ላንቺ ነው ኢትዮጵያ

ላንቺ ነው ኢትዮጵያ
ላንቺ ነው ኢትዮጵያ ላንቺ ነው …….ላንቺ ነው
ላነንቺ ነው ሃገሬ ላንቺ ነው………..ላንቺ ነው
ላንቺ ነው ኢትዮጵያ የተሰባሰብነው
ላንቺ ነው ሃገሬ እኛ የምንሞተው፡፡
ላንቺ ነው ኢትዮጵያ ላንቺ ነው……ላንቺ ነው
ላንቺ ነው ሃገሬ ላንቺ ነው…….ላንቺ ነው
ላንቺ ነው ነው ኢትዮጵያ የተሰባሰብነው
ላንቺ ነው ሃገሬ ደሜን የማፈሰው፡፡
በባርነት ሸክም ጀርባሽ የጎበጠው
በባለጌ መዳፍ ክብርሽ የጎደፈው
የስቃይሽ ስቃይ ሰማይ ለነደለው
አይንሽ እስኪጠፋ ደም የምታነቢው
ላንቺ ነው ኢትዮጵያ ህይወት የገበርነው፡፡
ወገን ደራሽ አጥተሽ ቅስምሽ ለተናደው
የመኖር ምኞትሽ ተሟጦ ያለቀው
ከውሻ ተሻምቸው ለሚያጡት ልጆችሽ
ለአለም ጨረታ ለቀረበው ፅንስሽ
ላንቺ ነው ኢትዮጵያ የደሙት ልጆችሽ፡፡
ላንቺ ነው ኢትዮጵያ ላነንቺ ነወ……..ላንቺ ነው
ላንቺ ነው ሃገሬ ላንቺ ነው………ላነንቸ ነው
ላንቺ ነው ኢትዮጵያ የተሰባሰብነው
ላንቺ ነው ሃገሬ እኛ የምንሞተው፡፡
ላንቺ ነው ኢትዮጵያ ላንቺ ነው……ላንቺ ነው
ላንቺ ነው ሃገሬ ላንቺ ነው………ላንቺ ነው
ላንቺ ነው ኢትዮጵያ የተሰባሰብነው
ላንቺ ነው ሀገሬ ደሜን የማፈሰው፡፡
የፈሰሰው አይንሽ በከሀዲዎች ጥፍር
በጅምላ ላጨዱት ለልጆችሽ ክምር
ለናዱት አንድነት ላረከሱት አገር
ለቀሙን ነፃነት ለጫኑብን ቀንበር
መልስ ሆኖ መጧል ደረትን ለአረር፡፡
በእምነት በመፅናትሽ ሀቅ መናገርሽ
ትናጋሽ ታፍኖ መናገር ያቃተሽ
መከራና ሀሳብ በማድያት ለኳሉሽ
የማታውቂው ባህር አስምጦ የተፋሽ
ላንቺ ነው ኢትዮጵያ የደሙት ልጆችሽ፡፡
ላንቺ ነው ኢትዮጵያ ላንቺ ነው…….ላንቺ ነው
ላንቺ ነው ሀገሬ ላንቺ ነው……..ላንቺ ነው
ላንቺ ነው ኢትዮጵያ የተሰባሰብነው
ላንቺ ነው ሃገሬ እኛ የምንሞተው፤
ላንቺ ነወው ኢትዮጵያ ህይወት የከፈልነው
ላንቺ ነው ሀሃገሬ የተሰባሰብነው
ላንቺ ነው አኢትዮጵያ ባንድነት የቆምነው
ላንቺ ነው ኢትዮጵያ እኛ እምንሰዋው
ላንቺ ነው ሃገሬ አእኛ እምንሰዋው ፡፡
አንዲ ህልምህን እውን እናደርጋለን !!!
ፍቱት አንበሳውን ! 

#FreeAndargachewTsige

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.