ፓትርያርኩ በሕግ አፍራሽነታቸው ጸኑ

በአ/አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ ምርጫ ከረዳት ሊቀ ጳጳሱ ጋራ እንዲግባቡ የተደረገው ጥረት አልተሳካም

  • መመሪያቸው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ኹለንተናዊ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ጠቅላይ ጽ/ቤቱ በዛሬው የቋሚ ሲኖዶሱ ስብሰባ ያቀረበውን ስጋት አጣጥለውታል
  • በአ/አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች ምርጫ እና ሥያሜ የፓትርያርኩን የአካሔድ ስሕተት ከማረም አንጻር የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ እና መመሪያ እንደሚሰጥበት ይጠበቃል

በሥራ አስኪያጅ ምርጫ እና ሥያሜ አለመግባባቱ አጋጣሚ፣ ፓትርያርኩ፡-

  • ረዳት ሊቀ ጳጳስ መርጦ ከማቅረብ ድርሻቸው በላይ በቅዱስ ሲኖዶሱ የሚወሰነው የመመደቡም ጉዳይ ከእርሳቸው ሓላፊነት ጋራ እንደሚያያዝ በመመሪያቸው ከመጥቀስ አልፎ፣ ‹‹እኔ[ሥራ አስኪያጅ] መድቤአለኹ፤ ሾሜአለኹ፤ የሚሠሩ ከኾነ ተስማምተው ይሥሩ›› በማለት የረዳት ሊቀ ጳጳሱን ሚና ፋይዳ ቢስ ማድረጋቸው፤
  • በብፁዕ ዋና ጸሐፊው የሚመራው የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት፣ የቋሚ ሲኖዶሱን መነጋገርያ ርእሰ ጉዳይ አዘጋጅቶ ለውይይት የማቅረብ ተግባሩ መሠረት፣ በትላንትናው ዕለት በአድራሻ የተጻፈለት የረዳት ሊቀ ጳጳሱ ጥያቄ በአጀንዳነት ተይዞ እንዲታይ ሲጠይቅ፣ ጉዳዩን ለውይይት ዝግ ከማድረግ አልፎ ብፁዕ ዋና ጸሐፊውን በአሳዳሚነት መውቀሳቸው

እንደ ቅዱስ ፓትርያርክ መጠን፣ ሕጉን ተገንዝቦ እና ጠብቆ ለቤተ ክርስቲያን ከአድልዎ የጸዳ አጠቃላይ አባታዊ አመራር በመስጠት ረገድያለባቸውን የታማኝነት ውስንነትና የአማሳኝ አማካሪዎቻቸውን በተለይም በተደጋጋሚ ሲጋለጥ የቆየውን የልዩ ጸሐፊአቸውን ተንኰል እና ክፋት በገሃድ ያረጋገጠኾኖ አልፏል፡፡

Source:: haratewahido

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.