የትግራይ ልዩ ኃይል በትግራይ! (የታጣቂዎች ፍጥጫ በእምባስነይቲ)

የታጣቂዎች ፍጥጫ በእምባስነይቲ
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፡

የእምባስነይቲ ማእከል የሆነችው ነበለት ከተማ በትግራይ ክልል ልዩ ሃይል ታጣቂዎች ኣጥለቅልቃለች።

የልዩ ሃይል ሰራዊቱ ወደ እምባስተይቲ መግባት ተከትሎ የኣከባቢው ፀጥታ ኣስከባሪ ምልሾችም ህዝቡን ከጥቃት ለመከላከል በፍጥነት ተደራጅተው በተጠንቀቅ ቁመዋል።

ቅዳሜ (የነበለት የገበያ ቀን) 29 / 08/ 08 ዓ/ም የትግራይ ልዩ ሃይል መትረየስና ሌሎች ዘበናዊ ከባድ መሳርያ የተጫኑ ፒክኣፕ መኪኖች ከተማዋ እያጨናነቅዋት የዋሉ ሲሆን(ብዶንጎላ/በድንጋይ/ ጀነራል ማራኺ እንዳላሉት) ብዛት ያለቸው እግረኛ ታጣቂዎችም ኑዋሪዎችና ወጣቶች እያስቆሙ፣ እያንገላቱና እያስፈራሩ ውለዋል።

የልዩ ሃይሉ እንቅስቃሴ የተመለከቱት የኣከባቢው ምልሻዎችም በፍጥነት ተደራጅተው ወታደሮቹ በመጋፈጥ ሊያስቆሟቸው ጥረት ኣድርገዋል።

ፍጥጫው እያየለ በመሄዱና ወደ ግጭት ማምራቱ የማይቀር መሆኑ የተረዱት የኣገር ሽማግሌዎች ተሰባስበው በሁለቱ ሃይሎች መሃል ገብተው ፍጥጫው ለማቀዝቀዝ መኩረዋል።

የኣገር ሽማግሌዎች ወታደሮቹ ማንነታቸውና በምን ኣላማ ወደ ኣከባቢው እንደመጡ የጠየቋቸው ሲሆን “ከክልል ፀጥታ እንድናስከብር ተልከናል”የሚል መልስ ኣገኙ።
የኣገር ሽማግሌዎች ለወታደሮቹ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ተረድተው ” ወጣቶችና ኑዋሪዎች ማንገላታትና የማሸበር ተግባር ኣቁሙ” ብለው ገሰጿቸው።

ምልሾችም ” እኛ ከኣቅማችን በላይ የሆነ የፀጥታ ችግር ኣለንና ኣግዙን ሳንል ማን በጉልበቱ ላካቸው? ኣሁን ከኣቅማችን በላይ የሆነ የፀጥታ ችግር የለብንም። ስለዚ ኣከባቢያችን ለቀው ይውጡልን” የሚል ሃሳብ ኣቅርበዋል።

ሽማግሌዎች “ግጭቱ ወደ ደም ማፋሰሱ ኣደጋ ከማደጉ በፊት ልዩ ሃይል በኣንድ ቦታ ተረጋግቶ እንዲቀመጥ፣ ወጣቶችና ኑዋሪዎች ማሸበር፣ ማንገላታት እንዲያቆም” ፤ ምልሾቹም ደግሞ “ልዩ ሃይሉ በክልል ሃላፊዎች ታዝዞ እንደመምጣቱ ለቃቹ ውጡልን ኣትበሉ፣ ኣደጋም እንዳትጥሉባቸው” ብለው በመንገር ግዝያዊ መረጋጋት እንዲፈጠር ጥረት ኣድርገዋል።

እምባስነይቲ እንዲገኝ የታዘዘው የትግራይ ልዩ ሃይል የህወሓት መሪዎች ህዝቡ በእርዳታ፣ ሴፍትኔትና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች ኣማካኝነት ኣስገድደውና ኣስፈራርተው ፀረ ህዝቡ ያካሄደው ሰለማዊ ሰልፍ የሚደረግና ህወሓት ባዘጋጀው ሰልፍ እንዲወጣ ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ በመክሸፉ የፈጠረባቸው ሽንፈት ለመበቀል ያዘመቱት መቺ ሃይል ነው።

የእምባስነይቲ ህዝብ 20 ዓመት ሙሉ ያቀረበው የወረዳነት ጥያቄ ምላሽ ሊያገኝ ባለመቻሉ በ16 / 08/ 08 ዓ/ም ሰለማዊ ሰልፍ በማካየድ ህወሓት እንደ ድርጅትና እንደ መንግስት ከወረዳው በይፋ ማባረሩ ይታወሳል።

የህወሓት መሪዎች “ይህ ጥያቄ መለስን ማለት በትግራይ ያለው በርካታ ጥያቄዎች እንዳዲስ እንዲነሱና እንድንመልስ ስለሚያስገድደን ኣንችልም” ብለዋል።

ህጋዊና ሰላማዊ ምላሽ መስጠት ያቃታት ህወሓት ኣሁን እንደ ታላቅ ወንድምዋ ደርግ ዱላና ጠበንጃ መርጣ ደብድባ ረግጣ ለመግዛት እስከ ኣፍንጫው የታጠቀ ልዩ ሃይል እሳት ኣስይዛ ወደ እምባስነይቲ ልካዋለች።

የህዝብ ጥያቄ የማይመልስ የበሰበሰ ድርጅት ብቻ ነው !

ነፃነታችን በእጃችን ነው።

Source: Amdom Gebreslasie

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.