ለንፁሃን ሲባል የክፉዎች ዘመን ይጠር (አብርሃም ታየ)

የአለም ፍጻሜ ምልክት ምንድን ነው? ታላቁ መጽሐፍ እንዲህ ይላል :- መንግስት በመንግስት ላይ ህዝብ በህዝብ ላይ ይነሳል :: ከዛም ዘመነ ጎግ ማጎግ የአውሬው አገዛዝ ሁሉንም ያስጨንቃል :: በግንባሩ ላይ 666 ምልክት የሌለው አይገዛም አይለውጥም:: በአንድ ፈጣሪ የሚያምኑ ሁሉ በይፋ ይገደላሉ:: እናት የሴት ልጇን ለቅሶ አትሰማም::

ሰማዕትነትን አንዳንዶች ይቀበላሉ ገሚሱ ለሰይጣን ያጎነብሳል:: መከራው ይበዛል:: “ለተመረጡት ፃድቃን ሲባል ግን ይሄ ክፋ ቀን ያጥራል:: ማቴ24 :22 ”

ይሄ አልፎ ደጉ የበጉ ንጉስ ስልጣኑን ይረከባል:: አረሙን የነቀለ የታገሰ ፍሬውን ይበላል:: እስከዚያው ግን እንጮሃለን ወደ ፈጣሪ

በባንዲራዋ ላይ የ ኢሉሚናቲ አርማ 666 ምልክት ኮከብ ያደረገው የኢትዮጵያዉ ሰይጣናዊ አገዛዝ የምጥ ጣር ያሰማል::

እነሆ በወልዲያ ከተማ ለጥምቀት የወጣው ታቦትህ በእጣን ፋንታ በአስለቃሽ ጭስ መታጠኑ አያስቆጣህምን? አገልጋዮችህ በየቦታው ሲንገላቱ ሲሰደዱ ሲታሰሩ ዝም የምትለው እስከመቼ ነው? የዋልድባ ገዳም ሲታረስ ወዲያዉ ጳጳሱንም መለስንም ባንድ ሳምንት የገላገለን የነዚህንም የክፋት ዘመን ገድብ::በምርጫ ዘጠናሰባት ማግስት ከኮልፌ ትምህርት ቤት ሲወጣ የገደሉት ህፃን ነቢዩ እንዲሁም በ2010 ጥምቀት በዓል ከመኪና ላይ እያለ ነጥለው ግንባሩን ብለው የደፉት የአስራ ሶስት አመት ልጅ ዮሴፍን የዮሴፍ አምላክ ለህፃናት ነፍስ ሲባል የክፉ አድራጊዎች ዘመን ያሳጥር!

አቤቱ በላይ በራስህ አርአያና መልክ የፈጠርከው የማንም ሰው በየእለቱ በነፍሰ በላው የወንበዴ ቡድን ሲገደል አያሳዝንህምን ለበቀልስ አያነሳሳምን ምነው ብድር የሚከፍል ውንድ ልጅ ጠፋ አያስብልምን? ፋሺስቱ ጣልያን ቅድስት አገር ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ ያሸነፍንበትን ወኔና አንድነት አድሰን እንነሳለን:: ዘመነኛው እና ዘረኛው ጥቁሩ ፋሺስት ወያኔ ከስር መሰረቱ አማራና ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ለማጥፋት ተመሰረተ ቢልም የጫካው ረቂቅ በአሁኑ ሰዓት ግን መላው የኢትዮጵያውያን ሙስሊም ምዕመናን ሳይቀር በግፉ በትር ክፋኛ ተጎድተዋል:: አሻንጉሊት መጅሊስ መሾሙ ሳያንሰው መብቴ ይከበር ባሉ የሃይማኖቱ መሪዎች ታስረዋል ዝግናኝ ድርጊት ተፈፅሞባቸዋል::

በተጭበረበረው የሙስሊሙ መጅሊስ ምርጫ ወቅት ፀጉር የሚያሳድጉትን እንላጫለን እንዳለ ራሱ መላጣውን የሞተውን መሰሪ ያራቅክ አላህ የት ነው ያለኸው?

ኦሮሞው እና አማራው ደማችን አንድ ነው ብለው በመዋደዳቸው ሌሎችም የጋራ ሃገር ኢትዮጵያን በማስቀደማቸው አዳምና ሄዋን የጋራ እናትና አባታችን እንዴት ደስ ይላቸው:: በቀራንዮ አደባባይ እስከመሰቀል የታመንክ ትርጉምህ ፍቅር ማለት እግዚአብሄር ነው የተባለልህ የብሄረሰቦች ፍቅርን ለዘለዓለሙ አጽናው :: ለዚህም የሰዎች መዋደድ የማያስደስተው ስይጣን ህወሃትን ለዘለአለሙ ወደሲዖል ወርዉረው:: እነሱማ የቆሪጥ ምሳቸውን አንዴ በቢሾፍቱ ገደል ሲረሽኑን አንዴ በሶማሌ ቀትር ሬሳችንን ሲጎት ቱ አንዴ በጨለንቆ ከነነፍሳችን ሲቀብሩን ሰነበቱ:: ወትሮም ቢሆን ክልላቹ አይደለም ተብለን የተፈናቀልን ከሃገራችን ወደ ሃገራችን ተንከራተትን:: ሰሜኑ ደቡቡ ምስራቁ ምእራቡ የሁላችንም አልነበሩምንም? እርጉም በሆነ በሄሮድስ ከመገደል ወደግብፅ እንደመሸሽ የባሰ ወደ ባህር ማዶ አሻግረን አማተርን:: ከአመፀኛው የወያኔ እጅ አምልጠን በሊቢያ በረሃ በአሸባሪዎች ተሰዋን:: ማንነታችንን እምነታችንን እንድንለዉጥ ከሚያስገድደን አጣብቂኝ ፈተና አታግባን:: የትዕግስታቸውን ልክ አልቆ የተመረጡት ፃድቃን ከመሳሳታቸው በፊት የስቃዩን ዘመን አሳጥርልን:: ነፃ ሊያወጣ የተሰለፈው አርበኛ ከሚማረክ ይልቅ ለዘመናት የቋመጠለትን ነፃነት እንዲያይ አድርግ::

ኢትዮጵያዊ መልኩን ነብር ዥጉርጉርነቱን አይለውጥም እንደተባለው ኢትዮጵያዊ ባህላችን አልገዛም ባይነታችንን ጀግንነታችንን ለጥቅም ብለን ከመናድ ና ከመካድ ሰውረን ለዘለዓለሙ አሜን::

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.