“ብየ ነበር!” እንዳይሆንብኝ እንጅ.. (ዳንኤል ተፈራ)

ዶ/ር አብይ ሚኒልክ ቤተመንግሥትን ከመቆጣጠሩ በፊት ለቲም ለማ እና ለማ መገርሳ መርቆ ለሸኘው ዶ/ር አብይ እድል ሊሰጠው ይገባል ብየ እዚችው የመወዛገቢያ ሚዲያ ፌሥቡክ ላይ ፅፌ ነበር። ማረጋገጥ ከፈለግህ ገፄ ላይ ገብተህ ተመልከት።

ለምን ካልከኝ፦
1. በሥድሳዎቹ እና በዚህ ማንነቱን ከኢትዮጵያዊነት እና ማን’ነኝነት ውሥጥ እየፈለገ ባለ ትውልድ መካከል የተገኘ ሥለሆነ ነው።

2. የህወሃትን ቁሞቀር ፖለቲካ፤ የበለው፣ እሠረው፣ አሥወግደው…. እዚያው እነሡ ውሥጥ ሆኖ በተወሰነ ደረጃ የመቃወም አዝማሚያ በማሣየቱ፤

3. ኢትዮጵያዊነትን ከፍ የሚያደርግን ፍንጭ በመመልከቴ፤
4. ኦሮሞ ጠባብ ሳይሆን፣ ባህሉና ወጉ ለጠባብነት ሩቅ ሆኖ ሣለ የፖለቲከኞች ድሪቶ ጠባብ አድርጎ በመሳሉ እና ከወንድሙ አማራው ጋር የጠላትነት ትርክት ተፈብርኮ ተሠጥቶአቸው የጎሪጥ እንዲተያዩ የተጎነጎነው የፖለቲካ ደባ ያበሽቀኝ ሥለነበር አብይን እድል ይሠጠው ብየ ነበር።

ፖለቲካች አሥቸጋሪ እና አሥጨናቂ እንደሆነ ከሚገነዘቡ መካከል ነኝ። ፖለቲካ ፌሥቡክ ላይ እንደመጦመር ቀላል አይደለም። በተለይ የአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካ ያው እንደሥሙ ቀንድ ነው። ከመዋጋት በሥተቀር መፍትሄ የሌለው ቀንድ።

በበኩሌ ዶ/ር አብይ በአጭር ጊዜ ነገሮችን ለማሥተካከል እያደረጉ ያለውን ጥረት የጎሪጥ ከመመልከት መጀመር አልፈልግም። ሥህተት ከመፍለግ መጀመር አልፈልግም። ይህንን የምለው ህወሃት ብቻ የተበተበውን ተንኬል ለመፍታት ትግሥት እና ጊዜ እደሚያሥፈልግ ሥለምገነዘብ ነው።

የዶ/ር አብይ እንቅሥቃሴ ፖለቲካን ከሰውኛ ማህበራዊ እሳቤ ጋር የቀላቀለ ነው። የሃገራችን ችግር በአብይ ብቻ ይፈታል ብሎ እጅን አጣምሮ መጠበቅ ሥህተት ነው። ወይም ሞኝነት። አሁን ሃገራችንን ቀጥ አድርገን ማቆም እፈልጋለን። ነገርግን ዜጎች በማነታቸው ብቻ ሠቆቃ እየተፈፀመባቸው ነው። አማሮች ላይ ደግሞ የከፋ ነው። ሣዑዲ የህክምና ሥህተት ሠለባ የሆነውን ብላቴና በመጠየቃቸው ብዙ ነገር እንዳሥብ አድርጎኛል።

ሥለዚህ አብይን ለሚያደርጉት ነገር እያመሰገንን ዋናዋ ኢትዮጵያችን ከፍ የምትልበት ላይ እናተኩር።
ሥላነበባችሁኝ አመሰግናለሁ!!

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.