ወይ ቤን ድኩማኑ – አምላክ ፍርፋሪ ለቃሚ ከመሆን ያውጣን!

የጦቢያ ነጭ ለባሽ

ከካናዳ ግራ የተጋባ ኑሮው ቋንቋ እንኳን በወጉ ሳይማር አቶ ለገሰና አላሙዲንን አቆላምጦ ቋሚ የአሸርዳጅነት ስራ የተሰጠው ቢንያም ከበደ (ቀለለ)ደግሞ ብሎ ብሎ ሄሊኮፕተራችንን መልሱ እያለ ሃገር ቆርሶ ለሰጠ የሽፍታ ቡድን ቋሚ ጠበቃ ሆኖ ሳያፍር፡ ወያኔ ተቆርቋሪ ሆኖ ፋታ ሳይሰጥ ላስገነጠላት የኤርትራ ምድር ግድ ሳይለው፡ ስለ ትግራይ የአፓርታይድ ስርዓት ንብረት ዛሬ አንደበቱ ተከፈተ።Ethiopia first, benyam kebede

በነገራችን ላይ የኢትዮጵያ አየር ሃይልን አፍርሰው፤ የኢትዮጵያ ባህር ሃይልን ከነባህር በሩ ቀብረው፤ የሃገራችንን መከላከያ ጦር በትነው፤ ዛሬ በትግራይ ክልል መናገሻውን ካደረገ ለቆየው የህወሃት አየር ሃይል፡ የኦህዲዱ ካድሬ ቢንያም ቀለለ ጥብቅና ሲቆም፤ በሺዎች የሚቆጠሩየኦሮሞ ተወላጆች እስርቤቶችን ባጨናነቁበተና እና በምሬት ብረት ያነሱት የኦሮሞ ለጆችና ሌሎች ኢትዮጲያዊያን ጀግኖች ደግሞ ምታ ነጋሪት ክተት ሰራዊት ባሉበት ሰዓት፡ ምን ያህል በወገኖቹ ህይወት ቁማር የሚጫወት ከሃዲ መሆኑም ለፍርድ እየተመዘገበለት ነው።

ቢንያም ቀለለ፡ ደብረዘይት አየር ሃይል ዛሬ ከስውር እስር ቤትነት እምብዛም ያልዘለለ እንደሆነና፡ እንዳንተ ዘጠኝ የሽንት ጨርቅ የታጠቁ ድኩማን ሳይሆኑ፡ የኢትዮጲያ የቁርጥ ቀን ልጆችን ማሰቃያ መሆኑን የሃገሩ ነገር የሚያንገበግበው ሁሉ የሚያውቀው ሃቅ ስለሆነ፡ ከፈቀዱላችሁ ከአንተ ቢጤው አድር ባይ እና ሃይለኛው ኮራጅ፤ ሃይለማሪያም ደለለኝ ጋር፡ (እሱ እንኳን ቁመት ሁለቴ ያጥፍሃል) የወያኔን ስካርፍ አድርጉና ቀጣሪዎቻችሁን አስጎብኙኝ በሏቸው አራት ነጥብ!

[እርግጥ ነው፡ ስራ በሚከበርበት ካናዳ ሰርቶ መኖር ያቃተው ይሄ የወሬ ቋት ቢንያም ቀለለ፡ የገዛ ጓደኞቹና ቤተሰቦቹ እስክሸማቀቁበት ድረስ፡ ቶሮንቶ በነጻ ህክምና ሚስቱን ለማስወለድ ካልሆነ በቀር፡ ሰርቶ ለመኖር እንድማይረግጣት የምናውቅ እናውቃለን ይሄም እየተመዘገበለት ነው። ]

ጭራሹኑ፤ 60% ንብረትነቱ የካናዳ መንግስት የሆነን የወርቅ ማእድን ፋብሪካ የትግራይ ነጻ አውጪ በምድርም ይሁን በአየር ደበደበው ብሎ ከወያኔ ሚዲያ ቀድሞ መመስከር፡ በራሱ ላይ የክስ መዝገብ እያከማቸ እንደሆነ አለማወቁ የድንቁርናውን ልክ የሚያሳይ ነው።

ሌላው ነገር፤ ቢንያም ቀለለ የኤርትራ ሰማይ ስትል፤ የኤርትራ ሰማይ፤ የኤርትራ ጦር የሚባል ነገር ለመፍጠር የቸኮሉትን ቀጣሪዎችህን ግፍ አንተ ስራ ሳትሰራ እያወራህ እና ዘር ከዘር እያባላህ እንድትበላ ስላረጉህ ዘንግተኸው ይሆናል፡ እኛ ግን ለአፍታ እንኳን እንዳልዘነጋነው አልገባህም ይሆናል።

ደግሞ ዘፈን ተመርጦ ልብ ውልቅ! እንዳንተ አታላዩ የሜጋው ሚዲያ በወቅቱ ጠፍጥፎ በሰራው ፕሮቶጋንዳ ተታለው በከንቱ ደማቸው ደመከልብ ሆኖ የቀሩ ወገኖቻችን ደም ሳይደርቅ፡ ሌላ ማሳሳቻ ልታዘፍን ያምርሃል? በካሳ ተሰማ ፋኖ ታጅበህ የኢትዮጲያን ህዝብ ዳግም ልታታልል? በሃሰት በኢትዮጵያዊያን ላይ እስከዛሬ ለቀለድከው ሁሉ ልጆቹ የት እንደወደቁ እንኳ በወጉ ሳይነገረው ተንቆ የተተወው ኢትዮጵያዊ ወገን አንተንም ሆነ ያቺ በር ጥርስ ጓደኛህን ዋጋችሁን የሚሰጥበት ጊዜ እየቀረበ ነውና ያኔ አሸው አንበሳው የሚለውን ዘፈን እንመርጥላችኋለንና አትቸኩል!

እደግመዋለሁ፡ የኢትዮጵያ መንግስት የምትሉት የወያኔ፡ ባለስልጣኑም ባለሃብቱም የጥቂት ወያኔዎችና የአንተ አይነት የአእምሮም የመንፈስም ድኩማንን እንዲሁም ሰው የጠላቸው ወንጀለኞች ስብስብ፡ ጦሩም ለወያኔ አዛዦች ጥቅም አስጠባቂነት የኢትዮጵያን ወጣት በማታለል የተደራጀ ሃይል፤ የኢትዮጲያ ልጆች ከወያኔ እየነጠቁ የወሰዱትና ገና የሚወስዱት አውሮፕላንም ሆነ ሄሊኮፕተር ሁሉ የሃገራቸው ንብረት፡ ማለትም የራሳቸውን ሃገር ነጻ የሚያወጡበት ትጥቅ ስለሆነ፡ ይልቅስ ለራስህና ለመሰሎችህ አልቅስ፤ በፍርፋሪ ህሊናችሁን ለሸጣችሁ፤ እውነተኛው ፋኖማ አገሩ ሊገባ ነው አራት ነጥብ!

የጦቢያ ነጭ ለባሽ
መጋቢት 16፤ 2007 ዓ. ም.