የአድዋ ህዝብ የህወሓት መሪዎች ልዩ ተጠቃሚ  ነው በማለት በባዶ ሆዱ በሁለት ምድጃ እሳት ተጠብሳል !!!! 

የአድዋ ህዝብ ፍትህና መልካም አስተዳደር  ልማት ተጠቃሚ አይደለም ። የሀወሓት መሪዎች የአድዋ ህዝብ በደጋፊነት ለማሰለፍና ከሌላ ወንድሙ ኢትዮጱያዊ  በተለይ ደግሞ ከትግራይ ህዝብ እንዲነጠል አድርገውታል ።

ኣስገደ ገብረስላሴ

ለተጠቀሰው ርካሽ  ፕሮፕጋንዳቸው ይሳካ ዘንድ  ለትግራይ  ህዘብ በጠቅላላ ለመነሳሳት ሲፈልጉ ከሌላላው  የሀገራችን ቢሄር  ብሄሰቦች  ለመለያየትና ለራሳቸው ቡልሽውነት  ደብቆ ትክሻ እንዲሆናቸው  ሲፈልጉ  የህወሓት አማራር  ከተሸነፈ  የትግራይ ህዝብ ይጠፋል እያሉ 27 አመት ነግደውበታል ።  አሁንም  ደኩተር አብይ ከመጣም  ሰበካቸው እቀጠሉበት ናቸው ።በትግራይ ክልልልም  ለመገነጣጠል ከፋፍለህ ግዛ ለሚል ፖሊሲያቸው   ለመሳካት የወረደ አገባብ ተከትለው  ለአድዋ ህዝብ   ብቻ  ሲሸውዱትና  መደበቂያ ሊጠቀሙበት ህወሓት  እና የህወሓት  አማራር ከሌሉ ወይ  ከጠፉ   አንተም ትጠፋለህ  ትምክህተኞችና ጠባቦች   አላማ አድርገው ይነጡላሀል  ስለሆነ  በሄድክበት ቦታ ዋስ ህወሓት ነው በማለት  በሀገር ደረጃ  ራሳቸውና ዘር መንዝራቸው  ያለ አግባብ ያበለጸጉዋቸው   መሪዎች  ቤት  ለቤት እየሰበኩ  የነሱ ተጠቃሚ ትጃሮች  በሴል (በህዋስ) አደራጅተው  እየሰበኩ  ከ99% የአድዋ ህዝብ  ወይ በድሮው የአድዋ አውራጃ  በ11 ወረዳዎች ከ700 000  በላይ የሚሆን ህዝብ   ውስጥ  ለውስጥ  እየከፋፈሉ  ህዝቡ ባይደግፋቸው ስጋት ፈጥሮ ዝምታ እንዲመርጥ  አድርገውት ነበር ።

ሀቁ ግን እንናገር  የአድዋ የገጠር ወረዳዎች ህዝብ  ከህወሓት ስርአት ፍትህ ልማት ፣ መልካም አስተዳደር  ተጠቃሚ አይይደለም። በመሆኑም እንደነበለት ( አምባስኔቲ ) ወረዳ ከ150 000 በላይ ህዝብ   ብዛት ያለበት ፣የህወሓት የተበላሸ አመራር አንቀበልም  በማለት  አንድ ልብ ሆኖ ከቀበሌ አስከ ፈደራል ፓርላማ ተወካዮች ሆነው ሽግራችን ያስተጋቡልናል ብሎ ወክሎዋቸው የነበረ የማይወክሉት መሆናቸው  ለሀዝብ ተወካዮች ፓርላማና  ለፈደረሽን ምክርቤት አመልክተው እስከአሁን  መልስ አልተሰጣቸው ።  የእባስኔት ወረዳ  የመንግስት ባለስልጣናት አባርሮ ራሱ በራሱ ነው የሚያስተዳድረው ። ይህ  ህዝብ ለህወሓት መሪዎች ተጽእኖ በማድረግ  ቡዙ ስራዎች  ተሰርተውለታል ።ግን አሁንም ስላልረካ እየታገሏቸው ይገኛሉ ። የዚሁ ወረዳ ብርቅዬ ልጅ የሆነው የመድረክ አረና ሰላማዊ ታጋይ በቢላዋ አናቶሚካል ተቆራርጦ ተጥለዋል ።

የፈረስማይና የሀሀለ  ወረዳዎች ሀዝብም የህወሓት መሪዎች እነስብሀት ነጋ ፣አባይ ጸሀዬ ፣ሀለቃ ጸጋይ በርሀ ፣ ስዩም መስፍን  እና ሌሎች ተራ የተላላኪ ካድሬ መልእክት  ይዘው እየሰበኩ  ህዝብ ለመረጋጋት ሄደው  ህዝቡ ግን  ተሰልፎ ማሳለፊያ መንገድ ከለከላቸው ። የክልሉ አስተዳዳሪዎች  እነ አባይ ወልዱ አለም ገብረዋህድ ፣ፈትለወርቅ ( ሞንጆሪኖም  አባርሮዋቸዋል ።

በአድዋ ከተማ ያለው መሰረተልማትም የተሰራው በፈደራል መንግስት ነው ።በማህበራዊ ግልጋሎት በሚመለከት የውሀ ግድብም የተሰራ  ለአድዋ ህዝብ ተብሎ የተሰራ አይደለም።   በህወሓት መሪዎች ባለቤትነት  የሚታወቅ ፣  ለአልመዳ ሁለቱ ተክስታይል ፋብሪካ ፣የጋርመንት (የጨርቅ ስፌት ፋብሪካ ) ፣ለእምነበረድ ፋብሪካ ፣ተብሎ የተሰራ ነው ።  እርግጥ  ነው እነ ስብሀት ነጋ እናመለስ ሌሎች ቡዱኖች ከላቸው ጠባብ አመለካከት ፣ዘረኝነት ተነስተው በተጨማሪ  የአያቶቻቸው በህዝብ የነበራቸው ጥላቻ ለመቅረፍ ታሰሳቢ በማድረግ ለእምነ በረድና ለጨርቅ ፋብሪካ የሚሆን ጥሬ እቃ ሽሬና ወልቃይት    ያለው ጥሬ እቃ በአካባቢው  በቅርበት  ፋብሪካው ከተተከለ  እጅግ ቡዙ   ወጭ የሚቀንስ  በአካባቢው ያለው ድሀ ማህበረሰብ  ስራ ሊፈጡሩለት እየቻሉ    እነዚህ  ፍጡራን   አድልዎ እንደፈጸሙ  ጸሀይ የመታው ሀቅ ነው ።

የአድዋና አካባቢዋ ህዝብ ግን እነዚህ ቡዱኖች ለርካሽ ጥቅማቸው ብለው የሰሩት  አድልዎ እጅ የለውም ።  እንዳው የሌላላ አካባቢ ህዝብ  አንተወውና አድዋ ከተማ ብንወስድ የከተማው ህዝብ ከግማሽ በላይ ነው የስራ አጥ ወጣት በጫትና በሽሻ ወዘተ ደንዝዟል   ወጣቱ ደግሞ አብዛኛው የተማረ ነው ። በገጠር ወረዳዎችም  በእገላ ፣የሓ ፣ብዘት ፣አዲአህፎሮም ፣አህሰአ እንትጮ ፣ወ ዘ ተ  ሁሉም ወጣት  ተሰድዋል ። ለዚሁ ማሳያ በአካቢው ህጻን ስማግሌ ከሞተ አስከሬን እሚሸከም  እድሜ ደረስ ወጣት የለም ።ይህ ሀቅ ግን በትግራይ ክል ያለው ወጣት የተሻለ ነው ማለቴ አደለም  ።እንዳው  የባሰው ተሰደዋል ።  ስለአድዋ  አስተያዬት ለመስጠት የተገደድኩበት  ግን በኢትዮጱያ ደረጃ ህዝቡ  በተሳሳተ መረጃ  እነስብሀትና ቡዱኖቹ  በተጠቀሙበት የአድዋ ህዝብ በባዶ ሆዱ ስለሚታማ  በሁለት ምድጃ እሳት መካከል  ስለተጠበሰ  ሁሉ ጊዜ ስለሚያሳስበኝ  ነው  ።
የውሀንስ ሀይለማርያም እኮ የአድዋ ከተማ ባለ አባትን አባቱና አያቱ ጸረ በእድ ገዥዎች የ የተዋጉ ስለነበሩ   በቂም በቀል  ሆን ተብሎ እየተሳቃዬ ያለው ሰው ። የውሀንስ ሀይለማርያም እኮ  ለሀገሩ ተቆርቋሪ ኢትዮጱያዊ ዜጋ  በመሆኑ በስደት ተምሮ ሰፊ ሙያ ስላለው በሰሜን ምእራብ ወረዳዎች ህዝብን ያሳተፈ  ሁለገብ ልማት ለማካዬድ እስትራተጅካዊ ጥናት አድርጎ ቢሌኖሮች እራኤላውያን ሸሪኮች ይዞ  መጥቶ ሲያበቃ ፍትህ አጣሁ  በማለቱ በኩማንዶዎች ተደብድቦ በጨለማ ቤት የሚገኜው  እ ፍትህ አጥቶ ያለው  የአድዋ ተወለጅ ነው  ። በመሆኑ የአድዋ ህዝብ ከጥቂቶች በስተቀር ተጠቃሚ አይደለም  ።

አንድ ሀቅ ግን አለ ከነስብሀትና ከነመለስ ፣እና ከሌሎች በዝምድና ፣በጥቅማጥቅም የተሳሰሩ ጥቂት የአድዋ ሰዎች  ግን ዘርን እየቆጠሩ ተጠግተው  የሀብታቸው ሙንጩ የማይታወቅ ቢሌኖሮችና ሚሊየኖሮች የሆኑ አሉ ። እነዚህ ከአድዋ ህዝብ ጋር አንመድባቸውም ።

በሌላ በኩል ደግሞ ከነስብሀት ነጋ  ጋር   አንጠጋም ያሉ እንደነ ትጃሩ ዳዊት ገብረእግዚአብሄር  ግን በኑጹህ ላባቸው ያፈሩት ሀብታቸው  ያፈሩት  በሀገር ደረጃ በሞቶዎች ሚሊዮን ብር የሚፈጅ ለወጣቶች ስራ እፈጥራለሁ ያለ ዳዊት ገብረእግዛቢሄርም እንደ የውሀንስ ሀይለማርያም  አልተደበደበም  አልታሰረም እንጅ ኢንቨስትመንት ተከልክለዋል ። ራያ ቢራ ሊሸጥ የተገደደውም በህወሓት መሪዎች ተጽእኖ  በተለይ የአባይ ወልዱና ቴድሮስ ሀጎስ  ተጽእኖ ነው ።

ከላይ የዘረዘርኩት እንዳለ ሆኖ ቁጥራቸው የማይናቅ በርከት ያሉ የአድዋ ሙሁራኖች ተማሪዎች   ግንደግሞ የነስብሀት ነጋ  ፣የመለስ ተጠቃሚዎች ያልሆኑ    የህወሓት መሪዎች ከሌሉ የአድዋ ህዝብ ይጠፋል  የሚል ፕሮፕጋንዳ ተጽእኖ ሆኖባቸው  ሞተው እያሉ አለን በማለት ለነዚህ ዘሮኞች ተደራጅተው  እንደመታገል  ዝምታን በመምረጥ  የህወሓት መሪዎች አፈና ለመቃወምና  ህገመንግስቱ በሚፈቅድላቸው ተደራጅተው በሰላማዊ መንገድ ለመታገል  ተነሳሽነት አይታይባቸውም  ።

የአድዋ ህዝብ ጸረ  ደርግ በተደረገው እልኽ አስጨራሽ ትግል በመሰለፍ ብዛትና በመስዋእት ብዛት ከሽሬ ቀጥሎ እሱነው ። በአ ጠቃላይ በጸረደርግ ትግል ወደ ትግል የዘመቱ ታጋዮች በሁሉም አውራጃዎች  ብዛት ሲሰላ 1ኛ ሽረ አውራጃ  2ኛ አድዋ አውራጃ          3ኛ  አክሱም አውራጃ  4ኛ ተንቤን አውራጃ ። 5 ኛአንደርታ አውራጃ   ።  6 ኛ ማይጨው አውራጃ ። 7 አጋሜ አውራጃ ። 8ኛ ክልተ አውለዕሎ አውራጃ 9ኛ ወልቀይት ጸገዴ አውራጃ 10ኛ ጸለምት የሰሜን ተራራ 11 ወረዳዎች   ።11ኛ  ሰሜን ሽዋና ደቡብ ጎንደር ፣ወሎ ይጠቀሳሉ ። ይህን ለመረጃ ያህል ጠቀስኩት እንጅ  አሁንም ወደ አድዋ ልምጣ እና የአድዋ ሙሁራኖችና ተማሪዎች በጸረ ደርግ ትግል አባታቸው አክስታቸው ፣አጎታቸው ፣ዘመዶቻቸው ፣ወይ ጎረቤታቸው  መስዋእት የከፈሉበት ስርአት በጥቂት የህወሓት ኢህአደግ የበሰበሱ መሪዎች ከነዘመድ አዝማዳቸው ሲጠልፉት እያዩ ዝምታ ከመምረጥ  ካመኑዋቸወ ተፎካካሪ ቅን ፓለቲካ ፓርቲዎች ጎን መሰለፍ ፣ወይ ራሳቸው ፓርት በመፍጠር ተፋካሪ ፓርቲ ቢፈጥሩ ጡሩ ይመስለኛለ  ካለበለዝያ ታሪክ ይወቅሷችኃል ።

በአድዋ ሀቀኛ ሊሂቃን ያስቀመጥኩት ድክመት ለአክሱም ፣ለሽሬ ፣ ለአጋመ ፣ለማይጨው አውራጃዎች (ዞኖች ) ሊሂቃንና ሙሁራን qተማሪዎች ፣  ይመለከታቸዋል ።
ይህ ሀቅ እቀጥልበት አለሁ
ከአስገደ ገብረስላሴ
ከመቀለ
01 /   09 /2010

 

   ሰበር መረጃ !!  ከአስገደ ገብረስላሴ ፣
————————

ከመቀለ  ታማኝ ምንጮች የተገኜ መረጃ እንደተረጋገጠው ከ 2 አመት በፊት በትግራይ ክልል አስተዳደር   የመንግስት መስራቤቶች በቢሮክራሲ ውጣ ውረድና የመልካም አሰተዳደር በፈጠረበት ችግር የተማረረ  ዲያስፖራ    የውሀንስ   ሀይለማርያም  ዘግነቱ  እስራኤላዊ  ፣ ትውልደ ኢትዮጱያዊ በትግራይ ክልል  አድዋ ከተማ የተወለደ  እንደሆነና  ስሙ የወሓንስ ሀይለማርያም  እንደሆነ  ለቤተሰቦቹና   በዲያስፖራው የደረሰበት ጉዳትና ኢሰብአዊ ድርጊት አዝነውና እንደዜጎች ተቆርቁረው ይከታተሉ ለነበሩና ላሉት  ግለጽ ሆኖላቸዋል ።  በመሆኑም እንኳን ደስአላቹ ።

ስለየውሀንስ ሀይለማሪያም  ሁኔታ ከአባይ ወልዱ  ጋር ተደባድቦ   በአባይ ወልዱ አጃቢዎች ኩማንዶዎችና በትግራይ ክልል ፖሊስ ኮምሽን  ልዩ ሀይል ኩማንዶዎች ፣ እንዲሁም የድህንነት አካላት ክፉኛ ተመትቶ  ወደ ልዩ እሱር ቤት ገብቶ በድብቅ ችሎት ተፈርዶ ከሁለት አመት በላይ አሁንም ጭምር  ከቤተሶቦቹና ጓዶኞቹ  ጋር ሳይጋናኝ ፣አድራሻው እንደማይታወቅ በማህበራዊ ሚዲያ ያገኜናት መረጃ  እናስታውቅ ነበር  ። እኖሆም  ዛሬ የተሻለ መረጃ አግኝተናል ለቤተሰቡና በሁሉም አካባቢ የምትገኙ ዲያሰፖራ   ጎዶኞቹ ደግሜ እንኳን ደስ አላችሁ !!!

በአሁኑ ጊዜ ዲያስፖራው የውሀንስ ሀይለማርያም የሚገኝበት   እሱር ቤት  ወይ ቦታ በዝያች ዝግ ቤት  በሽዎች ዜጎች ታስረው የሚገኙባት በመቀለ ከተማ  ማረምያ ቤት ይገኛል ለበለጠ መረጃ
ለማግኜት  ጥረታችን አያቋርጥም ።
ከአስገደ ገብረስላሴ ፣
ከመቀለ
29 / 08  /20 10  z

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.