ለአቶ በቀለ ገርባ እንዲሁም ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ሁሉ (ሰርፀ ደስታ)

አቶ በቀለ ገርባ

አሁን በከፍተኛ ፍጥነት እየተሰራጨ ያለውን የአቶ በቀለን ንግግር አደመጥኩት፡፡ እንደኔ ላለ ሰው ይሄ ብዙም አያስደነግጠውም:: እኔን ግን ሁሌ የሚያበሳጨኝ ጉዳይ አለ፡፡ ይህን ላለፉት 5 ዓመታት በግልጽ ስናገር ቆይቻለሁ፡፡ ዛሬ በቀለ ሲናገሩ የምትሰሙት የበቀለ ችግር አደለም፡፡ ሁላችንም ውስጥ የገባ አደገኛ ነገር እንጂ፡፡ አቶ በቀለ ፊት ለፊት መናገራቸው ነው ልዩነቱ፡፡ ኢትዮጵያ ያጣቸው ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚለው ሁሉ ኢትዮጵያዊ አደለም፡፡ የችግሩ መሠረት እጅግ የከፋ የዘረኝነት መንፈስ ተጠናውቶናል፡፡ ሊያውም የሚያሳዝነው በማናውቀው ዘራችን፡፡ ለምሳሌ አቶ በቀለን እነኳን ብንወስድ ዛሬ የአመኑበት ኦሮሞነት በደማቸው ውስጢ ሊይኖር ሁሉ እንደሚችል ልጠቁም አወዳለሁ፡፡ በዘረኝነት ላይ ደግሞ አንዳችን ለሌላው ያለን ጥላቻ እጅግ የሚዘገንን ነው፡፡ ብዙ ጊዜ አዝኛለሁ፡፡ ደስታችን የራሳችን ነጻ መውጣት እንኳን አደለም ሌላው ሲጎዳ ማየት እንጂ፡፡ ማስመሰል ግን ችለንበታል፡፡ እኔ ዛሬ ላይ ማንንም መለማመጥ አያዋጣም የሚል አቋም ላይ ደርሻለሁ፡፡

ወደ ሚሊየን የተጠጋ ኦሮሞ ሲፈናቀል ሲጮህ የምናየው ኦሮሞ ነኝ ብሎ የሚያስበው ብቻውን ነው፡፡ በውስጥ ደግሞ አለ፡፡አማራ ሲፈናቀል አማራ ነን ያሉት ኡኡ ማለት ብቻም ሳይሆን ሌላ ጽንፍ እንዲይዝ ነው፡፡ አብይ አማራ ክልል የሄደ ጊዜ የተባለውን ሰምተናል፡፡ ያንተ ወገኖች  አማሮችን እየገደሉ ናቸው፡፡ አስቡት የኢትዮጵያው ጠ/ሚኒስቴር (የአማራውም) የአንተ ብሔር ተብሎ እየታሰበ ምን ቢያደርግ ሊታመን እንደሚችል እንኳን፡፡ የአንት የእኔ መባባል ብቻ አደለም ከላይ እንደጠቀስኩት ነው፡፡ አልፎም በጠላትነት መተያየቱም እንጂ፡፡ በተለይ ተማርኩ በሙለው፡፡ ሚስኪኑ ሕዝብ እማ ይሄው ኢትዮጵያዊነቱንና ወንድማማችነቱን ለመመለስ መከራውን እያየ ነው፡፡

ብዙ ማለት አልፈልግም ለአቶ በቀለና ለሁላችንም፡፡ ለአቶ በቀለና ለሁላችንም ያልኩት፡፡ አቶ በቀለ  ፊት ለፊት ስለተናገረው እንጂ ይህ ችግር የሁሉም ስለሆነ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ሌለው (ሥም አልጠቅስም) ኦሮሞዎቹ ሲል በጆሮዬ ሰምቸዋለሁ፡፡ ልብ በሉ ይሄ ደግሞ በኢትዮጵያ አንድነት ሥም ተሰልፊያለሁ የሚል ዋና መሪ የሆነ ሰው ነው፡፡ ኦሮሞዎቹ ያለበት ሁኔታም ያው እኔ እነሱን አደለሁም ነው፡፡ ያሳዝናል!  መጀመሪያ እኔ ካልመራሁ ኢትዮጵያ ትፈራርሳለች ብሎ ማሰብ በራሱ ጥሩ ያልሆነ አመለካከት ነው፡፡ ሌላው ስለራስ ነጻ መሆን መታግል ጥሩ ሆኖ ሳለ ስለሌላው ነጻ መሆን መናደድ ግን ራሱ ከማሳዘንም ያበሳጫል፡፡

የኦሮሞ ብሔረተኛ ነን የሚሉት ጉዳይ በአንድ ወግን የአማራ ነን የሚሉ በሌላ ትግሬ ወያኔ ዳኛና ነጥብ ያዥ እየሆነ ሕዝባችን አሁንም መከራ ያያል፡፡ አንድ ነገር ግን በጣም ገርሞኛል፡፡ ከዚህ በፊት በለንደን የሆነው ነገር መቼም አልረሳውም፡፡ ከዛም በአትላነታ ቻርተር ያለው የአሮሞ ነኝ የሚለው ቡድን አሁንም የለቀቀን አልመሰለኝም፡፡ ይህን ጉዳይ በቀዳሚነት ኦሮሞ ነኝ ብሎ ያመነው ራሱ ሊዋጋው ይገባል፡፡ ብዙም ጊዜ አማርኛን ማንም ስለሚሰማ ችግር የለም፡፡ የኦሮሞ ብሔረተኛ ንነ ባዮች በኦሮምኛ ሲያወሩና በአማርኛ ሲያወሩ የሚያስተላለፉት መልዕክት ሁለቱን ቋንቋ ለሚያዳምጡ ግር ይላል፡፡ አማሮችም ያው ነው ሌላ ቋንቋ ስለሌለ እንጂ እርስ በእርስ የሚነጋገሩት ምንም አይለይም፡፡ በአጠቃላይ ሁሉም ጋር፡፡ አይደብረንም እኮ፡፡

አጋጣሚውን ለትግሬ ወያኔ ጥሩ ግበዓት እየሆነው ነው፡፡ አንድ ነገር ግልጽ እንዲሆንልን ያስፈልጋል፡፡ ዛሬ እኛ የእነሱ የምንል ነገ እድሉ ቢገጥመንና ሥልጣኑ ቢኖረን ምን ልናደርግ እንደሚችል ሕዝብ ከወዲሁ እየታዘበ እንደሆነ፡፡ ስለ ኦሮሞ ብናገር ይሻለኛል፡፡ ኦሮሞ ሌላው ችግር ኢትዮጵያዊነትን ለአማራ አሸክሞ መታየቱ ነው፡፡ ብሔረተኛ ነኝ ባዩን ማለቴ ነው፡፡ የኦሮሞ ነጻነት በኢትዮጵያ መፍረስ ላይ እንሚጸድቅ ዛሬም ብዙዎች የሚያምኑት ነው፡፡ በዛው ልክ ሌሎች ኦሮሞን እንደ ልዩ ጠላት ማየተም በዝቷል፡፡ ብዙ የኦሮሞ ነጻ አውጪ ነን ባዮች ከአማራ ለመራቅ ኦሮሞና ቀሪው የደቡብ ህዝብ ይላሉ፡፡ ሶማሌን ጨምሮ ማለት ነው፡፡ እኔ እንደማየው  መናገር የምችለው አውነት ግን ኦሮሞ ከኢትዮጵያዊነት ውጭ ከሁሉም ብሔረሰብ ይልቅ አደጋ ላይ ያለ ሕዝብ ነው፡፡ ዛሬ ኦሮሚያ እያሉ የሚጠሩትን ምድር ይዞ ኦሮሞ ለብቻው ቢገነጠል እንኳን ከውጭ በዙሪያው ከአሉት ሌሎች ሕዝቦች ከሚደርስበት ጥቃት ሌላ እርስ በእርስ እንድ ሊሆን የማይችል አኗኗር ያለው ሕዝብ ነው፡፡ ይሄንንም በሌላ ተርጉሙት ደግሞ፡፡ ምድር ላይ ያለው እውነት ይሄ ነው፡፡ የምንደባብቀው ነገር የለም፡፡ ከማንም በላይ ኢትዮጵያ ለኦሮሞ ታስፈልገዋለች፡፡  የኢትዮጵያን መፍረስ እንደ ማስፈራሪያ ለፖለቲካ ፍጆታ መጠቀም ከምንም በላይ ስህተት ነው፡፡ ለሕዝብም አለማሰብ ነው፡፡

ለብዙ ኦሮሞዎች የአብይ ነገር አልተመቻቸውም፡፡ አቶ በቀለም ያሉት ይሄንኑ ነው፡፡ የእኛ ሰው ከአሉት በኋላ ግን ለእኛ ሳይሆን ለሌሎች ሆነ ነው ዋና ችግራቸው፡፡ አንካካድ፡፡ አብይ ምን እንዲያደርግ እንደተፈለገ አልገባኝ ከአልሆነ በቀር እስከገባኝ አብይ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስቴር እንጂ የኢሮሞ ጠ/ሚኒስቴር አደለም፡፡ በዘር ቋት ሰዎችን ስንጨምር የምናሰበው አስተሳሰብ ያው እኔ ብቻ መሆኑ እንጂ፡፡ እየሰራም ያለው እንደ ኦሮሞነት ሳይሆን እንደ ኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስቴርነት ነው፡፡ ሌላ ቀርቶ ለማ የኦሮሚያ ፕሬዘደንት እንጂ የኦሮሞ ፕሬዘደንት ሆኖ ኦሮሚያን ማስተዳደር አይችልም፡፡ ይህ አስተሳሰብ ስለራቀን በጣም ተቸግረናል፡፡ እኔ የቧህ ሆኜ ነው መሰለኝ ከዚህ በፊት እንደውም አቶ በቀለ ለምርጫ መወዳደር ያለባቸው ጎንደር ላይ ነው ብዬ ነበር፡፡ አሁን በሰማሁት ድምጽ ግን እኔ እንጃ ዛሬ ኦሮሞም ኢትዮጵያዊነቱን ከምንም በላይ ፈልጓል፡፡

እባካችሁ ነገሮችን ለማስተባበል አንሞክር፡፡ አማራ ወይም ሌላ ስለሆንክ ዛሬ አቶ በቀለ የተናገሩትን አግዝፎ መጨፈር ኦሮሞ ስለሆንክ ደግሞ የኦቶ በቀለን ነገር ለማስተባበል አትሞክሩ፡፡ እስኪ ከኦሮሞው ለአቶ በቀለ ትችቱ ከአማራው ወይም ሌላ ከሆነው ደግሞ ማስተባበሉ በውሸት ሳይሆን ምን አልባት እኛ ከተረዳንው ውጭ የአቶ በቀለን ንግግር የተረዳ ከአለ፡፡ ከዚህ በተረፍ ኢትዮጵያዊ ሁሉ አሁን የተፈጠረልህን እድል አስብ፡፡ አብይ በዘረኝነት መረብ ለተጠለፍን አይመችም፡፡ እርግጥም ዘረኛም ሳንሆን የአብይን ነገር ላንወድለት እንችላለን፡፡ ያ መልካም ነው፡፡ ሰው የአመነበትን ነገር ባይወድ እውነተኛ ነው፡፡ በዘረኝነት ግን ሌላውን መጥላት በሰው ሳይሆን በሰማይ አምላክ ፊት የተረገመ ነው፡፡ አነሰም በዛም መቼም ቢያንስ ብዙዎቻችን ሐይማኖት አለን፡፡

አቶ በቀለ ቢቻልዎት ራስዎ በይቅርታም ይሁን ወይም በማብራራት በመጡ፡፡ ብዙ ሰው የምርም ከልብ የተማመነብዎት እጅግ ደንግጧል፡፡ እራሴ የገጠመኝ እዚህ ላይ ላጋራ፡፡ አንዷ ማመን አቅቷት የተተረጎመው ግን አውነት ነው? ብላ ወደኔ ላከች፡፡ እኔን አንደነገርኳችሁ ብዙም አልገረመኝ፡፡ እንዲህ ያሉ ነገሮችን ብዙ ጊዜ አይቻለሁና፡፡ በሌላ ሳይሆን በራሴ ብዙ ያየሁት እውነት አለ፡፡ አሁን ሳይ ፌስቡኩ ሁሉ ይሄንኑ ነው የሚያወራው፡፡ በየጓዳችን ብዙዎቻችን ምን እንደምናወራ እራሳችን እናውቃለን፡፡ ችግሩ በሚዲያ እንዲህ እንደሰደድ እሳት መቀጣጠሉ ነው፡፡ አቶ በቀለን በዚህ ጉዳይ እንዲናገሩ አሁን አለምናለሁ!  በዚህ ፕሮፓጋንዳ ማን እየተጠቀመ እንደሆነ አስቡት፡፡ ከዘር ልክፍት ከአልወጣን አዙሪቱ ይቀጥላል፡፡ አይደብርም ግን?!!

በመጨረሻም እንድ የመጻፈ ቅዱስ ቃል ሁሌ በጭንቅላቴ የሚያቃጭል ልንገራችሁ፡፡ ይት ላይ እንዳለ አላውቅም ቃሉን ግን አውቀዋለሁ፡፡ እግዚአብሔርን (እውነትን) ለማወቅ በአልወደዱት መጠን የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው ይላል፡፡ በቃ አንዴ ከእውነት ከወጣን ምን ማድረግ ይቻለል

ልዑል አምላክ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.