ይድረስ ፡ ለ ሰማያዊ ፓርቲ !! ትግላችሁ ለመፎካክር እንጂ ለመቃወም አይሁን !!

ይድረስ ፡ ለ ሰማያዊ ፓርቲ !!

ትግላችሁ ለመፎካክር እንጂ ለመቃወም አይሁን !!

ሰማያዊ ፓርቲ እንደሌሎቹ ፓርቲዎች ሁሉ በሀገራችን የዲሞክራሲ ለወጥ እውን እንዲሆን እያደረገ ላለው ትግል ከፍተኛ አድናቆት አለኝ፡፡ መንግስት ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ጀምሮት ከነበረው የይስሙላ ድርድርም እራሱን በማግለሉ በወቅቱ ውሳኔውን የሚገባ ነበር፡፡ ሰሞኑን ባነበብኩት ዜና ላይ ግን ሰማያዊ ፓርቲ ክመንግስት ጋር ወደተጀመረው ድርድር ተመልሶ እንዲገባ ተጠይቆ የውጪ አደራዳሪ ከሌለ አልሳተፍም አለ መባሉ የብስለት ማነስ ይመስላል፡፡

በመጀመሪያ ሰማያዊ ፓርቲ  አሁን ከማን ጋ ድርድሩ እንደሚካሄድ በትክክል የተረዳ  አይመስለኝም፡፡ ድርድሩ የሚካሄደው እንደ ሰማያዊ ፓርቲ ለውጥን ለማምጣት ከተነሱ የገዢው ፓርቲ የለውጥ አራማጅ ሀይሎች ጋ ነው፡ እነዚህ ሀይሎች የህዝቡን ብሶት አጀንዳቸው እድርገው የህዘቡን ጥያቄ አግባብ ነው በማለት ከህዝብ ጋ የቆሙ ናቸው፡፡ ክእነዚህ የለውጥ ሀይሎች ጋር  መተማመን  የሚቸግረው ለምንድነው? የውጪ ሀይልስ ዶ/ር አቢይ እያደረገ ካለው በላይ ምን ያመጣል ብለን ነው ተስፋ የምንጥልበት፡፡

ለውጥ አይመጣም የሚል ህሳቤም ካለ ተመልሶ መውጣትን ማን ይከለክላል? የበሰለ ፖለቲካ የሚያራምድ እና ለሀገር የሚያስብ ፓርቲ ማድርግ ያለበት ወደ ድርድሩ ገብቶ ዶ/ር አቢይ ቃል የገባውን እንዲፈፅም መፈተን ነው፡፡ የፖለቲካው ምህዳር እንዲሰፋ የምርጫ ህጉ እንዲሻሻል የመናገርና የመሰብስብ መብት እንዲሁም ፍትህ እንዲክበር መጠየቅ ነው በቀጣይ መሆን ያለበት፡፡ የእናቴ ቀሚስ አደናቀፈኝ አይነት ምክንያት መደርደር ለውጡን ከማጓተት ሌላ ምንም ጥቅም የለውም ፡፡ ሊጠቅም የሚችለው ወያኔን ብቻ ነው፡፤

መቼም በአሁን ሰአት በሀገራቸን እየሆነ ባለው ነገር ሁሉ ያልተደሰተ ኢትዮጵያዊ አለ ቢባል ለማመን የሚክብድ ነው ፡፡ ምክንያቱም በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ እግዚአብሄር አምላክ የደጋግ አባቶቻችንን ፀሎት ሰምቶ የምህረት አጁን ስለዘረጋልን እንጂ በሀገራችን ላይ አንዣቦ የነበረውን አደጋ እንዲህ በአጭር ጊዜ ተረጋገቶ የለውጥ ተስፋ ይመጣል ብሎ ለማሰብ እንኳን አስቸጋሪ ነበር፡፤

ያለማጋነን እየተደረገ ያለው ሁሉ ህልም እየመሰለኝ ሁሌ ከእንቅልፌ በነቃሁ ቁጥር ቶሎ ብዬ ኢንተርኔትከፍቼ የለውጡ ሂድት እውን መሆኑን እና እንቅፋት እንዳላጋጠመው ሳላረጋግጥ ከአልጋዬ አልነሳም፡፡ እስካሁንም ልቤ አላረፈም፡፡ የተጀመረው ለውጥ እንዳይደናቀፍ ስለምፈራ ፀሎቴ ሁሉ ዶ/ር አቢይን ክፉ እንዳይነካው ነው ምክንያቱም ሀገራችንን ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተነሳው ጠላት ዲያቢሎስ አያንቀላፋምና፡፡

ዶ/ር አቢይ እየወሰደ ያለው እርምጃ እና ስለ ሀገራቸን ያለውን ራዕይ በመገንዘብ ከነበርንበት ቅኝት ወጥተን በታደስ መንፈስ ክጎኑ ሆነን ልንደግፈው ይገባል እንጂ ቅድመ ሁኔታ እየደረደርን የባቡሩን ፍጥነት ለመግታት መሞከር እንደገና ወደማንወጣው አዘቅት ውስጥ ነው የሚከተን ፡፡ የሚፈለገው ለውጥ ሊመጣ የሚችለው የሚመለከተው ሁሉ ድርሻውን ሲወጣ ብቻ ነው፡፡

ዶ/ር አቢይ ከግማሽ በላይ ተጉዞ ወደ እኛ መጥቶ በተግባር እያሳየን ነው፡፡ እግዚአብሄር እድሜውን ያርዝመው እና ወንድማችን አንዳርጋቸውን ከእስር እንዲፈታ አድርጎ በሀሴት እና  በደስታ ሰሜት እንድንዋኝ አድርጎናል፡፡ ከዛም በላይ የጥላቻ እና የብቀላ ፖለቲካ አላስፈላጊ መሆኑን ሞዴል በመሆን ውድ ወንድማችን አንዲን በክብር ቤተመንግስት ድረስ ጋብዞ በወንድማዊነት ፍቅር አብሮት ፎቶ ተነስቶ አሳይቶናል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ መልዕክቱ በደንብ የገባችሁ አልመሰለኝመ አካሄዳችን በብስለት መሆን አለበት፡፡

ብዙ ተምረው በሆዳቸው የሚያስቡ ሳይማሩ ደግሞ በጭንቅላታቸው የሚያስቡ ስላሉ የተማረ ይግደልኝ የሚባለው አባባል ብዙም ባይመቸኝም ሰሞኑን ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ስለ ግንቦት 7 የትግል አቅጣጫን ስለመቀየር የተናገሩትን ስሰማ ኢትዮጵያ ምን ያህል በሳል ልጆቸ እንዳሏት ግን ምን ያደርጋል ስልጣን በጠመንጃ አፈ ሙዝ በሚያመልኩ ላይ እየወደቀ ዕድሜ ልካችንን እንባላለን፡፡

እስክዛሬ እጃችን እየገቡ ሳንጠቀምበት የባከኑ በዙ የታሪክ አጋጣሚዎች ይበቃሉ በታሪካቸን ላይ አሁንም ሌላ ጠባሳ ጥለን ማለፍ የለበንም፡፤ በመካሄድ ላይ ያለውንም የለውጥ ሂደት ማፍጠን እንጂ መጎተት የለብንም፡ ለውጥ ለማምጣት ሌላ የወንደሞቻችን ደም መፍሰስ የለበትም፡፡ ወደ ዃላ እያዩ ወደ ፊት መሄድ አይቻልም እና በመቻቻል እና በሰከነ ሁኔታ በመደማመጥ ያገኝነውን አእጋጣሚ ተጠቅመን ሀገራቸንን እንታደግ፡፡

 

በዚሁ አጋጣሚ መድረክም ወደ ድርድሩ እንዲገባ ምክክር ለማድረግ ወደ ቤተመንግስት መጠራቱን አንብቤያለሁ በጣም ደስ የሚል ዜና ነው፡፡ ዜናው ትክክልም ሆነም አልሆንም መቼም የመድረከ አመራሮች በትምህርትም በልምድም የበሰሉ ስለሆኑ አውራ ድርጅት ነን የሚለውን አስተሳሰብ ትተው በራሳቸው ተነሳሺነት ቢሆንም ለሌሎቻችን ምሳሌ በመሆን በውይይቱ በመሳተፍ ለሀገራችን የሚበጀውን መንገድ እንደሚመርጡ ባል ሙሉ ተስፋ ነኝ፡፡

በመጨረሻም ኢሳቶች በአሁን ሰአት በሀገራቸን እየተካሄደ ያለውን ለውጥ በመደገፍ በተለይ ስለ ዶ/ር አቢይ የምትዘግቡት ገንቢ ዘገባዎች በጣም ጥሩ ናችው ፡፡ ግን በወያኔ ላይ የምታካሂዱት ዘገባዎች ፅንፈኝነት ይታይበታል ይህ ጥላቻ የተሞላበት አካሄድ ድግሞ የለውጥ ሂደቱ ላይ አሉታዊ ተፀእኖ ከማሳደር እና የ ዶ/ር አቢይን የቤት ስራ ከማክበድ ወጪ ምንም ጥቅም የሚያመጣ አይደለም፡፡ እባካችሁ ቶናችሁን እንኳን ቀይሩ፡፡

እግዚአብሂር አምላክ ኢትYኦፕያን ይባርክ አሜን፡፡

በዲሉ በዛብህ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.