ስንት ጊዜ ያጭበርቡሩን !!! የግንበት 20 27ኛ አመት የድል በአል የህወሓት ኢህአደግ ብቻ በአል? (የኢትዮጰያ ህቦች በአል) ?? 

ይነብ አትሰልቹ ፣ሀቁን ለማወቅ ሞክሩ

ኣስገደ ገብረስላሴ

የጉንበት 20 ለ27 አመት ጊዜ የሚከበረው በአል ያለው ውጤት የኢትዮጱያ ህዝቦች ትግል ውጤት ነው ይህ የህዝብ ድል በሁለት ምእራፎች የተደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል ለዲሞክራሲ ለሰብአዊ መብት ጥጥበቃ ፣ለሀቀኛ ዲሞክራሲያዊ ህዝባዊ መንግስት ምስረታ ፣ለፍትህ ፣ለህግ የበላይነት ለመረጋገጥ ነበር ። ግን ይህ ህዝብ ግን በኢህአደግ ህወሓት ያገኜው ጥቅም የለም እቺ አገር የሀወሓት ኢህአደግ መሪዎች እና ሸሪኮቻቸው ጥቂት ትጃሮች ናቸው ። ጭቁኖቹ ገዥዎቹ ለመገርሰስ የህዝቦች የትግል በመተባበር የትግል አቅጣጫ እና የተከተሉት የትግል ምእራፎች የሚከተሉት ነበሩ ።ከነሱም ፣
1ኛ —ከበሰበሰው የዘውዳዊ አገዛዝ ስርአት ጀምሮ እስከ ደርግ ስልጣን የሚዝ ጊዜ የነበረ በሙሁራን ተማሪዎች መተባበር የተካየደው ሰላማዊ ትግል የከፈሉት መስዋእት፣ያሳለፉት እስር ሰቃይ እንግልት መግደል መከራ የነበረ የትግል ምእራፍ ነው ።
2ኛ — ወታደራዊው ደርግ የበታች መኮኖች እና መካከለኛ መኮኖች እንዲሁም የበታች ሽም ወታደሮች ስብሰብ የብዙሀኑ ተግል በመቀማት ከስርአቱ ዘበኝነት ወጥተው ዲሞክራሲያዊ ሞፈከር በመያዝ ከዘውዳዊ ስርአት ቀምቶ ስልጣን ከወጣ በኃላ ቡዙ ጊዜ ሳይቆይ ወታደራዊው ተፈጥሮው እና በህሪ አስገዱዶት ወደ ፍጹም ፋሽሽታዊ ስርአት በመቀየር ዜጎች ብጅምላ በመግደል በማሰር ፣የዜጎች ሀብት በመውረስ መጀመሪያ የሚያታልልበት የነበረ ዲሞክራሲያዊ መፎከር በመሰረዝ ወደ ፍጸም ፋሽሽትነት ተቀዬረ ።
ደርግ ጸረዲሞክራሲ መሆኑ ከተረጋገጠ በኃላ በመላው ሀገራችን የነበሩ ሙሁራን ወዝአደሮች ፣አርሶ አደሮች የመንግስት ሰራተኞች ፣የዘውዳዊ ስርአት ትርፍራፊ መካንንት (መሳፍንቶች ) በየአቅጣጫው ፣ በተደራጀና በተናጠል በመነሳሳት ቡዙ ቢሄራዊና አገር አቀፍ ፓለቲካዊ ፓርት ተደራጅተው ደርግ ሊወገድ የሚችል በደፈጣ ውግያ በተራዘመ የትጥቅ ትግል በማካየድ ነው የሚሉነበሩ ። ፣በሌላ በኩል ደግሞ በከተማ ትግል በመፈንቅለ መንግስት (kudeta) አድርገን ለውጥ ለማምጣት ይቻላል ብለው ሲነሱ ፣ሌሎች ደግሞ ደርግን ለመጣል ደርግን በመምሰል በውስጡ ገብተህ ለመስተካከል ይቻላል የሚሉም ነበሩ። እነዚህ ቡዱኖች በየተነሱበት የትግል ስልት የተለያየ ፕሮግራም እና ሞፎከር በመንደፍ በከተማም በገጠርም በመሰማራት ትግላቸው በመቀጣጠል ትግላቸው ቀጠሉ ። ሁሉም ግን በጠባብነትና በተምክህት ጭቃ የተነከሩ ነበሩ ።ደርግም ኢትዮጱያ ትቅደም ያለምንም ደም እያለ ሲዘምርና ዚያውጅ ቆይቶ የኃላ ኃላ ግን የህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ጥያቄና የህዝብ አመጽ እየገፋ ሲሄድ ። ወታደራዊ ደርግም የህዝቦች ጥያቄዎች በዲሞክራሲያዊ መንገድ በሰላም እንደመፍታት ፈንታ ከላይ እንደጠቀስኩት በታጋዮች ላይ በፈጠረው ግድያ እጅግ ቡዙ ቁጥር ስፍር የሌለው መስዋእት ከፈሉ ።ኢትዮጱያ ሀገራችን የዜጎች የደም ጎርፍ ታጠበች ፣የጦርነት አውድማም አየሀነች የዜግች ሀፍትም ወደመ ።

የጦርነት የደም መፋስስ በደርግና በጸረ ደርግ ሀይሎች ብቻ አልነበረም የተከፈለው ። እጅግም አስቀያሚና ደም አፈሳሽ ዘረኛ እልቂት ግን ለደርግም የስልጣን እድሜው ሊያራዝመው የቻለ ያትውልድ የነበረው የፓለቲካ እና የመስመር ሉዩነት በግዜው በማጥበብ ወይ በሂደት ልዩነቱ ለመፍታት ታሳቢ በማድረግ አንድነት ፈጥረው ለዋናው ጠላት እንደመምታት ፈንታ እርስ በእርሳቸው በውግያ በመፋለም በሁሉም ወገን እጅግ ቡዙ ወጣቶች ተላለቁ ።ደርግም አፎይታን አግኝቶ ወታደራዊ አቅሙን አሽቆልቁሎ የነበረው ለመጠናከር ጊዜ መሸመቻ ፈጠሩለት ። የደርግ ተቃዋሚዎች የነበሩ የፈጠሩት አለመተባበር እርስ በእርሳቸው መጣረስ ፣ጠባብ ቢሄርተኝነት ፣ዘረኝነት ፣ቂም በቀል እስከአሁንም በይህ ትውልድ እንደ ቅርሾ ሌጋሲ (ተወርሶ ) እየታዬ ያለው የቢሄርተኝነት ግጭት ፣መናናቅ ፈጥሮ ያለው የ60ዎቹ ትውልድ ፈጥረውት ያመጡት ጠንቅ ነው ።
ያትውልድ የፈጠረው እንቅፋት እንዳለ ሆኖ ግን በወቅቱ የነበሩ ጸረ ደርግ ሀይሎች ደርግን እያዳከሙ ለራሳቸውም እያደከሙ በመጨረሻው አብዛኛዎቹ ፓርቲዎች ጨርሰው ሲጠፉ ፣ጥቂቶቹም ፍጹም ሲዳከሙ ፣ ጥቂት በጣት የሚቆጠሩ እንደ ህወሓት ያሉ የደርግ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለይ ደግሞ ህወሀት ለትግራይ ህዝብ አስተባብሮ የራሱ የነበረ ጠባብና ጸረዲሞክራሲ ባህሪና ተግባር እስከአሁን ያለው ሆኖ ። የሚገርመው ነገር ግን ለትግራይ ህዝብ በተለያዩ መፈኮሮች በመያዝ ለ5 000 000 ህዝብ እንደ እንድ ሰው አንድ አስትንፋስ ፈጥሮ በየማህበረሰቡ ክፍል ሁሉም በየአቅሙ እንዲታገል በመደራጀት በአፍሪካ መንግስታት ካሉዋቸው ወታደራዊ አይል የማይመጣጠን ግዙፉ ወታደር 5 000 000 ህዝብ በሚሊዮን ለሚቆጠር የደርግ ወታደር በመንኮታከት የደርግ ስርአት አፍርሷል ።
ይህ ስል ግን ሌሎች የኢትዮጱያ ጸረ ደርግ ሀይሎች አልነበሩም ማለት አይደለም። ከላይ እንዳስቀመጥኩት አብዛኞቹ ሀይሎች ሲጠፉ ጥቂት እንደ ኦነግ ፣ኢህአፓ፣ ኢድዩ ፣ የአፈር ፓርቲዎች ፣አብነግ ፣ወ ዘ ተ ደካማ አቅም ይዘው ዳርዳር ወይ በስደት አልነበሩ ማለት አይደለም ህወሓት ግን ከ 1973 ዓም ጀምሮ ወደማኸል ሀገር ገባ ወጣ እያለ ቆይቶ ፣ ግን ጎን ለጎን ከኢህአፓ የፈራረሱ ጥቂት በአስር የሚቆጠሩ አባላት ያሉበት የኢትዮጲያ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ኢ ህ ድ ን ) የአሁኑ ባአዴን በመፍጠር የራሱ ትንታግ የሚባል ሰራዊት አጃቢ በተጨማሪ የህዝበ አደራጃጀት በገጠር እና በከተማ ህቡእ ፣ግልጽ አደረጃጀት የሚያካይዱ ፣የፍትህ ፣የፋይናንስ ባለሙያዎች በመመደብ እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም ፣ ኢህደን በህዝብ ተቀባይነት ሊያገኝ ባለመቻሉ ሁሉም የድርጅት ስራዎች በህወሓት ታጋዮች መጫናቸው ትልቅ ጫና ነበረ ፣ህወሓት ግን ከ1977 ዓ ም ጀምሮ ቀስበቀስ ሰሜን ጎንደር ፣ሰሜን ወሎ ፣በተለይ ደግሞ የሰቆጣ አውራጃ ከ1971 ዓ ም ጀምሮ በመቆጣጠር ህዝቡ አንቅቶና አደራጅቶ ወደምልሻነት ፣ከዛም ጠቅልለው ወደ ፓርት ተቀላቅለው ለመታገል ቡዙ ሽዎች ተሰለፉ ። ከ1982 ዓ ም እስከ 1983 ዓም ደግሞ ሰሜን ሽዋን ጨምሮ ሰሜን ጎንደር ፣ደቡብ ጎንደር ፣ሰሜን ወሎ ፣ምእራብ ወሎ በአስር ሽ የሚቆጠሩ ታጋየች ታገሉ ።
በወቅቱ ግን በተሰላፊዎች እና በወላጆቻቸው ለበአዴን የማይመች እና የሰው ሀይላቸው እንዳያድግ የሚያደርግ አንድ እንቅፋት ተፈጠረ ። እሱም ወደትግል ተሰላፊ ወጣቶች ወደ ህወሓት ካልሆነ ወደ በአዴን አንሰለፍም በማለት አሻፈረን በማለት ተቃወሙ ። መቸ እነዚህ ብቻ ከኢትዮጱያ ሰራዊት የተማረኩ ፣ራሳቸው ከደርግ አፈና አምልጠው የመጡ ከኤርትራ በሸአብያ ተማርከው የነበሩ ፣የትግራይ ፣የአማራ ፣የኦሮሞ ፣የደቡብ ፣የጋንቤላ ወዘተ ክልል ተወላጆች የሆኑ በሙሉ ልክ እንደ ስቢል ህዝብ ወደ ህወሓት ካልሆነ ወደ በአዴን አንሰለፍም አሉ በመሆኑም በፍላጎታቸው መሰረት ወታደራዊ እና ፖለቲካ ስልጠና ወስደው በመሳተፍ ቡዙ መስዋእት እየከፈሉ ከቆዩ በኃላ በ1983 ጥርወር ወር ህወሓት እና በአዴን ተቀላቅለው አንድ ፓርት ሆነው ኢህአደግ ( የኢትዮጱያ ህዝቦች አቤታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ) በመባሉ የሁለቱ ሰራዊት አንድ በአንድ እንኳን ተቅሊት (ቅልቅል ) ባይደረግም በአንድ አመራር ሆኖ በብርጌድ በሻለቃ ግን ጎን ለጎን ተቀላቅሎ በአማራር ደረጃ ተማእክሎ እየተመራ እስከ ጉንበት 20/1983ዓ /ም የጦርነቱ መቋጫ አስከሚገኝ አብረን ተጉዘናል ። ከዛ በኃላ የራሱ ታሪክ አለው ።

በሌላ በኩል ደርግን በሚሊዮን የሚቆጠር ሰራዊት የታጠቀ አቤታዊ ምለሻ የሚባል ነበረው በእጁ ይዞት የነበረ ሳይታጠቅ በባዶ እጁ በመንግስት ቢሮዎች ፣በንግድ ፣በፋብሪካ ፣በሌሎች ተቃማት የተሰገሰገው ሰራተኛ ፣ የገጠር አረሶአደሮች የከተማ ህዝብ ፣ የራሱ የደርግ ከመካከለኛ መኮኖኖች በታች እስከ ታችኛው ወታደር በምሬት ጠልተውት ስለነበሩ ውስጥ ለውስጥ እየሽረሸሩ የህሓት ኢህአደግ ሀይል ይምጣልን በማለታቸው ደርግን እንደፈለገው ሊያራሙዱት ባለመቻላቸው ።በውጭ በዲያስፓራም በፖሊስም በአይዶሎጅም እጅጉን ስለጠሉት ደርግ አራቱ እጁና እግሩ ተቆራርጦ በጥቂት ከፍተኛ መኮኖች እና ጥቂት የድህንነት ፣የኢሰፓ አባላት ተንጠልጥሎ አንድ እርምጃ ሊራመድ አልቻለም ነበር ።

የህወሓት ሰራዊትም ከ140 000 ተዋጊ ሰራዊት ፣ የበአዴን 4000 ( 4ርጅመንት ) ሰራዊት ፣ በ100ሽዎች
የሚቆጥ የትግራይ የሰቆጣ የሰሜን ገንደር እና የሰሜን ሽዋ የታጠቁ የገጠርና የትናንሽ ከተሞች ዘመናዊ ነፍጥ የታጠቁ ምልሻዎች ፣ከላይ የተጠቀሱ ክልሎችና ዞኖች ከሰራዊት ኃላ ተሰልፈው በሽ የሚቆጠር ቃሬዛ ይዘው የዘመቱ ወጣት አርሶ አደሮች ፣የከተማ ቀመስ ወጣቶቾ ጾታ በማይለይ ቁስለኛ ፣የተሰዋ የሚያለቁ የሚቀብሩ ወደ ህክምና የሚወስዱ ፣ከተዋጊ ሰራዊቴ ጋር አግሩ እግሩን እየገቡ ለመስዋእት ሳይሳሱ ውሀ ምግብ በመቅረብ የሰራዊቱ የቅርብ ለጅስቲክ በመሆን መስዋእት የከፈሉ ናቸው ። በተጨማሪ ህዝቡ አህያው ፣በቅሎው ፣ፈረሱ ፣ጊመሉ ይዞ እስከ አዲስአበባ ገብቷል በሌላ በኩሉ የህወሓት እስታፍ በደጀን ሆነው የግንባሩ ድጋፍ ሰጭ ሰራዊት 65 000 ሰራዊት ፣ በወታደራዊ ማሰልጠኛ ጣብያ ስልጠና ጨርሰው ቁጭብለው የተነስ ትእዛዝ ይጠባበቁ የነበሩ ዘመናዊ ነፈጥ የታጠቁ 75 000 ሰራዊት ጨምረው ። 140 000 ሰራዊት የህወሓት በድምር ከነግንባር ተዋጊ ሰራዊት ሲሰላ 280 000 ሰራዊት ነበር ። የበአዴን በግንባር ተዋጊ ሰራዊት 4000 ሰራዊት ፣በማሰልጠኛ ጣብያ 2500 ምልምል ሰልጣኝ በድምር ከነ ግባር ሰራዊት 6500 ሰራዊት ቀላል ነፈጥ ብቻ የታጠቁ ነበሩ ። በአዴን የስንቅ ትጥቅ ስታፍ የሚባል አልነበራቸውም ።የስታፍ ሰራተኛ በህሓት ነበር የሚሸፍንላቸው ። ኦሆዴድ ገና አልተደራጀም የነበረ ከምርከኞች ማኸል የተሰባሰቡ 300 የታጠቁ ታጋዮች ነበሩዋቸው ።ደርግ ከተደመሰሰ በኃላ በታጠቅ ጦርሰፈር ተጠናክረው ነው በሀወሓት ሰራዊት ታጅበው በህወሓት የህዝብ አስተዳደርና አደራጃጀት ተሞከሮ የነበራቸው ተመድቦላቸው ነው ወደ መላው የኦሮሞ ጠቅላይ ግዛቶች የተንቀሳቀሱ ። በአዴን እና ኦሆዴድ የፓሪቲዎቻቸው የልደት በኣላቸው ሲያከብሩ በራሳቸውና በህወሓት መሪዎች ለኢትዮጱያ ህዝቦች ማንሳፈፍያ ውሼት የሚነገረው ድራማዊ መግለጫ አሰመሳይ እና ውሼት ነው ። ሀቁ ግን ጸረ ደርግ የተደረገው ጦርነትና የተከፈለው መስዋእት በአጠቃላይ መራራ ትግሉ ተሸክሞት የመጣ የትግራይ ህዝብና ከሱ አብራክ የተፈጠሩ ኢትዮጱያውያን ትግራያኖች ልጆች ናቸው።
አንደዚህ አይነት የህዝብ የትግል መስዋእት መክፈል በተለይ የትግራይ ህዝብ ህወሓት ከደደቢት አዲስ አበባ እስከሚገባ 17 አመታት ፣ የትግል ዘመን ሁሉም ልጆቹ ፣የጭነት እንስሳ ፣የእርድ እንስሳ የጭነት መገልገያ ሁሉም አይነት ቁሳቁስ በማቅረብ ፣ በ100 000 ለሚቆጠረው ሰራዊት በነጻ አርሶ አምርቶ ፣የራሱ እንጀራ እየጋገረ ፣የወጥ የባልትና በርበሬ በአጠቃላይ የወጥ ነገር በማቅረብ ፣ቁስሎኞች ፣በሽቶኞች በማጠብ በመመገብ ፣ ሁለገብ እንክብካቤ በማድረግ በሁሉም የጦር የውግያ ግንባሮች በመሰለፍ በአስር ሽዎች የሚቆጠር ህዘብ ጾታ በማይለይ ከባድ መስዋእት ከፍለዋል ። ከ25 000 በላይ የገጠር እና ነጻ የወጡ የገጠር ከተምች ካድሬ ፣በ100 ሽዎች የሚቆጠሩ ዘመናዊ ነፍጥ የታጠቁ ምልሻዎች በአንድ እጃቸው ሞፎር በአንድ እጃቸው ነፍጥ በመያዝ ቄስ ፣ ሸህ በማይለይ ምልሻዎች ከሰራዊቱ እኩል መስዋእት ከፍለዋል ። ከ1977 ዓ ም በኃላም አዲስ ግንባሮች የምንላቸው በአርማጨሖ ፣በጃናሞራ ወረዳዎች በአጠቃላይ በሰሜን ጎንደርና ሰሜን ሽዋ ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ በአስር ሽዎች የሚቀጠሩ ምልሻዎች ታጠቀው ከሰራዊታችን ጎን ሆነው መሰዋእት ከፍለዋል። የሰቆጣ ዞንና የሰሜን አፋር 6 ወረዳዎችም እኩል ከሌላው የትግራይ ህዝ በታጋይነት በምልሻነት ተሰልፈው ከባድ መሰዋእት ከፍለዋል ። ይህ ሀቅ የትግራይ ህዝብ ውለታ ለመላው የኢትየጱያ ህዝብ አይነገረውም ። ከታጋዮች ጋር ተቀብሯል ፣ ይህ ህዝብ ሁሉም የትግራይ ህዝብ በደርግ ወራሪ ሰራዊት ፣በተዋጊ አውሮፕላን ፣ በመድፍና በምሳይል ፣በክላስተር ቦምብና ናፓልም ሞኖሪያ ቤቱ ከሰወስት ጊዜ በላይ ተቃጥሏል ።አንድአንዶችም እሰከ 6 ጊዜ የተቃጠሉ አሉ ። ተቃጥላሏል ።እንደ አብነት ለማቅረብ በሽሬ አውራጃ በታች አድያቦ ፣በሰየምት አድያቦ ፣በመደባይ ፣በላዕላይ ቆራሮና ታህታይ ቆራሮ ፣ አስገደ ፣ጽንብላ ፣በዛና በእንደርታ ሰሓርት ሳምረ ፣አላዕሳ ገርዓልታ ፣ በመቀለ ከተማ ፣በራያ በሙሉ የገጠር ወረዳዎችና ቀቤሌዎች ። በአክሱም በአንከረ ባርካኳ በአዴት በናዕደር ።በአድዋ በማይ ቅነጣል ፣በእንዳባጻህማ ፣ በእበስነይት ፣በሓሓይለ ፣በዓዲ አህፎሮም ፣ በእገላ አህሳአ ፣ዓደርባዕተ ወዘተ ።በዓጋመ ፣በሓወዜን ፣በሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በአየር ያለቁበት በኢሮብ ፣በአዘባ ወረዳዎች ። በክልተአውላዕሎ በአጽቢ ደራ ፣በወንበርታ ወዘተ ። በተንቤን በተንቤን ዓብይ አዲ ከተማ ፣በአበርገለ ፣በጣንቋ ምላሽ ፣በሀገረሰላም ፣በወርቃ አንባ ፣በአንበራ መጠቃ ፣ወ ዘ ተ ። በወልቃይት በመዘጋ ወልቃይት ፣ ቃፍታ ፣ዓዲረመጽ ፣ማይጋባ ፣የካዛ በረሀዎች ፣በደጀና ወ ዘ ተ ።በጸለምት በዲማ ምጫራ ፣በማይጸብሪ እና አከባቢዋ ፣በአንባ መድረ ፣በፍየል ውሀ ፣ ወ ዘ ተ ። በሰቆጣ ሁሉምወረዳዎች ።

ከላይ በተጠቀሱ አከባቢዎች መኖሪያ ቤታቸው ፣የአንስሳ ሞናኖዋቸው ፣የእርሻ የሰብላቸው ክምር ከነቤት ቁሳቁስና በጎተራ ያስቀመጧት ቀለብ እህል ቢያንስ ከሰወስት እስከ አምስ ጊዜ በወታደርና በተጠቀሱ የጦር መሰሪያዎች ተደብድባል ተቃጥሏ፣እንስሳ ዘቤት ታርዳል ፣በገበያ ወርደው በሀራጅ ተሽጧል ።

በዚህ ጽሁፍ ያስቀመጥኩት አርእስት የገንበት 20 የ27 አመት በአል የህወሓት ኢህአደግ በአል ( የኢትዮጱያ ህዝቦች የድል በአል ነው ) ብዪ በጥያቄ መልክ ያቀረብኩት በራሴ ልመልሰው ፣
በኔ እምነት የደርግ ፋሽሽታዊ ስርአት ብታምኑም ባታምኑም በነበሩ የትግል አመታት የሱማል የባእድ ወረራ በኢትዮጱያ ህዝብ የተባበረ ጡንቻ ትግል ቅስሙ የተሰበረው ወደጎን በመተው ፣በተረፈ ግን ደርግ የተወገደው ሀቁ ለመናገር ከተፈለገ የህወሓት ኢህአደግ ይቀበሉት አይቀበሉት ወደ ጎን ትተን የጉንበት 20 27 አመት ታግሎ ጸረ ፋሽሽቲ ትግሉን መቋጫ አግኝቶ ድልን የተጎናጸፈው የኢትዮጱያ ህዝብ የድል በአል ነው ። ድሉ ከ17 አመት በላይ እልኽ አሰጨራሽ ትግል ታግሎ ፣መስዋእት ከፍሎ ቢያመጣውም ፣የህወሓት ኢህአደግ መሪዎች አቅጣጫውን ቀይረው በመጥለፍ በህዝብ የተመረጠ ህዝባዊ መንግስት መመስረት የሚል አላማ አምነው ህዝቦች ታግለው ያመጡት ስርአት የቤተሰብና የሌቦች መንግስት አድረገውታል ። እኒህ ዘረኞችና ቤተሰቦች በተጨማሪ የሀገራችን ሉአሏውነት አሳልፎው የሰጡ ፣የባህር በራችን አሳጥተው ሀገራችን በኢኮኖሚ በጸጥታና ድንነታ ለአደጋ አጋልጠዋታል ።
የዘንድሮ ጉንበት 20 27ኛ የድል በአልም ጠልፈው የወሰዱት እናከብራለን በማለት የህዝብ ድጋፍ እናገኛለን ብለው ታሳቢ በማድረግ እና ለሌቦች ሸሪኮቻቸው ሙተው እያሉ አለን ብለው ተስፋ እንዲሆናቸው ነው ።
ሁሉ ህዝብ መረዳት ያለበት ግን ጉንበት 20 27 ኛው አመት የሚከበርበት በአል ሚሊዮኖች ዜጎች በፋሽት ደርግ በግፍ የጠፉበት በመሆኑ ሰማአታት በማስታወስ ማክበር አለብን ። በተጨማሪ የየዘንድሮ ጉንበት 20 ሌላ ተስፋ ይዞ የመጣ ይመስላል ? ተሰፋውም የህዝብ አመጽ ያመጣው የጠቅላይ ምንስቴር አብይ አህመድ የለውጥ አንፈትም እያሳዬን ያለው የለውጥ መንገድ እያመጣ ይመስላል የጉንበት 20 የህዝቦች አላማዎች የሚያሳካ ይመስላል ። ይህ ከነጥርጣሪያችን ጋር አንደግፈውና በተግባር እንመለከተው ። ?

የጉንበት 20 27ኛ አመት በአል የሀዝብ ነው ለህወሓት ኢህአደግ አይመለከትም ስል የህወሓት መሪዎች ከላይ በተቀመጠው ሀቀኛ የህዝቦች የተባበረ ትግል ለደርግ ባያዳክመው ንሮ ድሉ ሊቀለበስ ይችል ነበር ። እንመልከት ኦነግ ፣የጋንቤላ ፓርት ፣የአፋር ፣ ቢሄራዊ ፓርቲዎች ፣የኢህአፓ የኢድዩ ፣ የሜኤሶን ለሀገራዊ አድነት ትግል አላማቸው ምን ይሁን ምን እነሱ በጀርባቸው ያሰለፉት ህዝብ አርሶ አደር ነጋዴ ፣ወዝ አደር ፣ሙሁራን ፣ተማሪዎች የመነግስት ሰራተኞች ነፈጥ አንስተው ተፈልመዋል ፣ በከተማ ህቡእ ትግል ሲታገሉ በቀይ ሽብር ተረሽነው በጎደና ተዘርግተዋል !! ተገርፈዋል ፣በሂወታቸው ሳሉ በገልባጭ መኪና በገደል ገልብጦ እንደቁሻሻ የተገለበጡበት ፣ አጋጣሚ ነበር ።ዜጎች በአገራቸው ዜግነታቸው ተነጥቀው 17 አመት ሙሉ በሀገራቸው ተሸማቅቀው ነረዋል ፣ዜጎች ጎሳሳ ጎጃቸው ተወርሰዋል ። ድንበር አቃርጠው ተሰደዋል ፣ተንከራትተዋል ። ለዚሁ ነው የጉንበት 20 የድል በአል የኢትየጱያ ህዝቦች በአል ነው የምልበት ምክንያት ከላይ ያስቀመጥኩት ተጨባጭ መረጃ መነደርደርያ በማድረግ ነው ።

ከላይ የጠቀስኩዋቸው ደርግን ያዳከሙ ሀይሎች በ17 አመት የትግል ዘመን የህሓት መሪዎች 27 አመት ሙሉ የዋሹት ሀቁን ለመናገር ወይ መመስከር ማንም ዜጋ የሚያረጋግጠው ነው ።

የህዋሓት መሪዎች በ17 አመት የትጥቅ ትግል ዘመን የተከፈለው መሰዋእት 60 000 ሰራዊት ነው ብለዋል?
—————————————————— —
የተከበርከው የኢትዮጱያ ህዝብ በተለይ በቅርብ ያለኸው የትግራይ ህዝብ የተከፈለው መሰዋእት ፣የአካል ጉዳቶች ብዛት አንተ ከአበራክህ የወጡ ልጆችህ ስለሆኑ አንተ የትግራይ ህዝብ የምታውቀው አንተ ነህ ።አኔም የውሼት ውሼታቸው የተደበቀ እንዳልሆነ እኔም አውቃለሁ ። እኔም ወደ ህሓት ለመታገል ወደ ማሰልጠኛ ጣብያችን የመጣ ወጣት ከ1967 የካቲት 11 ቀን እስከ 1975 ዓ / ም ወደህወሓት ወታደራዊ መሰልጠኛ ገብቶ የሰለጠነ 95% ሰልጣኝ አውቆዋለሁ ምክንያቱም ራሴ ያሰለጠንከት በመሆኑ እነዛ 5 % ማን እንደአሰለጠናቸው ብዛታቸው አውቃቸው አለሁ ።ከዛበኃላ የሰለጠኑም በስንቅና ትጥቅ ፣በፋይናንስ ፣በትራንስፓር ከሌሎች ተዛማጅ ስራዎች እሰራ ነበርኩ ።በመሆነም በህወሓት ለመታገል በረሀ የወጣ ወጣት ፣የሰለጠነ ምልሻ ታጋይ በሚገባ የማወቅ እድል ነበረኝ ። እንግዲህ ያ በረኸኛ የህወሓት መሪዎች በነሱ መሀይምና ጨካኝ መስፈርት የወጣ የወንጀለኛ መቅጫ ህግና መተዳደርያ ደንብ የቀጣቸው ጀግኖች (ያጠፋቸው ) ሸአብያን ከሞት ለማዳን ተብሎ በኤርትራ ሳህል በረሀ ተራራዎች ተቀብሮው የቀሩ 22000 በላይ ከትግራወይት አብራክ የውጡ ለጋ ወጣቶች ደምረን ሂሳብ ካዋራረድን በትግራይ በዎሎ ፣በሰሜን ሽዋ በወለጋ ፣ በጎጃም ፣በሀረር በድሬዳዋ ወ ዘ ተ የተደረጉ ጸረ ደርግ ስርአት ጦርኖቶች የተከፈሉ መሰዋእት አልነበረም ማለታቸው ነውን ? ይህ ሀቅ ህሊና ካላቸው እነ አቶስዬ አብርሀ ስብሃት ነጋ ፣አባባይ ጸሀዬ ፣ ጀነራል ሳሞራ የነስ ፣ጀነራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ በሳህል ትግራይያኖች ወሰደው ወደእሳት የማገዱ እነ አርከበ ዕቁባይ ፣አውዓሎም ወልዱ ሳሞራ የኑስ ፣ጀነራል ታደሰ ወረደ ፣ ጀነራል ሰዓረ መኮነን ፣ጀነራል አበበ ተክለሀይማኖት ፣ከነሬል ስምረት ፣ አቶ መድሕን ፣ ወ ዘ ተ ራሳቸው በሀላፍነት መርተው ስለነበሩ ለህሊናቸው አይመሰክሩም ?? የህወሓት ሰራዊት አዲስ ምልምል ታጋይ እየሰለጠነ ሸአብያን ሁለት አመት የጠበቀ ፣ኃላም ቡዙ ተዋጊ ብርጌዶችና በአስር ሽ የሚቆጠር ተጠባባቂ ሰራዊት ሳህል እንዲገባ የወሰኑ የህወሓት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሓት ነጋ ፣ስዩም መስፍን ፣አባይ ጸሀዬ ፣ አርከበ እቁባይ አይመሰክሩም? ሌላስ መላው ማአከላይ ከሚቴስ አልወሰነም እኔ እማውቀው እኮ ወደ ሸአብያ ድጋፍ ሰጭ ሰራዊት አንስደድ እኔም አልሄድም አሻፈረኝ ብሎ የተቃወመ ሓዮሎም ብቻ ነው የነበረው ። ሌላው አማራር የህሓት ስራ አስፈጻሚ እንደ ሮበት በሪሞት የሚነዳው ነው ። ስለዚህ የህወሓት ማእከላይ ከሚቴ በሙሉ የኢሳኢያስ ሎሌ ነው የነበረው ማለት ነው ።

ስለዚህ እኔ እሚገባኝ በህሓት የሚመራ የ17 አመት የትጥቅ ትግል ፣ጦርነት የተሰው ሀርበኞች ብዛታቸው የሀወሓት መሪዎች አንደሚሉት የውሼት ፕሮፕጋንዳ ትተን ሀቁን እነመልከት የተግራይ ህዝብ ከ1967 ዓ /ም እስከመጨረሻ የትግራይህዝብ ልጆቹ ወደ ትግል የዘመቱ በየጎጡ ፣ቀበሌ ፣ ዘመድ ጎረቤት ወጥቶ የተመለሰ ወይ የቀረ ፣አካሉ የጎደለ ተቆጣጥሮ ሀቁን ይቆፍረው ይህም ታጋይ ፣ምልሻ ሽግ ወያነ (የገጠር የአርሶ አደር እና የትናንሽ የገጠር ከተሞች ካድሬ ) በአየር ፣በወራሪ ወታደር ፣ባልሆነ የወያኔ ደጋፊነሀ ፣ተላኪ ነህ ፣ህቡእ የከተማ ፣የገጠር ድርጅት ወይ ሰላይ ነህ ተብለው የተረሸኑ በከተማ በገጠር መሰዋእት የከፈሉ ሁሉም የህወሓት ታጋዮች ናቸው ይቆጠሩ ። በተጨማሪ የሰቆጣ አገው ህዝብ የሰሜን ህዝብ ከ1977 ጀምሮ ልክ እንደትግራይ ይጠና ።አንዲሁም ከ1982 ዓ / ም መስከረም ጀምሮ የሰሜን ወሎ ፣ሰሜን ሽዋ ፣ የደቡብ ጎንደርም በዛች አጭር ጊዜ ያደረጓት ሁለገብ ተሳትፎ የከፈሉት መስዋእት በዝርዝ ይጠና ።

ሌላ እስከአሁን የማይነገርላቸው በጸረደርግ ሀይሎች ተሰልፈው የተሰው የትግራይ ወጣቶች ሙሁራኖች በኢህአፓ ፣የኢድዩ ፣የጠራናፊት ፣የግንባር ገድሊ ሓርነት ትግራይ ፣(ገሓሓት) አባላት የጉንበት 20 የድል በአል በአላቸው ነው ሰማአታት ናቸውም ። ምክንያቱ 17 አመት ሙሉ ደርግን አዳክመዋል ። ሌሎች የኦነግ ፣የኢትዮጱያ ሱማል ተቃዋሚ ፓርቲዎች የጋንቤላፓርቲዎች የአፋርም ምንም እንኳን በኢህአደግ እንደገና ተመተው ለስደት ቢዳረጉም የደርግ እድሜ በማዳከምና በማሳጠር አስተዋጽኦ ነበራቸው ።

በ1997 ዓ /ም በመቀለ ከተማ ለፈደራል ፓርላማ በግሌ ለምርጫ ተወዳድሬ ነበር ።በዛን ግዜ ከያዝኩት አጀንዳ የህወሓት ጸረ ዲሞክራሲ ጸረ የደርግ ስረአት አሰወግዶ የመጣ ታጋይ ለነዚህ አንባ ገነን መሪዎች ተሸክሞ ያመጣቸው ጸረዲሞክራሲ ባህሪ እና በታጋይ ነው የሚል አጀንዳ ስለነበረኝ በአንድ ወር ተኩል በ486
ቀበሌዎች አጥንቸ እንደ ኖምና በመውሰድ ያገኜሁት ጥናት ፣
1ኛ የተሰው ታጋዮች 147 000 ከኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ውጭ ፣ በህወሓት ህግና ስነስርአት እና መተዳደሪያ ደንብ ከቀጣቸው (ካጠፋቸው ) ሳይጨምር ።ይህ ጥናት ግን በእኔ አቅም ለግዜው የሰበሰብት ነው እን ፣በጥልቀትና በስፋት ገና አልተጠናም ።
2ኛ አካል ጉዳቶኞች 126 000 በወቅቱ መሪዎች ይዋሹት የነበረ ከ10 00 በላይ ሰውም የማይቆጠር ሆኖ ብለው ይዋሹ ነበር ። አሁን ደግሞ ከ100 000 በላይ ማለት ጀምረዋል ።
ከነዚህ ውስጥ ጡሮታ (የሀኪሞች ቦርድ የተወሰነላቸው 4800 አሉ እነሱም የሚያገኛት አበል ከ180 ብር እስከ 400ብር ነበረች የቀረው አካል ጉዳተኛ ህክምናም የሆነ ድጋፍ የለውም ድኩማን ሆና ወደ ልመና ተሰማርተው ሁሉ ዜጋ እየተመለከተው ያለው ነው ።
3ኛ ምልሻ የተሰው 24 000 አካል ጉደተኞች 4300 በጊዜው ያጠናሁት ።በአየር የተገደለ ፣የተረሸነ ለማጥናት ጊዜ አልነበረኝም ። ለምልሻ ጡሮታ ወይ በሀኪሞች ቦርድ አስወስነው አበል ለማግኜት አልታደሉም በመሆኑ የህወሓት መሪዎች ከሀዲዎች ናቸው ። ይህ ጥናት ሀቀኛ የታሪክ ጸሀፊዎችና ተመራማሪዎች ቡዙ ያልተነገረለት ታሪክ ይቆፍሩ ነበር ። ግን ህወሓት አየጸፋቸውም ።
4ኛየተሰው ታጋዮች ምልሻ፣ሽግ ወንት ልጆች 345000
ይህ መረጃግን ሊመራመሩ ለሚፈልጉ መንደርደርያ ይሆናቸዋል ።
ታድያ ጉንበት 20 27ኛ የድል በአል የህወሓት ኢህአደግ ከሀዲ መሪዎች የድል በአል ?ወይ የኢትዮጱያ ህዝቦች የድል በአል ነው የሚባለው ? አሁንም ልድገመው ይህ የድል በአል የኢትዮጱያ ህዝብ በከተማ በገጠር መደብ በማይለይ የተረሸነበት ፣በጦርነት ያለቀበት ፣ሀብቱ የወደመበት ፣ካገር ባህርና ደንበር ተሻግሮ የተሰደደበት ስርአት በጉንበት 20 በአደባባይ ደርግን አፍሮ ያየበት የህቦች የድል በአል ስለሆነ ለዘልአለም ይከበር ።
አንድ አንድ ወገኖች ከህወሓት ኢህአደግ መሪዎች ካላቸው ቂምበቀል የነበራቸውና ያላቸው ፣የደርግ ስርአት ልዩ ተጠቃሚዎች የነበሩ የጉንበት 20 የድል በአል የኢትየጱያ ህዝቦች የድል በአል ሆኖ እያለ የህወሓት ኢህአደግ መሪዎች በአል አድርገው ይነግዱበታል ።
ጉንበት 20 ሁሉ ጊዜ የጭቁኖች የድል ቀን ፣
የፋሽሽቶች የመቃብር ቀን ናት !!
ከአስገደ ገብረስላሴ
መቀለ
19 /09 / 20 10

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.