ከአማራ ፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሲቪክና የማህብረሰብ ድርጅቶቸና የመገናኛ ብዙሃን የተሰጠ መግለጫ!

የአማራ ህዝብ ለሀገሩ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለውለታ ሆኖ ሳለ በጨቋኝነት ተፈርጆ ላለፉት ረጅም ጊዜያት ሲደርስበት ለቆየው የዘር ማጥፋት፣ የመፈናቀል፣ የማንነትና የህልውና አደጋዎች ራሱን ለመከላከል በተለያየ መልኩ ተደራጅቶ በመታገል ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል። ይህን እልህ አስጨራሽ ትግል በተቀናጀ መልኩ ለማካሄድ እንዲቻል የተለያዩ ድርጅቶች በአንድነት መስራት አስፈላጊ ነው። ስማቸው ከዚህ በታች የተጠቀሱ በተለያየ ዘርፍ የተደራጁ የአማራ ድርጅቶች ከየካቲት ፴ እስከ መጋቢት ፪ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም በሰሜን አሜሪካ ሲልቨርስፕሪንግ ሜሪላንድ ለ፫ ቀን የቆየ ዝግ የምክክር ጉባዔ አካሂደዋል።

ይህ በአይነቱ ልዩ የሆነ ጉባዔ የተለያዩ የአማራ ድርጅቶች የአማራ ህዝብ ያለበትን ችግር ተመሳሳይ ግንዛቤ በሚያስጨብጥ መልኩ የተካሄደ ነው። የምንታገልለት ህዝብም ሆነ ዓላማ አንድ በመሆኑ የእስካሁኑን ትግል የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ በጋራ የመስራትን አስፈላጊነት በአጽንኦት አስምሮበታል። የመፍትሄ ሀሳቦችን ለማፍለቅ ያመች ዘንድ የአማራውን ችግር ታሪካዊ አነሳስ በስፋት ተዳሷል። ከዚህ በመነሳት የየድርጅቱ ተወካዮች የመፍትሄ ሀሳብ ይሆናል ያሉትን ለመድረኩ አቅርበው ጉባዔው መክሮበታል።

የአማራ ድርጅቶች ተቀራርቦ ለመስራትና ለመደጋገፍ አንዲሁም አንገብጋቢ ለሆኑ የጋራ ጉዳዮች ቅድሚያ ለመስጠት በተቀናጀ መልኩ ለመታገል ስምምነት ላይ ተደርሷል። ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ያስችል ዘንድ የአማራ ድርጅቶች አመራር ሰጭ አካል እንዲቋቋም ተወስኗል። ይህ አካል የየድርጅቶችን መሪዎች ያቀፈ ሲሆን በየጊዜው እየተሰበሰበ ሁኔታዎችን ያጠናል፤ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን አንገብጋቢ ጉዳዮች ነጥሎ ያወጣል፤ ዕቅዶችን በመንደፍ ተፈጻሚ ያደርጋል።

የአማራ ሕዝብ ትግል ያሸንፋል!

 • የአማራ ህልውና ለኢትዮጵያ አንድነት
 • የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ)
 • ቤተ አማራ
 • የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ (አዲሃን)
 • የአማራ ህዝብ መድህን ንቅናቄ (አህመን)
 • ዓለም አቀፍ የአማራ ህዝብ ምክር ቤት
 • የዐማራ ዳግማዊ አርበኞች ንቅናቄ (ዐዳአን)
 • ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት
 • የአማራ ማህበር በሰሜን አሜሪካ
 • የአማራ ባለሙያዎች ማህበር (አምባ)
 • የአማራ ማህበር በሲያትል
 • የአማራ ማህበር በዳላስ
 • የአማራ ማህበር በሳንዲያጎ
 • የአማራ ማህበር በ አትላንታ
 • የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ህዝብ የአማራ ብሄርተኝነት የማንነት ጥያቄ
 • የአማራ ድምጽ ራድዮ
 • ልሣነ-ዐማራ
 • ብራና ራድዮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.