ግንቦት7 እና ኦዴግ ምንና ምን ናቸው …..!!! (ከታምራት ይገዙ)

ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም የጋሼ ሌንጮ ነገር በሚለው መጣጥፉ “አርበኞች ግንቦት7 እንደ ኦዴግ አይነቶችን እምነት የማይጣልባቸውን ድርጅቶች እንኳ ለአገር አንድነት ሲባል አቅፎ ለመጓዝ የማይቸግረው ድርጅት መሆኑን አስመስክሯል። ኦዴግ ለዲሞክራሲና ለአገር አንድነት የሚታገለውን ድርጅት “አላማህን ወድጀዋለሁና አብሬህ ልስራ” ቢል “ተወዳጁ” ድርጅት “እምቢ” ማለት ይቻለዋል? አይመስለኝም። እንዲህ ካለማ ከራሱ አላማ ጋር ተጋጨ ማለት ነው።”  እንደ እውነቱ ከሆነ ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም “እምነት የማይጣልባቸውን ድርጅቶች እንኳ ለአገር አንድነት ሲባል አቅፎ ለመጓዝ የማይቸግረው ድርጅት መሆኑን አስመስክሯል ሲል ይህ ወንድማችን አንድም የግንቦት 7 አባል አሊያም አፍቃሪ መሆኑን ነው የሚያሳብቀው ምክንያቱም ግንቦት ሰባት እንከን የማይወጣለት ድርጅት አድርጎ ለመሳል በማሰቡ::

በሌላ በኩል በኔ እይታ ኦዴግ ከግንቦት ሰባት ጋር ለመስራት ሃሳብ ያቀረብ አይመስለኝም ምክንያቱም ከዛ ቀደም ብሎ ኦዴግና ሸንጎ አብረው ሊሰሩ እንደተስማሙ በአዲስ ድምጽ ሬዲዮ ላይ ዶ/ር ቡሻ  የሸንጎ አባልና ዶ/ር ዲማ  ነጎ ቀርበው ሰፋ ያለ ውይይት አደርገው ነበር::  በኔ ግምት ይህንን የሰሙ የግንቦት ሰባት አመራሮች አገራዊ ንቅናቄ የሚባል ህብረት እንዲፈጠር ለዚህም ታዋቂ ግለሰቦችን ሲፈልጉ ለሸንጎ ጥሩ አመለካከት የሌላቸውን ፕ/ር ጌታቸው በጋሻውና ሻለቃ ዳዊትን ያገኛሉ እነዚህም ታዋቂ ግለሰቦች በስድስት ወር ውስጥ አዋክበው  አገራዊ ንቅናቄ የተባለውን በሲያትል ከተማ መሰረቱ::  ፕ/ር ጌታቸውም  በእለቱ በአንደበታቸው ሲናገሩ “ይህንን የመሰለ ጠንካራ ህብረት ለመመስረት እኔና ሻለቃ ዳዊት ስድስት ወር ነው የፈጀብን ብለው ነበር”::  እኔም የንን ምስረታ ከተመለከትኩ ቦሃላ የተረዳሁት አግላይ ከመሆኑ በላይ ያ ድርጅት እንዲቆቆም የታሰበውአንድም  ግንቦት ሰባት በመውደቅ ላይ ስለነበረ ለመታድግ አሊያም የግቦት ሰባት የቀን ቅዥት የነበረውን አውራ ድርጅት ሆኖ የመውጣት አባዜ ለማሳካት  መሆኑን በግልጽ ይታወቅ ነበር::  እኔም ያን አይነት የተኮላሸ አካህኣድ በመመልከት በዛ ሰሞን መጣጥፊ

<< የአሜሪካ ሰዎች ኑ ጠላ ቅመሱ

የካናዳ ሰዎች አውሮፓም ያላችሁ ኑ ጠላ ቅመሱ

እንደ መምህሩ አንደ ጌታቸው በጋሻው አንደ ሻለቃ ዳዊት እንድትጠነስሱ>> የሚል ትዝብቴ የያዘ ጹሁፍ አስነብቤ ነበር::

ሰሞኑን ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም “የጋሼ ሌንጮ ነገር በሚለው መጣጥፉ “አርበኞች ግንቦት7 እንደ ኦዴግ አይነቶችን እምነት የማይጣልባቸውን ድርጅቶች እንኳ ለአገር አንድነት ሲባል አቅፎ ለመጓዝ የማይቸግረው ድርጅት መሆኑን አስመስክሯል” ይለናል እንደ ኤውነቱ ከሆነ የጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም ጹሁፍ ፈረንጆች እንደሚሉት”ከነጭ ውሸትነት” ያለፋ አይደለም;;

በኔ እይታ የግንቦት ሰባትን አካሄድን ስመለከትው ከዚህ ቀደም እንደከተብኩት ይህ ግንቦት ሰባት ከተመሰረተ ጀምሮ ህልምና  የቀን ቅዠቱ ” አውራ ድርጅት” ሆኖ ህወሀት/ኢህኣዴግን  ድርጅት ለመተካት ነበር ሲቅበዘበዝ የነበረው እንጂ ኢትዮጵያንና ህዝቦቾን ለመታደግ አልነበረም የሚል እምነት አለኝ:: ይህንን እምነቴን የሚያጠናክርልኝ ግንቦት ሰባት ከተመሰረተ ጀምሮ ሌሎች ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ማለትም  በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ ድርድር አያስፈልግም የሚሉ ድርጅቶች አብረን እንስራ ሲሉት ጆሮ ዳባ ልበስ ያለ ድርጅት እንደነበረ እኔ በግሌ በተወሰነ ደረጃ አውቃለው ሌሎችም ያውቃሉ::

በ2012 በምንርብርት ከተማ ከዶ/ር በርሀኑ ጋር ቁርስ እየበላን ውይይት አድርገን ነበር በዛ ውይይት ላይ ከቀረበው  ጠያቂ ለምንድን ነው ግንቦት ሰባት እንደ ታሰበው ወደ ፊት በፍጥነት ሊጎዝ ያልቻለው የሚል ጥያቄ  ከአንዲት እህት ቀርቦ ነበር ዶ/ር ብርሃኑም ሲመልሰ ” ኤርትራ ውስጥ ያሉ የኦሮሞ ድርጅቶች ለአራት ለአምስት ስለተከፋፈሉ እነርሱን ስናስማማ ነው የከረምነው አሉን:: እኔም በዛላይ ያለኝን ጥያቄ ለመጠየቅ እጄን አነሳው ነገር ግን ዶ/ር ሌላ ቀጠሮ ስለነበራቸው የኔን ጥያቄ ለመቀበል ግዜ አልነበራቸውም::  ከስብሰባ ስንወጣ አንድ ሰው ቀረብ ብሎኝ ለዶ/ር ብርሃኑ የነበረህ ጥያቄ ምን ነበር ብሎ ቢጠይቀኝ የመለስኩለት “በኢትዮጵያዊነት የማያምኑ ድርጅቶችን ለማስታረቅ ከማሰብና ግዜ ከማጥፋት ይልቅ በኢትዮጵያዊ ሉአላዊነት ላይ ምንም ጥያቄ ውስጥ የማይገቡ ድርጅቶች አብራን እንስራ እያሉ እነሱን ወደ ጎን አድርገው  ከኢትዮጵያ እንገንጠል ከሚሉ ጋር ለመስራት ግዜ አችውን የምታጠፉት ለምንድን ነው? ግንቦት ሰባት ንቅናቄ እንጂ የተባበሩት መንግስታት ነው ወይ ኢትዮጵያ የምትባል አገር የለችም የሚሉትን ወገኖች ለማስታረቅ ላይ ታች የሚሉት የሚል ነበር ጥያቄዪ አልኩት:: ያም ሰው ጥያቄው ትገቢ ይሁ ወይንም አይሁ በሚገልጽ ምልክት ይመስለኛል አንገቱን ከፍ ዝቅ በማድረግ መለሰልኝ::

እንደ እውነት ከሆነ ግንቦት ሰባት ሲመሰረት እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ድርጅቱን በአባልነት ደረጃ ባይሆንም አቅሜ በሚፈቅደው ሁሉ ደግፌላሁ በመደገፌም የምጸጸትበት ምንም ነገር የለኝም ምክንያቱም ማንኛውም ድርጅት ለአገርና ለህዝብ የሚጠቅም ራይ ሲኖረው መደገፍ ከዛ አይነቱ ራይ ሲያፈነግጥ አለመደገፍ የሁላችንም ምርጫ ይመስለኛል በዚህ መልኩ የግንቦት ሰባትን አካሄድ  ከግዜ ወደ ግዜ ስመለከት ቡዙም አብሬ ለመጎዝ ፍላጎቴ እየጠፋ መጣ ምክንያቱም እንደኔ ተከታይ የሆኑትም ሆኑ በአባልነት የተመዘገቡት አብዝኞች በአካባቢዪ ያሉት ግለሰቦች ድርጅቱንም ሆነ መሪዎቹን ወደ ማምለክ ተለወጡ ይህም ለኔ የሚዋጥልኝ ሆኖ አላገኘሁትም ነበር በዚህ መሃል በ2013 በወረሃ ጥቅምት የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሀኑ (በወቅቱ ዶ/ር ነብሩ) ከአቶ አበበ ገላው ጋር የኢሳትን አመታዊ በዓል ለማክበር በምኖርብርት ከተማ ተገኝተው ነበር በአሉ ላይ  ፕ/ር ብርሀኑ ዛሬ እዚህ የምገኘው ለኢሳት ስለሆነ ስለ ግንቦት ሰባት ጥያቄም ሆነ አስተያየት አልቀበልም ነገር ግን በግንቦት ሰባት ላይ ጥያቄና አስተያየት ያላችሁ በነገው እለት ዳንፎርዝ በሚገኘው ምግብ ቤት ወስጥ ተግኝታችሁ መነጋገር እንችላለኝ አሉ::

እኔም በእለቱ ስብሰባው ላይ ታደምኩ የተለያዩ ጥያቄውችና መልሶች ከተደመጡ ቦሃላ እኔም ተራ ደረሰኝና ተነሳው ጥያቄም ከመጠየቄ በፊት ፕ/ር ብርሀኑ ስብሰባውን ሲከፍቱ እንዲህ በለው ነበር “አሁን እዚህ ያላችሁ ሰዎች ጥያቄ ብቻ አይደለም  ስድብም ካላችሁ መሳደብ ትችላላችሁ” ብለው ስለነበር እኔም ይህንን አልኮቸው “በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ  በአንድ ወቅት የኢትዮጵያ ንጉስ የነበሩ ሰው ሸንጎ ሰብስበው እሲቲ ስደቡኝ ይሉ ነበር ካዛም አንዱ ተነስቶ “ትገርፈኝም እንደሆነ ትገልኝም እንድሆን ከፊትህ ቆሚያላው ያ ለምጣም ሚኒሊክ ቢዪ ሰድቢያለው” ብሎ ተቀመጠ እርሶ ዶ/ር ብርሀኑ ዛሬ ያንን አባባል ነው ያስታወሱኝ ካልኩኝ ቦሃላ ጥያቄዪን እንዲህ በማለት በአስታተያየት ጀመርኩ::

ዶ/ር ብርሃኑ የደርጅቶት አባልና ደጋፊ የሆኑ ሰዎች ድርጅቱንና እርሶን ከመደገፍና ከማገዝ ባለፈ መልኩ እርሶን; ድርጅቶትን ግንቦት ሰባትና እንዲሁም ሚዲያን (ኢሳትን) ማምለክ ጀምረዋል ብዪ ወደ ግንቦት ሰባትና የሻቢያን ግንኙነት   በተመለከተ ገና ከመጀመሬ በዶ/ር ብርሃኑ በግራ በኩል ተቀምጣ የነበረች እህት  ስሜን በመጥራት ተቀመጥ ተቀመጥ አለች አሶን ተከትሎ ሌላው ወንድም  ከወደ በሩ ሆኖ ተቀመጥ ተቀመጥ አለ እኔም የእነዚህ ሁለት ሰዎች ጫጫታቸውን ከስጨረሱኩ ቦሃላ “ዶ/ር ብርሃኑ እርሶ ጥያቄ አይደለም ስድብም ካላችሁ ተሳደቡ ለማስተናገድ ዝግጁ ነኝ ብለው እድሉን ቢሰጡኝ እነዚህ ሁለት ሰዎች የሚሉትን ይሰማሉ?  እነዚህ ሰዎች የእርሶና የደርጅቶት ደጋፊዎች ሳይሆኑ የርሶና የድርጅቶት አሚላኪዋች ነቸው ይህንን በግዜ ካላስወገዱ የኾላ ኾላ ለርሶም ሆነ ለድርጅቶት ዋጋ የለውም ምክንያቱን  “አምልኮ ለፈጣሪ” እንጂ ለግለሰብ; ለድርጅትና ለሚዲያ አይደለም አልኮቸው :: ዶ/ር ብርሃኑም ሲመልሱ አንተ እንዳሰብከው አምላኪዎች ሳይሆኑ ካለው ግዜ አንጻር ነው ብለው መለሱ እኔም የተሰማኝን ተናገርኩ እርሳቸውም መልሳቸውን ተናገሩ::

በነገራችን ላይ ያን ግዜ ያዙኝ ልቀቁኝ ከሚሉት አምላኪዎች ግማሾቹ ለግንቦት ሰባት ስብሰባ ኤርትራ ደርሰው ከመጡ ቦሃላ በኤርትራ በኩል የሚደረገው ትግልም ሆነ  ጋዜጠኛ መሳይ መኮንንና ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም  ኤርትራ ድረስ ተጉዘው ያቀናበሩት ቅንብር ከጋዜጠኛ ስነ ምግባር የወጣና የልማታዊ ጋዜጠኛ ያዘጋጀው  መሆኑን በዓይናቸው አይተው ስለተረዱት አባቶቻቻን የሚሉትን አባባል “ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለየቅል” የሚለውን በማስታወስ ግንቦት ሰባትን አይንህን ለአፈር ብለው ቤታቸው መቀመጥን ከመረጡ ሰንበት በት ብለዋል::

ወደ ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም የጋሼ ሌንጮ ነገር ወደሚለው መጣጥፉ ስመለስ  ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም ሊነግረን እንደሚያስበው ሳይሆን ግንቦት ሰባት የተጎዘው ጉዞ ከፈረሱ ጋሪው ቀደሞ በሚዲያ አጃቢነት እንጂ በትግሉ ውስጥ እንደ መቆየቱ ምንም የስመዘገበው እሚንት የሆነ ነገር አይታይም:: ይህንን ከተመለከትኩ ቦሃላ በምኖርበት ከተማ ላሉ የግንቦት ሰባት አባል ለሆነና ለግንቦት ሰባት ጥሩ አመለካከት አላቸው ከምላቸው ወንድሞች የተለያየ ውይይት ሳደርግ የሚሰማኝን ከመናገር አልቆጠብም ነበር:: ለምሳሌ ሁላችንም እንደምናውቀው የግንቦት ሰባት ከፍተኛ አመራሮች በአንድ ወቅት ትግሉን ለመምራት ብለው ጠቅልለው ኤርትራ ገብተው ነበር አብረው እንደገቡ ሁሉ እብረው ወጥተው እንደነበር አይዘነጋም ይህንን በተመለከተ ከአንድ ወንድም ጋር ስወያይ “ኤርትራ የገቡት የግንቦት ሰባት አመራሮች ይህው ሁሉንም ነገር አይተው ተመልሰዋል ሁሉም እንደሚገነዘበው በኤርትራ በኩል የተሄደው ጉዞ ጥቅሙ ስላልታየ ለምን አሁን የግንቦት ሰባት አመራሮች ለግዜው የትጥቅ ትግሉን  ሙሉ በሙሉ ትተን (Suspended ) እድርገን ያለ የሌለ ሀይላችንን ሰላማዊ ትግሉ ላይ እንድናውል ግዜው የግድ ስለሚል ብለው ለአባላቶቻቸው ለውይይት አያቀርቡም ብለው ይህ ወንድሜ የሰጠኝ መልስ አንተ ሞኝ ነህ እንዴ” ግንቦት ሰባት ይህን የሚያደርገው ኢህአፓ ወይንስ ሸንጎ ደስ እንዲለው ነው የሚል መልስ ነበር የሰጠኝ” እኔም ስመልስለት ላካ ትግሉ ማን ደስ ይለዋል ማን ይከፋዋል ነው እንጂ የአገርና የህዝብ ጉዳት አይደለም የሚያሳስባችሁ በማለት ነበር የመለስኩለት::

የኦዴግ አመራሮች አገር ቤት እንደሚገቡ ስሰማ ይኽው ወዳጄ ጋ ስልክ ደውዪ ሳወራው ይህንን ጨዋታችንን አስታወስኩት እርሱም ስመልስ “አዎ ብለኽኝ ነበር ነገር ግን ዶ/ር አብይ ለስልጣን ይበቃል ብሎ ከሶስት ወር በፊት ያሰበ ማን አለ አለኝ” እኔም ስመልስለት የድርጅት መሪ የሚመጣውን ሶስት ወር ሳይሆን ፎር ካስት ማደረግ ያለበት ከዓመትና ከሁለት ዓመት ቦሃላ ምን ይመጣል ብሎ ካላሰበ ከኔ ከተራው ግለሰብ በምን ተሻለ ስለው መልስ አልነበረውም::

በአጠቃላይ በአሁኑ ዘመን የሚደረገውን ሁሉ በቀላሉ ለሚከታለልና ለሚያውቅ ሰው ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም ግንቦት ሰባትን ትክክለኛ መንግድ የተጎዘና “እንደ ኦዴግ አይነቶችን እምነት የማይጣልባቸውን ድርጅቶች እንኳ ለአገር አንድነት ሲባል አቅፎ ለመጓዝ የማይቸግረው ድርጅት ነው ሊለን ሞሞከሩ የተሳሳት ሙገሳ ለግንቦት ሰባት ለመለገስ ማሰቡን ነው የሚያሳየው ይህም በኔ እይታ ስህተት ከመሆኑ ባሻገር ድርጅቱ ከድጡ ወደ ማጡ እንደመክተትና ከስህተቱንም እንዳያርም ማድረግ ነው ብል ማጋነን አይሆንብኝም::

በመጨረሻም ለግንቦት ሰባት አመራሮችና አባላቶች እንዲሁም ለድርጅቱ ቅናዊነት ላላቸው ሰዎች ያለኝ መልእክት ፖለቲካ እንደ ሀይማኖት ”ዶግማ “ አይደለም ስለሆነም እንደ ግዜውና እንደ አካባቢው ሁኔታ የሚለወጥና የሚሻሻል ስለሆነ በዓሁኑ ሰዓት በዓለም ያሉ መሪዎች በተለይ ምዕራብያውያን  የአንድ ሀገር ህዝቦች እርስ ብረሳቸው ተዋግተው የመንግስት ለውጥ እንዲመጣ የሚፈልጉ እይደሉም ምክንያቱም በኔ እይታ ጦሱም ለነሱ እንደሚደርስ ያውቃሉና:: ስለሆነም ግንቦት ሰባት አመራሮች በመሳሪያ ትግል መንግስት መለወጥ የሚሉትን ሃሳብ ቀይረው ሙሉ በሙሉ በሰላማዊ ትግል ለመታገል ለአባላቶቻቸውም ሆነ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይፋዊ የሆነ መግለጫ የማውጫ ሰዓታቸው አሁን ይመስለኛል::

እርግጥ ነው የድርጅት አባላቶችም ሆኑ ደጋፊዎች በሁኔታው ላይደሰቱ ይችላሉ አማራሮቹንም በጥያቄ ሊያጣድፉ ይችላሉ በኔ እምነት መሪ ማለት ተከታዩን ማሳመን የሚችል ሰው ነው::  ይህንን ማድረግ የማይችል መሪ በፊትም የመሪነት ችሎታው አጠያያቂ ነበር ማለት ነው እያልኩ የዛሬን ጹሁፌን ልቆጭ::

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ይፈቱ!

አምላክ አገራችንን ኢትዮጵያን በምህረቱ ይጎብኝልን!!

 

 

4 COMMENTS

  1. ከጅ አይሻል ዶማ ወይስ አልሸሹም ዞር አሉ? ላንተ እስረኛ አንዳርጋቸው ጽጌ ብቻ ነው? ከፋሲል ምኑን ተሻልክ ታዲያ? በተረፈ ሌንጮም ብርሃኑ ብርሃኑም ሌንጮ ቀልቀሎ ስልቻ ስልቻ ቀልቀሎ።

  2. @ ታምራት ይገዙ

    የደርግ አብዮት ጥበቃ ልጅ ና የመዒሶን ገራፊ ርዝራዥ ሁሉ ፃፊ ና ዜና አንባቢ ሆነ። ወዛደራዊነት ናፈቃችሁ አይደል። ድሮም ከናንተ ምን ይበቃል። ሁለትህም የታሪክ ዐተላ ነህ።እናንተ ብሎ ለሃገር ተቆቝሪ። የደርግ አብዮት ጠባቂ የእውቀት ድኩማን ሁሉ።ዝም ብሎ በባዶ G 7 ን ከመንቀፍ ኣንተ ወይ በሱዳን ፤ በጅቡቲ ፤ ወይ በሱማሌ የተሻለ ስራ መስራት ሚቻል ከሆነ ሰርቶ ማሳየት ነው። ሁሉም የ G 7 ሰዎች ዕንደኣንዳርጋቸው የሞቀ ቤታቸውን ጥለው ነው ኤርትራ በረሃ የገቡት።ግንቦት 7 ማለት ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ በ1997 EC ወያኔዎችን በድምፁ አንፈልጋችሁም ያለበት ታሪካዊ ቀን ነው። የነ ኤሊያስ ክፍሌ Ethiopian Review ወሬ ና ያንተ ኣይነቱ የውሸት ችርቻሮ ይህንን እውነታ አይለውጠውም።

  3. ታምራት የዚህ ዘመን ፖለቲከኞች፡ አክቲቪስቶችና ጸሀፊ ነን ባዮች የጋራ መለያችሁ ግልብነትና ጥራዝ ነጠቅነት ነው። በየጊዜው ስምህን በተለያዩ ጽሁፎች አናት ላይ አየዋለሁ ጸሀፊ ደግሞ ቢያንስ ስለሚጽፈው ጉዳይ መሰረታዊ የሆ ነ ግንዛቤ እንዲኖረው ግድ ነው። የደርግና የመኤሶን ወንጀለኞች መደበቂያ ምናልባትም ከጴንጤ ቤተ ክርስቲያን ቀጥሎ እደግፈዋለሁ የምትለው Gim7 እና ESAT ናቸው። ፋሲል የኔ አላምም እንዳንተው የG7 ወዛደር ነው። ይህን ግልጽ እውነታ ሳታውቅ ቀርተህ ከሆነ ባትጽፍ ይሻልሀል። ከዚህ በተረፈ እኔ ያልኩት በሀገሪቲ በሞላ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ እስረኞች መኖራቸውን እያወቅህ ለምን አንድ አንዳርጋቸውን ብቻ ነጥለህ ጠራህ ነው። ሁሉም ለሚያምኑበት አላማ ሲሉ ነው የሚሰቃዩት አንዱን ከሌላው ማበላለጥ ጤነኛ አመለካከት አይደለም። በኔ እምነት ማንም ቢሆን በአመለካከቱ ምክንያት መቀጣት የለበትም። በተረፈ እኔ የመንገድ ላይ ቋንቋ ይከብደኛልና ወደ ተራ ስድብ አልገባም።

  4. ሰላም bazin በጹሁፍህ ቡዙ የፖለቲካ እስረኞች እያሉ ለምን የአቶ አንዳርጋቸውን ስም ብቻ አነሳህ የሚል ይመስለኛል እንደ እውነቱ ከሆነ ሚዲያ ተከታትለህ ከሆነ ባለፈው ሳምንት በተለያዩ አገሮች ኢትዮጵያ ውስጥ ጨምሮ አቶ አንዳርጋቸው ይፈቱ የሚል ጥሪ ይተላለፍ ነበር:: ባይገርምህ ኢትዮጵያውስጥ ያለው ተፎካካሪ ድርጅት የሞነው ሰማያዊ ፓሪት አቶ አንዳርጋቸው በተመለከተ የአንድ ቀን ውይይት አድሮጎ ነበር:: ታዲያ ድርጅታችወ ግንቦት ሰባት በውጪ አገር ሆኖ ያለደረገውን ሰማያዊ ፓሪቲ በአገር ውስጥ ሆኖ በድፍረት በማድረጉ የዛ አጋር ለመሆን በማሰብ ነው እንጂ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች እንዳሉ በመዘንጋት አይደለም:: በሌላ በኩል እርሶ ሌሎቸን ፐፖለቲካ እስረኞች በተመለከተ የአንድ ቀን ውይይት ቢያደርጉ ከመደገፍ ወደኻላ አልልም::
    ቸር ይግጠምን
    ከአክብሮት ጋር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.