ኢህአደግ የህዝብ አስተሳሰብ  ፍላጎት፣  የልብ ትርታ  ባለማዳመጡ ፣ ባለማንበቡ የፈጠረበት  ጣጣው ?  (አስገደ ገብረስላሴ)

የኢህአደግ ስርአት  ብቻው በዝግ ቤት  ከሚናጥ የ100 ሚሊዮን ህዝቦች የልብ ትርታና  ፍላጎት ቢያዳምጥና  በሀገራችን  ያለው ችግር  በመፍታት አቅም አላቸው የሚባሉ  ዜጎች በማሳተፍ  ለዘለቄታ የአስተሳሰብ የፓሊሲ  መሰረታዊ  ለውጥ ለማምጣት ቢሰራ ለዝህች ሀገርና ህዝቦቻ ፣ለኢህአደግም ፓርቲዎች  ይበጅ ነበር !!!

ኢህ አደግ ደርግን  አስወግዶ  ስልጣን ከያዘበት ዘመን  ጀምሮ እስከአሁን  በዝህች አገር የጥይት ድምጽ፣ሞት፣ትርምስ፣ስደት፣በዜጎችበሀይሜኖቶች፣ በቢሄር ፣በዘር ፣ ግጭት  ተለዩቶባት አያውቅም።
ኢህአደግ ግን  መጀመሪያ  ለማስመሰል ፍጹም ዲሞክራሲያዊ  በመምሰል ሁሉም አይነት መብቶች ፣የዜጎች ዲሞክራሲያዊ ተሳትፎ እንደሚፈቅድ እርግጠኛ ሆኖ ቃል ይገባ ነበር ። የመንግስት ቡዙሀን መገናኛዎችም  በአዋጆች ተጠምደው  ።

ኢህአደግ ግን መጀመሪያ  ንቁ የሆኑ  ዲሞክራሲያዊ  ጥያቄ  ያነሱ ለነበሩ ከበረሀ ተሸክመውት  የመጡ የራሱ ታጋዮች  በአስር ሽ የሚቆጠሩ  አሰራቸው አባረራቸው ። ቀጥሎ ምንም እንከን ያልነበራቸው በፋሽሽታዊው ደርግ ቢሮክራሲ   ወይ በግድም በውድም  ለመኖር ሲሉ ደርግን  ያገለገሉት   ለነበሩ ንጹሀንና  ወንጀለኞች ሳይለይ በታተናቸው  ለሰደት ቤተሰቦቻቸው ለመበታተን እንዲዳረጉ አደረጋቸው ።

ቆየት ብሎ መጀመሪያ ከበረሀ  እንደገባ  የተለያዩ ጸረ ደርግ የነበሩ ፓርቲዎች በወቅቱም የተለዬ ሀሳብ ይዘዉ የተደራጁ ባሉበት የሸግግር መንግስት እመሰርታለሁ ብሎ አወጀ ። በመሰረቱ  ያ አዋጅ አይከፋም ነበር ።

ኢህአደግ ግን በገባው ቃል እና ባወጃቸው አዋጆች አልጸናም ። በሽግግር መንግስት  የሚሳተፉ ፓርቲዎች ወዳጅና ጠላት በመለዬት በአንድ አንድ ከ1964 ዓ ፡ም ጀምረው ጸረ የነበሩ ስርአቶች የተደራጁና በነፍጥ ከደርግም  ከህወሓት  ሲፋለሙ የነበሩ በበረሀ በነበራቸው ግጭት ቂም በቀል በመያዝ ወደ ሽግግር መንግስ እንዳይ ገቡ ከልክሎ በውግያ ተፋለማቸው ። ሌሎቹም በሽግግር መንግስት ተሳትፈው  የነበሩም በተለያዩ  መንገድ ከሽግግር መንግስት እንዲባረሩ ተደርጎ በኢህአደግ  እና በሌሎች   ፓርቲዎች በጦርነት  ተጠምደው ወደ ከባድ ፍልምያ ገቡ ።

ኢህአደግ እና ሌሎች ፓርቲዎች ወደ  አላስፈላጊ ጦርነት ገብተው ሲተላለቁ  ቂም በቀሉም ወደ ህዝቦች ወርዶ ወደ ህዝብ ጥላቻ መተላለቅ ገባ ። እነዛ ፓርቲዎችም ከኢህአደግ ያላቸው ቅራኔ በአግባቡ እንደመፍታት ፈንታ ፣ህዝቡን በዘር ፣በሀይማኖት ፣በጎጥ በመለያዬት በህዝቦች መካከል ቂምበቀል ጥላቻ  ተሰፋፋ ። በቃ ኢህአደግ በፈጠረው የቂም በቀል  ጥላቻ የኢህአደግ  ተቃዋሚዎችም  ለኢህአደግ ሴራ በሳይንሳዊ ፓለቲካዊ መንገደ ተከትለው እደመፍታት ፈንታ ኢህአደግ በሚፈልገው መንገድ እየተነዱ ፣አንዱን ቢሄር በሌላው ቢሄር  ጥላቻ እንዲያሳድር ፣ድሀ ለድሀው  የመደብ  ወንድሙ እንዲጨፈጭፍ አድርገዋል።እያደረጉም ይገኛሉ።

አሁን ተፈጥሮ ያለው  ትርምስ ፣የዘር የቢሄር ግጭት አለመተማመንም  ፣በኢህአደግ አባል ፓርቲዎች እና አጋሮቻቸው ወደ ወረደ  ጥላቻ ፣መከፋፈል ፣ በውስጣቸው ያለው ቅራኔ ወደ ህዝብ ዘልቆ የእሳት ሰደድ እንዲፈጠር  በማድረግ  በህዝቦች ጭንቅላት የማይፋቅ ለምጥ በመፍጠር ፣በሀገራችን ሁሉ አቀፍ ስጋት እንዲፈጠር አድርገዋል ።
እነዚህ  ባለስልጣናትና ፓርቲዎች አሁንም 27 አመት ሙሉ ከፈጠሩት ስህተት  ተምረው  ተፈጥሮ ያለው ሸግር  በየደረጃው  ያለው ህዝብ ፣በተለይ ለሸግሩ በመፍታት ወሳኝ ሚና ያላቸው  በሙያም በተሞኩሮም የተካኑ ወገኖች ከየትም ይምጡ ፣የሆነ አመለካከት ይንሩዋቸው ላገራቸው ፣ለህዝባቸው ፣ለህሊናቸው የሚያስቡ ተመራማሪዎ ፣ዜጎች አሳትፈው ሳይንሳዊ መፈትሄ አንዲገኝ እንደመጣር ፈንታ  ፣27 አመት የተከተሉት የወደቀ የግርጭት የአፈታት ዘቤ ተከትለው  ቤት ዘግተው ብቻቸው  ባለህበት   እርገጥ  እያሉ ላለፉት ዘመናት  እየደገሙ ይገኛሉ ።
በአሁኑ ጊዜ   የኢህአደግ  ስርአት ባመነበት ራሱን በፈጠረው  የሙስናና የመልካም አስተዳደር እጦት  ፣ያልተመጣጠነ ንሮ ፣የውሼት የልማት  ዳታ  በመሳራጨት ህዝብ ማታለላቸው   ባመጣው ጠንቅ ፣በሁሉም አቅጣጫ በፈጠሩት ቂም በቀል እና ፍጅት  ፣የኑሮ ውድነት ህዝብ ከአቅሙ በላይ በሆነበት  አሁንም በቅንነት ለመፈትሄው እንደመጣር ለራሳቸው መኖርና አለሞነር  ብቻ ታሳቢ በማድረግ   ስለህዝብ  በሰላም መኖር አለመኖር ደንታ የሌላቸው ኢህአደጎች ፣
የወረደ ፦ እጅጉን አስቅኝ የሆነው ደግሞ በአሁኑ ጊዜ የጠቅላይ ምኒስቴር  ሀይለማርያም ደሳለኝ ከስልጣናቸው  መውረድ ተከትሎ  ክፍተት  ለሞምላት በማለት   ያች ስልጣን ለመጨበጥ  ሲሉ ፣ ግማሾቹ በከጅቢ  አጃቢነት  ፣ግማሾቹ በሲ አይ ኤ   አጃቢነት እና ተጽእኖ  ወንበራ ማንን ያዘ በማለት እንድ የኳሳን ጎል አግቢ  ጎል ለማስገባት  እንደሚሮጥ  ሁሉ  ወደ ጠቅላይ ምንስቴር ወንበር ጎል ለማስገባት ይሯሯጧሉ ።

ይህ  ሩጫ ግን  ቢሮጡ ቢሮጡ ከ100 ሚሊዮን የኢትዮጱያ ህዝቦች  ጋር በአይዶሎጂ ፣በፓሊሲ ፣  በአሰራር  በማህበራዊ ፣እኮኖሚ  አኗኗራቸው የተራራቁ  ሆነው ፣ስለእማይናበቡና መሰረታዊ የሆነ  ሩቅ ልዩነት ስላላቸው   ውጤቱ ባዶ ነው ።  ምክንያቱ ኢህአደግ 27 አመት ሙሉ በኮሚንስት አይዶሎጂና ኢኮኖሚ ፓሊሲ ጭቃ ተነክሮ ስለመጣ በተጨማሪ ኮሚንስት ለህዝብ  ወዳጅና ጠላት ፣ማኸል ሰፋሪ በማለት ስለሚከፋፍል ጭራሱም  ፣ ጸረዲሞክራሲ እና በሙሱና የህዝብ ሀብት ስለሚዘርፍ  ።   ህዝቡ ደግሞ በመሉ በራሱ መዋቅር ሳይቀሩ የካፒታሊዝም  አይዶሎጂና ነጻ ኢኮኖሚ ፓሊሲ ስለሚያምኑ ፣ የኢህአደግ ሰርአትና የኢትዮጱያ ህዝቦች ግንኜታቸው  ሆድና ጀርባ ናቸው ። በፍጹም አይስማሙም ።

አሁንም ኢህአደግ የጠቅላይ ምንስቴር ወንበራ ለመያዝ ቢሯሯጡ  ሀይለማሪያም ወርደው ደመቀ መኮነት ቢመጣ ወይ ዶ/ አብይ ቢመጣ ፣ወይ ሽፈራው ሽጉጤ ቢመጣ ፣ወይ አያደርጉትም እንጅ ፣አፋር ፣ሱማል ወይ ከሌላ ቢሄሮች ቢመጡ ሁሉም  ከኢህአደግ   የኮሚንስት   የኮሚኒስት ሳጥን  ውጭ ሊሆኑ አይችሉም   የሚል እምነት አላቸው  ።

በሌላ በኩል የኢትዮጱያ ህዝብ በሙሉ የኢህአደግ ባለስልጣናት ለስልጣን ሽኩቻ እንደሚሮሯጡት ሁሉ ስልጣን ወደ  ኦሆዴድ ትምጣ  ወይ በአዴን ይውሰዳት  ሱማል  ወይ አፋር   ይውሰዳት ቡዙ ትርጉም አይሰጠውም ።ሌላ ቀርቶ  የትግራይ ህዝብ ከህወሓት  ጋር የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽ ናቸው የሚባልለት   ከህወሓት ወደ ስልጣን እንዲመጣ አይፈልግም ።አንዳው ደጉተር አብይ ቢመጣ የሚሉ እጅግ ቡዙ ናቸው ። ይህ ስል ግን ከህወሓት መሪዎች የጥቅም ትስስር ያላቸው በጣት የሚቆጠሩ  የጠቅላይ ምኒስቴር ቦታ ከትግራይ መውጣት የለባትም የሚሉ ሰዎች ኣሉ።

ሌላ ግን የበአዴንና የኦሆዴድ ደጋፊ የሆኑ ወገኖች የራሳቸው ሰዎች ወደ ወንበራ እንዲመጡ ቤት ለቤት እዬዘሩ የሚሰብኩ አሉ ። እነዚህ ፍጡራን ስለክብራቸው  የበላይነት ይመለከታሉ እንጅ  በአጠቃላይ በኢትዮጱያ ህዝብ ያለው ሽግር እንዴት  ይፈታ የሚል  የሚገባቸው አይደለም ።

አሁንም የኢህአደግ አባል ፓርቲዎች  ባለፈው ጊዜ ከአንድ አመት በላይ በደረጉት ግምገማ  የእተናጡ በሚዲያዎቻቸው  ፊት  ቀርበው  ሲናዘዙ እንደከረሙ  ህዝብም በትእዝብት እንደአስገባው ነው ።
እንዳውም ባለፈው  27 አመታት በኢህአደግ በቡቁ ሳይንሳዊ አመራር አደግን ተመነደግን እያሉን ከርመው  ሁሉም ውሼት መሆኑ በመቀበል 27 አመት ሙሉ ትክክለኛ እስትራተጅካዊ አመራር በለመሰራታችን  ህዝባች ጎድተናል ።በውሼት የልማት ዳታ ህዝብ አታልለናል ። ቂም በቀለኞች ቡዙ ዜጎች ጎድተነናል ። ጸረ ዲሞክራሲና ኪራይ ሰብሳቢነት ፣ሙሱና አስፋፍተናል ። የዜጎች ዲሞክራሲያዊ ተሳትፎ አፍነናል ። አገሪቱ ቡቁ ዜጎች በመሳተፍ  ልተመራና ለመተካካት በዎች እንዲበቁ አላደረግንም ። የሀገራችን ሀብት ከሌቦች ባለሀብቶች ከቤተመንግስት እስከ ቀበሌ ኔት ወርክ በመዘርጋት ጉዳት አድርሰናል ። ለተቃውም ፓለቲካ በነጻ የመንቀሳቀስ መብት 27 አመት ሙሉ ገድበናል ወዘተ በማለት ቡዙ
ተከልክለው የኖሩት ተነግረዋ ። የአሁኑ ይባስ ግን ሁሉም ነገር ተዘግተዋል ። ስለዚህ የገባው ቃል በሙሉ ወይ 100% ተዘግተዋል ።
ከአስገደ ገብረስላሴ
12 /07  /2010

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.