የነውረኛው ብአዴን ጉድ! (አቻምየለህ ታምሩ)

ከታች የታተመው ገጽ ነውረኛው ብአዴን በ1986 ዓ.ም. ባሳተመው ድርጅታዊ ፕሮግራም ገጽ ሁለት ላይ ይገኛል። የሕወሓቱ ነውረኛ ድርጅት ብአዴን በፕሮግራሙ መግቢያ ላይ ፋሽስት ወያኔ «የአማራ ክልል» በሚል ከፈጠረው ክልል ውጭ የሚኖሩ አማሮችን «በአማራ ብሔር ስም የሚነግዱ ነፍጠኛ» ፣ «ትምክህተኞች» እና « የሌሎችን ብሔር፣ ብሔረሰቦች ጨቋኞች» ሲል ይገልጻቸዋል፤ እነሱንም እንደማይወክል ይነግረናል።

በብአዴን አስተሳሰብ ዛሬ በአምቦ፣ በኢሉ አባቦራ፣ በመተከል፣ በጅማ፣ ወዘተ. . . የሚኖሩና ቤታቸው እየተቃጠለ፣ ንብረታቸው እየተወረሰ፣ እየተገደሉ፣ እጃቸው እየተቆረጠና ቤት ተዘግቶባቸው እየተቃጠሉ እንዲፈናቀሉ እየተደረጉ ያሉት አማሮች «በአማራ ብሔር ስም የሚነግዱ ነፍጠኛ» ፣ «ትምክህተኞች» እና « የሌሎችን ብሔር፣ ብሔረሰቦች ጨቋኞች» ናቸው።

ከመተከል፣ ከአምቦ፣ከጅማ፣ ከኢሉ አባቦራ፣ ወዘተ ተፈናቅለው በየመንገዱ ስንት መከራ እየተቀበሉ ባሕር ዳር ድረስ ተጉዘው ችግራቸውን ለብአዴን ለማስረዳት ጽሕፈት ቤቱ ደጃፍ ሲደርሱ «ለምን ለአቤቱታ መጣችሁ?» እየተባሉ በሕወሓት/ብአዴን ቅልብ ፖሊሶች የሚታሰሩት፣ ከእንደራሴው ቢሮ ፊት ለፊት ባለው ሜዳ «ማደር አትችሉም!» የሚል መልስ እየተሰጣቸው የሚባረሩት ለብአዴን «አማራ ክልል» ከሚባለው ውጭ ያሉ አማሮች «በአማራ ብሔር ስም የሚነግዱ ነፍጠኛ» ፣ «ትምክህተኞች» እና « የሌሎችን ብሔር፣ ብሔረሰቦች ጨቋኞች» ስለሆኑና ብአዴን ደግሞ በፕሮግራሙ እንደነገረን የሚታገለው ነፍጠኞችና ተባባሪዎቻቸው ሲል የሚገልጻቸው የአማራ ክልል ከሚባለው ውጭ የሚኖሩ አማሮችን ለመቃወምና ለመታገል ስለሆነ ነው።

ነውረኛው ብአዴን ባሳለፍነው ሳምንት በደብረ ብርሃን ከተማ ተቆርቋሪ የአማራ ልጆች ከጎጃም መተከል ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን ርዳታ ይሆን ዘንድ የጀመሩትን የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ያስቆመው፤ እሁድ እለት የፋሲል ከነማና የባህር ዳር ከነማ የእግር ኳስ ቡድኖች ከመተከል ለተፈናቀሉና ጭፍጨፋ ለተፈጸመባቸው አማሮች ርዳታ ለማሰባሰብ ሊያካሂዱት ያሰቡትን የገቢ ማሰባሰቢያ ጨዋታ እንዳይካሄድ ያገደው ተፈናቃይ አማሮቹን «ትምክህተኞች» እና « የሌሎችን ብሔር፣ ብሔረሰቦች ጨቋኞች» ናቸው ብሎ ስለሚያምንና ሕወሓትም ነውረኛውን ብአዴንን የፈጠረው «ከክልላቸው ውጭ» የሚኖሩ የተባሉትን አማሮች እንዲቃወምለትና እንዲታገልለት ስለሆነ ነው። እነሆ ዶሴው!

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.