የትግራይ ምሁራን ቀጣይ ዝቅጠት ለምን? (ይድረስ ለገላውዲዮስ አርአያና ተኮላ ሐጎስ)

አደመ በላቸው

Tocola-Hagosለምሁሩና ሰዓሊው ዶክተር ተኮላ ሀጎስ እነ አቶ ይልማ በቀለ መልሰውለታልና በበኩሌ ጸረ ምኒሊክ፤ ጸረ አማራ በሆነው ዶክተር ገላውዲዮስ አርአያ ላይ ማተኮር እፈልጋለሁ። ይህ ሰው ማነው ወደሚለው ከመቀጠሌ በፊት ግን የአወናባጆች ሁሉ አጃቢና አዳናቂ ሆነን ነገር የምናበላሸው ራሳችን ኢትዮጵያውያን መሆናችንን መጥቀስ እፈልጋለሁ። የለየላቸውን ባንዶች፤ ወያኔዎች፤ ዘረኞችና አስመሳይ ሀገር ወዳዶች ትልቅ ሰው አድርገን መድረክ ሰጥተን ተጫወቱብን ባዮች ራሳችን ነን ። ልደቱ ክህደቱ? ስዬ አብርህ? ወዘተ ለመጪው አንድ ስብሰባ ለምሳሌ በዋሺንግተን ከተማ አለን የሚሉ ሴቶች ስብስብ ለዓመታት ወያኔን በአዲስ አበባ ያገለገለውን፤ ወያኔ ከወደቀ ኢትዮጵያ አበቃላት ትበታተናለች ብሎ ጽፎ ስንቱ ያወገዘውን በአንድ ተቺ የምሁር አተላ የተባለውን “ዶክተር በሉኝና ልሙት” መላኩ ተገኝን የክብር እንግዳ ብለው ጋብዘዋል። ጥፋቱ የራሳችን ነው። ኑ አደንቁሩን ካልናቸው፣ ኑ ትግላችን ላይ ውሃ ቸልሱበት ካልናቸው እነሱ ምን ያድርጉ?

ጸረ አማራው፤ ጸረ ምኒሊኩ ገላውዲዪስ ማነው? ሩቅ ሳንሄድ የትግራይ ተወላጅ ነው። ያኔ አብዮት ትግል ሲባል ጎርፉ–እሱን ብቻ ሳይሆን ብዙ ሌሎችንም–ወስዶ ኢሕአፓ ውስጥ ከተታቸው። ከከተማ ወደ አሲምባ ሄዶ ፋኖ ነኝ አለ። ሳይውል ሳያድር ወደ ወሎ ዘመቻ በሚለው በፍርሃትና ሌላም ጉዳት በማስደረስ ተከሶ ከቆየ በኋላ ወደ ሱዳን ተሸኘ። ከሱዳን — እንደ ሌሎች– ወደ አሜሪካ አቀናና ትምህርቱን ተከታትሎ ዶክተር ተባለ፤ ሌሎች ትግሉን ቀጥለው ከደርግም ከወያኔም ሲዋደቁ እሱ ቤተሰብ መሰረተ፤ ደረጀ። ኢትዮጵያ በተማሪው እንቅስቃሴ አንዴም ያልተሳተፈው የተኮላ ሐጎስም ጉዞ ተመሳሳይ ነው። ወያኔ ወደ ስልጣን ሊጠጋ ሰሞን ገላውዲዮስ ወየነ። ተገረ ይላሉ ዛሬ ዜጎች — ትግሬነቱ ገነፈለ ማለት ነው ይባላል። ተኮላም ወደ ወያኔ እስከ አዲስ አበባ ተጉዞና የጥፋት አማካሪ ሆኖ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተቀባን ቦታ ፈልጎ አልሆን ሲለው ተመልሶ ወያኔን ተቺ መሆኑን አንረሳም። ወያኔ ስልጣን እንደያዘ ገላውዲዮስ ወያኔን የሚያስደስትና ወያኔ የሚጠላውን አማራና ኢሕአፓ የሚያወግዝ መጽሃፍ በእንግሊዝኛ አሳተመ። የወያኔ መጽሔት የኢትዮጵያ ኮሜንታተር መጽሄትም ዋና አዘጋጅ ሆኖ የወያኔን ፕሮፓጋንዳ አሰራጨ። ወያኔን ማመስገን አይሁንብኝ እንጂ ወያኔ ለአድርባዮች መድሃኒትም መርዝም ነው። ሊሰግዱለት ያሉትን ያባርራል — ቂም አይረሳም ፤ አሊያም ነገ እኔንም ይከዳሉ ብሎ ወግዱ ይላቸዋል። ለገላውዲዮስም የተለየ መልክ አላሳየውም። ወግድ፤ በዚያው በሩቁ ነው ያለው።

ዛሬ በወያኔ አያያዝ ኢትዮጵያ እንደ ሶማሊያ የመሆን አደጋ አጋጥሟታል ሲባል ገላውዲዮስም ተኮላም እሪ እምቧ የሚሉት ያው ዘረኝነታቸውና ትግሬነታቸው ፈልቶባቸው ነው። ይህ ልክፍት አብዛኛውን የትግራይ ምሁር ተብዬዎች እያስጓራ ነው። አቶ ጌታቸው ረዳ ከፋሺዝም ደጋፊ ምሁሮች ጋር አቆራኝቶ በሚገባ አቅርቦታል። እኔም በበኩሌ ወያኔ ፋሺስታዊ የማይባልበት ምክንያት የለም ባይ ነኝ። ዘረኛ ፋሺስት–ኤትኖ ፋሺስት ነው። የወያኔ አቅጣጫ ኢትዮጵያን ሊያፈርስና ሶማሊያም መስል ሊያደርጋት ይችላል ሲባል ሁለቱ ትግራዊ ምሁሮች ወደ ቡራ ከረዩ ያመሩት ወያኔና በተለይም የትግራይ የበላይነት ስለተነካባቸው ነው። ጸረ የመለስ ወያኔ ነን እያሉ ግን የትግራይ የበላይነትን ስርዓት ደጋፊዎች በስየና አብርሃም በላይ (ኢትዮ ሚዲያ) የተወሰኑ አይደሉም ። ገላውዲዮስ አማራን እንደሚጠላ በብዙ ጽሁፎች ግልጽ አድርጓል። ቀዋስ ብጤው ተኮላም የተለየ አይደለም። ኢትዮጵያ ተነካች በሚል ጭምብል ሊጮሁ የሚሞክሩት የትግራይ የበላይነት የተከሰተበት አገዛዝ ሊጠቃብን ነው ብለው ነው። የአዞ እንባ ቢባሉ አግባብ ያለው ትችት ነው። አማራውን ከመንግስት መስሪያ ቤት በአስቸኳይ መንጥሩ ብሎ ለወያኔ ሰነድ ያቀረበው ማነው? ተኮላ። ወያኔ ለኢትዮጵያ የመጣ ዴሞክራሲያዊ መፍትሄ ነው ያለውና ሀገር ውዳድ ሀይሎችን ያወገዘው ማነው? ገላውዲዮስ! ትግራይ የምትኮራባቸው ልጆች አፍርታለች — ከአጼ ዮሓንስ ጀምሮ እነ አሉላና ስንት ጸረ ሙሶሊኒ አርበኞች፤ ባንዳን አሳፋሪዎች፤ እነ ተስፋዬ ደበሳይ፤ ፀሎተ ሕዝቅያስና ወንድሙ፤ ብንያምና ዮሴፍ አዳነ፤ ድላይና ሀርነት፤ ኧረ ስንቱን ጠቅሶ ማስፈር ይቻላል? እጅግ ብዙ ኢትዮጵያዊነታቸውን ለድርድር የማያቀርቡ የትግራይ ጀግኖች እምነታቸውን እንደታመኑ አልፈዋል:: የሀገራቸውም ኩራትና ጌጥ ሆነዋል:: ዛሬ ደግሞ ወያኔ የትግራይ መርገምና ማፈሪያ ነው። አፍቅሮ ወያኔ ያበለዛቸው እነ ገላውዲዮስና ተኮላም ማፈሪያ ናቸውና አኩሪ የትግራይ ተወላጆች አይደሉም። ምሁር ዶክተር ፕሮፌሰር እየተባሉ ሊቆላመጡ የማይችሉ ወዲህ አሉ ወዲያ በመሰረቱ ወያኔ ወይም የትግራይ የበላይነት ጠበቃ የሆኑ ናቸው። በቃን ብሎ ማጋለጥና ከፖለቲካው መድረክ ማግለል ዋና ግዳጅ ሊሆን ይገባል። ዘር ከልጓም ጠቅሶባቸዋል። ወያኔ ወደሚወድቅበት የታሪክ ቆሻሻ ጉድጓድ መጣል አለባቸው።

ዝምታን የመረጡት የትግራይ ወንድሞችና እህቶቻችንም በተለይ በውጭ የሚኖሩት ህሊናቸውን ከፍተው የዛሬዋን ኢትዮጵያ እውነታ ሊያዩና ሊያዳምጡ ይገባል:: የዛሬዋ ኢትዮጵያ ጥቂት ትግራይ በቀል ማፍያዎች የሚገዟት ነች:: የዛሬዋ ኢትዮጵያ የፖለቲካ አገዛዝ፣ ወያኔ በሚባለው የፖለቲካ ድርጅታቸው አማካይነት በእነኝህ ማፍያዎች የሚዘወር ነው:: የዛሬዋ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በኤፈርትና በግል ስም እነኝህ ማፍያዎች የሚቆጣጠሩት ነው:: የዛሬዋ ኢትዮጵያ የአገዛዝ አከላለል እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ1936 ላይ ጣሊያን የምሥራቅ አፍሪካ ግዛቷን በቋንቋ በመሸንሸን ከነደፈችው ሰነድ የተገለበጠና ዜጎች በዘር በረት የታጎሩበት ነው:: የዛሬዋ ኢትዮጵያ ዜጎች በየክልላቸውም ሆነ በሌሎችም የሀገሪቱ ክፍሎች እንደ ሁለተኛ ሰው እየታዩ፣ የትግራይ ተወላጅ መሆን የበላይነት የሚያስገኝባት ነች:: በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ሰፍኗል፣ ምጣኔ ሀብቷ ተመንድጓል የሚለውን ቀልድ ትተው ሀቁን በነፃ አእምሮ ቢያዩ ይበጃል:: ወያኔ ተያይዘን ወደምንተላለቅበት ገደል እየወሰደን መሆኑን ሳይመሽ በፊት ልብ ሊሉት ይገባል::
ድምፃዊው:

የኤርትራን ስንዴ አልበላም እርሜ ነው!
የትግራይን ስንዴ አልበላም እርሜ ነው!
ያጨደው መትረየስ፣ የፈሰሰው ደም ነው!

እንዳለው በደም የተገኘ የበላይነት፣ አሸናፊነት ደም ያስከፍላል:: ባዕዳን ለዘመናት ሞክረውት ያልተሳካላቸውን እና አሁን በጋሻ ጃግሬያቸው በወያኔ ባለሟልነት እየተዘጋጀልን ያለውን እርስ በርስ የመተላለቅ ድግስ፣ አሁኑኑ ተባብሮ በማምከኑ ትግል ሊሳተፉ ይገባል::

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.