በወሮበሎች አዚም የባዘንን አንሁን! (ሰርፀ ደስታ – የሳተናው አምደኛ)

ሰሞኑን ወንበዴው ወያኔ የሽብር አዋጅ አውጥታ ማንም ሰው ምንም ነገር መናገር አይችልም ብላ ሁሉንም ዝም በማድረግ የራሷን  የውንብድና ወሬ በሰፊው መንዛት ተያይዛለች፡፡ በዚሁ አጋጣሚ የክት የውንብድናና አረመኔነነት አጋሮቿን ከሞቱበት እያስነሳች ለውንብድናዋ እየተጠቀመች ነው፡፡ አሁን ላይ አብዳለች ወያኔ በምንም መልኩ ከአሸባሪነትና አረመኔነት በቀር አንደም አቅም እንደሌላት ሕዝብ ግልጽ ብሎለታል፡፡ አሁን ለሕዝብ አደጋ እየሆነ ያለው ግን በወያኔ የወሮበላ አስተሳሰብ እየተደናበረ የወያኔ ወሬ አናፋሽ የሆነው ተማርኩ የሚለው ጅላጅል ትውልድ ነው፡፡ ሰሞኑን ነጠቃ መንግስት ብላ ወሬ ጀምራለች፡፡ እድሜ ከሰጣት እንዲሁ የተጃጃለ ትውልድ 27 ዓመት  በመተቱም በሽብሩም ያደነዘዘችው ትውልድ ዛሬም ወያኔን እንደ ልዩ ነገር ያያታል፡፡ የወያኔና አጋሮቿን ኢሕአዴግ ብላ የሰራችው ቡድን በአጠቃላይ መንግስት ብሎ መናገር በራሱ እጅግ መዝቀጥ ነው፡፡ መንግስት አምባ ገነን ሊሆን ይችላል ግን መንግስት ጉልበተኛ ነው እንጂ ወሮ በላ አይደለም፡፡  ወያኔ በኢትዮጵያ ምድር 27ዓመት በገዥነት ሥም መኖር መቻሏ ዋና አቅም የሆናት ሕዝብን ከሕዝብ መለያየት መቻሏ ነበር፡፡ ይን ደግሞ ብቻዋን አልነበረም ኦነግ የተባለ ሌላ አረመኔና ወንበዴ አጋሯ ነበር፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያ ለገባችበት ምስቅልቅል ሁሉ ወያኔና ኦነግ በአንድነት ቆመው አገርን ለማፍረስ ሕዝብን ለመለያየት የቻሉትን ሁሉ አደርገዋል፡፡ አሁንም ሁለቱም በዚሁ አላማቸው ጸንተው ቆመዋል፡፡ ሰሞኑን ኦነግ የትግል አጋር ነኝ በሚል የሕዝብን ትግል በውጭ ኃይል እየተጋዘ በአገር ላይ የተነሳ ለማስመሰል ለወያኔ ለዘመናት የተጠቀመችበትን ማጃጀላ ዛሬም ለመጠቀም ይረዳት ዘንድ ምልክት ለመሆን ነበር የኦነግ የትግል አካል ነኝ ማለት ምክነያቱ፡፡ ኦነግ ኢትዮጵያ ምድር ላይ አንደም ቦታ እንደሌለ እኛ እናውቃለን፡፡ ወያኔ አንተ እንዲ በል እኔ ደግሞ በኤርትራ የሚደገፍ ቄሮ በማለት የወሬ አዚም እየነዛሁ እጨፈጭፈዋለሁ ነው፡፡ የወያኔና ኦነግ ዘላለማዊ ቃልኪዳን ይሄና ይሄ ብቻ ነው፡፡ ይህ ከአልገባን ዛሬም ገና ነን፡፡ ኦነግ በኦሮሚያ ክልል ኦሮሞን ኢላማ ለማድረግ ነው፡፡ በተመሳሳይ ግንቦት 7 የተባለው ድርጅት አማራን ኢላማ ለማድረግ ከወያኔ ጋር ውል እንደገባ ካልገባን ችግሩ ከወያኔ ሳይሆን ከራሳችን ነው፡፡ ግንቦት 7 እያደረገ ያው ኦነግ በኦሮሚያ እንደሚያደርገው ነው፡፡ ልብ በሉ አማራ እስከ ብዙ ዘመን ተገዳይ እንጂ መብትም ጠያቂ አልነበረም፡፡ አማራ ወያኔን የማስጋት እድል እየተፈጠረ ሲመጣ ግንቦት 7 የሚባል የኦነግ ተመሳሳይ ሥም አማራን ኢላማ ለማድረግ ዋና ምክነያት ሆነ፡፡ ሁለቱም በኤርትራ በኩል ነው እየታገልን ነው የሚሉት፡፡ ኤርትራ የኢትዮጵ ጠላት ተደርጋ ታይታለች፡፡ ይታያችሁ የኤርትራ ሕዝብ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላት መሆኑ ነው፡፡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖች ያለቁበት የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ሳይቀር ግን የሻቢያና ወያኔ ቁማር ድራማ እንደሆነ አውቀናል፡፡ ኢሳያስን ያዳነው መለስ ነው እኮ ሊያውም ኢትዮጵያውያን ወታደሮች እንዲያልቁ በማድረግ፡፡ እዚህ ቁማር ውስጥ ዛሬ በአጋርነት እየተጫወቱ ያሉት ኦነግና ግንቦት7፡፡ ኦነግም ሆነ ግንቦት7 የሚባል የታጠቀ ኃይል እንደሌለማ ከወያኔ በላይ የሚያውቅ የለም፡፡ ሲጀምር ኦነግና ግንቦት7 የሚንቀሳቀሱት በወያኔ እቅድ ነው፡፡ ደምህት የተባለ የታጠቀ ቡድን አለ፡፡ ይሄ ግን ወያኔ አንድ ነገር ብትሆን ተጠባባቂ ሆኖ ታጥቆ የሚጠብቅ እንጂ ወያኔን ሊዋጋ አደለም፡፡ ልብ በሉ ሻቢያ ደምህትን እንደ መነሻ አድርጋ ወያኔ አንድ ነገር ቢሆን ከኋላ ለመታደግ ነው፡፡ ሻቢያና ወያኔ እንዲህ ነው እየቆመሩብን ያለው፡፡ ይህን አንረዳም፡፡

ወያኔ ሰሞኑን ብቻዋን ወሬዋን እየነዛች ነው፡፡ ይሄን እየያዘ አዳሜ አብሮ ሽብር ነዥ ሆኖ እናየዋለን፡፡ እውነታው ግን የወያኔ ጀምበር እየጠለቀች መሆኑ ብቻ ነው፡፡ አይቀሬ የሆነው የወንብዴው ቡድን መሸነፍ ብቻም ሳይሆን እይሆኑ ሆኖ እንዲያበቃ እንጂ አሁንም አልቆላታል፡፡ ለማና ገዱ መናገር አልቻሉምና ለማና ገዱ እጅ ሰጡ አይነት ወሬ በሰፊው ይዛዋለች፡፡ ምድረ ዲያስፖራ በዚህ የወንበዴ ወሬ ሲፍረከረኩ ታይተዋል፡፡ እርግጥ ነው ዲያስፖራ ተብዬው ብዙው አጋጣሚውንም እንደመነገጃ ስለሚጠቀመው የወንበዴውን ውዥንበር ማባዛት ሥራው ነው፡፡ ዛሬም የኦነግ ባንዲራ በኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል አጋርነት ሥም በየአገራቱ አብሮ ሲያውለበልብ የሚታይ የባዘነ ዲያስፖራ ነው፡፡ ለመሆኑ ግን ኦነግን ለማስተዋወቅ ነው ወይስ ሰላማዊ ሰልፍ ነው?

ትንተና እንሰጣለን ብላችሁ የምትቀዣብሩ ከአልገባችሁ ዝም በሉ፡፡ ሆን ብላችሁ ከሆነ ግን ሥራችሁ ነው፡፡ የሕዝብን ትግል ለማፋጠን አንድ ደረጃ ከፍ የሚል እርምጃ ለመውሰድ እየተዘጋጀን ነው፡፡ ለ27ዓመት የወንበዴ ቅጥረኛ ሆኖ ሲያገለግል የኖረ የታጠቀ የኦሮሞ፣ አማራና ሌሎች የታጠቀ ኃይል ሁሉ ከሕዝቡና ዳረጎት እየሰጠ ከሚያኖረው ወንበዴ ቡድን እንዲመርጥ ልናሳስበው ይገባል፡፡ ኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ሳይኖራት 27ዓመት ሞላ፡፡ የደርግ እየተባለ የሚጠራው ሰራዊት እኮ የኢትዮጵያ ነበር፡፡ ይህን ብረሀነመስቀል አበበ ሰኚ በቅርቡ ቪኦኤ ይህን እውነት ጥሩ አድርጎ ገልጦታል፡፡ አሁን ያለው ወታደር የወያኔ ቅጥር እንጂ የኢትዮጵያ አደለም፡፡ በደርግ ጊዜ የነበረው ወታደር ታሪኩ ከንጉሱ የቀጠለ ነው እንጂ ደርግ የፈጠረው አደለም፡፡ ዛሬ አገር እንዲሀ በአለ ምስቅልቀል ገብታ ሊታደግ የሚችል ሠራዊት የጠፋው ምክነያቱ፣ በኢትዮጵያ ሠራዊትነት የሚጠራው የዛሬው የታጠቀ ኃይል በግልጽ የወንበዴው ወሮ በላ ቡድን የግል ቅጥር ነው፡፡ ይህን እውነት እንዲያስተውል በሰራዊትነት ተቀጥሮ ላሉት ሁሉ በተቻለን ሁሉ በማድረስ ወንበዴዎቹን እንዲበቀል ማድረግ ዋነኛ አላማችን ሊሆን ይገባል፡፡ ትግሬዎች አሁንም ጥሪ እየቀረበላቸው ቢሆንም ትግሬና ወያኔ እንድ ነው የተባለውን ብሂል ይበልጥ እያረጋገጡልን ይመስላል፡፡አዝናለሁ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብን እጅግ ተፈታትናችሁታል፡፡ እስካሁን ከልብ ሆኖ ወያኔን ሲቃወሙ ያየኋቸው ጥቂት ትግሬዎች ናቸው፡፡ መቃወሙ ቀርቶ ግን ሕሊና የሚያሳድፍ ነገር መናገርን ቢያቆሙ ለእነሱ እየመጣባቸው ያለውን አደጋ በአቀለላቸው ነበር፡፡ አዝናለሁ፡፡ ዛሬ ለብዙ ኢትዮጵያዊ ትግሬ የሆነው ድሮ ሰው የሚየስበው ሀይማኖተኛ፣ መልካም ህዝብ ምናምን የሚባለው ሳይሆን ፍጹም እምነት የሌለው አረመኔና ነውር የለሽ ስግብግብ ነው፡፡ አዝናለሁ፡፡ ይህን እውነት መናገር ስላለብኝ ነው፡፡

ሚዲያዎች የኢትዮጵያን ሕዝብ ትግል ያግዛሉ ብለን ብንጠብቅ ብንጠብቅ ምንም የለም፡፡ ቪኦኤና ዶቸቬሌ፣ ኤስ ቢኤስ ባይኖሩ የሕዝብ አይንና ጆሮ ነን የሚሉት እንደነ ኢሳት ያሉ በወያኔ የውዥንበር ወሬ የበለጠ ባባዘኑን፡፡ ሰሞኑን ኢሳት ግንቦተ7 በዚህ ቦታ እንዲህ አደረገ እንዲህ ሊያደርግ ነው የቀበሌ እስር ቤት ሰበረ ምናምን ወሬ ዋና ጉዳዩ ሆኖ ነው የሰነበተው፡፡ ይታያችሁ አሁን ማን ይሙት ወያኔን ለመጣል አፋፍ ላይ እየታገለ ላለ ሕዝብ ይሄ ተራ የወያኔ አጋር የሆነው ግንቦት 7 ወሬን መስማት የሚፈልግ አለ? ሌላው በኦሮሞ ሥም ሌላ ቲቪ ተከፍቷል ኦሮሚያ ቲቪ የሚል ይሄ ደግሞ የኦነግን ወሬ ነው የሚነዛው፡፡ ሁሉም ለወያኔ ግብዓት የሚሆን ፕሮፓጋንዳ ነው የሚነዙት፡፡ ማስተዋል ከሌላ ምን ይደረጋል፡፡

ሌላው ውዥንብር እምነትን አስመልክቶ ነው፡፡ መቼም በወሮበላው ወያኔ ዋና የወሮበላ መከማቻ ከሆኑት ዋነኛዎቹ ቤተ እምነቶች ናቸው፡፡ አሁን ችግር የለም ሀዋሪያ ነብይ ምናምን ሆኖ እንደልብ እየዘባረቁ ሕዝብን ማደንዘዝ ነው፡፡ ወያኔ የምትፈልገው ይሄንን ነው፡፡ በጽኑ እምነት ላይ ቆሞ አገርና ሕዝብን የሚያስብ ትውልድን ለማጥፋት ይሄ እንዱ የወሮበላው ቡድን ሥልት ነው፡፡ አገሪቱ በጠንቋዮች ተወራለች ቢባል ይሻላል፡፡ በዚህ ጉዳይ በትልልቅ የሕዝብና አገር ጉዳዮች ሲሳተፉ ያየናቸው ሳይቀሩ ቀስ ብለው ተራ ሀይማኖታዊ ያልሆነ ሰባኪዎች ሆነውልናል፡፡ ሐይማኖት ፍልስፍና ነው፡፡ ፍለስፍናው ደግሞ ከሁሉም የረቀቀ ነው፡፡ ማንም እየተነሳ ነብይ ሀዋሪያ ነኝ እንደሚለው አደለም፡፡ ኢትዮጵያ ለዘመናት በጠላት አልደፈር ያለችው በጽኑ እምነት ላይ በቆሙ አባቶቻችንና እናቶቻችን የሆነውን ያህል ዛሬ አገርና ሕዝብን የሚሸጡና የሚያመክኑ የሰይጣን መንፈስ የሰፈረባቸው አገሪቱን ወረዋታል፡፡

ትኩረት እንዳይኖረን ብዙ እየተረባረቡ ነው፡፡ እነሱ አያፍሩም እኛ ግን ወራዶችን ወራዳ ለማለት እናፍራለን፡፡ በቃ አካፋን አካፋ ዶማን ዶማ ማለት ተገቢ ነው፡፡ ፊት መስጠት አያስፈልግም፡፡ ወራዶችን ማክበር በወራዳ ሥራቸው መተባበር ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ንቁ፡፡ ወያኔ አሁን አብዳለች፡፡ አንዴ የወያኔ መሪዎችን ኢላማ ያደረገ ጥቃት እስኪጀመር ነው፡፡ ይህ ደግሞ በቅርብ ይሆናል፡፡ በዛው ልክ ሕዝብን ከሕዝብ አንድ የማድረግ ሥራ ይሰራ፡፡ ይሄ ኢሳት የሚባለው የግንቦት 7 ልሳን በሕዝብ ገንዘብ ከሚቀልድ ሚዲያውን ለሕዝብ አገልግሎት ማዋል ነው፡፡ ሚዲያዎች ህዝብን በመረጃ ለማነጽም ሆነ አመራር ለመስጠት ወሳኝ ናቸው፡፡ ኦኤም ኤን ተመክሮ ይሁን ሁኔታውን ለመጠቀም ብዙ መሻሻል ይታይበታል፡፡ ግን ገና ብዙ ይቀረዋል፡፡ ብዙ ጸረ ኢትዮጵያ የሆኑ ዛሬ የኢትዮጵያ ጉዳይ እያሳሰባቸው ነው፡፡ ከመጀመሪያውም ተናግሬ ነበር፡፡ ማንም ኢትዮጵያዊ ከኢትዮጵያዊነት በታች ኢትዮጵያ ውስጥ የመኖር እድሉ አደጋ ላይ፡፡ ኦሮሞ፣ ኦሮሞ፣ እያሉ የኦሮሞን ሕዝብ ከኢትዮጵያዊነት አምክነው ለወያኔ የጣሉት ከወያኔ ጋር ኦሮሞ ነን ባዮች ናቸው፡፡ ወያኔ ይህ ስለተሳካላት 27 እድል አገኘች፡፡ ኦሮሞ ኢትዮጵያነት ከእኔ በላይ ማለት ሲጀምር በፍርሀት መናድ ጀመረች፡፡ ሚስጢሩ ይሄው ነው፡፡ ባንዳን አገር ዋዳዶች ያስፈሯታል፡፡ አሁንም ግን ገና ነው፡፡ የአባቶቻችንን አጥንትና ደም ነው የተሳለቅንበት፡፡ ኢትዮጵያዊነት በደምና አጥንት የኖረ ነው ስንል መሳለቂያ ሆኗል፡፡ አገርን የገነቡ ከጠላት ጠብቀው ለትውልድ ያኖሩ ጀግኖች በወራዶች አፍ ተሰደቡ፡፡ ሚኒሊክና ጎበና የወራዶች አፍ ማሟሻ ሆኑ፡፡ ወሮበሎች ከበሩ፡፡ ከሚኒሊክ ጀምሮ በጦር ትምህርት ቤትነት የሚታወቀው ሆለታ ጦር ትምርት ቤት ሥሙ ተቀይሮ በወንበዴ ሥም ተሰየመ፡፡ ኃይሎም አርዓያ የሚባል ወንበዴ እንጂ ኢትዮጵያ ኃይሎም አርዓያ የሚባል ጀግና ኖሯት አያውቅም፡፡ መለስ ዜናዊ የተባለው ወንበዴ ሲሞት ጭራሽ እንዲመለክላቸው ፈለጉ፡፡ የመለስ ፓርክ በሚል ቀበሌ ሳይቀር የጣዖት ስፍራ አኖረች፡፡ የሆነውና እየሆነ ያለው ሁሉ እንዲህ ነው፡፡

ኢትዮጵያውያን ሁሉ በነገሮች አትባዝኑ፡፡ ትኩረታችሁን ሁሉ ይሄን ወሮበላ ቡድን ከምድረ ገጽ ማጥፋት ላይ ይሁን፡፡ ልዑል እግዚአብሔር ይረዳናል፡፡ እኛ ግን ከልብ መቆም አለብን!

ልዑል እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይጠብቅ! አሜን!

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.