የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2010(ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ገቡ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም፥ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እና ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ላቭሮቭ በጉብኝታቸው ወቅት ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር ተገናኝተው ይወያያሉ።

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ ከዚህ ቀደም በትምህርት፣ በሳይንስ፣ በግብርናና በሌሎች ዘርፎች በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነቶች ተፈራርመዋል።

ሚኒስትሩ ሰርጌ ላቭሮቭ በሚኖራቸው ቆይታም ከዚህ ቀደም በተካሄደው በ5ኛው የኢትዮ ሩሲያ የጋራ ኮሚሽን ጉባኤ ላይ በተደረጉ ስምምነቶች እና አፈፃፀም ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ።

ሁለቱ አገራት ይፋዊ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩበትን 120ኛ ዓመት በማክበር ላይ ይገኛሉ።

 

በሀብታሙ ተክለስላሴ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.