ተከሳሹ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ጋዜጠኞች በተገኙበት ቀረፃ እየተካሄደ መደብደቡን በችሎት ተናግሯል

መጋቢት 11/2010
ጌታቸው ሽፈራው

“ጉራጌ ስራ እንጂ ፖለቲካ አያውቅም” መርማረዎች
(በቅርቡ ከእስር የተፈታው ብሎገር ሙጅብ አሚኖ ዝርዝሩን ዘግቦታል)

በፀረ ሽብር አዋጅ የተከሰሰው ሰይፉ አለሙ ሶስት የመከላከያ ምስክሮቹን በ 19ኛ ወንጀል ችሎት አስደምጦ ለብይን ለሚያዚያ 17/2010 ተቀጠረ።

በትላንትናው እለት ሰይፉ አለሙ በተካተተበት በእነ ጌታሁን በየነ መዝገብ የተካተቱ ወንድሞቻችን በችሎት በመገኘት መከላከያቸውን አቅርበዋል።

በማዕከላዊ በደረሰብኝ ድብደባ ምክንያት ከመኝታዬ ተነስቼ ለሽንት መውጣት አልችልም ነበር፣ ዘሬን እየጠቀሱ ሲሰድቡኝ እና ሰብአዊ ድርጊቶች ሲፈፅሙብኝ ነበር ፣ጥይት ገዝተሀል፣ የሎጅስቲክ አባል ነህ ፣የግንቦት ሰባት አመራር ነህ እየተባልኩ ከፍተኛ ድብደባ ደርሶብኛል…በማለት ለገሰ ሀ/መስቀል ለ19ኛ ወ/ችሎት ዳኞች አስረድቷል።

ዛሬ መጋቢት 11/2010 በፀረ ሽብር አዋጅ የተከሰሰው ሰይፉ አለሙ ሶስት የመከላከያ ምስክሮቹን በ 19ኛ ወንጀል ችሎት አስደምጧል።

ወጣት ሰይፉ አለሙ በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ስነ ስርዓት ቁጥር 142(3) መሰረት የተከሳሽነት ቃሉን ለፍርድ ቤቱ አቅርቧ። በተከሳችነት ቃሉ ላይም ” ዘሬን ብቻ መሰረት ያደረገ ኢ ሰብዓዊ ድብደባ ደርሶብኛል፣ ጉራጌ ስራ እንጂ ፖለቲካ አያውቅም እየተባልኩ በመርማሪዎች ተሰቃይቻለሁ፣ በግዳጅ ከማላውቃቸው ሰዎች ጋር መሳሪያ አስይዘው በግዳጅ ፎቶ አስነስተውኛል፣ ሴት መርማሪዎች ምራቃቸውን እየተፉ በኤሌክትሪክ ገርፈውኛል፣ በማዕከላዊ ጥቃት ይደርስብኝ የነበረው በቤሄሬ ነው ጉራጌ ሌብነት እንጂ ፖለቲካን የት ያውቃል እየተባልኩ ምራቅ እየተተፋብኝ ነበር ስደበደብ የነበረው ፣ከዚህ በፊትም ማዕከላዊ ተይዘው የገቡ ብዙ ጉራጌዎች ተደብድበዎል ተኮላሽተዎል በዚህ ቤሄር ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት ሊቆም ይገባል፣ሰውነቴ ላይ የሚታዩት እነዚህ ጠባሳዎች ከእናቴ ማህፀን ስወለድ ያገኘሆቸው ሳይሆኑ በማዕከላዊ በደረሰብኝ ድብደባ ምክንያት ሰውነቴ ላይ የቀሩ ናቸው ፣ይሄ ሁሉ ድብደባ ደርሶብኝ ሰውነቴም መግሎብኝ ህክምና እንኮን አለገኘሁም ነበር ፣መርማሪዎች እየሰከሩ እየመጡ ከፍተኛ ድብደባ አድርሰውብኛል፣ የኢቢሲ የምርመራ ጋዜጠኞች በተገኙበት ቀረፃ እየተካሄደ ተደብድቤያለው፣…በማለት የሰጠ ሲሆን ከዚህ ቀደም በችሎቱ የተደበደበበትን ጠባሳ ለችሎቱ ያሳየ ሲሆን ዛሬም ሊያወልቅ ሲል አይተነዋል ብለው ዳኞች ከልክለውታል። ማዕከላዊንም የሲዖል መናሃሪያ ብሎ ገልፆታል። በችሎቱ ላይ የአሁኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለሰ አለም አንዱ ከደብዳቢዎች መሃከል ይገኛሉ በማለት አስገራሚና ከአንድ ሚኒሥትር እንዲህ ይጠበቃል? የሚል ጥያቄ እንድንጭርና እንድንገረም ዳርጎናል።

የቀረቡት የመከላከያ ምስክሮች አ/ቶ ተስፋዬ አያሌው፣ አ/ቶ ፋአድ ሙሃመድ ዩሱፍ፣ አ/ቶ አብዱልፈታ ሁንዴ በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ስነ ስርዓት ቁጥር 27(2) መሰረት ተከሳሽ የሰጠው ቃል በግዳጅ መሆኑን የደረሰበትን ድብደባና ስቃዮች በመጥቀስ አስረድተውለታል።

ፍርድ ቤቱም የአቃቤ ህግን ምስክሮችና የተከሳሾችን የመከላከያ ምስክሮች መርምሮ ብይን ለመስጠት ለሚያዚያ 17/2010 ቀጥሯል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.