አዋሽ40 ሌላው አማሮች የስቃይ ቦታ

ከዚህ በታች ከምታዮት የስም ዝርዝር ባሎቻቸው በአካባቢው በደረሰው ግጭት የሞቱባቸውና ግማሾቹ ወደ ጫካ የገቡባቸው የወሎ አማራ እናቶችና ህፃናት ስም ዝርዝር ነው።
ልጆቻቸውን የሚያበሉት በማጣታቸውና ከክልሉም መንግስት ምንም አይነት ድጋፍ ስላልሰጣቸው ከትላንት በስቲያ ወደ አዲስ አበባ ከተማ በመመጣት ልጆቻቸውን ከሞት ለመታደግ ለምነንም ቢሆን ልጆቻችን እናሳድግ ብለው ቢመጡም የመንግስት ወታደሮች ትላንት ጠዋት ለስልጠና በማለት ወደ 40 የሚሆኑ ወገኖቻችን አዋሽ 40 ወደሚባል ቦታ ወስዳቸዋል።ቦታው ሞቃታማ ስለሆነ በርሀብና በእንግልት ለደከሙ ህፃናት ህይወታቸው አደገኛ ነው።ስለዚህ መንግስት እየፈፀመ ያለውን ይሄን ኢ ሰብአዊ ድርጊት በአስቸኳይ አቁሞ ወገኖቻችንን ወደቀያቸው (ወሎ) በመመለስ መኖር የሚችሉበትን ቅድመ ሁኔታ እንዲያዘጋጅ ፅምፅ ልንሆናቸው ይገባል።
ፍትህ በአዋሽ40 ለሚገኙ አማሮች !!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.