የቤንሻንጉሉ የማንቂያ ደዎል ነው! በላዔ ሰቦቹ የመጨረሻውን ነጋሪት ሊመቱ ጫፍ የደረሱ ይመስላል፤ (መስቀሉ አየለ)

ባንድ ወቅት በውቁቱ ስዩም የተባለ ገጣሚ ጽፎት መሰለኝ እንዲህ የሚል ነገር ማንበቤ ትዝ ይለኛል።መጀመሪያ የሰው ልጅ እንስሳትን ነፍስ የላቸውም ብሎ እራሱን አሳመነ፤ ከዚያ ቦሃላ የፈለገውን እያረደ ለመብላት የሚገድበው የሞራል እሴት ከውስጡ በኖ ጠፋ ይላል።ምናልባት ገጣሚው ሃይማኖት ስለሌለው አገላለጡን ዘውር አድርጎ አስቀመጠው እንጅ ነገሩ እውነት ነው። ዘፍጥረት በደመ ነፍስ ይኖራሉ ይላልና።

ካሁን በፊት ለመጥቀስ እንደሞከርኩት ዲቶቭስኪና የጀርመኑ ፈላስፋ ፍሬደሪክ ኒቸ በአስራስምንተኛው ክዘመን መጨረሻ ወይንም ኤጅ ኦፍ ኢንላትመንት ላይ የተከሰቱ የክ/ዘመኑ ጥግ ጠቢባን ናቸው።ሁለቱም ሰዎች መጭውን መራር እውነት በተለያየ ግዜ ነገር ግን ተመሳሳይ በሆነ ይዘት አስቀምጠውት አልፈዋል። ዲቶቭስኪ ሲናገር “If there is no God, Nothing is Forbiden” አለ። ኒቸም በበኩሉ “If there is no God, everything is possible” አለ። ሁለቱን ጠቢባን ወደዚህ አይነት ድንዳሜ ላይ ያደረሳቸው ነባራዊ እውነት ከፊሉ እነ ዳርዊን ይዘውት በመጡት አይደፈር በሚመስል የሳይንስ ትንታኔ ከፊሉ በኮሙኒዝም ፍልስፍና መስከር የጀመረበት እና የሰው ልጅ በግልጽ ከአምልኮተ እግዚአብሔር መውጣት የጀመረበት ይልቁንም በአምልኮተ እግዚአብሔር መኖር የድንቁርና መግለጫ ነገር ግን አንድ ሰው በሳይንስ ሲያምን ደግሞ “If someone doesn’t beleive in God, it is simply because he/she have a critical thinking aparatus to undesrand science” የሚል አቋም የተያዘበት የክህደት የኑፋቄ ዘመን መባቻ ስለነበረ ነው። ዩኒቨርሱን በመተንተን እረገድ ለሶስት መቶ አመት ያህል ሳይንስ በሃይማኖት ላይ ይዞት የቆየው የበላይነት በኩዋንተም ፊዚክስ አፈር ድሜ እስኪበላ ድረስ ሃሳበ ድውያን የብዙዎችን ንጹሃን ነፍስ አርክሰዋል።

ወደ ተነሳሁበት ስመለስ ሁለቱን ጠቢባን እንዲህ እንዲናገሩ ያስገደዳቸው ነገር ሰው በክህደት ውስጥ መኖር ሲጀምር አለም ላይ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አደጋውን ቀድመው ገና በጠዋቱ አይተውት ስለነበረ ነው። በዚህም የተነሳ እነሱ ይህን በተናገሩ በቀጣዮቹ ሃያና ሰላላ አመታት ቦሃላ በአውሮፓና በኤሽያ አንድም የኮሚዩኒዝምን አይዲዮሎጅ በሃይል ለማስረጽ በተፈጸም የጅምላ ፍጅት; አንድም በአንደኛውና በሁለተኛው የአለም ጦርነት ሳቢያ ወደ ሁለት መቶ ሚሊዮን ሰው አለቀ። ሰው “እግዚአብሔር የለም” ብሎ ሲያምን እና ከክፋት የሚገድበው የሞራል ለከት ሲያጣ በቀናት ጀንበር ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ ለመፍጀት የሚያቆመው ምንም አይነት ልጏም እንደማይኖር ፍንትው ያለው መራር እውነት ለአለም እራሱን የገለጠበት ኩነት ነበር ማለት ይቻላል ። በስታሊንም ሆነ በሂትለር እንዲሁም የነርሱ የልጅ ልጅ በሆነው በዘመነ ወያኔም ያየነውም ይኽንኑ ነው ።

ወያኔ ሲጀምር እንዲህ በሙሉ ማንነቱ ከመገለጡ በፊት የእምነት ተቋማትን በማራከስና አገራዊ እሴቶችን ቀስ በቀስ በማፈራረስ እናት ኢትዮጵያን ለእርድ ሲያዘጋጃት እሩብ ክፍለ ዘመን ቆይቷል። ዛሬ ከአምሳ አመት በታች እድሜ ያለውና በሃይማኖት የሚኖር ሰው በትግራይ ምድር ፈልጎ እንደማያገኝ ማረጋገጥ ለሚፈልግ ሰው በሰሞነ ሁዳዴ መቀሌ ላይ የጾም ምግብ ፍለጋ ይውጣና ምን ያህል ጫማውን እንደሚጨርስ ሲያየው ይገባዋል።

ዛሬ የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ኢኒህን ድውያን መሸከም የማይችልበትና ጸሃያቸውም እየጠለቀች መምጣት ስትጀምር የከፋውን ማንነታቸውን ወደ ውጭ በማውጣት እነርሱም ሂትለርና ስታሊን እንዲሁም የሩዋንዳው ኢንተርሃሞይ በሄዱበት ጎዳና ተጉዘው ሚሊዮኖችን ለመፍጀት መንገድ መጀመራቸውን እያየን ነው። ሰሞኑን በቤንሻንጉልና በመሳሰለው የሰው ልጅ ላይ ሲፈጸም የምናየው ሰቅጣጭ ወንጀል ሁሉ ገና የምጥ መጀመሪያ ነው። ካላይ በምግቢያዬ ላይ እንደተባለው የሰው ልጅ በግና በሬን አርዶ የመብላት ስነልቦና ማዳበር የቻለው መጀመሪያ “እንስሳት ነፍስ የላቸውም” ብሎ በማመኑ እንደሆነ ሁሉ የትግራዩ ገዢ ጉጅሌውም ለሩብ ክፍለ ዘመን ያህል ለዚህ አይነት ላርጅ እስኬል ጀኖሳይድ ሲዘጋጅና ሲያከማች የኖረው ለክፉ ቀን የሚሆን ሃብትና ንብረት ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም “አማራ ጭራቅ ነው” በሚል እርሾ ተቦክቶ የተጋገረ እና ምንም አይነት ወንጀል ለመፈጸም የጭካኔ እጥረት የሌለበትን እምነት አልባ!- ሞራል አልባ! አንድ ሙሉ አረመኔ ትውልድ እያመረተም ጭምር ነው እንጅ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.