ዶ/ር አብይ አህመድ – አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር! (ዳዊት ከበደ ወየሳ)

(ኢ.ኤም.ኤፍ) በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የቀጣዩ ጠቅላይ ሚንስትር ጉዳይ ከጥቂት ሳምንታት ስብሰባ በኋላ፤ ዛሬ ምርጫ ተካሂዶ ዶ/ር አብይ አህመድ የኢህአዴግ ሊቀመንበር በመሆን ተመርጠዋል፤ ይህም በድርጅቱ አሰራር መሰረት የድርጅቱ ሊቀ መንበር በቀጥታ ጠቅላይ ሚንስትር ስለሚሆን፤ ቀጣዩ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር መሆናቸው ታውቋል።

በዚህ ምርጫ ወቅት የብአዴኑ ደመቀ መኮንን እራሳቸውን ከምርጫው አግልለዋል፤ የህወሃቱ ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን በውድድሩ ውስጥ ገብተው 2 ድምጽ ብቻ አግኝተዋል፤ ከደቡብ ሽፈራው ሽጉጤ 59 ድምጽ ሲያገኝ፤ ዶ/ር አብይ አህመድ ደግሞ 108 ድምጽ በማግኘት አሸናፊ መሆኑ ታውቋል። የብአዴኑ ደመቀ መኮንን የኢህአዴግ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ይቀጥላሉ።

ይህ ምርጫ እና ውጤቱ በጉጉት እንዲጠበቅ ያደረገው፤ በራሱ በኢህአዴግ ውስጥ የተፈጠረው የርስ በርስ አለመግባባት ነው። የዚህ የምርጫ ውጤት የሚያሳየው… በተለይ እራሱን የበላይ በማድረግ የአገሪቱን ፋይናንስ፣ መከላከያ፣ ደህንነትና ፖሊስ ኃይል፤ ለመቆጣጠር ሰፊ ትግል ያደረገው የህወሃት ቡድን መሸነፉን ነው። ዶ/ር አህመድ አብይ ወደ ስልጣን እንዳይወጣ፤ ህወሃት እና ደጋፊዎቹ ሰፊ ዘመቻ አድርገው ነበር። ይህ ምርጫ የህወሃትን ዘመቻ ጭምር ያከሸፈ መሆኑ ግልጽ ሆኗል።

ይህን በተመለከተ ዝርዝር ዘገባዎችን እናቀርባለን።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.