የህዋሓት በአዴን መሪዎች ለውጡ አይዋጥላችሁምን? በቃሬዛ ላይ ሆናችሁ ዘልኣለማዊ አገዝዝ ልትገዙን ነው ?

አስገደ ገብረስላሴ

የህወሓት በአዴን መሪዎች ጠ/ ምኒስቴር አብይ አህመድ አሊ የእናንተ አባታውያን መሪዎች አጥር ሰብሮ ጥሶ ከወጣ እኖሆ ከ60 ቀናት በላይ አሰቆጥሯል ። በነዚህ 60 ቀናት ውስጥ ከኢህአደግ አባታዎውያን aመሪዎች አስተሳሰብ ያፈነገጠ የሚመስል ከገመቱት በላይ እጅግ ቡዙ አመርቂ ስራዎች ሰርቷል ።እነዚህ አመርቂ ሰራዏች ግን ለህወሓት ኢህአደግ ነባር መሪዎች ፣የነሱ ጥገኞች ተከታዮች አክራሪ የአቤታዊ ዲሞክራሲ ታማኝ ካድሬዎች ፣ በአቋራጭ ያደጉ ኮንትሮባንዲስት ነጋዴዎች፣ ኢንቨስቴሮች በስጋት ምጥ ተይዘዋል አብይም እስከአሁን እየሄደባቸው የመጡ አቅጣጫዎች ለህወሓት ኢህአደግ መሪዎች ፣መስመራቸው ።በተለይደግሞ ጠ/ምስቴር አብይ አህመድ ድንገት ሳያስቡት የስራ መልቀቅያ የሰጣቸው የበአዴን ህወሓት መሪዎች እነ በረከት ስሞኦን አባይ ጸሀዬ ፣ስዩም መስፍን ፣ስብሀት ነጋ ፣ህላዌ የወሴፍ አርከበ እቁባይ ካሱ ዒላላ ወ ዘ ተ ሌሎችም የፓርላማ አባላት የሆኑ አነ አስመላሽ ወልደ ስላሴ ያሉባቸው በሀዘን ከመሰንበታቸው አልፈው ለምን ተሸንፍን የሚል አጀንዳ ይዘው የጭንቀት ግምገማ ሲያካይዱ እንደሰነበቱ ከአክሱም ሆቴል የወጡ ምንጮች ጠቁመዋል ።ከጉንበት 20 /09 /20 10 ዓ ም በፊት መቀለ መጥተው ሽፋናቸው የጉንበት 20 የኢትዮጱያውያን የድል በአል ፓኔል ለማቅረብ ሲሆን ዋናው ወደ መቀለ የተሰበሰቡበት አለማ ግን ተጀምሮ ላለው የለውጥ ሂደት ለመገምገም ፣ወይ ለውጡ እንዴት ይንኮላሻል የሚል ጥናት እና ሴራን ማጠንጠን እንደነበረ ። ከውስጣቸው የወጡ ምንጮች ጠቁሞዋል ።

ከላይ ያስቀመጥኩት አጀንዳ በተያያዘ መቀሌና የዞን ከተሞች ፣እንዲሁም በትግራይ ገጠር ህዝብ እጅግ ቡዙ የዘረኝነት ቅስቀሳ እና በትግራይ ያለአንዳች ልዩነት አንድ አመለካከት ይኑረን ከህወሓት ወጣ ያለ የአቤታዊ ዲሞክራሲ መስመር ያልሆነ አስተሳሰብ ወይ እምነት አያስፈልገንም በክልላችን ብሎም በሀገራችን ያለ አቤታዊ ዲሞክራሲ መስመር ሁሉም የጥፋት መንገድ ነው የሚል ቅስቀሳ ነው የሰነበተው ።
በሌላ በኩል አምና የነአባይ ወልዱ ፣ ገዱ እንዳርጋቸው ባደረጉት የኢንተር ሀሞወይ የእልቂት ቅስቀሳ በማድረግ ህዝብ ለህዝብ ያስተላለቀ ፣ንብረት ያወደመ ፣ለስደት ለመፋናቀል የዳረገ የዘረኝነት ቅስቀሳ እንደገና አገርሽቶበት ወልቃይት በምክንያትነት እንደመነሻ በማድረግ የህወሓት ካድሬዎችና በመቀሌ የሚገኙ ኤፍኤሞች ፣ድምጽ ወያነ ትግራይ ፣እንዲሁም የትግርኛ ተለብዥን በዘረኝነት መነሳሳት ተጠምደዋል ። እንደዚሁም በአማራ ክልል አማራ ቲቢ ፣ሬድዮ ፣ኤፈኤሞች በካድሬዎች የዘረኝነት ቅስቀሳ ከመጣጣፉም በላይ ወደ የእልቂት ጦርነትም ተቀራርቦ ነበር ።የኩማንድ ፓስት ወታደሮች በማኸል ባይገቡ ንሮ የኢንተርሀሞወይ እልቂት ይፈጸም ነበር ። በአጠቃላይ የአማራ በአዴን የህወሓት መሪዎች የአብይ ወደ ስልጣን መምጣት ፍጹም አልተዋጠላቸውም ። የሁለቱ ክልል ህዝብ ግን ጥቂት የፓርቲ አባላት ኪራይ ሰብሳቢዎች በስተቀር ፣ሌላ ህዝብ ግን ደስተኛ ነው ።በተለይ የትግራይ ህዝብ እነዚህ ሆዳሞች ይሂዱልን ድሮውስ ምን ለውጥ አመጡልን ከጅዎች አይደሉም ? እያለ በነጻ እየተናገረ ነው።
በተጨማሪ ከስልጣናቸው የተወገዱ የህወሓት አንጋፋ መሪዎች ነበር የተሳተፉበት በተለይ ስዩም መስፍን ስብሀት ነጋ ፣ አለም ገብረዋህድ ፣ የክልል ኮንፍረን መጀመሩ ተከትሎ ፣ ህወሓት ናድን የሚለው የተሰው ታጋዮች የባለ አደራ ኮንፍረንስ ፣ የህወሓት እናድን የተጋይ ነበር ፣ ከሰራዊት በጥሮታ የተሰናበቱ ማህበር የባለአደራ ማህበር ኮንፍረንስ ፣ የጦር አካል ጉዳቶኞች ኮንፍረንስ ፣ በወጣት ማህበር ስም የወረዳ፣ የቀበሌ ፣የመንግስት ሰራተኞች የህወሓት አባላትና ካድድሬዎች ኮንፍረን ፣ የሴቶች ማህበር ኮንፍረንስ ሌሎች ስብሰባዎች ሲካየዱ ሰንብተዋል ።የነዚህ ኮንፍረንሶች ፣ አለማ የህወሓት አንጋፋ መሪዎች ድንገት ከየነበሩበት የአማራር ቦታ ስለየተባረሩ ( ሰለተሰናበቱ ) የነሱ ሎሌ ካድረና የነሱ ሸሪኮች የሆኑ ኪራይ ሰብሳቢዎች ሙሶኞች ተሸነፍን በሚል ስሜት ስለተፈጠረ እሱን ለመረጋጋት አለን አልሞትንም ብለው ለመረጋጋት ታሳቢ በማድረግ ነው ።
በነዚህ ከንፍረንስ ዘረኝነት ማኸል ያደረገ ንዴት ቂምበቀል የተሞላበት ቅስቀሳ እንደነበር በኮንፍረንስ የነበሩ ተሳታፊዎች ውስጥ ምንጮች ጠቁመዋል ።
በዚሁ ከንፈረንስ የመጨረሻ ውሳኒያቸው እና ይዘውት የወጡ ሞፎከር በትግሪያኖች መካከል የሀሳብ ልዩነት አይኖርም !!!
ከአቤታዊ ዲሞክራሲ መሰመር ውጭ ሁሉም መንገዶች የጥፋት መንገዶች ናቸው !!
የህወሓት መስመር አሸናፊ ነው !!
ለትምክህትና ጠባብነት እንፋለማለን !! ወ ዘ ተ የሚሉ ሞፎኮ በሩ ።
እኔ እሚገርመኝ ህወሓት ከሞተ በ1985 ዓ ም ሞቶዋል ።ታድያ ህወሓት እናድን ሲሉ ህወሓት በሌለበት እንዴት ይድናል ?ምናልባት ህወሓት የሚል ስም እንደ እነ ሂትረል ፣መሶሎኒ ስሙ ሊነሳ ይችላል ፣መስመሩ ግን ተቀብረዋል ።ዘፋኝ እንዳለው ፣
አንጫወት እንጅ እጫወት በጣም
ከእንግዲ ልጅነት ተመልሶ አይመጣም !!
እንደተባለው አበቃ ህወሓት መስመሩ ሞቶዋል ተቀብራል!!
የህወሓት ኢህአደግ መሪዎች እባካቹሁ ለዝህች በአስር አመት የማትቆጠር እድሜያችሁ ለማርካት ስትሉ እኛ ከሞትን ሰርዶ አይብቀል የሚል የተስፋ ቆረጥ አስተሳሰብ ተውት ።
አስገደ ገብረስላሴ
መቀለ
25 / 09 20 10

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.