ታሰሪዎቹ አልተፈቱም – ታሪኩ ደሳለኝ

አንድ ላይ በቤሮቸው ከ 1 ሰአት በላይ ከናገሯቸ በኃላ መልሰው ወደ እስር ክፍሎቻቸው አስገብተዋቸዋል።

* ለምን ወልዲያ ሄዳችሁ
*የኮማንድ ፖስቱ ነገር

ዛሬ መጋቢት 17/2010 ዓም የደሩበት እስር ቤት ሄደን የጠየቅናቸው ሲሆን ወንዶቹ በኮማንድ ፖስቱ ከተያዙ ጋር በአንድ ክፍል ውስጥ ከክፍሉ አቅም በላይ በሆነ መልኩ 90 ሆነው እንደታሰሩ እና ቁጭ ብለው እንዳደሩ ነግረውናል። ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ብቻ ወገቡን ስለሚመው እንዲተኛ ተደርጓል። 70ዎቹ ከኦሮሚያ ክልል በኮመንድ ፖስቱ ያተያዙ ሲሆን አስሮቹ ደግሞ የሞባይላቹሁን የፊት ገፅ በባንዲራ አድርጋቹሀል ተባለው በኮማንድ ፖስቱ የተያዙ ናቸው።

ማህሌትና ወይንሸት በአንፃራዊነት ትንሽ የመተኛት እድል አጊንተዋል።

እንዲሁም ተመስገንን፣ እስክንደርን፣አንዷለምን ለምን ወልዲያ ሄዳችሁ ተብለው እንደተጠየቁ አውቀናል።

አሁን ጉተራ በተለምዶ ፔፕሴ የሚባለው ፖሊስ ጣቢያ ይገኛሉ።

ተመስገን ደሳለኝ
እስክንድር ነጋ
አንዷለም አራጌ
ዘላላም ወርቃገኘው
ወይንሸት ሞላ
ማህሌት ፍንታሁ
በፍቃዱ ሀይሉ
ስንታየሁ ቸኮል
ይድነቃቸው አዲስ
አዲሱ ጌታነህ
ተፈራ ተስፋዬ

መጋቢት 17/2010 ዓም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.