„ኢትዮዽያዊነት ሱስ ነው“ የወለደው የሎሬቱ ታቦተ – ዕንቡጥ! (ሥርጉተ ሥላሴ …የሳተናው አምደኛ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 09.04.2018 (ከመነኩሴዋ ሲወዘርላንድ)

„እግርህንም፡ ወደ፡ ፍቅር፡ አንድነት፡ ጎዳና፡ አቅና፡ የአግዚአብሄር፡ ዓይኖች፡ ወዳጆቹን፡ ይመለከታሉና፡ ጆሮውም፡
ልመናቸውን፡ ይሰማልና፡ ፍቅርን፡ ፈልጋት፡ ተከተላት። (መፅሐፈ መቃብያን ቀዳሚው ምዕራፍ ፳፪ ቁጥር ፪)

  • መነሻ።

https://www.youtube.com/watch?v=ROHm3nXvrCk

„ኢትዮዽያዊያን ያስደነቀው ወጣት“

  • !?!

ኧረ ስንቱን ሰማን ስንቱን ነገር አዬን? ስንቱን ተከዝንበት በስንቱን ሃዘን ገባን? ስንቱን መልካም ነገር በምን ያህል ገፋን? ስንቱን ጨርቅ ድሪቶ መጣጥፍ ተመኘን? ስንቱነን ደልድለን በስንት አባዛነው፤ በስንትስ ሸቀጥነው? ስንቱነን ከምረን ስንቱን ንደት አልነው? በምንያህል ተጓዝን ስንቱን ሰበሰብነው? ምንያህሉ ቀረን ስንቱን ተሻገርነው? ምን ያህሉን ሮጥን ስንቱን ጥለን ተጓዝን? ምንያህሉ ቀረን በስንቱ ተቋምን? ስንቱን ድልነሳነው በስንቱስ ተረታን? ስንቱ ገፋ አድርገን በስንቱ ተራመድን? ገልን ተሻግረን ስንቱን አባከነው? ስንቱን ፍቅር ሸሽተን በምን ያህልዋጋ ምን ያህል ቀበርነው? ቡናውን ጠጥተን ድንቅነሽን ትተን በስንቱ ኪሎ ነው ወደ ታች የዘገጥን? ስንቱን ሜትር መትረን በስንቱ ተሳን? ስንቱንስ አፍሰን ስንቱንስ ሰበሰብን? ስንቱን ዕንቁ ቀብረን መተት አሰኘን? በስንቱ ተጠዬቅ በስንቱ ተዳኘን? በስንቱ መማሰን ብክነትን ተመኘን? ስንቱን ሴራ አቅፈን ስንቱን ቅን አቀለልን? በምን ያህል ሚዛን ውስጣቸን አዘን? በራሳችን ፈቅደን በአሉታ ተጋለብን፤ ስንቱን ትልም አለምነው በህምስ ተባዝተን? ስንቱን ተኮራርፈን ስንቱን ቀን ገፋነው? በስንቱ ተስፋ ነው ምን ያህሉን ገበርን? በስንቱ ቀኝ ሄደን ግራ እንሁን ስንል፤ ስንቱን ራ ሽሽተን ከደባ ተጋባን? ስንት መከራ አለፈን ሰንቱን ተንከራተትን? ስንቱን እራብ ረስነት ውስጣችነን ረፍን? ስንቱን ምናምንቴ ድሪቶ ተሸከምን? ስንቱን ትውፊት አርክሰን ባለመሆን ተጋን? ስንቱን ሚስጢራችን በሸር ክር ጠለፍነው? ስንቱን ውበት ረስተን ተናጠል ተማጠን? ስንቱን ሰብል ስተን በድርት ተማዘዝን? ስንቱን እኛን ትተን በስንት አባዘነው? በምንያህል ርቀት ሽልንግን ቆጣጠርን ምን ያህል ቆፈርነው?

የኔዎቹ የማከብራችሁ ፣—- የቅኔው ልዑል ብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድህን ይሔውላችሁ ድንቅ መንፈሱ። ከውስጡ የሚንተገተገው ጉልበታም የኢትዮጰያዊነት ፍቅር፤ ከልቡ የሚንፎለፎለው ገናና ብሄራዊ ስሜት፤ ከልቡ የሚፈልቀው የደም ዋጋ ዕሴት ገድል የዛ አርበኛ ዓለምን ያስደመመ፣ የዓለም አዕምድ ርዕሰ ዜና የነበረው የዕድምታው ቀንዲል የጀግናው የኮ/ አብዲሳ አጋ ነው።

ይህን ለመገደብ የሚፈታተነው ወግድእልኝ እያለ በራሱ ውስጥ ለመኖር የቆረጠው ወጣት ኢትዮጵያዊነትን በሚስጢራቱ አዝምኖ ሆነበት። ቅኔውን ተቃኘው በሚያሰደምም ብቃትም በቀለበት። እንሆ ሎሬቱ አልሞተም ልጁነን ቀድሶ አስነሳ፤ ቃል ሥጋ ይሆን ዘንድ ዘመንም ፈረደ። ቀሰሰ የሎሬት ተስፋ እንደገና በብቁ ትውልድ ግርማ ለበሰና፤ ተሞገሰ ትናንት ታሪክ ቆመሰና፤ ተወደሰች ጥርኝ ነፃነት ናት እና!

ሎሬቱ አልሞተም አለ ይሄውና! በታቦቱ ብርታት ልጁን ቀደሰና ቅኔው ወረበ ተመስገን አለና። ተገኘ ነፃነት በሱስነት ግርማ። የቅኔው የኔታ ተነስተኽ ብታዬው፤ ይህን ቡቃያህን ማህሌት ታጎርሰው፤ ግን የኔታ አባቴ ይህን ዕንቡጥህን እንዲያው ምንስ ትለው? ተጠዬቅ የኔታ አንተን መሆን መቻል ምርቃት ትሰጠው?

የኔዎቹ አስኪ ይህን ወጣት የሎሬት ውስጡን – ህሊናውን – ብቃቱን – ልቅናውን – መሆኑን – ወኔውን ፍጥረተ ነገሩን ተቃኙት። የሚገርመው በታሪክ ሥነ – ግጥም ገንዘብ ሲሸለም ለመጀመሪያ ጊዜ አዬሁኝ። ወጣቶቹን እዮቸው ፍሰሃቸው – ሐሤታቸው ኢትጵያዊነት ብቻ ነው። ታፍኖ የኖረው በሐሤት በድል ጎኽ ፈነዳ፤ ታምቆ የኖረው ተነፈስ ዕድሜ „ለኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው።“ ይህን ለመቀማት መትጋት በውነቱ ከወንጀሎች በላይ ነው። የለማውን አብይ ጉዳይ ለማወቅ ዘመንን ይጠይቅ ሟርተኛው አያልቅበት ሁሉ ስንክሳሩን ይኮልም – ካልደከመው! የጣና ዘገሊላ ታምር የግዮን ሽልማት ይሄው ነው ገዱ! ይሄው ነው አንባው! „ኢትጵያዊነት ሱስ ብቻ ነው“ መንገዱ። በዚህ አጋጣሚ ሊቀ ሊቃውነቱን ፕ/ ዶር. ፍቅሬ ቶሎሳን እንኳን ደስ አለወት ማለትን ፈቀድኩኝ። ተሟሙተውለታል ለኢትዮጰያዊነት ዕጬጌው ማንነት። ለዚህ ነበር የተጉት። ተሳክቶላቸዋልም። በሥነ – ጹሑፍም ዘርፍ እንዲህ የመሰለ ተተኪ አፍርተዋል። ተመስገን። መኖር መልካሙ የሥነ – ህይወት ጥበቡ።

ይህ የህሊና አካል በሥነ – ውበቱ፤ በጥልቀት እናቱን ቀረባት፤ ውስጡን አጣጣመበት፤ መሆን ሆነበት፤ ጀግንነትን ሰፈነበት። ነገን አማተረ፣ ኢትዮጵያን ሲቀድስ ጽላቱን ሲሳለም፣ ሐሤቱ ገድለ – ታምራቱ ብጡል ነው ምዕቱ። ወስጡን በህብረ ቀለሙ አቀለመ። መኖሬን ወደድኩት ነገን ተሳለምኩት፤ መቼትን ቋጭቼ ዕድሜዬን ለመንኩት። ግን እኛስ የት ላይ ነው ያለነው? ይኽን ጉልበታም ቅኔ ቃናዊ ወስጥ ሞግተን መርታት እንችል ይሆን?! ተጠዬቅ ከራስ ጋር ይላል ቀኑም ሌሊቱም ቀጠሮ የለም ለዛሬ – ዛሬውኑ! ይህን የአናብስቱን ትንታግ ጽምጸት የአንበሳውን መንፈስ ከቶ ማሸነፍ ይቻል ይሆን? እጬጌው ሂደት ይመልሰው …

  • መዳረሻ።

አንተ የእኔ ደም መላሽ! ማርከሻ! ቅኔኛ የኔ ጌታ! ለዚች መከረኛ ፍዳዋ ለጠና „ጠይም አፈር“ እንኳን ተፈጠርክላት። ውድድድድድድ ++++++++++++ „መደመር መደመር መደመር መደመር“ ድልን ማነባበር፤ „መደመር መደመር መደመር አሁንም መደመር “ ታሪክን መመርመር። „መደመር መደመር መደመር ምንግዜም መደመር “ ውስጥን በመገበር። ትናንት „በመደመር“ ዛሬም „በመደመር“ ነገም „በመደመር“ አብሮነት ይቀመር! „በመደመር“ መርኽ ይበብልን ፍቅር፤ „መደመር“ „መደመር“ „መደመር“ „መደመር“ አደራን መዘመር! „መደመር“ „መደመር“ „መደመር“ „መደመር“ ድሉ ይነባበር።

„ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው!“

„ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ አራት ዓይናማ መንገዳችን ነው።

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።

የኔዎቹ በሉ የዚህን ትንታግ ልበሙሉ ወጣት ቅኔ ገጹንም እያያችሁ ይሁን ገላጭ፤ ታሪክ አቀራረብ ነው እና ያለው። እዬደገማችሁ፤ እዬሰለሳችሁ እንደ እኔ ኮምኩሙ መሸቢያ ጊዜ – ኑሩልኝን በመሸለም።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.