በመከላከያ ሰራዊት የተገደሉት የአኝዋክ ተወላጆች 2ሺ 500 ያህል እንደነበሩ ታወቀ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 19/2010)ጋምቤላ ውስጥ በመከላከያ ሰራዊቱ የተገደሉት የአኝዋክ ተወላጆች 2ሺ 500 ያህል እንደነበሩ የቀድሞ የጋምቤላ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ኦኬሎ አኳይ ገለጹ።

በሶስት ቀን ብቻ የተገደሉት 424 ወንዶች ሲሆኑ፣164 ሴቶች በመከላከያ ሰራዊት አባላት መደፈራቸውንም በቅርቡ ከወህኒ የወጡት አቶ ኦኬሎ አኳይ ዘርዝረዋል።

በታህሳስ 1996 በጋምቤላ ጭፍጨፋ በተካሄደበት ወቅት የክልሉ ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ ኦኬሎ አኳይ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ የወቅቱን ጭፍጨፋ በዝርዝር ተመልክተዋል።

ከኖርዌይ ወደ ደቡብ ሱዳን ያደረጉትን ጉዞ እንዲሁም ደቡብ ሱዳን ውስጥ ታፍነው ወደ ቃሊቲ ወህኒ ቤት የተወሰዱበትንና በወህኒ ቤት የቆዩበትን ሁኔታ በዝርዝር ለኢሳት ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.