ለ ‘’አንድ አማራ’’ አስተባባሪ ግብረ  ኃይል (ደምኢህሕ)

 የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ሕብረት(ደምኢህሕ) እና ጋምቤላ ክልላዊ ንቅናቄ

ለ ‘’አንድ አማራ’’ አስተባባሪ ግብረ  ኃይል

’’አንድ አማራ’’ ድርጅት መስራች ስብሰባ ላይ እንድንገኝ ለደረሰን የስብሰባ ጥሪ አዎንታዊ ምላሽ ስለመስጠት።

እንደሚታወቀው ባለፉት 27 ዓመታት በሃገራችን ኢትዮጵያ ላይ ይተንሰራፋውን አፋኝና ጨቋኝ የወያኔ አገዛዝ ከስር መሰረቱ ፈንቅሎ በመጣል ፍትሕና ዴሞክራሲ የሰፈነባት በዜጎች ነጻነትና እኩልነት ላይ የተመሰረተች ኢትዮጵያን እውን በማድረግ ተራማጅ ኃይሎች ምቹ በሆኑ ድርጅታዊ መዋቅሮች መሰባሰብና መደራጀት መተኪያ የሌለው ብቸኛ መፍትሔ መሆኑ የማያሻማ ሀቅ ነው።

በመሆኑም አሁን በኢትዮጵያ ባለው ወቅታዊ ተጨባጭ የፖለቲካ ቀውስ ያገባናል ወይም ይመለከተናል የሚሉ ቁርጠኛ የኢትዮጵያ ልጆች ትግሉ የሚጠይቀውን ማናቸውንም መዕስዋትነት በመክፈል በሁሉም አቅጣጫዎች የሚያደርጉትን ያለሰለሰ ትግል ወደምፈለገው ግብ እና ሥኬት ጫፍ ለማድረስ ‘’አንድ አማራ’’ በሚል የድርጅት ጥላ ሥር ለመደራጀት መታሰቡ የሚደገፍና የሚበረታታ ጉዳይ ነው።

ስለሆነም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ሕብረት እና የጋምቤላ ክልላዊ ንቅናቄም ከቆመለት ህዝባዊ አላማ አኳያ አንድ አማራ ድርጅት በትግል ጉዞው የሚያጋጥሙትን ፈተናዎችና ውጣ ውረዶችን በማለፍ አንዲት ዴሞክራሲያዊትና ህዝባዊት ኢትዮጵያን መፃኢ እድል ለመወሰን የታለመው

ድርጅታዊ ህልም እንድሣካ ሙሉ ድጋፍን ባለማመንታት ለመስጠትና የትግል አጋርነቱን ሲገልፅ በታላቅ ደስታ ነው።

በዚህም መሠረት ለድርጅታችን ካላችሁ አጋርነትና አክብሮት በመነሣት በመስራች ስብሰባችሁ ላይ እንድንገኝና ድጋፋችንን እንድንገልፅ የቀረበልንን ጥሪ በደስታ መቀበላችንንና    የድርጅቶቻችን ተወካዮች በስብሰባው ዕለት እንደሚገኙ እናረጋግጣለን።

 

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ሕብረት እና የጋምቤላ ክልላዊ ንቅናቄ::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.