በወያኔ ባንክ፣ የብር ኢንኩቤተር የተፈለፈሉ ሙሰኛ ቢሊየነሮችተለቀቁ!!! ‹‹ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር››

ከጥርጊያ ጎዳና ይቀርባል ብለው
በስርቆሽ በር ሄዱ ይሻላል ብለው፡፡››
የኢትዩጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ክቡር ዶክተር ተፈራ ደግፌ ሃገራዊ፣ ሙያዊ ፍቅርና ስብዕናቸው ማስታወሻ

የኢትዩጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ  አቶ ተክለወልድ አጥናፉ (አባባ ታምራትዋን!)፤ የኢብባ ምክትል ገዥ አቶ ዮሐንስ አያሌው (አባባ ታምራትቱ!)፤ አቶ በቃሉ ዘለቀ የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዜዳንት (አባባ ታምራትስሪ!)፣ ንፋስ አመጣሽ ቢሊየነሮች ንዋየ ጠንቆያቸው ‹አባባ ታምራት› ይሎቸዋል፡፡  በሃያ ሰባት ዓመታት፣ ብር እንደ እንቁላል የታቀፉት ሚሊዩነሮችና ቢሊየነሮች መኃል፤ ሽህ መሃመድ ሁሴን አላአሙዲ፣ አቶ ሳሙኤል ታፈሰ፣ አቶ ተክለብርሃን አምባዬ፣ ወይዘሮ አኢኮ ሥዩም፣ አቶ ቴዎድሮስ አሸናፊ፣ አቶ ዳዊት ገብርእግዚአብሄር ለናሙና ያህል ቀርበዋል፡፡

{1}የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክና የግል ባንኮች አድሎዊ የብድር ሥርጭት በክልላዊ መንግሥቶች፣ በኢኮኖሚ ዘርፎች ለግብርና፣ ለኢንዱስትሪና አገልግሎት ዘርፎች የተሠጠውን ብድር የ27 አመታት መረጃ ለህዝብ ማሳወቅ በሃገሪቱ ያለውን የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት የተዛባ በዘር ላይ የተመሠረተ የባንክና ፋይናንሻል ዘርፍ ዘረፋና ያልተመጣጠነ የክልሎች እድገትና በወያኔ ገንዘብ ባላሃብቶች በዘር ላይ የተመሠረተ ሚሊየነሮችና ቢሊየነሮች መፍጠርና መፈልፈል መረጃው ያሳያል፣

{2} ብሔራዊ ባንክ ለሃይማኖት ተቆማት የባንክ ፍቃድ መስጠቱን የዶክተር አብይ አህመድ መንግሥት እንዲያስቆም ህዝቡ ተቃውሞውን በህዝባዊ እንቢተኝነት መግለፅ አለበት፡፡ ወያኔ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ተቆጣጥሮ በወጋጋን ባንክ፣ በአንበሳ ባንክ፣ በእናት ባንክ አሁንም ደግሞ በዳሎል ባንክ በኩል እየዘረፈ ይገኛል፡፡ አበው ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ!›› ይላሉ፡፡ ኢኮኖሚውን የተቆጣጠረ ፖለቲካውን ይቆጣጠራል፡፡ ጥያቄችን የብሄራዊ ዳቦ ድርሻ ጥያቄ ነው!!! የወያኔ ኢኮኖሚ የኢፈርትና ሜቴክ ኃብት ሳይወረስ ነፃነት የለም!

{3} የኢትዩጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን፣ እምነት አማኞች አስራት አለመስጠትና ከህንፃ አለመከራየት እንዲሁም በሚቆቆመው የዳሎል ባንክ አለመጠቀም ህዝባዊ አድማ በኢሣት፣ በኦሮሞ ሚዲያ ኔት ወርክ፣ ሌሎች መገናኛ ብዙሃን አድማውን ለህዝብ ማዳረስ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው እንላለን፡፡

{4} የቻይና  የኮምኒስት ፓርቲው ጀነራል ሴክረተሪ  ሺ ጂን ፒንግ Xi Jinping የፀረ ሙስና ዘመቻ በበ18 ብሄራዊ ኮንግረስ ላይ በ2012 እኤአ ከገለፁ በኃላ የካድሬዎች ሙስናና ሌብነት በአደባባይ የተጋለጠው፡፡ ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል Transparency International በ2017እኤአ የቻይና በሙስና ከዓለም 180 አገራት 77ኛ  በመሆን ችላለች፡፡ የሙሰኛነት ወንጀል ውስጥ ጉቦ መቀበል፣ ገንዘብ መዝረፍ፣ ከበር በስተጀርባ ውል መፈፀም፣ የዝምድና ሥራ፣ የበላይ ጠባቂነት፣ የሃስት መረጃ ማቅረቡ ወዘተ ያካትታል፡፡  ሙስና እንደ ሰደድ እሳት ነው የአንድ አገርን የወደፊት ህልውና  የፖለቲካና ኢኮኖሚ ምሶሶን ቀስ በቀስ ይንዳል፡፡ በቻይና ሙስና መዋቅራዊና መዋቅራዊ ያልሆነ ተቆማዊ ሠንሰለት ያለው ዓይነት ሆኖ ተገኝቶል፡፡ መዋቅራዊ የሙስና ወንጀል የእዝ ሠንሠለቱ በኢኮኖሚና በፖለቲካ መንግሥታዊ መዋቅሮች ውስጥ አግድማዊና አማዳዊ  የመረብ ቆት በመዘርጋት ግንኙነቱ በስውር የሚካሄድ ዘርፈ ብዙ ቅርንጫፎቹ ያሉት፣ የትስስር ሰንሰለቱን  ለማወቅ ፈታኝ በመሆኑ መላ ስርዓቱ በስር ነቀል ለውጥ መተካት አማራጭ የለውም፡፡  According to Yan Sun, ssociate Professor of Political Science at the City University of New York, it was corruption , rather than democracy as such, that lay at the root of the social dissatisfaction that led to the Tiananmen square protests of 1989. . Corruption undermines the legitimacy of the CPC, adds to economic inequality, undermines the environment, and fuels social unrest. 1 በ2002 እኤአ ቻይና በሞት የቀጣቻቸው 12፣000 ሲሆኑ በ2007 እኤአ 6500 ሰዋች እንዲሁም በ2013/14እኤአ 2400 ሰዎች የሞት ፍርድ ተቀጥተዋል፡፡ በ2015 ቢሊየነሩ ሊዮ ሃን በማት ተቀጥቶል ወንጀሉም ሦስት ሰዎች በወንጀለኛ ወንበዴ ብድን በማስገደላቸው ነበር፡፡ በ2006 እኤአ ከዘጠኝ አመት በፊት ቢሊየነሩ ዮዋን ባዎጂንግ በሞት ተቀጥተዋል፡፡ ቻይና ከድህነት ወለል በታች የሚገኙ 400 ሚሊዮን ህዝቦች ስላሎት የሙስና ወንጀል በሞት ያስቀጣል፡፡ ቻይና የሞት ፍርድ የፈረደችባቸውን እስረኞች የሰውነት ክፍሎች ላይ ንቅለ ተከላ በማድረግ እንደምትሸጥ ይታወቃል፡፡ ፀሃፊው በሞት ቅጣት አያምንም፣ ሆኖም የህዝብ ንብረት ማስመለስና በእስራት መቅጣት ህግ ተግባራዊ መደረግ አለበት፡፡

“How much is an errant Chinese official’s life worth? Three million reminibi, or $463,000, according to a statement released on April 18 by Chinese judicial authorithies. The legal clarification makes the death penality applicable to anyone who either embezzeles, or accepts bribes of, that sum or more. But in certain “ especially serious” instances “with extremely vile impact, ” like when officials embezzle disaster-relife funds, stealing half that can be grounds for death by firing squad. 2” በኢትዮጵያ የሙስና ምንጭ ደካማ መንግስታዊ መዋቅር ሲሆን መንግሥት ማስፈፀም የማይችለውን አንድ ሽህ አንድ ፕሮጀክቶች በአንድ ጊዜ ነድፎ ሥራ ያስጀምራል፣ገንዘቡ ይዘረፋል፡፡ መንግሥት ግልፅ ያልሆነ የግብርና ታክስ በንግዱ ህብረተሰብ ላይ በመጣሉ የተነሳ ጉቦ በመስጠት የመንግሥት ሹሞችን መደለል ይቀጥላል፡፡ በኢትዮጵያ ገቢዎች ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር ሙሰኛው ገብረዋህድ  ወልደ ጊዬርጊስ፣ ሙሰኛዋ አዜብ መስፍንና አስመላሽ ወልደሥላሴ የብሄራዊ ሜታልና ኢንጂነሪንግ (ሜቴክ) ቦርድ አባል ፣ ጌታቸው አንባዬ የጠቅላይ ሚንስትሩ የህግ አማካሪሆነው ተሸመዋል፡፡ የህዝብ መፈናቀል ቀጥሎል፣ በሶማሌና ኦሮሞ ግጭት ከአንድ ሚሊዮን ህዝብ በላይ ተፈናቅለዋል፣ ከቤኒሻንጉል ከብዙ ሽህ ህዝብ በላይ ተፈናቅሎል፣ በጌዲዮና ጉጂ ዞን ከ200 ሽህ ህዝብ በላይ ተሰደዋል፣ አዲስ አበባ ሃና ማርያም ከ20 ሽህ ህዝብ በላይ ቤታቸው ፈርሶ ሜዳ ፈሰዋል፡፡ እነዚህ ዜጎች የመሬት ወረራ ሙስና ፈፅሟል ተብለው ከሆነ ለዋና ሌቦቹ የደረሰ ምህረት ለእነሱም መቸር ይኖርበታል፡፡ በቡራዩ የፈረሰው መስጂድና በህዝብ ላይ እርምጃ ወስደዋል፤ በአርባ ምኝጭ የአንድ መንደር ሰዎች ቤታቸው ፈርሶል ህገ ወጥ የቤት ግንባታ አድርጋችኃል በማለት የመንግስት ግብረ ኃይል ቤታቸውን አፍርሶል፣ አጋዚ ጦርና መከላከያው ህዝቡን አቁስሎል፡፡ ዜጎች ቤት የመስሪያ ቦታ በህገወጥ መንገድ ወሰዳችሁ ተብለው እንዲህ ዓይነት እርምጃ ሲወሰድባቸው የህዝብ ገንዘብ የዘረፉ ማፍያ ሌቦች ከህግ በላይ ሆነው የሚፈቱበት የወያኔ መንግሥት  የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈታ ካደረግህ ወያኔ አባላቶች የኢኮኖሚ የሙስና እስረኞች መለቀቅ አለባቸው ብለው የወያኔ ሹሞች ተፅእኖ ማድረጋቸው እሙን ነው፡፡ህለዚህ ህዝባዊው እንቢተኛነትና ተጋድሎ የወያኔ ሥርዓት እስኪወድቅ ድረስ መታገሉን መቀጠል የህልውናው ጉዳይ ነው እንላለን፡፡ በኢትዮጵያ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ህገ መንግሥቱ ወረቀት ያህል ክብደትና ዋጋ የሌለው፣ የፍታብሄርና የወንጀለኛ መቅጫ የዘመናት  መተዳደሪያ ህጋችን ተጥሶል፡፡ ከዚህ ዘመን ጀምሮ ህገ አራዊት ህገመንግስትና የፍታብሄርና የወንጀለኛ መቅጫ ህጋችን እንጦሮጦስ ወርደዋል፡፡  በሙስና፣ ኮንትሮባንድ ንግድና ኪራይ ሰብሳቢነት ህገውጥ ሥራ የግብር ማጭበርበርና መደበቅ ሥራን መግታት፡፡ የተጀመረውን የሌብነትና የሙስና እንቅስቃሴና የታሰሩት ግለሰቦችና የተወረሰው ንብረት የህዝብ ሃብት ማድረግ፡፡ በትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል፣ ጥናት መሠረት ኢትዮጵያ  በሙስና ከዓለም 180 ሃገራት 107ኛ ደረጃ፣ እንዲሁም ከአፍሪካ ሃገራት 20ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ በሙስና ከመቶ 35 በመቶ ውጤት በማግኘት ወድቃለች፡፡ የውጭ እዳና ጫናን ሙስና እያለ የሀገር እዳና ብድር መክፈል አይቻልም፡፡ የጠቅላይ ኦዲተር ፅህፈት ቤት ሃላፊ፣ የጸረ- ሙስናውን ትግል በነጻነት እንዲመሩና በሃገሪቱ ውስጥ የተስፋፋውን ሙስና፣ ኮንትሮባንድና ኪራይ ሰብሳቢነት ህገወጥ ግለሰቦችን ለፍርድ እንዲያቀርቡ ኃላፊነት መስጠት፣ ከህግ በላይ ማንም ሰው መሆን እንደማይችል በተግባር መገለፅ አለበት፡፡ ሃላፊው በተደጋጋሚ ለፓርላማ ያቀረቡት የኦዲት ሪፖርት ድጋፍ ተሰጥቶት በፍርድ ቤት ፍትህ እንዲሰጥና የህግ ተፈፃሚነት ተግባራዊ ማድረግ፡፡ ሙስና፣ ኮንትሮባንድ ንግድና ኪራይ ሰብሳቢነት ህገውጥ ሥራ ከነሰንኮፉ ነቅሎ መጣልና የአይነኬ የህወሓት/ኢህአዴግ ሹማምንትና የጦር መኮንኖች ንብረታቸውና ሃብታቸው በፀረ-ሙስና ኮሚሽን ማስመዝገብና የሃብትና የንብረት ምንጫቸው ለህዝብ ማሳወቅ ግድ ይላል፡፡ የሹሞች የህክም ወጪ በውጭ ምንዛሪ ይቁም!!!

ንፋስ አመጣሽ ቢሊየነሮችን የፈለፈሉ አንድ ዓይና የባንክ ሙያተኞች!!! የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ‹‹የኢኮኖሚው ፋይናንስ አቅርቦት ደጀን›› ‹‹የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  ኢንዱስትሪው እየተሰፋፋ ነው፡፡… በባንኩ ዘርፍ ኢኮኖሚውን በመደገፍ የአንበሣውን ድርሻ ከሚይዙት ባንኮች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቀዳሚው ነው፡፡ …ባንኩ ከተመሰረተበት ነሐሴ 23 ቀን 1934 ዓ/ም ጀምሮ እስካሁን ድረስ የሚጠበቅበትን የባንክ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ አቶ ኤፍሬም መኩሪያ ገልፀዋል፡፡ …ባንኩ ሚያዝያ ወር ላይ በ1935 ዓ.ም በሁለት ቅርንጫፎች ሥራውን የጀመረ ቢሆንም ላለፉት 75 ዓመታት ተዳራሽነቱን በማስፋፋት አሁን 1235 ቅርንጫፎች ለህብረተሰቡ የባንክ አገልግሎት የሚሰጥበት ደረጃ ላይ ለመድረስ ችሎል፡፡… በአሁኑም ጊዜም በባንክ ቁጠባ ሂሳብ የከፈቱ ደንበኞች ቁጥር 16.6 ሚሊዮን መድረሱን ገልጸዋል፡፡… ባንኩ የሰጠው የብድርና ቅድመ ክፍያም መጠንም በየጊዜው እያደገ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜም 152.9 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተገልጾል፡፡…ባንኩ ሥራ ሲጀምር የባንኩ ጠቅላላ ተቀማጭ 100 ሚሊዮን ብር አይበልጥም ነበር፡፡ ሆኖም በየጊዜው በተሠሩ ሥራዎች ተቀማጩን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ ችሎል፡፡ ዛሬ ላይ ተቀማጩ 382.2 ቢሊዮን ብር ደርሶል፡፡ ይህም ገንዘብ የማቅረብና ኢኮኖሚውን የመደገፍ ሚናውንም በተሸለ መልኩ እንዲወጣ አስችሎታል፡፡ የባንኩ የሠራተኞች ቁጥር ከ40 አይበልጥም ነበር፡፡ አሁን ከ33 365 ሽህ ሠራተኞች የሥራ እድል ፈጥሮል፡፡ ባንኩ በወቅቱ አራዳ ጊዮርጊስ የነበረውን ሕንጻ በመከራየት ሥራ የጀመረ ሲሆን በሂደት የራሱ ህንፃዎች በመገንባት አገልግሎቱን በማስፋፋት በአዲስ አባባና በክልል ከተሞች በመገንባት የተደራሽ ጉዞውን ቀጥሎል፡፡…የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  በአሁኑ ጊዜ 495.4 ቢሊዮን ብር ጠቅላላ ብር አለው፡፡›› 3

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክና የቤቶችና ቁጠባ ባንከ በቀጭኑ ሽቦ ቀጭን የወያኔ ትዕዛዝ ለእከሌ 20፣ ለእከሊት 40 ሚሊዮን ብር፣ አንድ ቢሊዮን ብር አበደረው!!!! በኢንኩቤተር ውስጥ የገባ እንቁላል እንኮን ሃያ አንድ ቀናት ጠብቆ ነው ጫጩት ሆኖ የሚፈለፈለው፡፡ የኛዎቹ ሚሊየነሮችና ቢሊየነሮች ደግሞ ሽበጥ ተጫምተው፣ ቁምጣ ታጥቀው፣ ቦንብ አገልድመው፣ ክላሸን አንግተው፣ አህያ እየነዱ ሲመጡ ቤት ለእንቦሳ አልናቸው፡፡ በሃገራችን 95 በመቶ የደሃ ልጆች ነን፡፡ እነዚህ ሃብታሞች በእርሻ ግብር፣ በማኑፋክቸሪንግና በአገልግሎት ዘርፎች ተሠማርተው ምርት አምርተው ሃብት አላፈሩም፡፡ በግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመን  ባለጸጎችን እርሻና ፋብሪካዎች፣ ደርግ ሃብታቸውን ወረሳቸው፣ ወያኔ ደግሞ ያን ሃብት ነቀላና ተከላ ለእራሱ አደረገ፣ ሁሉም ማስረጃ ተሰድሮ ተሰድሮ ተከማችቶል፡፡ ሁሉም በሚሠራበት መረጃውን ያጠናቅር፣ ሌቦችን ሙሰኞችን ያልታገለ በተባባሪነት ያስጠይቀዋል፡፡ ህግን አለማወቅ ከተጣያቅነት አያድንምና!!!  ዛሬማ ‹‹ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  ጠቅላላ ሀብቱ ግማሽ ትሪሊዮን መድረሱ ተገለፀ፡፡ የባንኩ ሀብት ግማሽ ትሪሊዮን ወይም 495.4 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱ የተገለፀው፣ የባንኩ ኃላፊዎች ህዳር 19 ቀን 2010 ዓ/ም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡… የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  በአሁኑ ጊዜ 43 ቢሊዮን ብር ካፒታልና መጠባበቂያ ፣ 152.9 ቢሊዮን ብር ብድርና ቅድሚያ ክፍያዎች፣ 382.2 ቢሊዮን ተቀማጭ ገንዘብ፣ 14.6 ቢሊዮን ብር ትርፍ፣ 16.6 ሚሊዮን ደንበኞች፣ 1589 ኤቲኤም ማሽኖች፣ 1.36 ሚሊዮን የሞባልል ባንኪንግና 6985 የክፍያ መፈፀሚያ ማሽን አሉት፡፡የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  የ75 ዓመት የአልማዝ ኢዮቤል ክብረ በዓሉን ያከብራል፡፡›4  ጉድና ጅራት ከሆላ ነው እንዲሉ የባንኮች ብድር አሰጣጥ ፍትሃዊነትና እኩልነት ለክልሎች ፣ ለተለያዮ ኢኮኖሚ ዘርፎች፣ለመንግሥታዊና የግል ዘርፍ፣ ለፓርቲ የንግድ ድርጅቶች የ27 አመታት የጨለማ ዘመን ታሪክ ያወጣዋል ለዚህ ሆድ አደር  የወያኔ ተገዥ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ፣ ምክትል ተገዥ አቶ ዮሐንስ አያሌው፣ አቶ በቃሉ ዘለቀ እና የኢትዩጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ፣ በኢትዮጵያ የባንክ ፋይናንሻል ዘርፍ ታሪክ የማይረሳው የሃገር ክህደት ፈፅመዋል፡፡ የሃገር ክህደት አንድ ቀን ያስጠይቃል! ልጆቻችሁ ይጠይቆችኃል! በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በወያኔ ኢፈርት ኢንኩቤተር የተፈለፈሉ ቢሊየነሮች!!! ዳሎል ባንክ፣ Dalol Bank SC የኢትዮጵያን የባንክ ኢንዱስትሪ የተቀላቀለውን፣ በኢትዩጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ (አባባ ታምራትዋን!)፤ በወያኔ ታዘው፣ ለሌሎች የተከለከለ ለአባባ ታምራት ልጆች የተፈቀደው፣ የወያኔ ኢፈርት ዳሎል ባንክ ኢንኩቤተር የተፈለፈሉ ሚሊየነሮች በቅርብ የተቆቆመው 17ኛ የሆነውን የግል ባንክ  ነው፡፡ እንደ አዲስ ፎርቹን ዘገባ ዳሎል ባንክ፣ በኢትዮጵያን ንግድ ባንክ የተከፈለ ካፒታል ግማሽ ቢሊዮን ብር ያለውና በኢትዮጵያዊያን ዜጎች ብቻ የወያኔ አክሲዮን የባለቤትነት ድርሻ አለው፡፡ የፕሮጀክቱ ማናጀር የሆኑት አቶ ነብየልዑል ደበበ ሲሆኑ፣ አቶ ጥላሁን አባይ አማካሪ፣ ዶክተር መስፍን አርዓያ እና ሙሉየለት ካሣ ማጣፈጫ ጨው ይጠቀሳሉ፡፡ ባንኩ 10 ቅርንጫፎች በአንድ አመት ውስጥ ይከፍታል፡፡ በሌላ በኩል እንደ ኢሣት ዜና ዘገባ ዳሎል ባንክ፣ የኢትዩጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲን 19 በመቶ  ድርሻ ሲኖራት 63 በመቶ የ16 የወያኔ ኢፈርት ባለሃብቶች ድርሻ እንዲሁም 18 በመቶ ትንንሽ አክሲዮኖች ለሚገዙ የተለየያዮ የህብረተሰብ ክፍሎች ለሽያች ቀርቦ ተሸጦል፡፡ ዳሎል ባንክ ቤተክርስቲያኒቱ በልዮ ልዮ ባንኮች ያስቀመጠችው 12 ቢሊዮን ብርን በመጠቀም ለማንቀሳቀስ መዘጋጀቱንም የቤተክርስቲያኒቱ ምንጮች ገልፀዎል፡፡ ዳሎል ባንክ አማኞች በሚሰጡት አስራትና ከህንፃ ኪራይና ከመሳሰሉት የተገኘ 12 ቢሊዮኑ ብር ገቢ በተለያዮ ባንኮች የተቀመጠ ነበር፡፡ ብሔራዊ ባንክ ለሃይማኖት ተቆማት የባንክ ፍቃድ እንደማይሰጥ በመግለፁ ከወያኔ ኢፈርት ባለሃብቶች ጋር ግንኙነት መጀመሩንና ከህወኃት ባለሥልጣኖች ከተሠጠው ድጋፍ ባሻገር የብሄራዊ ባንክ ገዢው አቶ ተክለወልድ አጥናፉ የሌብነቱ ተካፋይ በመሆን ወንድማቸውን አቶ መንግሥቱ አጥናፉ በዋና አደረጅነትና አማካሪነት እየሰሩ መሆናቸውንም መረዳት ተችሎል፡፡ አስራ ስድስቱ የወያኔ ኢፈርት የብር ቅርጫ መደብ የደረሳቸው ባለሃብቶች ውስጥ አቶ አዘዞም አየለ፣ አቶ ኃይለሥላሴ አንባዬ፣ አቶ ብርሃኔ ግደይ፣ አቶ አትክልቲ ይህደጎ፣ አቶ ታደሰ ደስታ፣ አቶ ሙለይ አዲስ፣ አቶ ሃጎስ ሃድጉ ገብረእግዚአብሄር፣ እንዲሁም ሙሉ ታምራት እያንዳንዳቸው በ25 ሽ አክሲን በግል የ25 ሚሊዮን ብር ባለድርሻ መሆናቸውን ለብሄራዊ ባንክ ከቀረበው ሰነድ ላይ መመልከት ተችሎል፡፡ ተካሃፍ ትሬዲንግ፣ ታምሪን ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ፣ ቢ ኤን ቲ ኢንደስትሪ ኤንድ ትሬዲንግ፣ ወርቃ ትሬዲንግ ሃውስ ተባሉ የትርጋይ ባለሃብቶች ኩባንያዎችም  እያንዳንዳቸው በ25 ሽ አክሲን በግል የ25 ሚሊዮን ብር ባለድርሻ መሆናቸውን መረዳት ተጭሎል፡፡ አቶ አዲስ ገብረማርያም፣ ሙሉ ሚዛን ትሬዲንግ፣ አቶ በርሄ ሃጎስ፣ ሉችያ ተስፋዬ ገብረመስቀል ደግሞ ከ5 ሚሊን ብር እስከ 12 ሚሊዮን 500 ሺ ብር አክሲን መጋዛታቸውን መረዳት ተችሎል፡፡ ከዳሎል ባንክ ውስጥ 328 ሚሊን 801 ሺ ብር የወያኔ ኢፈርት ተወላጆችና ኩባንያዎች ድርሻ ሲሆን፣ 19 በመቶው የቤተክህነት ድርሻ በመሆን የተቆቆመ ባንክ መሆኑን ዘግቦል፡፡  በወያኔ ዘመን የኢትዩጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲን የንግድ ድርጅትነትና በዘር ላይ የተዋቀረ ተቆም ሆናለች፡፡ በኢትዮጵያ የ16 የግል ባንኮች ጠቅላላ ካፒታል 28 ቢሊዮን ብር ነው፡፡ በአጠቃላይ ያበደሩት ብድር 135 ቢሊዮን ብርነው፣ ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘባቸው 200 ቢሊዮን ብር እንደሆነ ተገልፆል፡፡ ወያኔ ኢፈርት የብር ረብጣ ለአባሎቹ እንዲነግዱ ይሠጣል፡፡

የኢትዩጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ኃብት መሠረቱ የህዝብ ሃብትና ንብረት ነው ምክንያቱም የሃገሪቱ የኦርቶዶክስ እምነት አማኞች በሚሰጡት አስራትና ከህንፃ ኪራይና ከመሳሰሉት የተገኘ 12 ቢሊዮን ብር የህዝብ ሃብት ነው፡፡ የኢትዩጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በሃገሪቱ በተከሰተ የዘር ግጭት የተነሳ ሁለት ሚሊዮን ህዝብ በሃገር ውስጥ ቀየውን ለቆ በተሰደደበት ምንም እርዳታ ሲያደርጉ አይታይም፣ እናት አባት ያጡ ህፃናትን ሲያሳድጉ አልታየም፣ አረጋዊያንን ሲጦሩ አልታየም፡፡ እነዚህ የንግድ ሃይማኖት አባቶች፣ በባንክና ፋይናንሻል ዘርፍ መስቀላቸውን ሰቅለው፣ በዘር ላይ የተመሠረተ ባንክ መሥርተው  ህዝብ ለመመዝበር  ቆርጠው ተነስተዋል፡፡ ህዝብ መውሰድ የሚገባው እርምጃ አንደኛ  የኦርቶዶክስ እምነት አማኞች  አስራት አለመስጠትና ከህንፃ ኪራይ አለመከራየት እንዲሁም በሚቆቆመው የዳሎል ባንክ አለመጠቀም በኢሣት፣ በኦሮሞ ሚዲያ ኔት ወርክ፣ ሌሎች መገናኛ ብዙሃን አድማውን ለህዝብ ማዳረስ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው እንላለን፡፡

ተክለብርሃን አምባዬ፣ ‹‹የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ለተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን ድርጅት የሰጠው ብድር 4 ቢሊዮን ብር መድረሱን የኢሣት ምንጮች ሚያዝያ 29/2010 ዓ/ም አስታወቀዋል፡፡ ለተክለብርሃን አምባዬ በአንድ ቢሊዮን ብር ብድር አኪር የተባለውን የኮንስትራክሽን ድርጅት የኢንጅነር አወጣህኝ ኪሮስ ንብረት መግዛታቸው ታውቆል፡፡ ለተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን ድርጅት፣ ለአቶ በቃሉ ዘለቀና ለአቶ በረከት ስምዖን ቪላ ቤት ገንብተው ማስረከባቸውን የባንክ ምንጮች መረዳት ተችሎል፡፡… ዛግዌ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህንፃ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አካባቢ  የሠሩት ለተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን ድርጅት ሲሆኑ፣ የኤሌትሪክና የካሜራ መስመሮችን የመዘርጋትና የመግጠሙን ሥራ ወንድማቸው ሲወስዱ የቢሮ እቃዎቹን የማቅረብ ሥራ ሚስታቸው መሰጠቱ ታውቆል፡፡ እንዲሁም ሕዳሴ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህንፃ መገናኛ አካባቢ የተገነባው፣ ለተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን ድርጅት ከጨረታ ውጪ የተገነባ መሆኑ ይታወቃል፡፡… የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  ፕሬዜዳንት አቶ በቃሉ ዘለቀ ብአዴን አባል ፣ የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት አቶ አባይ ፀሃዬ፣ የህወሓት/ኢፈርት አባላቶች ስም ከባንክ ብዙ ብድር እንዲያገኙ በማድረግና የአዲስ አበባ ከተማን ቦታ በቀጥተኛና በተዘዋዋሪ መንገድ የወያኔ የጦር አበጋዞች መንግስት የሲቪልና ጀነራል መኮንኖች ፎቅ እየገነቡ እንዲጠቀሙና ኢኮኖሚውን በመቆጣጠር የፖለቲካ በትረ ሥልጣናቸውን ለሃምሳና መቶ አመታት ማስቀጠል ነው፡፡

ተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን፣ Teklebrehan Ambaye Construction Plc (TACON),  በአቶ ተክለብርሃን አምባዬ ወያኔ ኢህአዴግ ስልጣን ላይ ከወጣ በሆላ  የተመሠረቱት ድርጅት ነው፡፡ በአሁኑ ግዜ ከአምስት ቢሊዩን ብር በላይ በሚያወጡ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ግንባታ እየሰራ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡ ከነዚህ ፕሮጀክቶች ውስጥ በሲኤምሲ አካባቢ የሚገነባው የሚኒስትሮች መኖሪያ ቪላ ቤቶች፣ የ40/60 የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ፣ የአፍሪካ ኢንሹራንስ ባለ 11 ፎቅ ሕንፃ በ143 ሚሊዩን ብር የግንባታ ወጭ፣ ለኢትዩጵያ ንግድ ባንክ ልደታ ቅርንጫፍ ግንባታ፣ በትግራይ ክልል የሚገነባ ብሔራዊ ስታዲየም፣ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የሚገነባ የስፖርት አካዳሚ፣ ለከተማ ልማት፣ ለቤቶችና  ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የሚያከናውናቸው ፕሮጀክቶች ከሚጠቀሱት ሥራዎች መኃል ይገኛሉ፡፡ ከአገር ውጭም በሱማሊያ የመቆዲሾ ዐየር ማረፍያና ማኮብኮቢያ ኤርፖርት፣ እንዲሁም በደቡብ ሱዳን በመንገድ ሥራና በውኃ ቁፋሮ ሥራዎች ተሳትፎል፡፡ በ2002ዓ/ም ጥናት መሠረት የአዲስ አበባ ከተማ መሬት በሪል ስቴት ልማት ስም የተላለፈላቸው የ160 ግለሰቦችና ድርጅቶች አንዱ ተ/ብርሃን አምባዬ ሪል እስቴት የቦታው ስፋት 100,000 ካሬ ሜትር ቦታ ወስዶል፡፡

የያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ፣ በሜይ 17ቀን 2015 እኤአ በኢትዩጵያ ሄራልድ ጋዜጣ ላይ በወጣው መረጃ መሠረት በያዩ ወረዳ፣ በኢሉ አባቦራ ዞን በ54 ሽህ ስኩየር ሜትር መሬት ላይ የተገነባው የያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ ሁለት የዩሪያና አንድ የዳፕ ፋብሪካዎች ስራን ያካትታል፡፡ፋብሪካዎቹ ሲጠናቀቁ 300,000 ሽህ ቶን ማዳበሪያ በአመት ያመርታሉ ተብሎ ቢታቀድም እቅዱ እንደከሸፈ ተገልፆል፡፡ የፋብሪካው ግንባታ በ11 ንኡስ ኮንትራክተሮች ተሰጥቶል፤ ማለትም ለማዳበሪያ ፋብሪካ፣ ለተርማል ፓወርና ለኮል ማይኒግ ፕሮጀክቶች ይገኙበታል፡፡ በአጠቃላይ 2,000 ሽህ ሠራተኞች ስራው ቢያከናውኑም እስካሁን ድረስ 11 ቢሊዩን ብር ወጥቶበት 28.8 በመቶ ብቻ ስራው መሠራቱን የመከላከያ ሚንስቴር፣ የብረታ ብረት ኮርፖሬሽን (የሜቴክ) የኬሚካል ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን ዴሬክተር ጀነራል ተሾመ ለማና ካፒቴን ኢንጂነር ባያብል ይሁኔ ገልፀዋል፡፡ ተክለብርሃን አንባዬ ኮንስትራክሽን የግንባታውን የሲቨል ስራ በመስራት 42 በመቶ ማከናወኑን ገልፀዋል፡፡ ተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን፣ ከሜቴክ ጋር እሰራለሁ ብሎ የተረከበውን  የያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ የኢንቨስትመንት ወጪ 77 ቢሊዮን ብር ለህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት ቀርቦ ተጠያቂ ተክለበርሃንና ሜቴክ ተጠያቂ ሣይሆኑ ቀርተዋል፣ በኢትዮጵያ የህግ የበላይነት የለም፣ አይነኬ  ወያኔ የፈለፈላቸው የንግድ ሸሪኮች ስለሆኑ ማንም አይነካቸው፡፡ ተክለብርሃን በወያኔ ዘመን ቢሊየነር የሆኑት ውስጥ የሚጠቀስ መሠረተ ደሃ የነበረ ሰዎች ውስጥ አንዱ ነበር፡፡ በመከላከያ ሚንስቴር፣ የብረታ ብረት ኮርፖሬሽን  የተገነባው የያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ በ2013/14 መጨረሻ ተጠናቀው ያልቃሉ ተብሎ ቢገመትም ያለአንዳች ጨረታና ያለበቂ ጥናት የተጀመሩት ፕሮጀክቶች ገንዘብ ውሃ በልቶቸዋል፡፡ ፋብሪካዎቹ በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በ2016/17 እኤአ ይደርሳሉ ብለው የብረታ ብረት ኮርፖሬሽን ወቶአደሮቹ ኢንጅነሮች ቃል ገብተዋል፡፡ የያዩ ዩሪያ ማዳበሪያ ኮምፕለክስ ፕሮጀክት በ2004 ዓ/ም ሲጀመር በ24 ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ በማሰብ ነበር፡፡ የፕሮጀክት ውል  የታሰረውም የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን በአዋጅ ተቆቁሞ ስራ ከመጀመሩ በፊት በቀድሞው ፕራይቨታይዜሽንና የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ በኩል ከብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ጋር ሲሆን፤ ኮርፖሬሽኑ 2005 ዓ/ም ተቆቁሞ 2006 ዓ/ም ስራውን በይፋ ሲጀምር የፕሮጀክቱ አፈፃፀም 22 በመቶ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ፕሮጀክቱ አሁን 44 በመቶ ደርሶል እስካሁን 5.7 ቢሊዮን ብር ወይም የአጠቃላይ ወጪ 60 በመቶ ለኮንትራክተሩ ክፍያ መፈፀሙን ጠቅሰዋል፡፡ የፕሮጀክቱ የ2009ዓ/ም አፈፃፀም 4.22 በመቶ ሲሆን፣ በ2010ዓ/ም ሩብ አመት ደግሞ 1 በመቶ በታች ብቻ መሆኑ ፕሮጀክቱን አፈፃፀም ብቃት ስጋት ላይ ጥሎታል፡፡ የፕሮጀክቱ ቀሪ ሥራዎች ውስብስብነት ፕሮጀክቱ በተባለው ጊዜ አይጠናቀቅም፡፡ ለግብአት ግዢ የውጭ ምንዛሪ ችግርና የሜቴክ የዕውቀት ክህሎትና አደረጃጀት አቅም ውስንነት ተደማምሮ የፕሮጀክቱ ህልውና አዋጪነት ከወዲሁ በኪሳራና ሙስና ተውጦል፡፡ ‹‹የኬሚካልና ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን በያዩ ማዳበሪያ ኮምፕሌክስ ፕሮጀክት ግንባታ መጎተት ምክንያት ለከፍተኛ የእዳ ጫና መዳረጉን አስታወቀ፡፡… የኮርፖሬሽኑ የጥናትና ልማት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተባባል ውድነህ፤ ኮርፖሬሽኑ ለፕሮጀክቱ ማስፈፀሚያ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እስካሁን ድረስ በሦስት ጊዜ የብድር ክፍያ 10.6 ቢሊዮን ብር የተበደረ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ በተያዘው አመት እስከ መስከረም ወር መጨረሻ ድረስ 2.3 ቢሊዮን ብር መልሶ ለወለድ ክፍያ ማዋሉን ጠቅስዋል፡፡ኮርፖሬሽኑ በየወሩ 70 ሚሊዮን ብር የባንክ ወለድ ይከፍላል፡፡ ፋብሪካው በተያዘለት የጊዜ ገደብ አላለቀም፡፡››

በላይነህ ክንዴ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  የወሰዱት ብድር 2 ቢሊዮን ብር መድረሱን ምንጮች ለኢሣት ገልጠዋል፡፡ በላይነህ ክንዴ የኢትዮጵያ ሆቴል መግዛታቸው ይታወቃል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  ብዙዎቹን እዳዎች ሆነ ወለዱን መሰብስብ አለመቻሉን የባንክ ምንጮች ገልፀዋል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  ፕሬዜዳንት አቶ በቃሉ ዘለቀ የተበላሸ ብድር  በማለት እዳውን በመሰረዝ የሙስና ሥራው ይታወቃል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  ፕሬዜዳንት አቶ በቃሉ ዘለቀ ወጋገን ባንክ ያስገነባው ህንፃ ውስጥ ቢሮ መከራየቱ ታውቆል፡፡ የጥቅም ግጭት ማስከተሉ ግልጽ ነው፡፡ በተመሳሳይ ወጋገን ባንክ፣ ለገሃር አካባቢ ያስገነባው ህንፃ ውስጥ ሁለት ፎቅ ወለል ሙሉ ብሄራዊ ባንክ መከራየቱ ታውቆል፡፡ ሕወኃት/ ኢፈርት የባንክ ፋይናንሻል ሴክተሩን በመቆጣጠርና ኢኮኖሚውን ጠርንፎ በመያዝ የበላይነቱን አግዝፎል፡፡ ወጋገን ባንክ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  በተወሰደና ባልተመለሰ 1.8 ቢሊዮን ብር ከተገነቡ የህወኃት ኩባንዎች እንዱ ነው፡፡ በፎርብስ መፅሄት ዓመታወ ገቢያቸው ከ50 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከሆኑት ኢትዮጵያውያን መኃል አቶ ቴዎድሮስ አሸናፊ፣አቶ ብዙአየሁ ታደሰ፣ አቶ  ከተማ ከበደ፣ ወ/ሮ አኪኮ ሥዩምና አቶ በላይነህ ክንዴ ይገኙበታል፡፡

አቶ ቴዎድሮስ አሸናፊ፣ ሳውዝ ዌስት ሆልዲንግ የተባለ ግዙፍ የኢንቨስትመንት ቡድን መስራች የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ አሸናፊ ይባላሉ፡፡ ባለሃብቱ በተለያዩ የቢዝነስ ሥራዎች ላይ የተሰማሩ የህወኃት/ ኢፈርት የቢዝነስ ሽርካ ለመሆናቸው ‹‹የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ›› ከዴሬክተር ጀነራል አሰፋ አብርሃ የደርግን መንግሥታዊ ዘርፍ ወደ ህወኃት/ኢህአዲግ የፓርቲዎች መንግስታዊ ዘርፍነት በማዘዋወር ሳውዝ ዌስት ሆልዲንግ የሃገሪቱን ምጣኔ ኃብት  በማዕድን፣በሚኒራል ውኃና በሆቴል ዘርፍ አገልግሎት፣እንዲቆጣጠር አድርገዋል፡፡ ሳውዝ ዌስት ሆልዲንግ ከፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ በርካሽ ዋጋ ከተሸጠላቸው ድርጅቶች ውስጥ፡-ሳውዝ ዌስት ኢነርጂ፣ በነዳጅ ፍለጋ ሥራ ላይ የተሰማራ ኩባንያ ሲሆን፣ በሶማሌ ክልል በኦጋዴንና በጋምቤላ ክልል የነዳጅ ፍለጋ ፕሮጀክቶች በመምራት ላይ ይገኛል፡፡ ለነዳጅና ጋዝ ፍለጋ የተረከቡት ምሥራቃዊው የአገሪቱ ክፍል በሃገሪቱ ከፍተኛ የነዳጅና ጋዝ ክምችት አለው ተብሎ ይታመናል፡፡ የጋምቤላ ኢትዮጵያ ሆቴል፣ ሳውዝ ዌስት ፒኤልሲ ባለቤት አቶ ቴዋድሮስ አሸናፊ ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር በ3,750,000  ሚሊዮን ብር በ21/7/2005ዓ/ም ገዝተውታል፡፡ በአምቦ ውኃ ማዕድን በ19,782,807 ሚሊዩን ዶላር ተሸጠ፣ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር አቶ በየነ ገብረ መስቀልና ሳውዝ ዌስት ዴቨሎፕመንት አቶ ቴዋድሮስ አሸናፊ ተፈራርመዋል፡፡ መንግሥት በአምቦ ማዕድን ውኃ አክሲዮን ማሕበር ያለውን የ33 በመቶ የአክሲዩን ድርሻ ለአምቦ ኢንተርናሽናል ሆልዲንግ ሊሚትድ በሚል ስያሜ ለሚታወቅ ሳብ ሚለር ከተባለው የደቡብ አፍሪካ ኩባንያ ጋር ተጣምረው ገዝተዋል፡፡ ሳውዝ ዌስት ሆልዲንግ ሁለት የኮካኮላ ፋብሪካዎች ከኢስት አፍሪካን ቦትሊንግ፣ የተሸጠበት ዋጋ 64,030,000 ሚሊዩን ብር ጋር ተጣምረው በ5/15/95 ዓ/ም ገዝተዋል፡፡

ወይዘሮ አኢኮ ሥዩምየኦርኪድ ቢዝነስ ግሩፕ ወይዘሮ አኢኮ ሥዩም ባለቤት/ የሙስና ኮማሪት! አዜቡ መስፍን እህት/ በደቡብ ሱዳን ውስጥ በጄነራል ፃድቃን ገብረትንሣይ በተመቻቸላት የሽርክና ንግድ በደቡብ ሱዳን በኮንስትራክሽን በትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ እንዲሁም የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች በማቅረብ የደለበ የዶላር ኃብት ከምድረ-ደቡብ ሱዳን እንደዘረፉ ውስጥ ሃገር ወዳድ የትግራይ ልጆች አሳውቀዋል፡፡በተጨማሪም ኦርኪድ በሃገር ውስጥ በከባድ ጭነት ማመላለሻ ኩባንያው  የመሶቦ ሲሚንቶን ምርት ለህዳሴው ግድብ ሥራ በማቅረብና በማጎጎዝ ዘርፍ የትግራይን ህዝብ የመዘበረ የንግድ ተቆም ነው፡፡ ኦርኪድ በመንገድ ኮንስትራክሽን ኩባንያው በብዙ ቢሊዩን ብር ፕሮጀክቶችን በመገንባትና በመሠረት ቁፋሮ ግንባታ ሥራ ኩባንያም አለው፡፡ በፎርብስ በተባለው መፅሄት ዓመታዊ ገቢያቸው ከ50 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንዳላቸው ይፋ ሆኖል፡፡

የህወሃት/ኢህአዴግ ዘመን የሆቴሎች ኢንቨስትመንት መር ኢኮኖሚ

የወያኔ መንግሥት በሆቴል ኢንቨስትመንት ባለሃብቱ 30 በመቶ ገንዘብ ካቀረበ ባንክ 70 በመቶ ብድር ያቀርብለታል እንዲሁም ባለኃብቱ  በፕራይቬታይዤሽን የገዛቸው የመንግሥት እርሻዎች፣ ፋብሪካዎች፣ የወርቅ ማዕድን፣ ሆቴሎች 35 በመቶ የእጅ በዕጅ ክፍያ ሲሆን 65 በመቶው ደግሞ በአምስት አመታት ውስጥ የሚከፈል ነው፡፡ በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብድር በማቅረብ የመባሽር ሥራ ይከውናል፡፡ እነዚህ የህዝብ ኃብቶች ለህዝብ በአክሲዮን ተሸጠው፣ የህዝብ ንብረት ማድረግ ይቻል ነበር፡፡ በእነዚህ ድርጅቶች ውስጥ ይሰሩ የነበሩ ብዙ ሽህ ሠራተኞች ተባረዋል፣ ድርጅቶቹ የያዙት ሥፋፊ ቦታዎች በመሸጥ ባለኃብቶቹ ሚሊየነሮች ሆነዋል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣‹‹በፋይናንስ አቅርቦት ችግር የ15 ባለ ኮከብ ሆቴሎች ግንባታ እየተጎተተ ነው››   በአዲስ አበባ ከተማ 15 ባለ ኮከብ ሆቴል ፕሮጀክቶች ግንባታ እየተካሄደ ቢሆንም፣ ብድርም ሆነ የውጪ ምንዛሪ ማግኘት ባለመቻላቸው ለከፍተኛ ችግር እየተዳረጉ መሆኑ ታወቀ፡፡ {የሰንሻይን ግሩፕ ባለቤት አቶ ሳሙኤል ታፈሰ፣ በአዲስ አበባ ቦሌ መድኃኔዓለም  አካባቢ ማርዬት የሚያስተዳድረው፣ በሐዋሳ ከተማ ደግሞ ሒልተን የሚያስተዳድረው፣ ሆቴል በመገንባት ላይ ናቸው፡፡} {የዩቤክ ኤሌክትሪካል ኢንተርፕራይዝ ባለቤት አቶ ብርሃኔ ግደይ፣ እስካሁን 700 ሚሊዮን ብር የወጣበት ሲሆን  ኢምፔሪያል አካባቢ ከስፖርት አካዳሚ ጎን እየተገነባ ያለውና የሰዊዘርላንዱ ግዙፍ ኩባንያ ሞቨንፒክ ሆቴልና ሪዞርት ሆቴሉን ለማስተዳደር ግንባታውን ለማጠናቀቅ 16 ሚሊዮን ዶላር ብድር ከባንክ ማግኘት አልቻለም፣ የሆቴል ግንባታው በባንክ ብድር የሚካሄድ በመሆኑ ብድሩ እየተከማቸ መሆኑን በመግለፅ፣ መንግሥት የውጭ ምንዛሪ እንዲያቀርብ  አቶ ብርሃኔ ጠይቀዋል፡፡} {የኔክስስ ሆቴል  ባለቤት አቶ ዳዊት ገብረ ፃዲቅ፣ የሆቴል የማስፋፍያ ፕሮጀክት አካሂዶ የውጪ ምንዛሪ መፈለግ ከጀመረ ሁለት ዓመታት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሆቴል ግንባታ ብድር መስጠት ማቆሙንና ለግንባታ ማጠቃለያ የሚሆን የውጭ ምንዛሪ እያቀረበ እንዳልሆነ ፕሮጀክቶቹን እያካሄዱ የሚገኙ የሆቴል ኢንቨስትሮች ይናገራሉ፡፡5}

በኢትዩጵያ የሆቴሎች ኢንቨስትመንት፣  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብድር አቅርቦት፣ በአዲስአበባና በየክልሎቹ ከተሞች የተገነቡትን የብሄር ብሄረስብ የገንዘብ አቅርቦት መረጃው ይገለፅ ቢባል ህወሃት ለምን ተብሎ ብሎ እንደሚሞገት ምንም ጥርጥር የለንም፡፡ አንድ ሃቅ ግን አለ የህወሃት/ኢህአዴግ የፖለቲካ ድርጅቶች በግለሰቦች ስም  በኢትዩጵያ የሆቴሎች ኢንቨስትመንት ሃብትን እንደሚያስተዳድሩ ተጨባጭ መረጃዎች አሉን፡፡ በየከተሞቹ በተለይ በአዲስአበባ፣ አዳማ፣ ሃዋሳ፣ ባህር ዳር፣ መቀሌ፣ በመላ ሃገሪቱ ባሉ ከተሞች ውስጥ ትላንት ምንም ገንዘብ የሌላቸው የኔ ብጤ፣ መሰረተ ደሃ ሰዎች ወደላይ በመንኮራኩር መጥቀው ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ሲገነቡ ማየት የተለመደ ክስተትና በህወሃት/ኢህአዴግ አየር በአየር የኃብት ምንጩ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢንኩቤተር የተፈለፈሉ ልጅእግር ሃብታሞች ከባንክ ብድር በመውስድ ከህዝብ የተዘረፈ ገንዘብ መሆኑን የባንክ ባለሙያ መሆን አይጠይቅም፡፡ በህወሃት/ኢህአዴግ ዘመን የሆቴሎች ኢንቨስትመንት መር ኢኮኖሚ እስኪመስል የሆቴል ግንባታ እንደተከናወነ ባለፈው ሃያ ሰባት ዓመታት ውስጥ ብዙ ማስረጃዎች ማቅረብ ይቻላል፡፡ ከነዚህም ውስጥ በተለይ ባለ አምስትና አራት ኮኮብ የሆቴል ኢንቨስተሮች፣ 30 በመቶ ባለሃብቱና የባንክ ዘርፍ 70 በመቶ ብድር በማቅረብ በናሙናነት ያህል አንባቢዎች ለማስላት ይችሉ ዘንድ የቀረበ መረጃ ነው፡፡ ወያኔ ለአባላቶቹ 30 በመቶውን መነሻ ጥሬ ገንዘብ (ካፒታል)እና ቢዝነስ ጥናት  እየሠጠ አባሎቹ ከባንክ 70 በመቶ እየተሠጣቸው መላ አገሪቱን ወረሮት፣ የማፍያው የደደቢት ሥውር ኢኮኖሚ ሚሥጢር ይሄ ነው፡፡  የወያኔ ኃብት የአባሎቹ እንጅ የትግራይ ህዝብ አይደለም፡፡ የትግራይ ህዝብ የተዳፈነ እሳተ ጎሞራ ነው፣ ጎሞራው ርዕደ መሬት የተቀላቀለበት፣ ንጥነጣዊ ስጥመት ማስከተሉ አይቀሬ ነው፡፡

{1} ሽህ መሃመድ ሁሴን አላአሙዲሸራተን አዲስ፣ ባለ አምስት ኮኮብ ሆቴል ባለቤት ሽህ መሃመድ ሁሴን አላአሙዲ ኢንቨስትመንት ወጭ 200,000,000 (ሁለት መቶ ሚሊዩን ዩኤስ ዶለር) በ1998እኤአ ሥራ ጀምር፡፡ መቶ አርባ ሚሊዮን ብር ከባንክ ብድር የተገኘ፡፡ ሜድሮክ ከ 5 አስከ 10 ቢሊዮን ብር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብድር ያለበት ድርጅት ነው፡፡ የሜድሮክ ሆቴሎች፣ (MIDROC) Hotel)፣ (ሜድሮክ ሆቴሎች ውስጥ (1) ሸራተን አዲስ  በሽህ መሃመድ ሁሴን አላአሙዲ የሳውዲ አረቢያ ዜጋ በሁለት መቶ ሚሊዩን ዩኤስ  ዶላር በ1998 እኤአ በአዲስአበባ  ከተማ የተገነባ ባለ አምስት ኮኮብ ሆቴል ሲሆን 293 የመኝታ ክፍሎች አሉት፡፡ (2)ሆራ ራስ ሆቴል በሜድሮክ ኢትዩጵያ የሆቴሎች ዘርፍ በመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ በስምንት ሚሊዩን ሰባት መቶ ሽህ ብር የተሸጠ ሆቴል ሲሆን 55 የመኝታ ክፍሎች ያሉት በደብረ ዘይት ከተማ ሆራ ሃይቅ የሚገኝ ጥንታዊ ሆቴል ነው፡፡ ሆቴሉ በ9/4/96 እኤአ ከተሸጠ ጀምሮ ላለፉት 19 አመታት ተዘግቶ የግለሰቡና የግብረአበሮቹ መዝናኛ ለመሆን በቅቶል፡፡ ሆራ ሃይቅ የኦሮሞ ህዝብ የእሬቻ በዓል የሚያከብርበት ሥፍራ ሲሆን ሆቴሉ እስከአሁን አገልግሎት ባለመስጠቱ የኦሮሚያ ክልል ሙሰኛ ሸማምንት ምንም አላሉ፡፡ (3) ብሉ ናይል ሆቴል፣ባህርዳር በሜድሮክ ኢትዩጵያ የሆቴሎች ዘርፍ የተገዛ ሆቴል ይገኛል፡፡ 4-አብዬት ራንዴቩ፣ አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ከእስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፍት ለፊት የሚገኘው ራንዴቩ ካፍቴሪያ ወይም አብዬት ራንዴቩ በመባል የሚታወቀው በወ/ሮ እንይሽ አስረስ የሼክ መሃመድ አላ-ሙዲ ሚስታቸው እንይሽ አስረስ በ2,800,000 ሚሊዬን ብር በመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ተሸጦላቸዋል፡፡ሆቴሉ በ6/25/97 እኤአ ከተሸጠ ጀምሮ ላለፉት ሁለት አስርት ተዘግቶ አገልግሎት ባለመስጠቱ የአዲስአበባ ሙሰኛ ከንቲቦችና አስተዳደር ሌላው ግለሰብ ባለሃብቶች ለመስራት የገዙትን መሬት አልሰራችሁም እያሉ መሬቱን በመንጠቅ ሲገኙ ከህግ በላይ የሆኑት አላ-ሙዲና ሚስታቸው ምንም አልተባሉ፡፡ በፒያሳና በሌሎች ቦታዎች አጥረው የሚገኙት ቦታዎች ለንግዱ ህብረተስብ በእኩልነት ፍትህና ርትህ የሚሰጥ መንግስት ባለመኖሩ መጥፎ አርአያ ያላቸው ቦዘኔ ኢንቨስተር ለመባል በቅተዋል፡፡

{2}  አቶ ሳሙኤል ታፈሰ፣ ማሪዬት ሪዞርት ሆቴል፣ ባለ አምስት ኮኮብ ሆቴል (ሁለቱ አዲስ አበባ አንዱ ሃዋሳ) ባለቤት አቶ ሳሙኤል ታፈሰ፣ ኢንቨስትመንት ወጭ እያንዳንዳቸው 500 ,000,000 (አምስት መቶ ሚሊዩን ብር ጠቅላላ 1.5 ቢሊዮን ብር) በ20–እእአ ሥራ ጀምር፡፡  አንድ ቢሊዮን ሃምሳ ሚሊዮን ከባንክ የተገኘ ብድር ነው፡፡ አቶ ሳሙኤል ታፈሰ፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ ሰንሻይን ህንጻና ቢሮ የገነቡ ሲሆን፣ በተጨማሪም በቦሌ መድኃኒያለም ፊት ለፊት 5 ዘመናዊ ቪላ ቤቶች ገንብተዋል፡፡ ሰን ሻይን ኮንስትራክሽን Sunshine Construction በአቶ ሣሙኤል ታፈሰና በባለቤታቸው ንብረት የሆነው ስን ሻይን ኮንስትራክሽን በ1984 ተመሠረተ ነበር፡፡ ድርጅቱ ለ1000 ሠራተኞች ቆሚና ለ6000 ግዜዊ የስራ እድል ፈጥሮል፡፡ ስን ሻይን በመንገድ ሥራ፣ በንግድና የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ፣ ግድብ ሥራ ላይ ተሠማርቶ ይገኛል፡፡ ስን ሻይን በ2009 እኤአ የ 207 ሚሊዩን ዶለር የኮንትራት ሥራ  በመስራት ላይ ይገኝ ነበር፡፡ አቶ ሳሙኤል ታፈሰ፣ በምድረ አሜሪካ ትልቅ ቪላ ቤቶች ገንብተዋል፡፡ በ2002 ጥናት መሠረት የአዲስ አበባ ከተማ መሬት በሪል ስቴት ልማት ስም የተላለፈላቸው የ160 ግለሰቦችና ድርጅቶች አንዱ ሰንሻይን ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማ የቦታው ስፋት 262,868 ካሬ ሜትር ቦታ ወስዶል፡፡

{3} አቶ የማነ ገብረሥላሴ፣ ካፒታል ሆቴል፣ ባለ አምስት ኮኮብ ሆቴል ባለቤት አቶ የማነ ገብረሥላሴ፣ ኢንቨስትመንት ወጭ 720 ,000,000 (ሰባት መቶ ሃያ  ሚሊዩን ብር) በ2013እእአ ሥራ ጀምር፡፡ካፒታል ሆቴል የተገነባው ከውሃ ልማት ሚኒስትር የመንግስት መስሪያ ቤት ስፊ ቦታ ተነጥቆ እንዲሁም በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች የነበሩ ሸዋ ዳቦ ቤት ቦታን (ባለቤቱ በብስጭት ቦታቸውን በተነጠቁ በሶስት ወራቸው ሞቱ)እንዲሁም  ሸዋ ጌጥ ሆቴል የነበረውን የአቶ ገላጋይ ሚኒስትር የነበሩ ካርታ ያለው ቤታቸውን በግፍ በመንጠቅ የተሠራ ሆቴል ሲሆን ገና ሲጀመር ፍህታዊ ባልሆነ መንገድ የተገነባ ሆቴል መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ፡፡ ከመንግስት መስሪያ ቤቶች ንብረት የሆኑ መሬትን/ቦታን በመንጠቅ ለሚፈልጉት ሰዎች መስጠት የተጀመረው በአቶ አርከበ አቁባይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ በነበሩበት ግዜ ነበር፡፡ ካፒታል ሆቴል ባለቤቶች ልጅ እግሩ ባለኃብት የማነ ገብረሥላሴና የስዩም መስፍን ሽርካ መሆኑን የአዲስአበባ ሰዎች ያወጋሉ፡፡

{4} አቶ ብርሃነ ግደይ፣ ዮቤክ ቢዝነስ ኩባንያ፣ ባለ አምስት ኮኮብ ሆቴል (ሁለቱ አዲስ አበባ ) ባለቤት አቶ ብርሃነ ግደይ፣ ኢንቨስትመንት ወጭ እያንዳንዳቸው 700 ,000,000 (ሰባት መቶ ሚሊዩን ብር ጠቅላላ 1.4 ቢሊዮን ብር)፡፡አቶ ብርሃነ ግደይ፣ ዩቤክ ቢዝነስ ኩባንያ በመባል የሚታወቀው ኩባንያ የኤሌትሪክ ዕቃዎችን በማቅረብ፣ የእቃ ማሸጊያዎችንና የኤሌትሪክ ኮንዲውቶችን በማምረት ስራ ላይ ተሰማርተዋል፡፡ አቶ ብርሃነ ግደይ በተጨማሪ ኢንፔሪያል ሆቴል አካባቢ ሁለት ባለ አምስት ኮኮብ ሆቴሎች ገንብተዋል፡፡ የሆቴሎቹ ጠቅላላ ስፋት 2400 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ባለ አሥራ አምስትና ባለ አስር ፎቅ ሕንፃዎች በሁለት ሽህ ካሬ ሜትር ሥፍራ ላይ ያረፉ ሲሆኑ 275 አልጋዎች አሎቸው፡፡ ለሁለቱ ሕንፃዎች እስካሁን 475 እስከ 600 ሚሊዩን ብር አውጥተዋል፡፡ አቶ ብርሃነ ግደይ ሠንጋ ተራ ሠፈር፣ ከሆቴሎቹ አጠገብ የሚገኝ ከ500 እስከ 600 ካሬ ሜትር ቦታ ተሠጥቶቸው እስከ 10 ፎቅ ከፍታ ያለው የፓርኪንግ ሕንፃ ለመገንባት ቦታ መንግስትን ጠይቀዋል፡፡

{5} ራዲሰን ብሉ፣ባለ አምስት ኮኮብ ሆቴል ባለቤት ሪዚዶር ሆቴል ግሩፕ፣ኢንቨስትመንት ወጭ አምስት መቶ ሚሊዩን ብር በ2012እእአ ሥራ ጀምር

{6} አቶ ረዘነ አያሌው፣ ፀሜክስ ሆቴል፣ ባለ-ኮኮብ ሆቴል ባለቤት አቶ ረዘነ አያሌው፣ ኢንቨስትመንት ወጭ ሠላሳ ሰባት ሚሊዩን ዮኤስ ዶላር

{7} አቶ አስቻለው ከበደ፣ ጎልደን ቱሊፕ ሆቴል፣( ቁጥር አንድና ሁለት ሆቴል)፣ ባለ አራት ኮኮብ ሆቴል ባለቤት አቶ አስቻለው ከበደ፣ ኢንቨስትመንት ወጭ 550,000,000 (አምስት መቶ ሃምሳ ሚሊዩን ብር)

{8} ወ/ሮ ትልቅ ሰው፣ ባህርዳር ሆቴል፣ ባለ – ኮኮብ ሆቴል (ሌሎች 3 ሆቴሎች በሦስት ክልሎች አሎቸው) ባለቤት ወ/ሮ ትልቅ ሰው፣ ኢንቨስትመንት ወጭ 400,000,000 (አራት መቶ ሚሊዩን ብር ከባንክ ብድር የተወሰደ) በ2015እኤአ ሥራ ጀምር

{9} ወ/ሮ አዲስ ገብረማርያም፣ አዲሲኒያ ሆቴል፣ ባለ – ኮኮብ ሆቴል ባለቤት ወ/ሮ አዲስ ገብረማርያም፣ ኢንቨስትመንት ወጭ መቶ ሚሊዩን ብር

{10} አቶ በላይነህ ክንዴ ኢትዮጵያ ሆቴል፣ ባለ – ኮኮብ ሆቴል አቶ በላይነህ ክንዴ፣ ኢንቨስትመንት ወጭ 800,000,000 (ስምንት መቶ ሚሊዩን ብር የባንክ ብድር የተወሰደ) በ20–እኤአ ሥራ ጀምር ከመንግሥት የኢትዮጵያ ሆቴል መግዛታቸው ይታወቃል፡፡

{11} አቶ ከተማ ከበደ፣ ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል፣ ባለ አራት ኮኮብ ሆቴል አቶ ከተማ ከበደ፣ ኢንቨስትመንት ወጭ ከአምስት መቶ እስከ ስምንት መቶ ሚሊዩን ብር የባንክ ብድር የተወሰደና  ከመንግሥት የአቃቂ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ መግዛታቸው ይታወቃል፡፡

{12} አቶ ዳዊት ገብረ ፃዲቅ፣ ኔክሰስ ሆቴል፣አራት ኮኮብ ሆቴል፣የኢንቨስትመንት ወጭ ከአምስት እስከ ስምንት መቶ ሚሊዩን ብር የባንክ ብድር

{13} አቶ ገምሹ በየነ፣ ኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል፣ ባለ አምስት ኮኮብ ሆቴል አቶ ገምሹ በየነ ፣ ኢንቨስትመንት ወጭ ከአምስት መቶ እስከ ስምንት መቶ ሚሊዩን ብር የባንክ ብድር የተወሰደ፣ የኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል ባለቤት {አሜሪካ ኮብልሎ የገባ}፣

{14} አቶ ቴዋድሮስ አሸናፊ፣ የጋምቤላ ኢትዮጵያ ሆቴል፣ ሳውዝ ዌስት ፒኤልሲ ባለቤት አቶ ቴዋድሮስ አሸናፊ ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር በ3,750,000  ሚሊዮን ብር በ21/7/2005ዓ/ም ገዝተውታል፡፡

{15} አቶ ፍፁም ዘአቡ አስግዶም፣ እቴጌ ጣይቱ ሆቴል፣ አቶ ፍፁም ዘአቡ አስግዶም፣ በህወሃት/ኢህአዴግ ዘመን፣ በመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ በደርግ አገዛዝ ስርዓት የተወረሱ መንግስታዊ ድርጅቶችን ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዘወወር በ1994 ዓ/ም በአዋጅ የተቆቆመ ድርጅት ዴሬክተር ጀነራል አሰፋ አብርሃ (ስዬ አብርሃ ወንድም) 05/19/99እኤአ ለእህታቸው ባል አቶ ፍፁም ዘአቡ አስግዶም፣እቴጌ ጣይቱ ሆቴል በአምስት ሚሊዩን ሁለት መቶ ሰባ ሦስት ሽህ ብር (5,273,000 ) ሸጡላቸው፡፡ አቶ ፍፁም ዘአቡ አስግዶም፣የጉለሌ የሳሙና ፋብሪካ በ12/23/1996 አ/ም በ22,370,000 (በሃያ ሁለት ሚሊዩን ሦስት መቶ ሰባ ሽህ ብር) ገዝተዋል፡፡እንዲሁም ሐረር ፕሪንቲንግ ኢንተርፕራይዝ ማተሚያ ቤትን በ1,164,000 (አንድ ሚሊዩን አንድ መቶ ስድሳ አራት ሽህ ብር)  በ10/18/1995 ዓ/ም ገዝተዋል፡፡

{16} አክሱም ሆቴል፣ በአዲስ አበባና በመቐለ ተገነቡ ሆቴል አላቸው ባለቤቱ ፣የቀድሞው የሎምባርዲያ ሬስቶራንት ባለቤት የነበሩት በፍርድ ቤት ንብረታቸው ቢመለስም ቅሉ ንብረታቸውን የወሰዱት የአክሱም ሆቴል ባለቤት ሬስቶራንቱን አልመለሱም፡፡ የአክሱም ሆቴል ባለቤት በአዲስአበባና በመቐሌ ሆቴሎች አሎቸው፡፡ የሎምባርዲያ ሬስቶራንት ለባለቤቱ አልተመለሰም፣ህግ የለም በህግ ፊት ሁሉም ሰው እኩል አይታይም፣ ፍትህ የለም!

{17} አቶ ዳዊት ገብረእግዚአብሄር፣ በ27 ዓመታት ውስጥ ቢሊየነሩ ቱጃር የሆኑትና የራሳቸው አይሮፕላንና ጎሽ የሚባል የግል አውሮፕላን አገልግሎት በመስጠት ዳጎስ ያለ ገቢ ያገኛሉ፡፡ የወያኔ ፖሊት ቢሮ አባል ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር (ሞንጆሪኖ) ወንድም ሲሆኑ፣ራያ ቢራ ፋብሪካ Raya Brewery ፋብሪካው ከአዲስአበባ ከተማ 667 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው በማይጨው ከተማ በ150,000 ስኮየር ሜትር ቦታ ላይ ያለምንም ሊዝ ክፍያ ተገነባ፡፡ የክልሉ መንግስት ለተፈናቀለው ገበሬ 15 ሚሊዩን ብር ካሳ ከፍሎል፡፡ የአክሲዩን ኩባንያው በ2,241 በላይ ባአክሲዩኖችን ድርሻ የተመሠረተ ነው፡፡ የግንባታው ወጭ 1.5 ቢሊዩን ብር ነው፡፡ራያ ቢራ ፋብሪካ ከኢትዩጵያ ንግድ ባንክ 974 ሚሊዩን ብር ብድር እንዳገኘ ይታወቃል፡፡ ራያ ቢራ አክሲዩን ማኅበር፣የፋብሪካው የማምረት አቅሙ 710 ሽህ ሄክቶ ሊትር ነው፡፡ለፋብሪካው ማሽን መግዣና ተከላ 678 ሚሊዩን ብር (36 ሚሊዩን ዶላር)ለችኮዝላቪያና ጀርመን ካንፓኒዎች ይከፈላል፡፡የቦርድ ሊቀመንበር የቀድሞው የህወሃት የጋንታዎች መሪ፣በኃላም የሃገሪቱ ኢታማዥር ሹም ሌተናል ጀኔራል ፃድቃን ገብረትንሣይ ናቸው፡፡ ከአክሲዩኑ ድርሻ 248 ሚሊዩን ብር(13 ሚሊዩን ዶላር) ቢጂአይ (42 በመቶ) የባለቤትነት  ድርሻ አለው፡፡ እንዲሁም አቶ ዳዊት ገብረእግዚአብሄር፣ በዱባይ  በተለያዩ ኢንቨስትመንት መስኮች የተሰማሩ ልጅ እግር የዘመኑ ባለሃብት (25 በመቶ) የባለቤትነት  ድርሻ አላቸው፡፡ በሌላ ዜና ደግሞ ዳዊት ገብረእግዚአብሄር 20 ሚሊዩን፣እየሱስወርቅ ዛፉ 10 ሚሊዩን ብር፣ ረዘነ አያሌው 5 ሚሊዩን ብር ኢንቨስት አድርገዋል ይላል፡፡  ንፋስ አመጣሽ ቢሊየነሮችን የፈለፈሉ አንድ ዓይና የባንክ ሙያተኞች!!! ለሌተናል ጄኔራል ጻድቃን ገብረ ትንሳዔ የራያ ቢራ ፋብሪካ ሲያቆቁሙ ከንግድ ባንክ 974 ሚሊዩን ብር ብድር መውሰዳቸውና ወዲያው ራያ ቢራን ለቢጂአይ ዓየር በዓየር መሸጣቸው ይታወሳል፡፡ አሁን ደሞ ለቢጂአይ ኢትዮጵያ አዋሽ ባንክ 750 ሚሊዮን ብር ብድር እንዲሰጠው በማመቻቸት ቢጂአይ በራያ ቢራ ውስጥ ካለው የ42 በመቶ ድርሻው በተጨማሪ፣ ቀሪውን አክሲዬኖች ለመግዛት ከ2.5 ቢሊዮን ብር ለባለአክሲዮኖቹ ለመክፈል የዓየር በዓየር ንግድ ጻድቃን የባንኩን ብድር አመቻችተዋል፡፡ አቶ ዳዊት ገብረእግዚአብሄርም ከራያ ቢራ ሽያጭ  የአንበሳውን ድርሻ ጥቅም ተቀራምተዋል፡፡ በተመሳሳይ ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ፣ በህወሃት/ኢህአዴግ ዘመን ሐበሻ ቢራ አክሲዩን ማኅበር የግንባታው ወጭ 1.4 ቢሊዩን ብር ነው፡፡ ከኢትዩጵያ ንግድ ባንክ 377 ሚሊዮን ብር ተበድረው ነበር፡፡ የሆላንዱ ባቫሪያ ኩባንያ ከፍተኛ የአክሲዩን ባለድርሻ ነው(49 በመቶ)17 ሚሊዩን ዶላር አክሲዩን ገዝቶል፡፡የማምረት አቅሙ ከ300 እስከ 500 ሽህ ሄክቶ ሊትር ነው፡፡

{18} የኢትዩጵያ ሪቬራ ኢንተርናሽናል ሆቴል (Ethiopian Riviera International Hotel)የህወሃት መከላከያ ሚኒስትር ስር የሚገኘው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ/ሜቴክ)፣ የኢትዩጵያ ሪቬራ ኢንተርናሽናል ሆቴል (Ethiopian Riviera International Hotel) ባለ ሦስት ኮኮብ ደረጃ ያለውን የአቶ አለም ፍፁም ንብረት የነበረውን እንዲሁም ፒቪሲና ፕላስቲክ ማኑፋክቸሪንግ ፋብሪካ በ140 ሚሊዩን ብር ለመግዛት ስምምነት አድርጎል፡፡ በተመሳሳይ ኢምፔሪያል ሆቴል (Imperial Hotel) በተመሳሳይ ሜቴክ በአዲስ አበባ የሚገኘውን ኢምፔሪያል ሆቴል በ60 ሚሊዩን ብር ገዝቶ ሆቴሉን የእንግዳ መቀበያ ለማድረግ አቅዶል፡፡ የህወሓት መንግስት ለሆቴል ኢንዱስትሪ ዘርፍ እድገት መንግሥት የሚሰጣቸው ማበረታቻ ዘርፈ ብዙ ናቸው፡፡ ሆቴሉን ለመገንባት የሚያስፈልጉ የብረት ጥሬ እቃዎች፣ የሆቴል ውስጥ የባህር ማዶ አልጋ፣ ቴሌቪዝኖች፣ ሪፍሬጀተሮች፣ ወዘተ በብዛት በማስገባት ማለትም ለአንድ ሆቴል የተጠየቀውን ለአምስት ሆቴል የሚሆን ዕቃዎች ከውጪ በማሰገባትና በመሸጥ አምስት መቶ እጥፍ ትርፍ በማግኘት የሙስና ወንጀል በመፈፀም ዋናዎቹ ተዋናዮች ናቸው፡፡

የወያኔ ኢህአዴግ የሙስና ቴያትር፣ የወያኔ ኢፍትሃዊ ሥርዓት በኢትዮጵያ፣ ወያኔ የሙስና ንጉሥ ነው! ሁለተኛው የወያኔ የሙስና ቴያትር የተቀነባበረው፣ በፋይናንስ ደህንነት መሥሪያ ቤት፣ በገቢዎችና ጉምሩክ፣ በዋና ኦዲተር፣ እንዲሁም ከጠቅላይ አቃቢ ሕግ መሥሪያ ቤት የተውጣጣ የቴያትር ኮሚቴ ከ120 በላይ ነጋዶዎችን በተጠርጣሪነት በጥቁር መዝገብ አስፍሮ ነበር፡፡ ለወራት ያህልም የሂሳብ ባለሞያዎቻቸውን በመጥራት፣ስልካቸውን በመጥለፍ፣ ድንገተኛ ፍተሸ በማድረግ መረጃ ሲያሰባስቡ እንደነበረ ከነዚህ መሃልም በመጀመሪው ዙር የእስር ማዘዣ ይወጣባቸዋል ተብለው የሚገመቱት 18 የሚሆኑ ከፍተኛ ነጋዴዎች ነበሩ፡፡ የብዙዎቹ ክስ ከታክስ ሰወራ ጋር የሚያያዝ ወንጀል ነበር፡፡ በከፍተኛ ሙስና ተጠርጥረው የመንግሥት ኃላፊዎች ቁጥር ወደ 40 ማሻቀቡን ገልፀው በቴሌቨዝን፣ ሬዲዬ፣ ኤፍኤም ሬዲዬ የሙስና ድራማው ተለፍፎ ነበር፡፡ በተጠረጠሩበት ሙስና ወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸው በቁጥጥር ሥር ያልዋሉ ባለሃብቶች ውስጥ፣ ገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን ፣ የኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል ባለቤት {አሜሪካ ኮብልሎ የገባ}፣ የማነ ግርማይ ጠቅላላ ሥራ ጠቆራጭ፣ አሰር ኮንስትራክሽን ኩባንያ ባለቤት {አሜሪካ ኮብልሎ የገባ} እና አቶ ስህን ጎበና፣መሠረት ዓለሙ፣ አብዶ መሐመድ፣ እውነቱ ታዬና ስንዱ ታደሰ ዲኤምሲ ኮንስትራክሽን ኩባንያ ባለቤትነት በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች የሚገኙና በቁጥጥር ሥር ያልዋሉ ባለሃብቶች ንብረትና ተንቀሳቃሽ የባንክ ሒሳብ ታግዶ ንብረት አስተዳዳሪ እንዲሾም፣ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመር ቡድን ያቀረበው አቤቱታ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የንብረት እግዱ እንዲሻሻል ትእዛዝ ሰጥቶ ንብረት አስተዳዳሪ ይሾም አቤቱታ ተቀባይነት አጥቶል፡፡  የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመር ቡድን ድርጅቶቹ በመንግሥትና በህዝብ ላይ ያደረሱት ጉዳት በድምሩ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በመሆኑ ለጉዳት ማካካሻ የሚሆን ንብረት አሳግዶል፡፡ ሆኖም የተዘረፈው የህዝብ ሃብት ተጣርቶ ሲመለስ አልታየም፡፡ በተጠረጠሩበት ሙስና ወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸው በቁጥጥር ሥር የዋሉ ባለሃብቶች ውስጥ፣ በእነ አቶ መላኩ ፈንታ የክስ መዝገብ ቁጥር 141352 ከግብር ጋር በተገናኘ ክስ ተመሥርቶባቸው እንዲከላከሉ ብይን የተሰጣቸው ውስጥ ዋስትና መብታቸው  ገንዘብ በዋስትና አስይዘው ከእስር እንዲፈቱ የፌዴራል ከፍተና ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ትዕዛዝ ሠጥቶል፡፡ አቶ ነጋ ገብረ እግዚአብሔር፣ የነፃ ትሬዲንግ ባለቤት {750 ሽህ ብር ዋስትና }እና አቶ ገብረ ሥላሴ ገብሬ የኮሜት ኃላፊነቱ ተወሰነ የግል ማህበር {500 ሽህ ብር ዋስትና }፡፡ ገብረዋህድ  ሙሰኛው ተፈቶል፣አቶ ከተማ  ከበደ ኬኬ ድርጅት ባለቤት ተፈተዋል፣ አቶ ጌቱ ገለቴ ባህር ማዶ ከኮበለሉ ቆይቶል፣ አቶ አለማየሁ በወርቅ ንግድ የተሰማሩ ሃያ ሁለት የሚገኘው የሌክስስ ፕላዛ ፎቅ ባለቤት ውጭ ሃገር ኮብልለዋል ወያኔ እያመቻቸላቸው ያስመልጣቸዋል፡፡ አቶ መላኩ ፈንታ ዋነኛዎቹ ሌቦች በሰረቁት ገንዘብ ዋስ  ሆኖቸው {500 ሽህ ብር እስከ 750 ሽህ ብር ዋስትና } ገንዘብ አስይዘው ሲወጡ አቶ መላኩ ፈንታ በእስር መቆየት በሃገሪቱ ፍትህ አለ ለማለት አያስደፍርም፡፡ በሌላ በኩል የብረታብረት ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ጀነራል ማናጀር ነበሩት ብርጌደር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ከሥልጣናቸው ወርደዋል ሆኖም 77 ቢሊዮን ብር ሙስና ወንጀል ይጠየቁ አይጠየቁ አልተገለፀም፡፡ በሌላ በኩል ሜጀር ጀነራል ዶክተር ተክለብርሃን ወልደአረጋይ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢንሣ) መሪ የነበሩት የባህር ማዶና የሀገር ውስጥ የስለላ ተግባር በመፈፀም የሚታወቁትም ከሥልጣናቸው የመነሳት ምክንያት ከኤች አር 128 መፅደቅ በሆላ በመፍራት እንደሆነ ይነገራል፡፡ በተመሳሳይ በአዲሱ ሚኒስትሮች ካቢኔ ያልታጩት አቶ አባይ ፀሃዬ የስኮር ኮርፖሬሽን ሓላፊ በነበሩ ጊዜ የተፈፀመ የሙስና ወነጀል  ተጠያቂነት መቼ እንደሚሆን ቀነ ቀጠሮ አልተሰጠም፡፡ ከልማት ባንክ ብድር የወሰዱ የጋምቤላ እርሻ ባለሃብቶች ዝርፊያ መቼ ለፍርድ እንደሚቀርቡ አልታወቀም፡፡ የብሄራዊ ደህንነቱ ምክትል ወልደሥላሴ ተለቀዋል፡፡ በሃገሪቱ የህግ ሉዓላዊነት እስካልተከበረ ድረስ፣ የአጋዚ ነፍሰ ገዳች ለፍርድ እስካልቀረቡ ድረስ፣ ፖለቲካ እስረኞች እስካልተፈቱ ድረስ መሬት አትረጋም፣ ሰላም የለም፡፡ የመሬት ቅርምቱ ሙሰኞች ተጋልጠው ለፍርድ እስካልቀረቡ ድረስ ሰላም የለም፡፡

በኢትዩጵያ የሆቴል ኢንድስትሪ ዘርፍ ያሉ ተግዳሮቶች፣ በተለያዩ ጥናቶች በኢትዩጵያ የሆቴል ኢንድስትሪ ዘርፍ ያሉ ተግዳሮቶች ውስጥ፣

1ኛ/ ሆቴል ለመገንባት የሚያስፈልግ በቂ መሬት አለማግኘት፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት በኢትዩጵያ የከተማና ገጠር መሬት በመሸጥ የሚተዳደር መንግስት ነው፡፡ በዚህም የተነሳ የተገነቡት ሆቴሎች በተለይ በአዲስአበባ ከተማ ውስጥ ብዙዎቹ፤ የመኪና ማቆሚያ ቦታ የሌላቸው፣ ለህዝብ መዝናኛና ለልጆች መጫውቻ ስፍራ የሌላቸው፣ አረንጎዴ የመናፈሻ ስፍራ የሌላቸው፣ የመዋኛ ገንዳዎች የሌላቸው ናቸው፡፡

2ኛ/ በኢትዩጵያ የሆቴል ኢንድስትሪ ዘርፍ የፋይናንስ አቅርቦት ችግሮች አሉበት፡፡ እንደ ዓለም ባንክ የኢኮኖሚ ጥናት መሠረት  2016እኤአ የኢትዮጵያ ዓመታዊ አማካኝ ብሄራዊ ምርት (ጂዲፒ)  $72.374  ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የህዝብ ብዛትም 102,403,196 ሚሊዮን  ሆኖል፡፡ የጂዲፒው እድገት አስተዎፅኦ በግንባታው ዘርፍ 2.1 በመቶ፣ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ 0.9 በመቶ፣ አእንዲሁም በአገልግሎት፣ በንግድና ሆቴል ዘርፍ 2.2 በመቶ መሆኑ ተዘግቦል፡፡ ‘‘Ethiopia has a GDP of $72.374 billion as of 2016 and a population of 102,403,196 according to World Bank’s economic outlook. The GDP growth can be attributed to the construction (2.1 %), manufacturing (0.9 %) and services, trade and hotels sector (2.2%).6’’

3ኛ/ የሃገሪቱ የግብርና ምርት አስተማማኝ አቅርቦትና የጥራት ችግር የተነሳ የሆቴሉ ዘርፍ ከባህር ማዶ የግብርና ምርቶችን በማሰገባት ይጠቀማሉ፡፡ የውጭ ጎብኝዎች ምግብ፤ ውሃ መጠጦች፣ መኝታ አልጋ፣ ፍራሽ፣ ቲቪ፣ ዲሽ፣ ዋይፋይ፣ የኢንተርኔት አገልግሎት ወዘተ የሆቴሉ ኪነ-ሕንፃ ዲዛይን/ፕላን፣ የሆቴል ስም(ሒልተን፣ ሸራተን ወዘተ) ፓተንት ራይት የሆቴሉ ህንፃ የተገነባበት የውጭና የውስጥ ማቴሪያሎችና ዲኮሬሽኖች፣ ወዘተ በሙሉ ከባህር ማዶ ሀገራቶች በሃገሪቱ የውጭ ምንዛሪ የሚገዙ በመሆናቸው የሆቴል ኢንቨስትመንት እንደ ኢትዩጵያ ላሉ ደሃ ሃገራቶች ከሆቴልና ቱሪዝም የሚያገኙት ጥቅም በጣም አናሳ ነው፡፡ እንዲያውም ዘርፍ በሃገሪቱ ሽርሙጥናን፣ ግብረሰዶምን፣ ድራግ፣ ወንጀል በማስፋፋት ጉዳት አለው፡፡ በተለይ በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽንና ሌሎች ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች ግዜ የሚታዩ ነውሮች ለታዳጊው ትውልድ መልካም ስነምግባር የሚያስተምር አይደለም፡፡ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ከ750 ሚሊዩን ዶላር ያህል ገቢ በዓመት ታገኛለች፡፡ ከወጣው የኢንቨስትመንት ወጪ ጋር ሲነፃፀ ግን ገቢው በጣም አናሳ ነው፣ ለዚህም ዋና ምክያት በሆቴል ኢንቨስትመንት ዘርፍ ብዙው የመጠጥና የምግብ፣ የኩሽና እቃዎች፣ የላውንደሪ እቃዎች፣ ሪፍሬጀተርና ዲፕ ፍሪዘር ወዘተ 80 በመቶ ግብአቶች ከባህር ማዶ ሀገራት በውጭ ምንዛሪ ተገዥተው የሚመጡ መሆናቸው በማስረጃና በጥናት የተረጋገጠ ነው፡፡ የዓለም ባንክ ለሆቴልና ቱሪዝም ማስፋፍያ ብድር አይሰጥም፡፡

4ኛ/ የህዝብ እንቢተኛነትና ተጋድሎ ምክንያት  የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ተደጋጋሚ የአስቸኮይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ ምክንያት በሃገር ውስጥ ያለው የህዝብ አለመረጋጋትና መፈናቀል፣ ድህነት፣ ርሃብና ስደት የተነሳ፣ እንዲሁም የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት በሆቴል ኢንድስትሪ ዘርፍ የቱሪስቶች የደህንነት ሁኔታ ላይ ችግር ሰለሚፈጥር የጎብኝዎች ፍሰት ይቀንሳል፡፡ ማጠቃለያ፣ በኢትዩጵያ የሆቴልና ቱሪዝም ኢንድስትሪ ኪነ-ህንፃ ግንባታ በሃገራዊ ባህል በተገነቡ ማራኪ ዘመናዊ ጎጆ ቤቶች በሃገራዊ ጥበቦች ማለትም  የዶርዜ ሃይዞ ጥበቦች፣ የሸክላ ስራዎች፣ የቡና መስተንግዶ፣የኢትዩጵያ የፆም ምግቦችና ብርቅዬና ድንቅዬ የእደ ጥበብ የስጦታ እቃዎች፣በጎብኝዎች ተፈላጊነት አግኝተዋል፡፡ በጫካዎችና ማራኪ ሃይቆች አካባቢ በሃገር ውስጥ እቃዎች የተገነቡ ሆቴሎች የብዙ ቱሪስቶች መስህብ በመሆን ተወዳጂነት አግኝተዋል፡፡ በአሁኑ ግዜ በአዲስአባባ ከተገነቡ ዘመናዊ ሆቴሎች የበለጠ ትርፍና የውጭ ምንዛሪም የሚያሽገኙት እነዚህ ሆቴሎች ናቸው፡፡ የሆቴልና ቱሪዝም ኢንድስትሪ ይገኛል የሚባለው ጥቅም ከኢንቨስትመንቱ ወጭ ከፍተኛነት፣ ከሚፈጥረው የስራ እድል አናሳነትና ከሚያስገኘው የውጭ ምንዛሪ ዝቅተኛነት አካያ ሌሎቹ ዘርፎች አዋጭነት አጠያያቂ አይደለም፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሆቴል ዘርፍ ብድር አለመስጠቱ ተገቢ ይሆናል፡፡ የባንክና ፋይናንሻል ዘርፍ ሙስናና ሌብነት አገር አያሳድግም!!! የህግ ሉዓላዊነት በኢትዮጵያ ይከበር!!! ያለ ኢኮኖሚ ነፃነት፣የፖለቲካ ነፃነት የለም!!! አንዳርጋቸው ፅጌና የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!!!

(ተፃፈ ወርሃ ግንቦት 2010 ዓ/ም)

ምንጭ

{1} Wikipedia/corruption in China.

{2} time.com/ china sets death-penality threshold for corruption cases

{3}  የካቲት 7 ቀነቀ 2010ኣ/ም አዲስ ዘመን ጋዜጣ

{4} የኅዳር 20 ቀን 2010ኣ/ም አዲስ ዘመን ጋዜጣ

{5} ሚያዝያ 3 ቀን ሪፖርተር ጋዜጣ

{6} info@ethiopianebassy.be

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.