ኢህአዴግ ሽመልስ ከማልን ከምክርቤት እጩነት ቀንሶታል የሚባለው እውነት ነው? (የአዱ ገነት ልጆች ትብብራችሁ አይለየኝ።)

ኤርሚያስ ለገሰ  (የ መለስ ትሩፋቶች)

Ermias Legesseበነገራችን ላይ አበባን አግኝቻታለሁ። እንደለመዱት ልጆቿን ከቤት አባረው የሰው ጥገኛ አድርገዋቸዋል። ቤቷን በርብረው ንብረቶቿን የጅብ እራት አድርገውታል ። ይህ የሚጠበቅ ነው።
ጊዜና ሰአቱ ሲፈቅድ ህውሀት ማህበራት ላይ ምን ሲሰራ እንደነበር ( በተለይም ሴቶች : በአንድ ወቅት የሴቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ነበረች)…የወይዘሮ አዜብ ረጃጅም እጆችና ሎሌዎቿ…ኢህአዴግ ቢሮ የሚጐነጐኑ ሴራዎች ( ከ1999 -2001 አ•ም• በኢህአዴግ ቢሮ የአዲሳአባ ክንፍ ስራ አስፈፃሚ ነበረች)…የሕውሐት ድብቅ አላማና የአዲሳአባ ማስተር ፕላን ( በቅርብ ጊዜ በአባይ ፀሐዬ ፊትአውራሪነት በተቋቋመው ኮሚቴ ውስጥ አባል ነበረች) … ወዘተ ትነግረናለች ተብሎ ይጠበቃል ።
የህውሀት ምላሽ (ግምት):
ያጋጣሚ ነገር ሆኖ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ በአሁን ሰአት በአሜሪካን / ቨርጂኒያ ለስራ ጉዳይ መጥቷል። እናም ከጊዜያቶች በኃላ ቮኦኤ ሲጠይቀው አይኑን በጨው አጥቦ እንዲህ የሚል ምላሽ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል ፣
” አዲሱ! በአጋጣሚ እኔ በእረፍት ምክንያት አሜሪካ ነበርኩ። ወዳጆቿን አግኝቻቸው ነበር። የአበባ ባለቤት አሜሪካን ስለሚኖር ምርጫ ሰጣት። ወይ አሜሪካ መቅረት፣ አሊያም ወደ አዲሳአባ መመለስ። ልጅ ወልደዋል መሰለኝ ለመቅረት ወሰነች።… እውነቴን ነው የምልህ ጐበዝ ሲቪል ሰርቪስ ሠራተኛ ነበረች። ከዛ በተረፈ ፓለቲካውንም ኢህአዴግንም አታውቀውም። እርግጥ ነው የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ እንዴት እንደሚሰራ ልምድ ለመውሰድ ኢህአዴግን ወክላ ለአንድ ወር ሄዳ ነበር።”

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.