የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ም/ፕሬዝደንት ከችሎት ውጭ በሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች ላይ ወሰኑ

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዝደንት አቶ ገረመው ገ/ጻድቅ በሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች ላይ ከችሎት ውጭ በግላቸው መወሰናቸውን የሰማያዊ ፓርቲ የምዕ/ጎጃም ዞን ጊዜያዊ አስተባባሪ አቶ አዲሱ ጌታነህ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለፀ፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ የዞኑ መዋቅር ዕጩዎቻችን ያለ አግባብ ተሰርዘውብናል በሚል ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ አቅርቦ የነበር ሲሆን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ምድብ ችሎት የሰማያዊ ፓርቲ የዱር ቤቴ ዕጩዎች የተሰረዙት ያለ አግባብ በመሆኑ በዕጩነት እንዲቀርቡ ወስኗል፡፡

በተመሳሳይ የቀሪዎቹን ወረዳዎች ዕጩዎች ክርክርን ይዞ የነበረው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ምድብ ችሎት ለውሳኔ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበር ቢሆንም የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ም/ፕሬዝደንት ጉዳዩን እኔ አየዋለሁ በማለት ጉዳዩን ከሁለተኛ ምድብ ችሎት ከወሰዱ በኋላ የሌሎቹ ወረዳዎች ዕጩዎች በዕጩነት እንዳይቀጥሉ በግላቸው መወሰናቸው ተገልጾአል፡፡

በአንድ ፍርድ ቤት በተመሳሳይ ጉዳይ ላይ የተያዘ ክርክር ተመሳሳይ ውሳኔ ሊሰጠው ይገባ እንደነበር ግልጽ ነው ያለው አቶ አዲሱ ‹‹ፕሬዝደንቱ ዳኞቹ ለዕጩዎቹ እንደሚወስኑ ስላወቁ ጉዳዩን ከደኞቹ ቀምተው ወስደው በግላቸው ወስነዋል፡፡›› ሲል ውሳኔውን ተቃውሟል፡፡

‹‹በአንድ ፍርድ ቤት በተመሳሳይ ጉዳይ የተለያየ ውሳኔ ሊቀርብ አይችልም፡፡ ሁለተኛ ጉዳዩን መጨረስ የነበረባቸው መጀመሪያም ጉዳዩን የያዙት ዳኞች ነበሩ፡፡ በሶስተኛ ደረጃ ም/ፕሬዝደንቱ ብቻቸውን ማየት አልነበረባቸውም፡፡ ጉዳዩን ችሎት ሳይሰየም በራሳቸው ስለወሰኑ የዳኞች ፊርማ የለበትም፡፡ ከምንም በላይ ግን ውሳኔው ትክክልና ግልጽም ባለመሆኑ የውሳኔ ግልባጭ ሊሰጡን አልቻሉም፡፡›› ሲል ም/ፕሬዝደንቱ ከህግ ውጭ በሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች ላይ መወሰናቸውን ገልጾአል፡፡

11067649_677252355733759_7267272117094212038_n

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.