የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ በደህንነቶች ከለቅሶ ቤት ተባረሩ

የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ በብአዴን/ኢህአዴግ ካድሬዎችና ደህንነቶች ከለቅሶ መባረራቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ በደሴ ከተማ ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው በዕጩነት የቀረቡት አቶ ተስፋየ ኃይሌ የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆኑ ግለሰብ የቀብር ሥነ ስርዓት ደሴ ከተማ ላይ በተፈፀመበት ወቅት በመገኘታቸው የ‹‹ሰማያዊ ፓርቲን ቲሸርትን ለብሰህ ለቅሶ ላይ መገኘት አትችልም›› ተብለው በካድሬዎችና ደህንነቶች መባረራቸውን ገልጸዋል፡፡

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር እሁድ መጋቢት 20/2007 ዓ.ም ለሚያደርገው ሰልፍ የሰማያዊ ፓርቲ ቲሸርትን ለብሰው ቅስቀሳ ላይ የነበሩት አቶ ተስፋየ ኃይሌ ከቅስቀሳ መልስ የፓርቲያቸው አባል የሆነው ግለሰብ የቀብር ሥነ ስርዓት ላይ መተገኙበት ወቅት ከካድሬዎች ከፍተኛ ወከባ እንደደረሰባቸውና በኋላም እንዲወጡ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

ሆኖም ‹‹ካድሬዎች ከለቅሶው ካባረሩኝ በኋላ ህዝቡ ምን አገባችሁ፣ ለቅሶ መድረስ መብቱ ነው፡፡ ብሎ እንደገና እንድመለስ አድርጓል፡፡›› ሲሉ አቶ ተስፋየ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

Source-ነገረ ኢትዮጵያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.