የጋዜጠኛ ወብሸት ታየ አዲስ መጽሓፍ “ኢትዮጵያዊነትን የመመለስ ተጋድሎ” በሚል ርዕስ በቀናት ውስጥ ለንባብ ይበቃል

 መፅሐፉ በዋነኝነት የረዥም ዘመን አኩሪ ታሪክ ያላት አገራችን ሲውሰበሰቡ በመጡና በመጨረሻም ግልፅ አደጋ ሆነው በተጋረጡብን ሁነቶች ምንነት፣ በሂደቱ ውስጥ የነበሩት ስልታዊ ሸፍጦችና የተዋናዮቹ ማንነት የተገለፁባቸው ዓይነተኛ መንገዶች ከዝርዝር መፍትሔዎቻቸው ጋር ቀርቦበታል።
   በተያያዘም የታሪካችን አካል ሆኖ በቆየውና ዕልባት ባላገኘው የእስርና እስረኞች ጉዳይ ላይ ከሃያ ዓመታት በላይ ከታሰሩት አንስቶ ሕይወታቸውን በየእስር ቤቱ ስላሳለፉት ኢትዮጵያውያን ወደሁዋላ ከ40 ዓመት በላይ መለስ በማለት ብዙዎች ይዘከራሉ።
   ዴሞክራሲና ሚዲያ፣ ፖለቲካዊ ስልጣን የሃብት ምንጭ በሆነበት የአገራችን ገመና የተያያዝነው ትግል ያጋጠሙትና ሊያጋጥሙት የሚችሉት ፈተና ወዘተ…
     ሌሎች ጉምቱ ጉዳዮችንም አካቷል።
በቀናት ውስጥ ለንባብ ይበቃል!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.