ዜና ደቡብ አፍሪካ …. የህወሃት ጉዳይ አስፈጻሚና ተወካይ የሆነዉ የኢትዮጵያ ኢንባሲ በደቡብ አፍሪካ ቅጥር ግቢዉን ዘግቶ እንዲሸሸ ተደረገ

ልዑል ዓለሜ

የአክቲቪስት ገዛኽኝ ገብረ መስቀልን በክብር መሰዋት ተንተርሶ ግድያዉን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ያስፈጸመዉ ጉጅሌዉ ወያኔ ኢንባሲ በር ፊት ለፊት የኢትዮጵያ መሐበረሰብ ማሕበር የጠራዉን የተቃዉሞ ሰልፍ መጋፈጥ ተስኖት ኢንባሲዉን ለመዝጋት ተገዷል።

በአዲስ አበባ የሚገኘዉ የዶ/ር አብይ ጠ/ሚኒስቴርነት ሹመት በትኩስነቱ እያለ ካስፈጸማቸዉ አደገኛና ትልቅ ስህተቶች አንዱ እና ትልቁ በአክቲቪስት ገዛኽኝ ገብረ መስቀል ላይ ተግባራዊ እንዲሆን የተወሰነዉ የግድያ ወንጀል ነዉ ይህን ወንጀል የፈጸመዉ አካል ግዜ ይወስዳል እንጂ የትም መሸሸግ አይችልም ነገር ግን ዛሬ ለግዜዉም ቢሆን ኢንባሲዉን ዘግቶ ለመደበቅ ሞክሯል።

ይህ ኢንባሲ በኢትዮጵያዊያን ላብ እና አግባብ ባልሆነ መንገድ ከግብር በሚሰበሰብ ጥሪት ኪራዩ የሚከፈልለት ሆኖ ሳለ ወያኔያዉያን እንደፈለጉ ሊዘጉትና ሊከፍቱት ፈጽሞ የማይችሉበት ግዜ እንደሚመጣ ክስተትቱ ዛሬ በትክክል ግልጽ ሆኖ ታይቷል።
በዚሁም በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እዉነት የወያኔ መንግስት በግድያዉ ወንጀል ላይ እጁ ከሌለበት ገለልተኛ የሆነ ጉዳዩን አጣሪ ቡድን ተዋቅሮ ወንጀለኞቹ ለህግ እንዲቀርቡ ይተባበር የሚል መልእክት ለማሳለፍ ቢሄዱም የወያኔ ጉዳይ ማስፈጸሚያ ቢሮ መልእክቱን ላለመቀበል እጁም በትክክል በጉዳዩ ላይ እንዳለበት በሚያረጋግጥ መልኩ ኢንባሲዉን ከርችሞ ተሰዉሯል።

የጀግናዉ ገዛኽኝ ገብረ መስቀል ገዳዬች በህግ ተይዘዉ ለህግ እስኪቀርቡ ድረስ እስከ አምጨረሻዉ እንታገላለን ያሉ የደቡብ አፍሪካ ነዋሪ ኢትዮጵያዊያን እጅግ ጨዋነት በተሞላበት መንገድ የተለያዩ የአለም አቀፍ ሚዲያዎች በተገኙበት መእክታቸዉን አስተላልፈዉ ወደ መጡበት በሰላም ተመልሰዋል።

በምስሉ ፊት ለፊት ላይ ያለው ጀግናዉ ገዛኽ ነብሮ ከምስሉ ጀርባ ያለዉ ወንጀለኛዉ እና ዘግቶ የፈረጠጠዉ የህወሃት ወያኔ ኢንባሲን ይመልከቱና አሸናፊዉን ይወስኑ።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.