የትህነግ/ህወሓት ካድሬዎች የፋሲል ከነማ ማሊያን እንዲቃጠል ወሰኑ (ጌታቸው ሽፈራው)

~የፋሲል ከነማ ማሊያን በመልበሱ የታሰረው “ወልቃይት ትግራይ ነው” ብሎ አስተባብሎ እንዲወጣ ተጠይቋል

የትህነግ/ህወሓት ካድሬዎች ወልቃይት ውስጥ የፋሲል ከነማ ማሊያን በመልበሱ ብቻ የታሰረው ፍቃዴ አሰፋ ለብሶት የነበረው የፋሲል ከነማ ማሊያ እንዲቃጠል መወሰናቸውን ገልፀውለታል። ወጣት ፍቃዴ አሰፋ በታሰረበት ወቅት ከሽራሮ እንደመጡ የተነገረላቸው ኮረኔሎች አስወልቀው የቀደዱበትን የፋሲል ከነማ ማሊያ እንዲመልሱለት ሲጠይቅ “እንዲቃጠል ወስነናል” የሚል መልስ እንደሰጡት ለማወቅ ተችሏል።

በተጨማሪም ወጣት ፍቃዴ አሰፋ ከአሁን ቀደም በፌስቡክ ወልቃይት የአማራ መሆኑን በፌስቡክ ይፅፍ የነበር ሲሆን ወልቃይት የትግራይ ነው ብሎ ካላስተባበለ እንደማይፈቱት ነግረውታል። ወጣት ፍቃዴ ወልቃይት አማራ ነው የሚለውን አቋሙን እንደማይቀይርና እንደማያስተባብል ተናግሯል።

የትህነግ/ህወሓት ባለስልጣናት ፍቃዴ አሰፋን በኮማንድ ፖስቱ እንዳሰሩትና ፍርድ ቤት እንደማያቀርቡት ገልፀው የነበር ሲሆን ዛሬ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ ተወስኗል ሲባል አስተባብሎ እንዲፈታ ጠይቀውታል።

ወልቃይት ውስጥ የፋሲል ከነማ ማሊያን በመልበሳቸው ሌሎች ወጣቶችም ለእስራት የተዳረጉበት ጊዜ እንደነበር የተጠቀሰ ሲሆን አማርኛ ሙዚቃ መስማት፣ መናገርም እንደወንጀል ሲቆጠር ቆይቷል። ቀሳውስት በአማርኛ ሰብካችኋል ተብለው መታሰራቸው ይታወሳል።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.