የኢትዮጵያዊያን የእስፖርት ፌደሬሽን ከጠቅላይ ሚንስትሩ የክብር እንግዳ ልሁን ጥያቄ (ደረጀ ገረፋ ቱሉ)

ESFNA የተብለው በአሜሪካ የኢትዮጵያዊያን የእስፖርት ፌደሬሽን ከጠቅላይ ሚንስትሩ የክብር እንግዳ ልሁን ጥያቄ ቀርቦልኛል ብሎ በመግለፅ ለደጋፍዎቹ እና ለአባላቱ የማህበረሰብ ላይ ድምፅ ማሰባሰብ አካህዷል።
በዚሁ መስረት የጠቅላይ ሚንስትሩን መገኘት የደገፉት 65% ሲሆኑ መገኘት የለበትም ያሉት ደግሞ 35% ናቸው።
በሌሎች የዲያስፖራ ዲህረ ገፆች የተሰበሰቡ ድምፆች 75% አከባቢ ጠቅላዩ እንዲገኝ የሚፈልግ ነው።
ጥያቄው እዚህ ላይ ነው ።

1 በዲሞክራሲያው መሪህ የሚንተደደር ከሆነ የአባላት እና የደጋፊ ድምፅ ገዥ ነው። በማንኛውም መስፈርት አባላት እና ደጋፊን ወክለው የቦርዲ አባላት የሚሆኑ ወገኖች የአባላት እና የደጋፊን ፍላጎት ያራምዳሉ ተብሎ ይታሰባል ሳይሆን ያንን ማድረግ የግድ ነው።በዲሞክራስያዊ አካሄድ እና ተጠያቂነት ያለበት ስርዓት ካለ የቦርድ አባላት አከራካሪ ነገር ስገጥማቸው እና የነሱ ውሳኔ የአባላቱን ፍላጎት የማያራምድ ከመሰላቸው ለመተማመኛ የአባላቱን ፍላጎት ለማወቅ አስተያየት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ያሰባስባሉ። በዲሞክራስያዊ መሪህ የአባላት እና ደጋፊን ፍላጎት በይፋ ከተረዳህ እና ያንተ ፍላጎት ከአባላት እና ከደጋፊው ፍላጎት ከተፃረረ ያንተ ድርሻ ቦታውን መልቀቅ ነው ። ከዚያ ውጪ የነሱን ድምፅ ዘለህ ከሄድክ በህግም ባይሆን በሞራል ደረጃ legitimacy የለህም። ስለዚህ ውሳኔውን ከመወሰንህ በፊት ስልጣን መልቀቅ የግድ እና የግድ ነው።ይህ የሚሆነው ዲሞክራሲያዊ በሆነ ስርዓት ነው።እኛም ያው ፌደሬሽኑ እንደስሙ ይሆናል ብለን የአባላቱን እና የደጋፍያቸውን ግልፅ የሆነ ፍላጎት ያከብራሉ የሚል እምነት ነበረን።ነገር ግን የፌደሬሽኑ መሪዎች የዲሞክራሲ መሪህ አፍሪካ ውስጥ ያለውን ያህል እንኳን አልገባቸውም።የአፍሪካ አምባገነኖች ቢያንስ በቀጥታ እንዲህ አያደርጉም።ወይ መጀመሪያውንም ቀብጠው ወደ ድምፅ አይሄዱም።ከሄዱም ያጭበረብሯታል እንጂ እንዲህ በግላጭ አይዋረዱም።የኛዎቹ ግን አካላቸው ተሻግሮ ቢሄድም መንፈሳቸው አሁንም ያው የአፍሪካ ነው።ያውም የአፍሪካ ጫካ ውስጥ! !
የኛዎቹ ውሃ ውስጥ ቢኖሩም አይረጥቡም።ምክንያቱም አስተሳሰባቸ በሆነ ጊዜ ላይ ነክሷል።ምንም ያህል አሜሪካ ቢኖሩም የዲሞክራሲ መሪህ የሚባል አይገባቸውም።ለነገሩ ለረጅም ጊዜ በመኖር ቢሆን ድንጋይ ዋና ይለምድ ነበር።

2 ከሁሉም በላይ ገራሚው ነገር የጠቀሷት ህግ ናት።ህግ የአባላትን ፍላጎት መዕከል አድርጎ ነው የሚረቀቀው።ህግ ከብዙሃኑ አባላት እና ደጋፊዎች ፍላጎት ከተፃረረ ህጉን እራሱ በአባላት እና ደጋፊዎች ውሳኔ ታስቀይራለህ እንጂ አባላት እና ደጋፊዎች የማይቀበሉት ህግ ህግ አይደለም። የደጋፍዎች ድምፅ ከግምት ውስጥ የማይገባ መተዳደሪያ ህግ ህገ አራዊት ነው።
አለበለዚያማ ኢህአዲግም ህግ አለው እኮ!!
ኢህአዲግ እነ እስክንድርን እና አንዷለምን ያሰረው የእራሱን ህገ አራዊት አጣቅሶ እንደሆነ እነዚህ የፌዴሬችን አመራር አባላት ያውቁ ይሆን?

3 እኛ ሀገር ቤት ያለን ኢትዮጵያዊያን ያልተመቸንን የኢህአዲግ ህግ ታግለን እያስቀየርን ነው።የማይመቹንን እና አምባገነን የኢህአዲግ ሰዎች ታግለን በሚመቹን እያስቀየርን ነው።የተቀየሩትም የኛ የህዝቡን ፍላጎት በመከተል ህገ አራዊት እና የዚያ አምላኪዎች ያሰሩአቸውን ሰዎች እያለቀቁ ነው።የኢትዮጵያ ህዝብ ባይታገል ዛሬ ያየናቸው መሪዎቻችን ወደ ስልጣን አይመጡም።እነሱ ወደ ስልጣን ባይመጡ በህገ አራዊት ሰበብ የታሰሩ ብርቅዬ ልጆቻችን አይፈቱም ብቻ ሳይሆን የሚንወዳት ሀገራችን እጣ ፋንታ እራሱ አጠያያቂ ነበር።ይህ በትግል ተቀይሯል።
አሁን በሀገራችን ተስፈኛ ነን!!
አሁን በሀገራችን ጦር የተማዘዙ ወንድማማቾች ተቃቅፈው ጎን ለጎን እየሄዱ ነው።
አሁን በሀገራችን የምንፈልገውን መልበስ እና መናገር አያስከስስም።አያሳስርም።
አሁን በሀገራችን ብርሃን በብርሀን ነው።
እናም ጨላምተኝነት እና ለደጋፉው እና አባላት የማይገዛ ሃይል መንፈሱ ከዚያ ወደኛ እንዲመጣ እና እንድበክለን አንፈቅድም።
ምክንያቱም የተገኘው ነገግ በቀለድ የተገኘ ነገር አይደለም እና!!
ይህ ሁሉ በቃልድ አልተገኘም።ጨለምተኞች ገለል ያሉት በከባድ መስዋዓትነት ነው።ስለዚህ አሜሪካ ያሉት ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ጨለምተኞችን ገለል በሉልን ማለት አለባቸው።እኛ አሁን ፍቅር በፍቅር እያሆንን ነው።ጨለምተኝነት በተስፋ እየተተካ ነው።ስለዚህ ካነሳችሁ ፍቅር እና ተስፋ ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ export በማድረግ እንተባበራችኃለን።
እናም እንህን የማይረጥቡ አሳዎች ፣እንህን ዋና የማይለምዱ የውሃ ውስህ ዲንጋዮች አትመጥኑንም እና ተነሱልን በሉአቸው። 

4 ልብ እንዲባልልኝ እምፈልገው ጠቅላይ ሚንስትሩ የፈለጉት ሁሉ ይደረግ እያልኩ አይደለም።እያልኩ ያለሁት አባላት እና ደጋፊዎች በይፋ የፈለጉት ነገር የግድ መሆን አለበት።
ለምሳሌ 65% አባላት የጠቅላይ ሚንስትሩን በበዓሉ ላይ መገኘት ተቃውመው የቦርድ አባላት እንዲገኝ ቢወስኑ የኔ ምክር ጠቅላዩን በፍፁም አትድረስባቸው የሚል ነበር።አሁን ግን ነገሩ የተገላብጦሽ ነው።
የአባላት መብት እና የዲሞክራሲ መሪህ በይፋ ተጥሷል።ይህ ደግሞ መታረም አለበት።
ሰውዲ ፣ሱዳን ፣ ኬኒያ ያሉት ዜጎቻችን መብት እና ክብር ያሳስበናል ስንል አሜሪካ ያለት ዜጎቻችን መብት በማይረጥቡ አሳዎች ሲጣስ አያሳስበንም ማለት አይደለም።
የምንገዛው በመሪህ ከሆነ አሜሪካ ያሉትም ሆነ ደሃ ሀገር ያሉት የዜጎቻችን ክብር ሲደፈር ሁሉንም ሊያሳስብ ይገባል።
ይህ የዜጎችን ክብር በአደጉት ሀገር ውስጥ ተደረጅቶ መድፈር ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.