የወያኔ ዐረ-ኢትዮጵያዊነት ገሀድ ወጣ፤ ለጋራ ጥያቄ የጋራ ትግል ያስፈልጋል።

የተሰጠ መግለጫ

መጋቢት14 ቀን 2010ዓ.ም

የወያኔ ዘረኛ፣ መድልኦዊ የአምባገነን አገዛዝ ኢትዮጵያ አገራችንን የባሕር በር አልባ ያደረገ፣ መሬታችንን ለሱዳን አሳልፎ የሰጣ፣ አንዲሁም የአገሪቱን ለም መሬቶች ለባዕዳን ፣ ለአራብ፣ለሕንድ፤ ለቱርክ፣ ለማሌዢያ፣ — ወ.ዘ.ተ ለብዙ ዓመታት ከመቸብቸብ አልፎ ገንዘቡን የበላ፣ የአገሪቱ የስልጣኔ ምንጭና እድገት መሰረት የሆነውን ትምህርት ለመግዳል ባለው መሠሪ ዓላማ ትውልድ ገዳይ የትምህርት ፖሊሲ በባለሙያዎች ሳይሆን በካድሬዎቹ አማካይነት አንዲቀረጽ በማድረግ ትምህርት ላይ ትልቅ ወንጀል የፈጸመ፣ የአገሪቱን ታሪክ ለማጥፋት ባለው ቁርጠኛ አቋሙ በዩኒቨርሲቲዎች፣ በኮሌጆች፣ በሀለተኛ ፣ በመለስተኛና በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የታሪክ ትምህርት እንዳይሰጥ ወይም የውሸት ታሪክ ትምህርት እንዲሰጥ ያደረገና በሕዝቡ ዘንድ ተወዳጅ ከሆኑት ከድርጅት መሪዎች እስክ ግለሰብ ድረስ የገደለና ያስገደለ የማፊያ ቡድን ነው።  በነዚህ  ታላላቅ  አገራዊ  ወንጀሎችና   ክህደት  ነው  ወያኔ  ጸረ-ኢትዮጵያ፣  ጸረ-ኢትዮጵያዊነትና ጸረ-ሕዝብ ነው የተባለው። ይህን የክህደት ተፈጥሮአዊ ተግባሩን ወያኔ ከስልጣን በሕዝብ ትግል እስከሚወገድ ድረስ ይቀጥላል እንጂ ይተዋል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው።

ወያኔና ተባበሪ ተላጣፊ ድርጅቶች በስብሰናል የኢትዮጵያ ሕዝብን ይቅርታ እንጠይቃለን ያሉቡት ቃል ውሎ ሳያድር መሰሪው ወያኔ የአስቸኳይ ጊዚያዊ አዋጅ በማወጅ ቅዳሜ መጋቢት 1 ቀን 2010 ዓም በደቡቡ የአገራችን ክፍል በቦረና ዞን በሞያሌ ከተማ የወያኔ አጋአዚ ነፍሰ ገዳይ ጦር ቤት ለቤት በማሳስ፣ በመንገድ ላይ ሰላማዊ እንቅስቃሴ በሚያካሄዱ ዜጎቻችን፣ በቡና ቤት፣ በሻይ ቤቶች ፣ በገበያና በሱቅ ሆነው መደበኛ ስራቸውን ሲያከናውኑ በነበሩ የ7 እና የ10ዓመት ህፃነትን ጨምሮ ከ13 በላይ ዜጎችን አልሞ በመተኮስ በግፍ ሕይወታቸውን አጥፍቷል። በርካቶችንም አቁስሏል።

በዚህ የግፍ ግድያ ወቅት የሙያ አጋራችን የሆነው በ2008 ዓም በኦሮሚያ ክልል በትምህርት ቤቱ ውስጥ ላበረከተው ትልቅ የትምህርት ስራና ላሳያው የሙያ ስነምግባር ሁለተኛ ደረጃ ተሸላሚ ፣ በአካባቢው ሕዝብ፣ በትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ተወዳጅ ፣ የአንድ ልጅ አባት ፣ የ34 ዓመት ጎልማሳ ርዕሳ መምህር የነበረው/የሆነው ታምሩ ነጌሶ በእረፍት ቀኑ ቅዳሜ መጋቢት 1 ቀን 2010 ዓም ጊዜውን ሰውቶ በመዶ ሚጎ ት/ቤት ውስጥ ከተወሰኑ መምህራን ነገር ያደርገው የነበረውን የትምህርት ስራ ጨርሶ ወደ ቤቱ ሲመለስ መንገድ በማቋረጥ እያለ የአግኣዚ ነፍሰ ገዳይ ጦር በሶስት ጥይት ደብድቦ ሕይወቱ እንዲጠፋ አድርጓል።

ይህን የወያኔን የግፍ ግድያና የጅምላ ጭፍጨፋ በመሸሽ ከ60ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ጎረቤት አገር ኬኒያ ሊሰደዱ በቅተዋል።የወያኔን ዘረኛ ድርጊት የሞያሌ ከተማ ካንቲባ ለመገናኛ ብዙኃን እንደገለጹት ሠራዊቱ የባእድ ጦር እንጂ የኢትዮጵያ አይመስልም ብለዋል። ታዲያ በዚህ ድርጊቱ ወያኔ ኢትዮጵያዊ ነው? ለኢትዮጵያ ሕዝብ የቆመ ነው? ቀደም ሲልም በተለያዩ ቦታዎች ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያዉያንን ከትውልድ ቄያቸው ክኖሩበት ስፍራ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን እንዲፈናቀሉ ያደረገ ፀረ-ሕዝብ ዘረኛ ቡድን ነው። ላለፉት 27 ዓመታት ወያኔ ኢትዮጵያዊ አይደለም የተባለው እነሆ ዛሬ ገሀድ ወጣ። ሰላማዊ ሕዝብ በወያኔ ሠራዊት በጠራራ ጸሐይ በጥይት እየተደበደበ ይገኛል። በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ ይህን የወያኔን በቦረና በሞያሌ ከተማ ህዝብ ላይ የፈጸመውን አራማኔያዊ ግድያ፣ በሕዝብ ላይ ያደረሰውን የአካል ማቁሰልና ጉዳት፣ ማፈናቀልን በጥብቅ ያወግዛል፤ ይኮንናል። እንዲሁም በሌሎች ቦታዎች በጎንዳር፣ በወልቂጤ፣ በነቀምት፣ በደምቢዶሎ   —ወ.ዘተ  በሚገኙ   ኢትዮጵያዉያን ወገኖቻችን  ላይ  የፈጸመውን  ግድያ፣  አስራት፣  የመሬት  ቅሚያ፣  የትምህርት  ክፍለ  ጊዜያት  ብክነትን፣የተማሪዎችና የመምህራን እስርን፣ የአካዳሚክ ነፃነት መታጣትን በጥብቅ ይቃወማል።

በአሁኑ ሰዓት የወያኔ አገዛዝ ከምንጊዜውም በላይ በፖለቲካ ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ቀውሶች ውስጥ ተዘፍ  ይገኛል። የሕዝቡ በወያኔ አልገዛም፣ እምቢ አሻፈረኝ በማለት የጀመረውን ሕዝባዊ ሰላማዊ ትግል፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ፣ ከቀን ወደ ቀን እያደገ የመጣበት፣በወያኔና በኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል ያለው ቅራኔ ከመክረሩ የተነሳ ሊበጠስ የተቃረበበት ጊዜ ላይ እንገኛለን።

በሌላ በኩል ደግሞ የወያኔ አገዛዝ እንደቀድሞው ሊገዛ ያልቻለበት በሁሉም መስክ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ተቀባይነትን ያጣበትና እየተዳከመ የመጣበት ሁኔታ ይስተዋላል። እኩል ባልሆኑ ኃይሎች መካከል  ሁኔታ  የተፈጠረበት  ክስተት  ነው( Equilibrium between unequal forces) ለስር ውጥ ሁኔታዎች ግን ይህን ግል ከዳር ለማድረ ህሊናዊ ሁኔታዎች ያልተሟሉበት በሂዳትም ክፍተቱን ለመሙላት ትግል እየተካሄደ ያለበት ሁኔታ ላይ ደርሰናል።

የሕዝቡ ጥያቄ ከአካባቢ የውስጥ ጥያቄዎች በመዝለል አገራዊ ቅርዕ እየያዘ የመጣበት ሁኔታ ይታያል።ወያኔ በቃ፣( Down Down Woyane) ወያኔ ይወደም ፣በወያኔ አንገዛም ፣ ሁሉንም ያካተተ የሽግግር መንግስት ይቋቋም  ፣  የአዋጅ  ጋጋተ  የሕዝቡን  ትግል አይገታም፣  ስር  ነቀል  ለውጥ  ይደረግ  ወያኔ  ይወገድ  የሚሉ  ሕዝባዊ መፈክሮች በስፋት እየተስተጋቡ ይገኛሉ። የቀረው ይህን ወሳኝና ወቅታዊ መፈክሮችን በማንገብ  በየአቅጣጫው  በሁሉም  ስፍራ  እየተፋፋመ  ያለውን  የሕዝቡን  እምቢተኝነት  የአልገዛም ባይነት እርምጃዎችን ከግብ ለማድረስ ትግሉን ማስተባበርና ማስተሳሰር ነው። ለጋራ ጥያቄ የጋራ ትግል ያስፈልጋል። ስለዚህ በተለያዩ ቦታዎች በተለያዩ ስሞች በግንበር ቀደምተኝነት ትግሉን የሚካያሄዱ  ወጣቶች  በጋራበህብረ  እንዲነሱ  ማድረግና መርዳት የጊዜው ጥያቄ ነው። አገራችን ኢትዮጵያ የሁላችንም ናት ከወጣቶቹ ጎን ሁላችንም መቆም አለብን። ለወጣቶቹ የቅርብ አጋዥ ኃይል መምህራን ናቸው። መምህራን በ1966ቱ አብዮት ወቅት ከወጣቶች ጎን በመቆም ለለውጡ መወለድ አስተዋጽኦ እንዳደረጉ ሁሉ ዛሬም የትግል ልምዳቸውን በመጠቀም በሰሜን በደቡብ፣ በምስራቅ በምዕራብ እንዲሁም በመሐል አገር እየተቀጣጠለ በወጣቱ ግንባር ቀደምተኝነት የሚካሄደውን ትግል አገር አቀፍ ቅርዕ እንዲይዝ ማስተባበርና ማያያዝ ታሪካዊ ግዴታቸው ነው።መምህራን በሁሉም ቦታ የስራ ማቆም አድማ በማድረግ ትግሉ ይበልጥ ጉልበት እንዲያገኝ የድርሻቸውን እንዲወጡ በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ በዚህ ወሳኝ የትግል ወቅት ጥሪውን ያቀርባል።

ሕዝባዊ አመጹ ተፋፍሞ ይቀጥል!!!

የወያኔ ነፍሰ ገዳይ አጋአዚ ጦር ለፍርድ መቅረቡ የማይቀር ው!!! ለጋ ጥያቄዎችንን መልስ ለማግኘት የጋራ ትግል ይስፈልጋል!!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.