና። አቅም የላችሁም – የብቃት። እርሾ የላችሁም ሐገር መምራት የሚያስችል ንድፈ ሃሳብ። እጃችሁን ያወጣው እንደ ድርጅት ኦህዲድ እንደ ግለሰብ የገዱ መንፈስ ነው። ዕድሜ ለኦህዲድ ጥንካሬ ቀያሽ ለለማ መንፈስ ለአጋዡና ለመከታው የገዱ መንፈስ በሉ። ሞክራችሁት ነበር እኮ ጎንደር ላይ ተሳከ? መራራ ስንብት ነበር። አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ኦህዲድ በግልም በጋራ ጥንካሬ በአይዲኦሎጂ ጥራትም ለውጥም አንቱ ነው። እንደ ልካችሁ፤ እንደ መጠናችሁ ለመኖር መፍቀድ በውዴታ ምርጫው አሁን ነው፤ ካልሆነ ግን የሚሆነው አይታወቅም። ከታሪክም፤ ከህዝብ ፍቅርም ሳጥንም ሳይኮን እንደባከናችሁ ብን …. ብትን …

ከህዝብ ጋር የወገኑት እንደ ድርጅት ኦህዲድ፤ ብአዴንም በገዱ መንፈስ ውስጥ ያሉ አንበሶች፤ ከ88 አብቼዎች ውስጥ ያሉም ደቡብ ህዝቦች ከኖሩም እንኳን ለዚህ ክብር አበቃችሁ ማለትን እሻለሁኝ። ይህ ታላቅ ገድል ነው። ያላሰብነው፤ ያላለምነው የመንፈስ ደስታ አጎናጽፋችሁናል። ተጋድሏችሁ ባክኖ አይቀርም – ይዘከራል። ሰውን ከማዳን በላይ የቤት ሥራ የላችሁም እና … አሁንም ባሩድን፤ ካቴናን ሳትፈሩ ከህዝብ ጎን ቆማችሁ በዕውነት ማሳ ትውልድን በማትረፍ ዘመናችሁን ሥሩ! ኦህዲድን ደግፉ! የመፍትሄ መንገዱን ተቀላቀሉት። ሥርዬት ነው።

 • ስለመቅድማዊነት።

አድርጎት ነው ብለናል። የልብ አድርሱ ኦህዲድ እኔ ነኝ ቀዳሚው ባለታሪክ እያለን ነው። እሰይ … አስይ ብለናል እልልም ብለናል። እኛ እናንተ ይህን ድፈሩት እንጂ ቁንጮ ነን ማለታችሁ ያለመነው ነበር። ቀረብን ብለን አንከሳችሁም፤ አንፎካክራችሁም። ያን የበታችነት አማጩን ባይታዋርነት፤ በራስ መተማመንን ፈታኙን የሴራ ድርን በጣጥሳችሁ ከዚህ ስለደረሳችሁ ኩራታችን ናችሁ። ለዚህ ያበቃችሁ የለማ አብይ መንፈስም የተመሰገነ ይሁን። ቅደሙን! ለመልካም ነገር ሰውን ሰው ለማድርግ፤ ሐገርንም ሐገርን ለማድረግ ነውና ቅንነታችሁ ተምርንበታል። በእናንተ ውስጥ ደማችን አለ። በእኛ ውስጥም ደማችሁ አለ። ስለዚህ ሁኑበት! ብለናል ኢትዮጵያዊነት እንዲህ አምሮበት ሳዳምጠው ደግሜ በሻማ ብርሃን አጅቤ ነው በርቱልኝ የእኔ አንበሶች እምለው። ድርሳኔ ነው። መንፈሴም ልቦናዬም ለሰከንድ ከእናንተ ተለይቶ አያውቅም … ክሳችሁናል። ጊዜ ታሪክ ይሰራል። ታሪክ የሰጣችሁን መሳናዶ አሟልታችሁ መገኘታችሁ ተስፋችን ሁናችሁልናል። ስንት ረቂቅ ነገሮችን እንደ አሸነፋችሁ ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው። በዚህ ሂደት ከጎናችሁ ያልተለዬው የአቶ ገዱ እንዳርጋቸው፤ የዶር አንባቸው እና የሌሎችም ቅኖች መንፈስም የተመሰገነ ይሁን። አሜን።

 • የቋያ።

በቋያ እዬተለበለበ ያለው ግራ ቀኙ ጤናየነሳው ጉንፋናም መንፈስ እንዴት ከተስፋዬ ገበረ ጃርት መንፈስ አምልጠህ መንፈስህን ኢትዮጵያ ላይ ልታሳርፍ ቻልክ? በዬት ሾልከህ ከዚህ ደረስክ? በዬትኛው የስለላ መረብ ሳትታይ ቀርተህ ነው እንዲህ ያመለጥከን? በዬትኛው ጎዳና ተጉዘህ ነው በመላ ኢትዮጵውያን ቅን መንፈስ ባለሙሉ እንደራሴ የሆንከው? አና ብለህ የመንፈስ የሁሉ ጌታ ለመሆንህ የታደልከው እንዴት ተብሎ ነው? ጥርስ ተነክሷል በኦህዲድ የለውጥ ሐዋርያት ላይ። ይህ ቁጭቱ፤ እልሁ፤ በቀሉ የለማ መንፈስ ተሸናፊ እንዲሆን በትጋት እየተሰራበት ነው። የለማ ተቋም ተሸናፊ ቢሆን የበቀሉን ሰይፍ በእጥፍ ድርብ ይቀጥላል። ለዚህም ነው የሴራው መሃንዲስ አቶ ደራጎን ከሸጎሪያቸው ብቅ ብለው የማስጠንቀቂያ መርዛማ ንፋስ ረጫ ረጫ ያደረጉት …. በጀርባቸው ለእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ህልም ሲባዝኑ የኖሩት የኤርትራው ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂም ለአፍታ የማይዘናጉበት ምህዳር ነው ይህ የጦርነት ቀጠና። „የናቅፋ“ ትንሳኤ ውሃ የበላው ቅል ሲሆን እያዩ ዝም ይላሉ ማለት ዘበት ነው። ሌላ ሥራ የላቸውም – ባክነዋል። ፋታ አጥተዋል። ሰላማቸው ታውኳል። ዕድሉ ሊያመልጣቸው ስለሆነ ያለ የሌለ ሃይላቸውን አስተባብረው መርጉን ሊለቁት ተሰናድተዋል። እና እቴጌ ኢትዮጵያ ይህን የመመከት የመንፈስ አቅም ማሰባሰብ፤ የሻብያን ህልሙን ሆነ ቅዠቱን በቁሙ የማስቀረት ክህሎቱ የለሽምን? አለሁሽ የሚል የጥቁር አንበሳ ዘብአደር አቅም ያዋጣ … ከኤርትራ ባርነት የኢትዮጵያ ነፃነት ይበል።

ለዚህ ነበር እኮ አማራ ሲታጨድ፤ ሲሳደድ የኖረው። አሁን ያ መንፈስ ሃይለምህረቱን በረከቱን ባፈሰሳባቸው ቅዱሳን ላይ ረቮ ባልተሳበ ቦታ፤ ጊዜ እና ሁኔታ ጎህ ቀደደ። ሁነኛ የእኛ የሁላችን የሚባል አደራ ተረካቢ ተገኘ። የመንፈስ ልቅናው መሰረት ያያዘ በመሆኑ ህሊናዬ ተበላ። አየር ላይ ለመጀቦን ያልፈቀደ፤ መሬት ያያዘ አቅሙን ጨብጦ ሐገሩን ሊያሰከብር ወደፊት ለመገስገስ ቆረጠ። ስለሆነም ንጹህ ልብ በፍቅራዊነት ተሸለመ። እና ማበድ ሲያንስ ነው? አማራን በይፋ በፖሊሲ ደረጃ ከምድረ ኢትዮጵያ ለማጥፋት የተሴረው ሴራ ምክንያትም እንሆ ለአደባባይ በቃ። ዘመን አንዲህ ይክሳል። „ገብያ የሚሰጠውን የእናት ልጅ አትሰጠውም“ የሚሉት ጎንደሬዎችም ለዚህ ነው።

ባለፈው የብሮድካስት የወቀሳ ስብሰባ እና የኩምታ ክምር ሸክም የታጠቀው መንፈስ በ27 ዓመት ለተወሰነች ደቂቃ የአማራ ሙሁራን ውይይት ያ ሁሉ ድንፋታ፤ አሁን OBN የሚሰራውን የአማራ ሚደያ እንኳን አልሰራበትም። መግቢያው፤ ማያያዣ ስንኞቹ ቅላፄው ጽድቅ በምድር ያሰኛል። ውስጡ ላልተበረዘውና ላልተከለሰው የኦህዲድ መንፈስ ገረዱ መሆንን መምረጥ ክብር ነው – ለእኔ። እኔ ለኢትዮጵያ ሎሌ ለመሆን የማልፈቅድ ከሆነ ስለምን ተፈጠርኩኝ? ስለዚህም እርቀቱን ቅኖቹ ትመዝኑበት ዘንድ የሴራ ቅርሻ ጠቀርሻ አቶ በረከት ስምኦንም የአዬር ላይ መፈራገጥ አብሾ ስላሰኘው ለመጋት ሊንኩ ተልጥፏል ጥቂቱ …

ሙንሙን ያደርጓታል ኢትዮጵያዊነትን – ኢትዮጵያንም፤ … ጥላቻንም አትቅረብን ይሉታል፤ ዘረኝነትንም ተቀበር ብለውታል፤ የ21ኛው ምዕተ ዓመት የጥቁር አንበሳ ጀግንነት ወራሾች ባለ አደራ እኛ ነን ብለው በልበ ሙሉነት ተሰናድተዋል። ለዘመኑ የኢትዮጵያዊነት እኛዊነት፤ ለኛዊነት ኢትዮጵያዊነትም አብዮትም ባለሜዳሊያ ናቸው። አርበኝነታቸውን በንጽህና ሲያበረክቱ ለመንፈሳችን ስለሆነ ልቅናቸው ረቂቅ ነው። ይብራኩ። ይኑሩልን። አምላካችን ይጠብቅልን። አሜን!

 • የውስጥነት ድምጸት።

ኢትዮጵያ እንዲህ አማረበት፤ ዘንካታ ሙሉ ወርዷን ተላብሳ መቀነቷን ሸብ አድርጋ፤ በሹሩባዋ ላይም ያሰኛትን ጌጥ አክላ፤ ይሄው በልሳነ ወርቁ ኢትዮጵያዊነት በOBN ተዘነከተች፤ አቶ በረከት ስምኦን መንፈሰዎት ድንገት ከእሳት የገባ ብላስቲክ እንዳይሆን ውሃ ቢጤ ያዘጋጁ፤ ወይንም ኮማም እንዳይመጣ ቀይ መስቀልን ጠጋ ይበሉ …

ኢትዮጲያዊነትን እና አንድነት 20 05 2010

ሰበር ዜና – አቶ ለማ መገርሳ አስደንጋጭ ኢህአዴግ ፍራቻ እና ጥላቻ ተቀላቅሎበታል Ethiopia

Ethiopia የኦሮሚያ ባለስልጣናት “ሴራ ተሸርቦብናል” አሉ

 

 • እርገት።

የኔዎቹ የጸሎት አጥር ቅጥር ሲታከልበት ለመንገዱ ጥበቃ፤ ለክብረቱም ጽናት፤ ለህይወቱም ስለበረከት ይሆናል። በዬትኛውም ዘመን ልናገኘው ለማንችለው ብሩህ ተሰፋችን ጥንግ ድርብ እንሁንለት። መከታ፤ ጋሻ፤ እንሁንለት። እንበርታ። ስለነበረን ዘንካታ ጊዜ ኑሩልኝን በግርማ ሞገስ ልሸልም።

 

„ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“

(ከሐዋርያዊው አቶ ለማ መገርሳ የአማራ እና የኦሮሞ የፍቅር ምክክር በግዮን ንግግር የተወሰደ።)

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!

ኢትዮጵያዊነት የመዳኛ ዓራት ዓይናማ መንገድ!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

መሸቢያ ጊዜ።

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.