ታላቅ ክብር ለአቶ ገዱ አንዳርጋቸው (ዠነበ ዐናት)

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

ብዙውን ጊዜ ብዙዎች ብአዴን በድን ነው ይላሉ እኔ ግን በዚህ እንደማልስማ በተለያዩ ጊዜያቶች በቪዲዮ መልእክቶቼ ላይ አስቀምጬዋለሁ ይህንንም ስል ብአዴን በውስጡ ችግር የለበትም ማለቴ አይደለም ። እንዲያውም ከማንኛውም ድርጅት በላይ የትግራይ አፓርታይድ ስርዓት ሴራ ተጎንጉኖበት ያለበት እንደ ብአዴን የለም ። ሆኖም ግን በዚህ ሁሉ አስቸጋሪ መንገዶች አቶ ገዱ ብዙ አመርቂ ስራዎችን ሰርተዋል ።

ታዲያ በዚህች ትንሽ ጭላንጭል አየር በመጠቀም የአማራውን መብት በማስጠበቅ ደረጃ እንዲሁም የአማራውንና የኦሮሞውን ህዝብ በማቀራረብ ቁጥር አንድ ስፍራ የሚይዙት የክልሉ ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ናቸው ።

አቶ ገዱ ከዚህ ቀደም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትን ወደ አማራ ክልል በመጥራትና የሁለቱን ህዝቦች ወንድማማችነት በማቀራረብ ታላቅ የሆነ ስራ መስራታቸው አይዘነጋም በዚህም ስራቸው በከፍተኛ ሁኔታ የተበሳጩት የትግራይ አፓርታይድ ሰዎች የሁለቱን ህዝቦች ወንድማማችነት መርህ አልባ ግንኙነት በማለት ለሁለቱ ታላቅ ህዝቦች ያላቸውን ንቀት ከማሳየታቸው በላይ በተለይ በትግራይ ባለስልጣናት ጥርስ ከመነከስ በተጨማሪ ከስልጣናቸው ለማስወረድ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉ ቢሆንም አቶ ገዱ በብአዴን ውስጥ ባላቸው ተሰሚነትና በሳል አመራራቸው የህወሓት እርሳቸውን ከስልጣን የማስወረድ ሴራ ሊሳካላቸው አልቻሉም ።

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አሁን ደግሞ ሰሞኑን በተካሄደው የኢህአዴግ ሊቀመንበር ምርጫ ላይ የድርጅታቸውን ከፍተኛ አመራሮች ከበረከት ስምኦን ላይ በመነጠል የብአዴን ድምፅ በአጠቃላይ ለዶክተር አቢይ እንዲሄድ በማድረግ የሁለቱን ህዝቦች ወንድማማችነትና ፍቅር ወደ ማይበጠስ ደረጃ ላይ ያደረሱት ታላቅና በሳል መሪ ናቸው ።

በተለይ ይህ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ምርጫ አቶ ገዱ ከማንም በላይ ለዶክተር አቢይ መመረጥ ጉልህ ሚና የተጫወቱ ታላቅ ሰው ናቸው ። እንደሚታወቀው እነ በረከት ስምኦን ጭምር በማስፈራራትና በመደንፋት እንዲሁም በግል በመጥራት ድምፃቸውን ለሺፈራው ሽጉጤ እንዲሰጡ ለማድረግ ቢሞክሩም አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በተቃራኒው ደመቀ መኮንን ከምርጫው ሂደት ራሱን እንዲያገል በማድረግና የብአዴን ድምፅ ለዶክተር አቢይ እንዲሄድ በማድረግ ከስልጣን ጥመኝነት ይልቅ ለወንድማማችነት ቅድሚያ በመስጠት ከማንም በላይ ጉልህ ሚና የተጫወቱና የትግራይ አፓርታይድ ሴራን ብጡስጥሱን ያወጡት ጀግና ናቸው ።

አቶ ገዱ ክብር ይገባዎታል ።
ዘነበ ዘ ቂርቆስ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.