የፌደራል ጠ/አ/ህ በሽብር ወንጀል ተከሰው የሚገኙ የ114 ተከሳሾች ክስ እንዲቋረጥ ለፍርድ ቤት ደብዳቤ አስገባ

ቢቢኤን(BBN) የናንተው ድምፅ

የፌደራል ጠ/አ/ህ በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሽብር ወንጀል ተከሰው ጉዳያቸውን ለሚከታተሉበት ለ 19ኛ ወንጀል ችሎት እና ለ4ኛ ወንጀል ችሎት ደብዳቤ ማስገባቱ ታወቀ።

ዛሬ ሚያዚያ 3/08-10 ጠቅላይ አቃቢ ህግ ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በተለያየ የሽብር ወንጀል ተከሰው ጉዳያቸውን እየተከታተሉ ያሉ ተከሳሾች በአጠቃላዩ 114 ግለሰቦች ፋይላቸው ተቋርጦ እንዲለቀቁ በደብዳቤ አሳውቋል።

አቃቤ ህግ ክሳቸው ይቋረጥልኝ ያላቸውን የ114 ግለሰቦች መዘርዝር ለ19ኛ ወንጀል ችሎት እና ለ4ኛ ወንጀል ችሎት ፅህፈት ቤት ማስገባቱን ተከትሎ የችሎቱ ዳኞች ፌርማ አርፎበት ከዛሬ ጀምሮ ከማረሚያ ቤቶቻቸው ይለቀቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.