ዘራፊዎችን ለማጋለጥ  ሁሉም ይተባበር!!

May16,2018
Oneamhara1@gmail.com
www.oneamhara.org

ዘራፊዎችን ለማጋለጥ  ሁሉም ይተባበር!! 1በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው በደል፥ ሰቆቃ፥ ስደታና ሞት ቀጥሎሏል። በአንድ አማራ ጽኑ እምነት አሁን ካለው የባሰና የከፋ ከመምጣቱ በፊት ጠላት በመቀነስ ላይ ያተኮረ ትግል መደረጉ ተገቢ ነው በሚል ሙሉ እምነት ይዘን ዘረኛውና እብሪተኛው የትግራይ ጽንፈኛ ቡድን ላይ በማነጣጠር ትግላችንን አጠናክረን ይዘን እንገኛለን። ይህ ጽንፈኛ ተገንጣይ የትግራይ ወያኔ ቡድን አማራውን በግንባር ቀድምትነት ጠላት አድርጎ በመፈረጅ በተመቸው አጋጣሚ ሁሉ በደል እየፈጸመ ይገኛል። በቅርቡ የተቀየሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድም የአማራውን ህዝብ መሰረታዊ ጥያቄና የመኖር ህልውና በማረጋገጥ ረገድ እየሰሩ አለመሆናቸዉን ሁሉም የሚያውቀው ሃቅ ነው።

ምንም  እንኳን  ጠ/ሚ  አብይ  አማራው  የሚፈልገውን  ጥያቄ ለመመለስ ባይችሉም በሚያደርጓቸው ትግሎች ላይ የጋራ ጠላታችንን የሚያነጣጥር ከሆነ አብረን መተባበር አለብን ብለን እናምናለን። ከሰሞኑ በተናገሩት የባለስልጣኖችን ሃብት የመያዝና ወደ ሃገር የማስመለስ ጉዳይ ከሁሉም በላይ የህወሃትን አባላት እና የዘረፋ አጋሮቻቸዉን እንደሚመለከት በማመን አብረን መቆም እንዳለብን እናምናለን። አማራውን ከቀየው በማፈናቀል፥  ሃብት  ንብረቱን  በመዝረፍ  አልፎም መጭው ትውልዳችን ከፍሎ የማይጨርሰውን ዕዳ በመበደር የትግራይ ዘራፊ አምባገነኖችና ሆዳም አሽከሮቻቸው ሃብት ማካበታቸው ግልጽ ነው።

ስለሆነም እነዚህ ጽንፈኛና ተገንጣይ የትግራይ ወያኔ አባላትና ስራ አስፈፃሚዎቻቸዉ የኦህዴድ፥ ብአዴን፥ ዴህዴግ ጥቅመኞች በራሳቸው፥ በልጆቻቸው፥ በዘመዶቻነውና በጏደኞቻቸው በተለያዩ የውጭ ሃገራት ያጠራቀሟቸዉን ቤቶች፥ የንግድ ድርጅቶች፥ መኪኖች፥ መርከቦች፥ የእርሻ ቦታዎችና በተለያዩ ባንኮች የተከፈቱ ኣካውንቶችን ከመረጃና ማስረጃ ጋር በማጠናከር የሃገራችንን ሃብት እድናስመለስ እና በህግ ጠተያቂ ይሆኑ ዘንድ ለመታገል በጋር እንድንቆም ጥሪ እናቀርባለን።

በአንድ አማራ ንቅናቄ እምነት የአማራው ታሪካ ብቸኛው ጠላት ፥ ጠባቡና ትምክተኛው የትግራይ ተገንጣይ ቡድን ህወሃት በመሆኑ፤ የእርስ በርስ ሽኩቻን ወደዳር በማለት ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ! አንድ አማራ ለሁሉም አማራ! በሚል የዚህ ዘመቻ የትግል አካል እንድትሆኑ ለሁሉም የአማራ ማህበረሰብና ለጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጥሪ እናስተላለፋለን።

ትግላችን አማራው በነጻነት አያቶቹ በገነቧት ሃገሩ ኢትዮጵያ ላይ በክብር መኖር እስካልቻለ ፥ የሃገሩ እኩል ዉሳኔ ሰጭና ተጠቃሚ እስከሚሆን ድረስ ቀጣይ ነው። ነገር ግን በጋራ ጠላታችን ላይ በሚደረግ ማንኛውም የትግል እንቅስቃሴ ላይ ጠንካራ ክንዳችንን በማንሳት ጠላታችንን ድባቅ እንመታለን።በዚህ ጉዳይ ላይም የአንድ  አማራ ንቅናቄ ኣመራር ኣካላት ከዚህ በፊት ይሄን ጉዳይ በማጥናት ስራ ከጀመሩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ጋር  እንዲሁም  ከአማራ የህግ ባለሙያና ከውጭ ሃገር የመንግስት አካላት ጋር አብረን እየሰራን መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።

እዉነተኛ አማራ እንኳንስ ተነጋግሮ፥ ተያይቶ ብቻ መግባባት አለበት!!

የአንድ አማራ ንቅናቄ

Oneamhara1@gmail.com www.oneamhara.org

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.