“የምኒልክን ቤት መለስ አረከሰው” (ከታምራት ይገዙ)

ይህንን ለመንደርደሪያነት የተጠቀምኩበትን ስንኝ (ግጥም መጀጀሪያ) የተዋስኩትና ስሙን ብቻ የለወጥኩት  የተገጠመላቸው የጥንቱ አርበኛ ለነበሩት ለአፄ ዮሐንስ ነበር::  እኔ ደሞ አገራችንን ኢትዮጵያን ከሀያ አመታት በላይ መርተዋትና በመጨረሻም ለሦስት  ክንድ መሬት የበቁት ነፍሳቸውን ይማረውና ሞቹ አቶ መላስ ዘናዊ ወደ አላስፈላጊና ወዳልተጠበቀ ቀውስ ውስጥ እንዳስገቡን ቡዙ ምሳሌዎች ማቅረብ ቢቻልም እዚህ ላይ መዘርዘሩ ግዜ ማጥፋት ስለሆነ ወደዛ ሳልገባ ስማቸውን ብቻ በመጥቀሰ አልፋለው :: ባይሆን ሰሞኑን የቡዙዎቻችንን ቀልብ የሳበው ዶ/ር አቢይ አህመድ ወደ ጠ/ሚ  መምጣት በተመለከተ እኔም የራሴን እይታ የሆኑትን ልበል::

ማንኛውም ፍጡር ለመኖር በመጠኑም ቢሆን እምነት ሊኖረው ይገባል: ጤነኛ ኑሮ ለመኖር እምነት ከኛ ጋር መኖር አለበት ያላአንዳች እምነት አብሮ መኖርም ሆነ አብሮ መስራት አይቻልም:  ስለ እምነት ለመጻፍ ያነሳሳኝ ዶ/ር አቢይ አህመድም ለጠ/ሚ መሾም እንዳንድ ውንድሞች እንደሚሉት ህወሃት ግዜ ለመግዛት ያደረገው ነው ሲሉ በተለያዩ የመገናኛ ቡዙሀን ትንታኔ ሲያቀርቡ በመስማቴ ነው::  እርግጥ ነው መጠርጠርና አለማመን  በተወሰነ ደረጃ ተገቢ ይመስለኛል በተለይ በአጼ ሀይለስላሴ የአገዛዝ ዘመን መጨረሻ ላይ ለተፈጠረ ትውልድና ከደርግ ዘመን ቦሓላ እስከ አሁኑ የህወሀት ዘመን የተወለዱ ኢትዮጵያኖች ቢጠረጥሩና በማንኛውም ሰው ላይ እምነት ባይኖራቸው በእኔ እይታ የሚፈረደባቸው አይመስለኝም::  ለምን ለሚለኝ እንደሚከተለው ልተንትን::

እኔ ተወልጄ ባደኩበት ሰፈር አቶ እገሌ የሚባሉ ሰው ነበሩ እኝህን ሰው የሰፈሩ ሰዎች በሽክሽኩታ እገሌ እኮ ነጭ ለባሽ ነው እያሉ ሲያወሩ ነው እየሰማን ያደግናው::  አንድ ቀን ነፍስ ካወቅን ቦሃላ በደርግ ዘመን መሆኑ ነው እንዱ አብሮ አደጋችን  ጋሽ እገሌ እኮ ነጭ ለብሰው አያቁም ለምንድ ነው ነጭ ለበሽ የምቱሎቸው ብሎ በመጠየቁ ነው በአጼ ሀይለስላሴ ዘመን ለነበሩ የስለላ ሰራተኞች የተሰጠ የቅጽል ሰም መሆኑን የተረዳናው::

ሌላው ደሞ በደርግ ዘመን እኔ በምኖርበት ቀበሌ ሳይሆን በጎረቤት ቀበሌ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ሁለት ወንድሞቻችን ይህን ዓይነት ስራ ውስጥ በመግባታቸው የሰፈር ልጆች እነዚህ ወንድሞች ጆሮ ጠቢ እያልን እንጠራቸው ነበር :: ቀሰ  ቀሰ እያሉ ግን እነዛ ሁለት ልጆች ስራቸውን አጠናክረው በመስራት ከየቀበሌው በጣት የሚቆጠሩ ወጣቶችን መለመሉ ደርግ አስረኛ አብዮቱን ካከበረ ቦሃላ መሆኑ ነው መሰለኝ ታክሲ ሹፌሮች ሁሉ ሳይቀሩ ጆሮ ጠቦዎች ሆነው ነበር::

ህወሀት/ኢህዓዴግ ስልጣን ሲይዝ ሳር ቅጠሉ ጆሮ ጠቢ ሆነ የወጣቶች ፎረም በማለት ወይም የሴቶች ፎረም  አሊያም የአዛውንቶች ፎረም በማለት ከየቤቱ አንድ ሰው ማግኘት ቻለ ለዚህ ይመስለኛል ታዋቂ የፖለቲካ መሪዎች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በየ አደባባዩ  ህወሀት/ኢህዓዴግ ህዝቡን አንድ ለአምስት በሚል መረሆ ጠፍንጎ ይዞታል እያሉ ይነገሩ የነበሩት:: እርግጥ እኔ በግሌ ይህንን ከሚሉ ታዋቂ የፖለቲካ መሪዎች ይህንን አልጠብቅም ምክንያቱም ድርጅትን እየመሩ ለተከታያቸው አንድ ላምስት ጠጠፍንገን ተይዘናል ሲሉ ያላስተዋሉት ነገር ቢኖር ተከተዮቻቸውን ፈሪ ማድረጋቸውን አለማወቃቸው ነው::

ይህንን በተመለከተ አንድ የድርጅት መሪ በምኖርበት ከተማ ለስራ ጉዳይ መጥተው በነበረበት ወቅት ካረፉበት ቤት እራት እየበለን ሰለ አንድ ለአምስት ጉዳይ አነሳሁባቸው እሳቸውም “ትክክል የሆነ ነገር ነው ሁሉም ያውቀዋ”  አሉኝ::  እኔም በዚህ መልክ ጠየኮቸው” እናንተ የድርጅት መሪዎች ሆናችሁ በየ አጋጣሚው ሁሉ ህወሀት/ኢህዓዴግ አንድ ላምስት የሚባል የመሰለያ ወጥመድ አለው ስትሉ እናንተን የሚከተሉ የድርጅት አባላቶች ሁሉ ከናንተ አንደበት የሚወጣውን በመስማት እውነትነት አለው በማለት ህወሀት/ኢህዓዴግ ለመታገል አይፈሩም ወይ ብላቸው ?” ፈገግ በማለት “እሱ ሊሆን ይችላል” በሱ መልክ አላየነውም ነበር ያሉኝ::

ከላይ ለማስረዳት የሞከርኩት በአጼ ሀ/ስላሴ ዘመን በሰፈር ውስጥ የነበሩት ነጭ ለባሾች (ህዝብ ደህነቶች) በጣት የሚቆተሩ የነበሩ ሲሆን በደርግ ዘመን የነበሩት ጆሮ ጠቢዎች (ህዝብ ደህነቶች) ከበቀበሌ ደረጃ ከፍ ብለው በታክሲ ሹፌርነት የተሰማሩት ሁሉ በመግባት በርከት እንዳሉ ነው በህወሀት/ኢህዓዴግ ዘምን ደሞ ከሰፈር አሊያም ከቀበሌ ሳይሆን ከቤተሰብ አንድ ሰው እንደሚኖር ነው::

ወደ ተነሳሁበት የሰሞን ዾ/ር አብይ በጠቅላይ ሚ/ር ነት መመረጥን በተመለከተ የሚስነዘሩት ፍራቻና ጥርጣሬ እየተሰማ ያለው ጆሮ ጠቢ በበዛበት ዘመን ከተወለዱትና ከአደጉት የህብረተሰብ ክፍል ሳይሆን ነጭ ለባሽ በሚባልበት ዘመን ወጣት ከነበሩ ወንድሞቻችን መሆኑን ሳስተውል በግሌ አግርምት ፈጠሮብኛል ምክንያቱም ጆሮ ጠቢ እንደ አሸን በፈላበት ዘመን ተወልዶ ያደግ ሰው ቢጠራጠር አሊያም በማንኛውም ሰው ላይ እምነት ባይኖረው ተወልዶ ያደገበት ስርዓት ውጤት  ስለሆነ አይፈረድበትም ባይ ነኝ:: እንድ ላምስት የሚባሉት ከመምጣታቸው በፊት በውጪ አገር መኖር የጀመረ ሰው ከሚገባው በላይ ሲጠራጠርና በተወሰነ ደረጃ እንኮን ማመን ሲያቅተው ለሁላችንም ግራ የሚያጋባ ነው::

በእኔ እምነት በተወሰነም ደረጃ ቢሆን እምነትና ተስፋ በአዲሱ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ላይ ማሳደር ያለብን ይመስለኛል ምክንያቱም እምነት የህብረተሰብ የጋራ ህብት ነው እምነት በህብረተሰብ መካከል ጥርጣሬን አስወግዶ መደጋገፍንና መተሳሰብን የሚፈጥር  ለመግባበትና አብሮ ለመስራት የመጀመሪያው ደረጃ ነው የሚል እምነት አለኝ:: ለዚህም ይመስለኛል ጠቢባን ” እምነት ህብራተሰብን የሚያቆራኝ ሙጫ ነው” ያሉት::

እኔ እንደማስበው እምነታችን የሚመነጨው ከራሳችን ውስጣዊ ስሜትና የሞራል ዳኝነት ነው ይህ ከሆነ ደሞ ሁላችንም እንደ ሰማነው ዶ/ር  አብይ በተመረጠበት ቀን ያደረጉት  ንግግር ያለፉትን ችግሮች በውይይት በመፍታት ወደ ፊት ሊመጡ የሚችሉትን ችግሮች ከሌሎች የተፎካካሪ ድርጅቶችና ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ለመወጣት ፍላጎት: ብቃትና ችሎታ እንዳላቸው ነው የገለጹት እንደ እውነቱ ከሆነ ቢያንስ ከሃምሳ ፐርሰንት በላይ የሚሆን ኢትዮጵያዊ ንግግራቸውን በአውንታዊነት ነው የተቀበለው የሚል እምነት አለኝ ይህ የሚያሳየው አባቶቻችን  <<ከአነጋገር ይፈረዳል ከአያያዝ ይቀደዳል>>እንደሚሉት መሆኑ ነው::  እንግዲህ ሃምሳ ፐርሰንት የሚሆነው ህዝብ በአነጋገሩ ፈርዶ ስልጣኑን <<ይሁንሎት>> ካለ ቀጥሎ ደሞ አያያዛቸው ታይቶ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚላቸውን እንሰማለን:: ባይሆን በሰማነው እምነት አሳድረን ወደ ተግባር ሲሄዱ በቅርብ እርቀት እየተከተልን የህዝቡን ጥያቄ እንዲመልሱ ድጋፍም ጫናም ማድረግ ነው ያለብን እላለው::

እርግጥ ነው በደርግ ዘመን ያለፍናቸው አስራ ሰባት  አመታት አንዲሁም በህወሀት ዘመን  ሀያ ሰባት አመታት እንዲህ በቀላሉ የሚረሱ እንዳልሆኑ ጠንቅቄ አውቃለው:: እንዚህ ሁለት መንግስታቶች በኢትዮጵያኖች ውስጥ ያለውን የመተማመንና የመከባበርና የአብሮ መኖርን አከርካሪ አጥንቱን ሰብረው እንደጣሉት ለሁላችንም ግልጽ ነው:: በተለይ በተለይ ንፍሳቸውን ይማረውና ሞቹ አቶ መለሰና ድርጅታቸው ህወሀት/ኢህኣዴግ  ከሁሉ የከፋ ዘመን ነበር ቢባል ማጋነን አይሆንም:: ሞቹ አቶ መለስ ትልቅ አገር እየመሩ የሳቸውን ትንሽነት ያሳዩበት ንግግር በትግራይ ያደረጉት ንግግር ነው ያን ንግግር “እኔ ከናንተ በመወለዴ” የሚለው ሲሆን ሌላው ደሞ ትንሽነታቸውን የሚያሳብቀው አባባል”የአክሱም ሃውልቶች ለደቡቡ ምኑ ነው” ያሉት ንግግርና እስከ ህይወታቸው ፍጻሜ ድረስ በስልጣን በቆዩበት ዘመን አገራችንን ኢትዮጵያን ያስተዳደሮት  “ይህች አገር” እያሉና አንዳሉ ነበር ለሶስት ክንድ መሬት የበቁት::

የዘመኑ እርበኞች ቄሮዎችና ፋኖዎች እስከ መሰዋትነት በስከፈለ ትግል እነ ዶ/ር አቢይ አህመድም እንደ ሰውም እንደ ድርጅትም ከህወሃት/ኢህኣዴግ አስከፊ አገዛዝ ሙሉ በሙሉ ባይባልም በከፍተኛ ደረጃ ነጻ የወጡበትና የሃገራቸውን ህዝብ በፈለጉት ሰዓትና ቀን ስብስበው ለማናገር የበቁበትና በአጼ ሀይለስላሴ ዘመን ዋጋ እንደነበረው ዓይነት ፓስፖርት ያወጡበት ሳምንታት ነው:: ጎሽ የዘመኑ አርበኞች ቄሮዎችና ፋኖዎች ይህ ፓስፖርት ለሁለም ኢትዮጵያዊ እንደሚደርሰን ተስፋ አደርጋለው::

ቡዙ ሰው እንደሚያውቀው በአጼ ሀይለስላሴ ዘመን ፓስፖርት የያዘ ሰው አንድ አውሮፓ አገር ውስጥ ከገባ እብዛኛው የአውሮፓ አገርን ያለምንም ቨዛ መግባትና መውጣት ይችል እንደነበር በዘመኑ ፓስፖርት የነበራቸው ሲያወጉ አድምጫለው:: የአውሮፓ አገሮች ኢትዮጵያዊያንን ቨዛ መጠየቅ የጀመሩት በደርግ ዘመን ነበር::

ክብር ለዘመኑ አርበኞች ቄሮዎችና ፋኖዎች ዶ/ር አቢይ አህመድ ይንን ፓስፖርት እንዲይዙ በማድረጋችሁ ምክንያቱም ሞቹ አቶ መለሰም ሆኑ አቶ ሀ/ማርያም ደሳለኝ እንድሁም ሁሉም የህውህውት አባላቶች አገራችንን ኢትዮጵያ ይህች አገር እንዳላሉ ሁሉ ዶ/ር አቢይ አህመድ ፓስፖርቱን እንደያዙ ነው እንደ ወሃ ሲጠማንና እንድ ምግብ ሲርበን የነበረውን የአገራችንን የኢትዮጵያ ስም በግማሽ ሰዓት ውስጥ ሰላሳ ሰባት ግዜ ሲጠሮት የሰማነው:: ይህ ሰላሳ ሰባት ግዜ የተጠራችው ኢትዮጵያ አገራችን እያንዳንዶ ቃል ለህወሀት መሪዎች በውስጣቸው ያለው የኢትዮጵያ ጥላቻ እንደ ፊኒጢጣ ቡግንጅ ከስሩ ፈንግሎ የሚያወጣላቸውና አለፍ ሲልም የሚፈወሱበትና ኢትዮጵያዊንተን የሚያገኙባት  ክትባት ነው:: ወደዱም ጠሉም አዲሱ ጠ/ሚ ዶ/ር አቢይ አህመድ ትዮጵያዊነትን ለህወሃት አመራሮች “እንቆቆ እንቆቆ” አሊያም  “ኮሶ ኮሶ” እያላቸው እንዲጋቱ ነው ያደረጋቸው የሚል እምነት አላኝ:: ዶ/ር አቢይ አህመድ  በመቀሌ ባደረጉት የአስራ አምስት ደቂቃ የትግርኛ ንግግራቸው ከአጠገባቸው ቆመው የነበሩት ዶ/ር ደብረ ጺዮን ስይወዱ በግድ ኢትዮጵያ የሚለውን ቃል ከአስር ግዜ በላይ ለማዳመጥ ተገደዋል::

ታድያ እዚህ ጋ ለአጼ ዮሃንስ የተገጠመወን ስንኝ ስሞቹን ለወጥ በማድረግ

“የምኒልክን ቤት መለስ አረከሰው

የጣይቱንም ቤት ህወሃት አረከሰው

አንተ አብይ ግባና በሞቴ ቀድሰው” ብልለት ከህወሃት ወጪ ያለ ሰው ቅር ይሰኝ ይሆን?::

ይህንን የሰላም ፓስፖርት በዘመኑ አርበኞች ቄሮዎችና ፋኖዎች ያላሰለሰ ትግል ስለያዙ ይመስላኛል  ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድም በተጎዙባቸው በጅጅጋም ሆነ በአምቦ እንዲሁም በትግራይ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ  ሆሳዕና በሚል ስሜት እየተቀበሎቸው ያለው እርሳቸውም የወጣቱን ውለታ በተወሰነ ደረጃ ለመመለስ ይመስላል በህወሀት መሪዎች የዘመኑን አርበኞች ቄሮዎችና ፋኖዎችን ቴሬርስቶች ስለሆኑ ክስ ይከፈትባቸዋል ብሎ እንዳላለ ሁሉ በአምቦ ንግግራቸው ለቄሮዎች ከአክብሮት ጋር ሰላደረጉት ትግል ምስጋና ያቀረቡት::  በእኔ እምነት የዘመኑን አርበኞች ቄሮዎችና ፋኖዎች የተደረገላቸውን አክብሮት ከልብ በመቀበል ድጋፋቸውን እየሰጡ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ቃላቸውን ጠብቀው የተናገሩትን አገራዊ መግባባትን ከሁሉም ቅድሚያ እንዲሰጡት ከአለፈው በበለጠ ለሰላማዊ ትግል መነሳሳት አለባቸው ምክንያቱም የተናገሩት ቃል ቃል ብቻ ሆኖ እንዳይቀር የዘመኑን አርበኞች ቄሮዎችና ፋኖዎች ትግላቸውን ወደ ምዕራፍ ሁለት  ማሸጋገር አለባቸው::

በመጨረሻም በኔ እምነት በአሁን ሰዓት ሊመለስ የሚገባው ጥያቄ ያለፈውን አመታቶች ለታሪክ ጻሃፊዎች ትቶ ዛሬን ምን ብናደርግ ነው ለነገ የተሻለ ስርዓት መስርተን ለልጆቻችን አስረክበን የምናልፈው ብለን እራሳችንን መጠየቅ ያለብን የሚመስለኝ::

እኔም የዛሬን ጹሁፈን ሆሳዕና በአብይ ጾም ለተገኘው አብይ እያልኩ እደመድማለው::

ፈጣሪ ቸር ያሰማን!

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.