ኢስላማዊ መንግስት ሊመሰረቱ ሞክረዋል በሚል በሃሰተኛ ወንጀል የተከሰሱትና በእነ አቡበክር አብደላ መዝገብ የተካተቱት ግለሰቦች ከ 4 እሰከ5 አመት በሚደርስ የእስር ጊዜ ተቀጡ

ቢቢኤን) በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች “ሃይማኖታዊ ዓላማን ለማራመድ በመንግስት መመራት የለብንም፣ ለመንግስት ግብር ሊከፈል አይገባም እና እስላማዊ መንግስት መመስረት አለብን” በማለት ተንቀሳቅሰዋል በሚል ሃሰተኛ ክስ በፌደራሉ አቃቤ ህግ ክስ የተመሰረተባቸውና በእነ አቡበክር አብደላ መዝገብ የተካተቱ ግለሰቦች የቅጣት ውሳኔ እንደተላለፈባቸው ታወቀ።

ኢስላማዊ መንግስት ሊመሰረቱ ሞክረዋል በሚል የተከሰሱት በእነ አቡበክር አብደላ መዝገብ የተካተቱ ግለሰቦች ዛሬ መጋቢት 19/2010 ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት 4ተኛ ወንጀል ችሎት በመገኘት የቅጣት ውሳኔ ለማድመጥ በተቀጠሩት መሰረት ውሳኔ ተሰጥቷል።

አንደኛ ተከሳሽ አቡበክር አብደላን ጨምሮ፤ በመዝገቡ 2ተኛ፣3ተኛ፣6ተኛ፣8ተኛ፣10ኛ ተከሳሾች ባስገቡት የቅጣት አስተያየት ላይ አፈፃፀምን በተመለከተ ” ሰው ሰራሽ ህጎችን አለመከተልን እንጂ ሌላ ጉዳት አላደረስንም” በሚል ያቀረቡትን አቤቱታ ፍርድ ቤቱ ተቀብሎ እርከኑን “ዝቅተኛ” ብሏል። እንዲሁም የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውን ከመኖሪያቸው ወረዳዎች ባቀረቡት መሰረት ከተያዘላቸው እርከን 20 ወደ እርከን 18 ዝቅ እንዲል አድርጎላቸዋል። አፈፃፀሙና ጊዜው ከ 2006 ቡሃላ ስለሆነ በመመሪያ 2/2006 እንዲቀጡም በማለት ፍርድ ቤቱ ወስኗል።

የፌደራሉ አቃቢ ህግ በፀረ ሽብር ህጉ 652/2001 አንቀፅ 7/1 በመጥቀስ ሃይማኖታዊ መንግስት ሊመሰርቱ ነበር የተባሉት ተከሳሾች የ 4 ዓመት ፅኑ እስራት የተበየነባቸው ሲሆን የተቀሩት ደግሞ በሌሉበት የቅጣት ማቅለያ ስላላስገቡ የ 5 አመት ፅኑ እስራት የተላለፈባቸው ሲሆን ጉዳያቸው በሌሉብት እየታየ ያለባቸው ግለሰቦች በስተቀር አብዛሃኛዎቹ ተከሳሾች ማረሚያ ቤቱ በሚሰጠው አመክሮ መሰረት በቅርቡ ከእስር እንደሚለቀቁ ታውቋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.