በሞያሌ ከተማ ዜጎች በአጋዚ በግፍ ተገደሉ #ግርማ_ካሳ

የለማ ቡድን ሰላምና መረጋጋት ማምጣት አልቻለም በሚል፣ ዜጎች ለመጠበቅ፣ ሰላምን ለማምጣት ነበር ሕወሃት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማጭበርበርም ቢሆን እንዲታወጅ ያደረገው። ሆኖም ብዙዎቻችን እየደጋገምን እንደተናገረነው አጋዚ በገባበት ብታ ሁሉ እልቂት ስለሆነ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በ እልቂት ላይ እልቂት በደም መፈሰ ላይ ደም መፍሰስ እያስከተለ ነው።

በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ላለፉት አንድ ሳምንታት ቢያንስ ከ20 በላይ ዜጎች በአጋዚ የተገደሉ ሲሆን ጦማሪ ስዩም ተሾመን ጨምሮ በሺሆች የሚቆጠሩ ታስረዋል።

ዛሬ ደግሞ ከአስራ ሶስት በላይ ሰላማዊ ዜጎች በሞያሌ ከተማ በግፍ እንደተገደሉ መረጃዎች እየቀረቡ ነው። ከሃያ በላይ የቆሰሉ ሲሆን በሺሆች የሚቆጠሩ ከተማዋን ለቀው ለደህንነታቸው ሲሉ እየተሰደዱ ነው።

ከተገደሉ ወገኖች መካከል፡

1) አቶ ተማም ነጋሶ የማዶ ሚጎ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር
2) አቶ እርሚያ በዳኔ (ምግብ ቤት የሚሰሩ)
3) አቶ ካኑ ጋሮ
4) አቶ ወሎ ዋቆ
5) አቶ ጌታቸው ተስፋዬ
6) አቶ አሸናፊ ታማራት
7) አቶ ጎሎ
8) አቶ መሐመድ ኡርጄ
9) አቶ ጣቲ ሻማ
10) አቶ መሐመድ ቃምጴ

የሞያሌ ከተማ በሁለት ክልሎች ስር ያለች ከተማ ስትሆን፣ ከዲላ ወደ ኬኒያ በሚወስደው መንገድ ከተማዋን ለሁለት የሚከፍል ሲሆን፣ ከመንገዱ በስተ ምእራብ የኦሮሚያ ክልል የቦረና ዞን አካል ሲሆን ከመንገዱ በስተም ምእራብ ደግሞ የሶማሌ ክልል የሊበን ዞን አካል ነው።

በገጠር ችግር አለ ተብሎ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ከአንድ ቀን በፊት እንዲወጣ ተደርጎ የነበረ ሲሆን ፣ ዛሬ የኦነግ ታጣቂዎችን ለመከላከል ነው በሚል አጋዚ ወደ ሞያሌ ከተማ እንዲገባ ተደርጎ ነው በህዝብ ላይ እልቂት እንደተፈጸመ የሚነገረው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.