‹‹የጂቲፒ ቱ፣ ሞቱ!!! የዓሣ ግማቱ ከአናቱ!!! ›› ‹‹ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር››

  ‹‹እምቢልታ  መለከት፣ የሚሰማው የት ነው
                                           አንዱም በስርቆሽ በር፣ አንዱም በግቢ ነው፡፡››    ማኅተመ ወርቅ እሼቴ 1927 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ብሔራዊ ፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር የሌላት አገር ናት ፡፡ የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት ሃገሪቱን በዘጠኝ የቆንቆ ክልሎች መንግሥታት ከሸነሸናት ጀምሮ የክልሎች የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ማለትም የትግራይ፣ የኦሮሚያ፣ የአማራ፣ የደቡብ ወዘተ በመተካቱና  አፈፃፀም አራምባና ቆቦ ሲረግጥ 27 ዓመታት ተቆጥሮል፡፡ ከገሙ ቅንቁላሎች፣ጫጩቶች አይፈለፈሉም!!! የዓሣ ግማቱ፣ ከአናቱ!!! የቀድሞው ብሔራዊ ፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር፣ ሃገሪቱን ኢኮኖሚያዊና መልከ-ምድራዊ /ጂኦግራፋያዊ ክልሎች በመከፋፈል (የሰሜን፣ ደቡብ፣) ኢትዮጵያ ፕላን ቀጠና ጽህፈት ቤቶች በመመሥረት  ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ የኢኮኖሚ እቅድ በጋራ መንደፍ አስፈላጊ ነው፡፡ የብሔራዊ ፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር፣ የህወሃት/ኢህአዴግ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት የክልል የፖለቲካ ፖሊሲዎች በዋናነት የሚያጠነጥኑት

{1} አንደኛ፣ ቆንቆ ተኮር /ዘውግ ተኮር ፖለቲካዊ የክልል ፖሊሲ በብሔራዊ ኢኮኖሚያዊና መልከ-ምድራዊ /ጂኦግራፋያዊ ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲን መተካት ይኖርበታል፡፡

{2} ሁለተኛ፣ የክልል ያልተማከለ የኢኮኖሚ እቅድ ስርአት መዘርጋት (Decentralized Planning Systems) በተማከለ ብሔራዊ የኢኮኖሚ እቅድ ሥርዓት (Centralized Planning Systems) ማስተሳሰርና ማቀናጀት ያስፈልጋል፡፡

{3} ሦስተኛ፣ በክልሎች ውስጥ የኃብት ክፍፍል ስርጭት አመዳደብ (Inter-Regional Allocation of Resources) ብሔራዊ ፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ተቆጣጣሪነት፣ በግልፅነት፣ ፍትሃዊና ሚዛናዊ ማድረግ፡፡

{4} አራተኛ፣ ብሔራዊና ክልላዊ የመዋለ ንዋይ /ኢንቨስመንት ፖሊሲዎች በመንደፍ፣ ትስስርና ቅንጅት እንዲኖራቸው ማድረግ፡፡

{5} አምስተኛ፣ የብሄራዊና ክልላዊ የስልጠናና እውቀት ክህሎቶች በመንደፍ አስፈላጊውን የሰው ኃይል ልማት ማጎልበት ያስፈልጋል፡፡ የትምህርት ፖሊሲውን ከዚህ አኮያ መቅረፅ፣ ትውልድ ገዳይ እውቀት አምካኝ የሆነውን የወያኔ የትምህርት ፖሊሲ በአፋጣኝ መቀየር፡፡

{6} ስድስተኛ አህጉራዊ፣ ብሔራዊና ክልላዊ የውሃ ተፋስስ ልማትና የግብርና እርሻ መስኖ ልማት እቅድ መንደፍ አስፈላጊ ነው፡፡

{7} ሰባተኛ፣ የኮሜርሻል ገበያ ተኮር የግብርና ምርቶች (ቡና፣ ሠሊጥ፣ የቅባት እህሎች፣ ጫት፣ ቅመማ ቅመም ወዘተ) አምራች ለሆኑ ክልሎች አስፈላጊውን የብሔራዊ መሠረተ-ልማቶች ግንባታ የመንገድ፣ የባቡር መሠመርና የዓየር ትራንስፖርት አገልግሎቶች በቅድሚያ መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡ የኮሜርሻል ገበያ ተኮር የግብርና ምርቶች አምራች አካባቢዎች በማድረግና ምርቶቹን ወደ ወደቦችና ኤርፖርቶች በማጎጎዝ፣ በዓለም አቀፍ የውጭ ንግድ በመሸጥ  ለሃገሪቱ የውጭ ምንዛሪ (ዶላር፣ ዩሮ፣ ፓውንድ) ገቢ ማግኘት የህልውና ጥያቄ ነው፡፡ ለሃገሪቱ ኢኮኖሚ ዘለቄታዊና ቀጣይነት የውጭ ምንዛሪ ገቢን አስፈላጊ ለሆኑ የምርት መገልገያ እቃዎች የካፒታል ጉድስ (ማሽነሪዎች፣ ፋብሪካዎች፣ ትራክተሮች፣ ነዳጅ፣ ማዳበሪ ወዘተ)ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት ብሄራዊ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ መገንባት አማራጭ የለውም፡፡ ስለሆነም ኢትዮጵያ ብሔራዊ ፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር በማቆቆም  ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ የኢኮኖሚ እቅድ በጋራ መንደፍ አስፈላጊ ነው፡፡

በመንግሥት ውስጥ መንግሥት!!! (A State With In a State)

አንድ አገር ብሄራዊ ኢኮኖሚዋን ለመገንባት መሠረተ ልማቶን በእቅድ ለመገንባት የውጭ ምንዛሪ የሚስገኙ የግብርና ምርቶችና የማእድን ዘርፎች የሚወጡበት አካባቢ በቅድሚያ መንገዶች፣ የባቡር መስመሮች፣ ኤርፖርቶች ፣ ሃድሮፓወር ኤሌትሪክ ኃይል ማሰራጫ፣ ወዘተ ማስፋፋት አለባት፡፡ በዚህም መሰረት የኦሮሚያ፣ የአማራና የደቡብ ክልሎች የቡና፣ ሠሊጥ፣ የቦለቄ፣ የአበባ፣ የጫት፣ የወርቅ ወዘተ ምርቶች ወደ ውጭ በመላክ ሦስት አራተኛውን የሃገሪቱን የውጭ መንዛሪ ስለሚያስገኙ ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል ነበር ይላሉ የምጣኔ ኃብት ጠበብቶች፡፡ የወያኔ መሠረተ ልማት በጠባብ ብሄርተኛነትና በአድሎ ላይ የተመሰረተ ምንም ዓይነት የውጭ ምንዛሪ አስተዋፅዖ በማያደርጉ ከልሎች ላይ ኢንቨስት በማድረግ ለምሳሌ ወደ ትግራይ የሚምዘገዘገው የኢሌትሪክ ባቡር ምን ምርቶች ይዞ እንደሚመላለስ መልስ ይሠጥበት፣ የተከዜ ሃይድሮፓወር ኤሎትሪክ ኃይል ማመንጫ 360 ሜጋዋት ያመነጫል ተብሎ 75ሜጋዋት እንኮ ማመንጨት ያለመቻሉ በጥናት ላይ ያልተመሠረተ መሆንና በሃገሪቱ የገሪማ ሜይዴይ የመስኖ ልማት ያለ ጥናት በመሠራቱ ከ4 ወደ 10 ቢሊዮን ብር ኢንቨስትመን ወጪ መሆኑ ወዘተ ሃገሪቱን ለውጭ ዕዳ ዳርጎል፣ በዚህም ምክንያት በክልሎች ያልተመጣጠነ እድገት በመፍጠር ላይ ይገኛል፡፡ ወያኔ የሃገሪቱ ብሄራዊ ኢኮኖሚ በክልላዊ ኢኮኖሚ በመተካቱ በመንግስት ውስጥ ስውር መንግስት በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ የሃገሪቱ ብድርና የዕዳ ጫና የተከሰተው በዚህ ምክንያት በመሆኑ ሊታረም ይገባል፡፡ በተመሳሳይ በክልላዊ ዘውግ ተኮር ፍቅር የተነሳ አንዳንድ ክልሎች የግብርና ምርቶች(ቡና፣ ሠሊጥ፣ የቅባት እህሎች፣ ጫት፣ ቅመማ ቅመም፣ የቁም እንሰሳት፣ የወርቅ ምርት  ወዘተ) ወደ ጎረቤት ሃገሮች በመላክ የውጭ ምንዛሪ ያግበሰብሳሉ ብሎም ገንዘቡን ወደ ባህር ማዶ ሀገራት ያሸሻሉ፡፡ የህወሃት /ኤህአዴግ የፌዴራልና ክልላዊ መንግስታት የፖለቲካ ካድሬዎችና የጦር አበጋዞች ሓብት ማግበስበስ ሲያፋጥን የክልሉን ህዝብና የብሄራዊ ኢኮኖሜችንን እድገት ያቀጨጨ መሆኑን መገንዘብ ይኖርብናል፡፡ በሃገሪቱ የሠፈነው የፌዴራልና የክልል መንግስታት የሞኖፖሊ ኢንፓየር የግሉ ዘርፍ ባለኃብት ስራን በመንጠቅ ኢኮኖሚውን በእዝ ኢኮኖሚ ጠርንፎ የያዘና የመሬት ኃብትን፣ የባንክ ፋይናንሻል ዘርፍና የኢፈርትና ሜቴክ ልዮ ልዮ ንግዶች  በመንግስት ስም የህወሃት /ኢህአዴግ ሹማምንቶች ንብረት በማድረግ ሰፊውን የኢትዩጵያ ህዝብ ጭሰኛ ያደረገ የክልሎች የትግራይና ሶማሌ የጦር አበጋዞች ስርአተ አገዛዝ ነው የሰፈነው፡፡ በመቀጠል የህወሓት ስርአተ አገዛዝ ዘመን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድና አፈፃፀም  ኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን በአጭሩ እንቃኛለን፡፡

የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድና አፈፃፀም፣ ከ2008-2012 ዓ/ም

ሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድና አፈፃፀም ውድቅ ሆኖል ስለዚህ  ብሔራዊ ፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር  ተቆቁሞ አዲስ የተቀናጀ ብሔራዊና ክልላዊ እቅድ ማውጣት ይኖርበታል፡፡

የሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድን ያዘጋጁት ተጠያቂ የሆኑ ሚኒስትሮች ኮሚቴ አባላት፡-

{1} የማክሮ ኢኮኖሚ ጉዳዩች፣ የዕቃዎችና አገልግሎቶች የውጭ ንግድ ኮሚቴ፤ሱፊያን አህመድ፣ ንዋይ ገብረአብ፣ ተክለወልድ አጥናፉ

{2} ግብርናና የገጠር ትራንስፎርሜሽን  እቅድ ኮሚቴ፤ በረከት ስምኦን፣ ካሱ ኢላላ፣ ተፈራ ደርበው፣ ካሊድ ቦምቦ

{3} የኢንዱስትሪ ልማትና የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ ኮሚቴ፤ አርከበ እቁባይ፣ ዓባይ ፀሐዬ፣ አህመድ አብተው፤

{4} የሰው ኃብት ካፒታል ማሳደግና የቴክኖሎጅ አቅም ግንባታ ኮሚቴ፤ ደመቀ መኮንን፣ አስቴር ማሞ፣ አዲሱ ለገሰ፣ ሽፈራው ሽጉጤ

{5} ዘመናዊ የከተማ ልማትና የኮንስትራክሽን ዘርፍ አቅም ኮሚቴ፤ ዓባይ ፀሐዬ፣ መኩሪያ ኃይሌ፣ ደሪባ ኩማ

{6} ወሳኝ የመሠረተ ልማት ግንባታዎችና የማስፈፀም አቅም ግንባታ ኮሚቴ፤ ደብረጽዩን ገብረሚካኤል፣ ወርቅነህ ገበየሁ፣አለማየሁ ተገኑ

{7} ልማታዊ መልካም አስተዳደር፣ሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነት ኮሚቴ፤ አስቴር ማሞ፣ መኩሪያ ኃይሌ፣ ከበደ ጫኔ፣ ጌታቸው አምባዬ

{8} ዴሞክራሲን ማስፈን፣ብሔራዊ መግባባት መፍጠርና ሚዲያና ኮምኒኬሽን ኮሚቴ፤ አባዱላ ገመዳ፣ ካሳ ተክለብርሃን፣ ሬድዋን ሁሴን

በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤትና ብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን፤ በእነዚህ ኮሚቴዋች የታቀደው ሃገራዊ እቅድ ከ2008-2012 ዓ/ም ብሔራዊ ሰነድ እንደሆንና በዚህም መሠረት የሁለተኛው  የኢትዩጵያ እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መነሻዎች፣ ግቦችና ዋና ዋና አቅጣጫዎች ላይ ዕቅዱን ከአፈፅፀሙ ጋር በማነፃፀር የሹማምንቱ ተጠያቂነት ለህዝብ መቅረብ ይገባዋል እንላለን፡፡ በእቅዱ አፈፃፀም የነበሩ ስኬቶችንና ተግዳሮቶችን ነቅሶ በማሳየት የተንሸዋረረና የተለጠጠ ያልተሳካ ዕቅድን እንደተሳካ አድርጎ በመገምገም የታዩ የሙስና ወንጀሎችና፣ በዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የተጋለጡ የመንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶች  አገሪቱን ኢኮኖሚ አዘቅት በመክተታቸው፣ እቅዱን ያፀደቁ የኮሚቴ አባላቶች የፕሮጀክቶች ክትትልና ቁጥጥርና ግልፅ አሠራር መዘርጋት ባለመቻላቸው አፈፃፀሙ ከጅምሩ ጂቲፒ ቱ እቅድ ወድቆል፡፡ የሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ  ተግባራዊ ያልሆኑ ስራቸው  ሳይሰራ ብዙ ገንዘብ የፈሰሰባቸውና፣ ዝቅተኛ የፕሮጀክቶች አፈጻጸም የተከናወነባቸው ሙሰኛ ሹማምንቶች በተጠያቂነት ለፍርድ መቅረብ ግድ ይላቸዋል፡፡ በኢትዮጵያ በመንግሥት ውስጥ ሥውር መንግሥት አለ፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግስትን መሥርቶ፣  ብሄራዊ ኢኮኖሚውን በክልላዊ ጠባብነት ስሜት ያልተመጣጠነ ክልላዊ የኢኮኖሚ ዕድገት አስፍኖል፡፡ የትግራይ ክልላዊ መንግሥት  ኢፈርት/ሜቴክ የማፍያ ስውር ኢኮኖሚ ዘርግቶ፣ ህቡዕ የወያኔ ሥርወ መንግሥት ገንብቶል፡፡ ወያኔ እድሜ ልኩን በኃይል ሃገራችንን መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ በሰለጠነ የዲጅታል ቴክኖሎጅ ዘመን በጦር መሣሪያ አስፈራርቶ ለመግዛት ይከጅላል፡፡ በዚህ ግሎባላይዜሽን ዘመን ዓለማችን ወደ አንድ መንደርነት በተቀየረችበት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ በይነ መረብ መረጃ የዘመነበት ዘመን በድብቅ ህዝብ እየገደለ፣ እያሰረ፣ እየገረፈና እያፈናቀለ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ወያኔ የሥልጣን መንበሩን ለማቆየት የሃገሪቱን መከላከያ ሠራዊት ኃብትና ንብረት የዓየር ኃይል የጦር ተዋጊ አውሮፕላኖችን ከደብረ ዘይት ነቅሎ፣ ውቅሮ ተራሮች ቦርቡሮ ከቶል፡፡ የኢትዮጵያ ታንከኛ ብርጌድ ወደ ትግራይ ዘወራቸው፣ ወያኔ ወታደራዊ ትዕይንት (Military parade) በማሳየት በስልጣን ጥማት ተውጦል፣ ዴሞክራሲ አፍኖ በኃይል ለመግዛት ቆምጦል፡፡  ወያኔ በጦር ኃይል በመተማመን የትግራይን ህዝብ ከኤርትራ፣ አፋር፣ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ሱማሌ፣ ወዘተ ወገኖቹ ጋር ጠላት አፍርቶለታል፡፡ በትግራይ በተደጋጋሚ እያሳየን  በመንግሥት ውስጥ ሥውር መንግሥት  መገንባቱን ተያይዞታል፡፡ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድና አፈፃፀም አራምባና ቆቦ ሆኖል፡፡ በመጨረሻም ወያኔ መንግሥት ያፈረሰውን፣ የኢትዮጵያ ፕላን ኮሚሽን  መሥሪያ ቤት  ዳግም ማቆቆም ለተገቢው ሥራ እውቀትና ክህሎት ያላቸው ምሁራን ዳግም መሰባሰብ ያስፈልጋል፡፡ ጥቂት የማይባሉ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ተጠሪዎቻቸው ዓመታዊ እቅድ ከአፈጻጸም ጋር ሲተያይ ሰፊ ልዩነት እንደሚስተዋል ይታያል፡፡…ይህ መራራቅ እንዴት ሊመጣ ቻለ? በሃገር ላይስ ምን ችግር ያስከትላል? መፍትሄውስ ምን ሊሆን ይችላል? በሚለው ላይ ምሁራን የአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህራን የተለያዩ ሃሳቦችን በማቅረብ ይከራከራሉ፡፡››

ፕሮፌሰር ዶክተር አለማየሁ ገዳበአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ክፍለ ትምህርት መምህር ‹‹የእቅድ አለመሳካት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ችግር ብቻ ሳይሆን የመንግሥትም ነው ይሉና፣ ለአብነትም መንግሥት ከመጀመሪያው  የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ውስጥ ዋና ዋና ከሚባሉት እቅዶቹ ያሳካው 25 በመቶውን ብቻ መሆኑን ባካሄዱት ጥናት ማረጋገጣቸውን ይጠቁማሉ፡፡ በእቅድና አፈፃፀም መካከል የተራራቀ ክፍተት ለምን ተፈጠረ በሚል ጥናት ማካሄዳቸውን በማሳየት በወሰዶቸው ሁለት መስሪያ ቤቶች እቅድና አፈፃፀም የተራራቀበት ምክንያቱ በባለሙያና በተሞላ የሰው ኃይል አለመታቀዱ ነው ይላሉ፡፡ የእቅድና ቅንብር፣ የቅንጅትና የመናበብ ጉድለት እንደሚስተዋል ይጠቅሱና ተገቢውን እቅድ በማውጣት በኩል ችሎታ፣ አቅምም ሆነ እውቀት አለመኖሩን በጥናታቸው ማረጋገጣቸውን ይጠቁማሉ፡፡…. የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ፣ ላይ በአምስት አመት  መጨረሻና በዓመት ውስጥ ምን መሠራት እንዳለበት መዘርዘሩን፣ በእቅድ ዘመኑ መጨረሻ ግን ግቡን ሲመታ እንደማይታይ ያመለክታሉ፡፡ እቅዱን ያላሳኩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችም ሆኑ ሌሎች ተጠሪ ተቆማት ተጠያቂ አለመደረጋቸውንም በችግርነት ይገልጻሉ፡፡ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ሁለት እቅድ አፈጻጻም አማራጭ መቀመጡ ማምለጫ ስልት ነው፡፡ ምክንያቱም ደግሞ ‹‹ለጥጠን ነው ያቀድነው›› የሚባል ከሆነ ተጠያቂነት አይኖርም ሲሉ ያብራራሉ፡፡ እቅድ ሲታሰብ መጀመሪያ የመሰራት እቅም መኖሩን፣ ግቡንም በአግባቡ መረዳት ተገቢ መሆኑን ያብራራሉ፡፡ የእቅድና አፈፃፀሙ ዝቅተኛ ሆኖ ሳለ አብዛኛውን ጊዜ በግልፅ ሲነገር አይስተዋልም፤በዚህ የተነሳም መጠየቅ የተገባው አካል ከተጠያቂነት ሲያመልጥ ይታያል፡፡ ተጠያቂ የሆነ አካል ባለመኖሩ ደግሞ እቅድና አፈፃፀም በተደጋጋሚ ሲለያዩ ይስተዋላል፡፡ መፍትሄው ፕላን ኮሚሽን  በመባል የተቆቆመው መስሪያ ቤት በባለሙያዎች ተደራጅቶ ሊሰራ ይገባል፤ በተለያዩ መሥሪ ቤቶችም ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ኤክስፐርቶች ማጠናከርም ያስፈልጋል፡፡ይህ ካልሆነ ግን እቅድና አፈፃፀም ይጣረሳል፡፡  ለጥጦ ማቀዱንም አስር ድስት ትዶ አንዱንም ማማሰል እንዳለመቻል ጥቆጠራል ሲሉ ያስገነዥባሉ፡፡ ለአብነትም የስኮር ፕሮጀክቶችን ይጠቅሳሉ፡፡ ፕሮጀክቶቹ በኤክስፐርቶች ታቅደው ቢሆን ኖሮ ተጠናቀው ብድር መክፈል በተቻለ ነበር፡፡ አሁን ሥራው ሳይሰራ ብድር መክፈል መጀመሩን ነውያመለከቱት፡፡ መንግሥትም ችግሮችን ለመቆቆም መበደሩን ጠቅስው፤ ይህም በአገሪቱ ላይ ከባድ የእዳ ጫና እንደሚያመጣ፣ ብድሩን ከውጭ አገር 31 በመቶ ከአረግ ውስጥም 31 በመቶ በጥቅሉ መተኑን ወደ 62 በመቶ እንዲደርስ ማድረጉን ይጠቁማል፡፡ ብድር ከ40 በመቶ ባይበዛ መልካም መሆኑንም ያስረዳሉ፡፡ ፕሮጀክቶቹ ምንም ዓይነት ጥቅም ባላመጡበት ሁኔታ በአሁኑ ወቅት መንግሥት በአማካይ እስከ አንድ ቢሊዮን ብር እዳ ይከፍላል፡፡ ጠቅላላ የውጭ ንግዱ ሥስት ቢሊን ዶላር መሆኑን ይጠቅሱና፣ ከዚህ ውስጥ አንድ ቢሊዮኑ እዳ መሆኑን ያመለክታሉ፡፡ ሂደቱ የብር ዋጋ እየወረደ እንዲመጣ፣ግሽበትም እንዲከተል ምክንያት እንደሚሆን፣ በዚህም መጀመሪ ተጎጂ ድሃው የህብረተሰብ ክፍል መሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡ በየሚኒስትር መሥሪ ቤቱ በጥሩ ኤክስፐርቶች የተዋቀረ የፕላንና የፕሮጀክት አዋጭነትን የሚያጠና ቡድን ማቆቆም ለዚህ መፍትሄ እንደሚሆን ይጠቁማሉ፡፡ ኃላፊነታቸውን ያልተወጡ አመራሮችን እና ሌሎችን ተጠያቂ ማድረግ እንደሚገባም ያመለክታሉ፡፡››

አቶ ኢብሳ ጌታሁን፣ የምጣኔ ኃብት ተመራማሪ ‹‹ እቅድ ግቡን እንዲመታ የተማረ የሰው ኃይል፣ ገንዘብ፣ አደረጃጀት መሰረታዊ ጉዳዬች ናቸው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የማይተገበሩ እቅዶችን ለጥጦ መያዥ እንደሚተይም፣ አብዛኛውን ጊዜ ተለጥጦ የሚታቀደው መንግሥታት በድጋሚ መመረጥ ከመፈለጋቸው ጋር ተያይዞ ነው፣ ይህም የህዝብን አመኔታ ለማትረፍ ከመሻት እንደሚመነጭ ገልጸዋል፡፡ የቱንም ያህል በባለሙ ቢታቀድና ገንዘብም ቢኖር እቅዱበራሱ ግብ ይመታል ብሎ ማሰብም የዋህነት ነው፤ ታቀደውን በሚገባ የሚፈጽም የሰው ሃይል ነው፡፡ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ሁለት አማራጮች ማስቀመጡ ምንም ችግር እንደማይኖረውና ከሁለት አነዱን ማሳካት ከተቻለ መልካም መሆኑን ም ይጠቁማሉ፡፡ ካለው ኃብት በታች አቅዶ ‹‹መቶ በመቶ አሳካለሁ›› ማለቱም ሂነ መስራት የማይጫለውን አቅዶ አንሶ መገኘት ፋይዳ እንደሌላቸው ያስገነዝባሉ፡፡ ሁለቱም አስራር የአገሪቱን ኢኮኖሚ  እንደሚጎዳ ይገልፃሉ፡፡ የአገሪቱን ኃብት በአግባቡ ለመጠቀም በባለሙያ አቅዶ መስራት እንደሚገባ፣ ይህም ለአገሪቱ የኢኮኖሚ ልማት የላቀ ሚና እንዳለው ያስገነዝባሉ፡፡››

ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር ብርሃኑ ደኑ፣  በአዲስ አበባ ኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር ‹‹ እቅድ ሲወጣ በርካታ ጉዳዬችን ታሳቢ ማድረግ አለበት፡፡ ከአቅም በላይ መታቀድ እንደሌለበትም ያስገነዝባሉ፡፡ እቅድና አፈፃፀም የሚለያዮት አንድም ከውች አገር የሚገቡ እቃዎች እጥረት ሲያጋጥም ነው፡፡ እነዚህ ችግሮች ከግምት ውስጥ አስገብቶ ማቀድም የተለመደ አይደለም፡፡ ፕሮጀክቶች ተሞልተው ወደሥራ መገባትና የተሸለ አፈፃፀም ማስመዝገብ ያልቻሉት በሩጫ የታቀዱ በመሆናቸው ነው፡፡ ይህም አቅምን ከግምት ውስጥ ያለማስገባትን እንደሚያመለክት ይጠቁማሉ፡፡እቅድ በባለሙያ መታቀዱና ተገቢውን ግብዓት ማሞላቱ በራሱ አፈፃፀሙን ያሳምረዋል የሚል እምነት የላቸውም፡፡ እቅዱን ስኬታማ ሊያደርገው የሚችለው ክትትልና ተጠያቂነት ነው፡፡ ለጥጦ ማቀድ የፖለቲካ ትርፍ ማግኛ ነው፡፡ የማይተገበር እቅድ መታቀድ የለበትም፡፡ በተገቢው ባለሙያ የማቀድን አስፈላጊነት ይጠቅሱና ለሙያተኛውም ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ይናገራሉ፡፡ ‹‹ ሙስና፣ እቅድ ስኬታማ እንዳይሆን ያደርጋል›› ለዚህም ተጠያቂነትን ማስፈን የግድ መሆኑን ነው ያመላከቱት፡፡  አመራሩ በዲሲፕሊንና በአስተባባሪነት መንፈስ መንቀሳቀስ እንደሚኖርበት፣ ካለፉት ስህተቶች መማርም እንደሚያስፈልግ ያስገነዝባሉ፡፡‹‹ እቅድና አፈጻጸም ያለመጣጣሙ ከቀጠለ በአገር ኢኮኖሚ ላይ ውድቀትን ያስከትላል፡፡ ይህም በህዝብ ዘንድ ተቃውሞ እንዲቀሰቀስ ያደርጋል፡፡›› በማለት የምጣኔ ኃብት ምሁራኖች ምክረ ሃሳባቸውን ለግሰዋል፡፡›› 1

{I} የአንደኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ (GTP) ከ2003 እስከ 2007 ዓ/ም ጀምሮ የተከናወነ እቅድ ሲሆን፤ የመንግስትና መንግስታዊ ልማት ዘርፍ ድርጅቶች የግንባታ ወጪ ከፍተኛውን ድርሻ እንዳለው ይታወቃል፡፡ የመንግስት የበጀት ወጪና ከበጀት ወጪ በመንግስታዊ ልማት ዘርፍ አጠቃላይ የግንባታ ወጪ ድምር 1.26 ቲሪሊየን ብር ነበር፡፡ በሌላ አገላለፅ፣ በአምስቱ አመት ውስጥ፤ የመንግስታዊ ልማት ዘርፍ የግንባታ ወጪ 41 በመቶ የአመታዊ አጠቃላይ ብሄራዊ ምርት ይሸፍናል፡፡ በአጭሩ ለመግለፅ በሚቀጥሉት አመታቶች ውስጥ፣ ከአጠቃላይ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ሁለት አምስተኛው በመንግስታዊ ዘርፍ ወጪ እንደሆነ ታውቆል፡፡ የመንግስታዊ ዘርፍ ወጪ ልዩ የሚያደርገው ነገር ቢኖር ያልተለመደ  የካፒታል ወጪ (capital expenditure) ሲሆን ከአጠቃላይ የመንግስታዊ ወጪ 56 በመቶ እሰከ 61 በመቶ ከፍ እንዳለ ይታወቃል፡፡ በሌላው የአፍሪካ ሃገራቶች የመንግስታዊ ዘርፍ ወጪ ለካፒታል ወጪ 25 በመቶ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በኢትዩጵያ የመንግስታዊ ዘርፍ ወጪ በተለይ፤ ለካፒታል ወጪ (ለመንገድ ሥራ፣ ለኤሌትሪክ ማመንጫ ግንባታ ሥራ፣ ለውኃ አቅርቦት፣ ወዘተ) በጣም ከፍተኛ ሲሆን ለካፒታል መሣሪያዎች (ማሽነሪዎችና የተግባር መገልገያ መሣሪያዎች ግዥ ይውላል፡፡ A five-year Growth and Transformation Plan (GTP) enacted in early 2011 has set the stage for an even bigger role for public sector spending in the coming years. For the five-year GTP period as a whole, the sum of budgetary government spending and off-budget spending by public enterprises is programmed to reach Birr 1.26 trillion, or an average of 41 percent of GDP per year over five years (Table 1.3). In short, the equivalent of two-fifths of total economic activity will be linked to public sector activity in the coming years. One of the most distinctive features of the public spending envisaged above is the unusually high level of capital expenditure, which will see its share rising from 56 to 61 percent of total government expenditure. 2 We find that Ethiopia now has the highest capital expenditure share in government spending among African countries, where the normal capital expenditure share in government spending is near 25 percent (Table 1.4). This means that much more spending is being funneled to capital projects (roads, power plants, water systems, etc.) and to capital equipment (machinery and equipment imports), rather than to current expenditure items such as wages, salaries, and operational and maintenance costs.

1 Data for government expenditure based on MOFED budget data. Credit to government and credit to public sector figures from the IMF Staff Report of November 2010 (www.imf.org), with FY 2010/11 representing estimates.

2 Beyond the high concentration on capital spending, two equally notable elements of the GTP public sector spending plans are its large borrowing requirements and its substantial foreign currency demands, issues that are addressed later in Chapter 7.4 Ethiopia Macroeconomic Handbook 2011-12

{II} የሁለተኛ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ከ2008 እስከ 2012 ዓ/ም የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ፋይናንስ ዘርፍ፣{በአጠቃላይ ለሁለተኛ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ወይም ማስፈፃሚ በአምስት አመት ፕሮግራም ውስጥ 2.4 ትሪሊዩን ብር ይጠይቃል፡፡} {2.4 ትሪሊዩን ብር ወጪ ለመሸፈን በ2012 ዓ/ም መጨረሻ ላይ የሚኖረው የአገር ውስጥ የገቢ አቅም 2.03 ትሪሊዩን ብር ነው፡፡ በመሆኑም የበጀት ጉድለቱ ዕርዳታን ጨምሮ 341.2 ቢሊዩን ብር ይሆናል የሚል ታሳቢ በረቂቅ እቅዱ ተይዞል፡፡} {}ዕቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ የሚፈለገው የውጭ ምንዛሪ 119.5 ቢሊዩን ዶላር እንደሚሆን የተገመተ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ የኢንዱስትሪው ዘርፍ 30 በመቶ ማለትም (35.85 ቢሊዩን ዶላር)፣ የአገልግሎት ዘርፍ ደግሞ 41.7 በመቶ ማለትም (49.8315 ቢሊዩን ዶላር) ለሌሎች ዘርፎች ቀሪው (33.8185 ቢሊዩን ዶላር) እንደሆነ ይገመታል፡፡ የመንግስታዊ ዘርፍ ኢንቨስትመንት ወጪ ዕቅድ ለሚቀጥሉት አምስት አመታት መሠረት አስፈላጊ፣ የካፒታል ወጪ ሃገሪቱን ለማሳደግ ያስፈልጋል፤  ከሚያካትታቸው ውስጥ የተፈጥሮ  መሰረተ-ልማት ግንባታ ለሰው ኃይል፣ለእቃዎችና ለአገልግሎት ዘርፍ መጎጎዣነትና ለገበያ ኢኮኖሚ የሚያስፈልጉ መንገዶች፣ባቡር መስመር መዘርጋት፣የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጨት፣ኤሌትሪክ መስመርና ኤሌትሪክ ቆት ማከፋፈያ መዘርጋት፣ የውኃና የፍሳሽ አገልግሎት ወዘተ የመሳሰሉት ይካተታሉ፡፡ የአንደኛውና ሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድና አፈፃፀም በማነፃፀር ቀሪዎቹን ሁለት አመታት ታሳቢ በማድረግ ነው፡፡

የሁለተኛ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ከ2008 እስከ 2012 ዓ/ም ተግዳሮቶች፣ በተከሰተው የህዝብ አልገዛም ባይነትና ህዝባዊ ተጋድሎ  እቅዱ ሊጨናገፍ ችሎል፡፡ የሁለተኛ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ከሚጠቀሱት ዋና ዋና ችግሮች መኃል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፤

{1} ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት (Foreign Direct Investment Inflows) ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ለሃገሪቱን የኢኮኖሚ ዘርፍ የሚያስከትለው ጉዳት በተመለከተ በሃገሪቱ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት ይቀንሳል፡፡ ሰላም በሌለበት ሃገር የባህር ማዶ ኢንቨስተሮችን አይስብም፣ እንዲያውም ያፈሰሱትን ምዋለንዋይ ሸጠው ለመውጣት  ይገደዳሉ፡፡ በሃገራችን የኢኮኖሚ ነፃነት ከሚገለፅባቸው ዋና ዋና መርሆዎች ውስጥ አንዱንም አታሞላ፡፡ አንደኛው የህግ የበላይነት፣የፍትህ ሥርዓት መከበር፣የንብረት ባለቤትነት መብት መከበር፣ የመንግሥት ሙስናን ለመዋጋት ያለው አቅም የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡ የሃገር ውስጥና የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች የህግ ሉዓላዊነት ያለበት ሃገር መዋለ-ንዋያቸውን አፍሰው በነፃነት ኃብት ማፍራት ይሻሉ፡፡ ህግና ፍትህ ባለበት ሃገር ቀጥተኛ የውጪ ኢንቨስትመንት ፍስት ከአመት አመት እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ በኢትዩጵያ ህግ የለም፣ ፍትህና ርትህ አይሠራም፣ የዜጎች ንብረት የማፍራት መብት የለም፡፡ በኢትዩጵያ የህወሓት መንግሥት በሞኖፖል የተያዙ ንብረቶችና ኃብቶች መካከል፡-በሃገሪቱ የመሬት ኃብት የህወሓት መንግሥት በመሆኑ የግብርና፣የማኑፋክቸሪንግና አገልግሎት ዘርፍ ክፍለ ኢኮኖሚ እድገቱ የቀጨጨ ለመሆን በቅቶል፡፡ ህዝባችን የመሬት ኃብት ንብረት የመያዝ መብትና ነፃነት ስለሌለው በርሃብ አለንጋ ይሰቃያል፡፡ ህዝቡን መመገብ የማይችል መንግሥት ህዝቡን መግዛት አይችልም፡፡ በሃገሪቱ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት በ2008እኤአ (109 ሚሊዮን ዶላር)፣በ2009እኤአ (211 ሚሊዮን ዶላር)፣በ2010እኤአ (288 ሚሊዮን ዶላር)፣በ2011እኤአ (627 ሚሊዮን ዶላር)፣በ2012እኤአ (279 ሚሊዮን ዶላር)፣በ2013እኤአ (1281 ቢሊዮን ዶላር)፣በ2014እኤአ (2132 ቢሊዮን ዶላር)፣በ2015እኤአ (2168 ቢሊዮን ዶላር)፣2016እኤአ (አልተገለጸም)፣ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት ነበር፡፡‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንት ቀጥተኛ የውጪ ኢንቨስትመንት ፍስት በጣም ይቀንሳል፡፡››

{2} ካፒታል ኩብለላ፣ ከሃገሪቱ በህገወጥ መንገድ የሚወጣ የውጪ ምንዛሪ ካፒታል ኩብለላ Capital flight ከ2 እስከ 3 ቢሊዮን ዶላር በአመት እንደሚደርስ የአፍሪካው ልጅ  ታቡ ኢንቤኪ አጋልጠዋል፡፡ በአጠቃላይ በህወኃት/ኢህአዲግ መንግስት የልማት ድርጅቶች ኢንተርፕራይዝ ዕዳ 27 ቢሊዩን ዶላር በላይ ብድር እንዳለባቸው ዝርዝር ጥናቱ ያሳያል፣ ከዚህ ውስጥ 7 ቢሊዮን ዶላር እዳቸውን ከፍለዋል ብንል እንኮ ከ15 አስከ 20 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ እንዳለባቸው፣ መንግስት ከ30 እስከ 35 ቢሊዮን ዶላር ጋር ሲደመር ሃገሪቱ በትንሹ 50 ቢሊዮን ዶላር እዳ አለባት እንላለን፡፡የልማት ድርጅቶች ኢንተርፕራይዝ ኦዲት አለመደረጋቸው ዋንኛ ምክንያት ሌብነትና ሙስኝነት መሆኑን አይ ኤፍ ኤም የኦዲት ሪፖርት በየአመቱ እንደማያቀርቡና መንግሥት ሪፖርት እንዲየቀርቡ እንዲያደርግ ምክረ  ሃሳባቸውን አካፍለዋል፡፡

{3} ብድርና የዕዳ ጫና፣ አይ ኤም ኤፍ በኢትዮጵያ የሚገኙ ‹የመንግሥታዊ ልማት ድርጅቶች› ያለባቸውን እዳና የዕዳ ጫና ምን ያህል እንደሆነ ከመግለፅ ታቅቦል፡፡ በአጠቃላይ መንግሥትና ‹የመንግሥታዊ ልማት ድርጅቶች› ከባህር ማዶ ብድር እንዳይወስዱና ሃገሪቱ ከመካከለኛ ወደ ከፍተኛ Ethiopia were changed from moderate to “high risk of debt distress.”  የኢትዮጵያ የዕዳ መሸከም ጫናና ወለድ የመክፈል አቅም አስጊ ደረጃ ላይ ደርሶል መድረሱንና የዕዳ ጫናው ለከፍተኛ አደጋና ስጋት ሃገሪቱን ይዳርጋታል፣ ወደፊት እዳዋንም ለመክፈልም ከፍተኛ ዋጋ ይስከፍላታል ሪፖርቱ ብሎል፡፡ ከተለያዩ መረጃዎች በጥናት በተገኘው መሠረት ግን ‹የመንግሥታዊ ልማት ድርጅቶች› ያለባቸውን እዳ {6.1}የኢትዬጵያ አየር መንገድ በአጠቃላይ ከ 2008እኤአ እስከ 2014እኤአ የኢህአዲግ መንግስትና የኢትዬጵያ አየር መንገድ ድርጅት 5,608,000, 000 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር፣ {6.2}ኢትዬ ቴሌኮም፣በአጠቃላይ፣ከ2006 እኤአ እስከ 2013እኤአ የቻይና መንግስት ከቻይና የቴሌኮም ካንፓኒ፤ዜድቲኢ ZTE Corporationና ሀዊ Huawei Technologies Co. Ltd. የቻይና ኮምኒስት ፓርቲ ንብረት የሆኑት ድርጅቶች ጋር የኢትዬጵያ ቴሌኮምኒኬሽን ኮርፖሬሽን (አሁን ኢትዬቴሌኮም) የ4.8 ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር (72,142,100,000 ቢሊዬን ብር) ብድር በመፈራረም የእዳው ክፍያም ከኢትዩጵያ የሠሊጥ ምርት ወደ ቻይና በመላክ እንደሚወራረድ ይታወቃል፡፡ {6.3} የኢትዬጵያ መብራት ኃይል ባለሥልጣን(5 ቢሊዩን 490 ሚሊዬን ዶላር ብድር እንዳለበት ጥናቱ ያሳያል፡፡) {6.4} የኢትዮጵያ ስ£ር  ኮርፖሬሽን አጠቃላይ የግንባታ ስራ ወጭ 100 ቢሊዩን ብር (5.5 ቢሊዩን ዩኤስ ዶለር) እንደሚሆን ሲገመት ማሽነሪዎች ለመግዛት ግማሹ በውጭ ምንዛሪ ገንዘብ ይሻል፡፡የኢትዮጵያ ስኮር ኮርፖሬሽን 500 ሚሊዩን ዩኤስ ዶለር ብድር ከቻይና ልማታ ባንክ (China Development Bank Corp.)  ጋር ተፈራረመ፡፡ {6.5} የኢትዩጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ያለበት በአጠቃላይ ብድር 5 ቢሊዩን 4 ሚሊዩን ዶላር ብድር ሥራው ተጠናቆል፡፡ “In 2012 China Civil Engineering Construction Corp.and China Railway Group Ltd. are working on sections of the 656 kilometer trade route connecting Addis Ababa to Djibouti at a cost of over 1 billion USD each.’’…“Until 2015 Ethiopia is building 4,744 kilometers of electrified railway lines at a cost of 5.9 billion USD 110.8 billion birr/ to satisfy transport demands in the country.” {6.6} የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት፣ ግንባታ በአራት አቅጣጫዎች እየተገነባ ሲሆን፤በአጠቃላይ 34 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ነው፡፡ ለግንባታው ወጭ 475 ሚሊዩን ዶላር ሲሆን፣ከዚህ ውስጥ 85 በመቶ ከቻይና ኤግዚም ባንክ በብድር የተገኘ ሲሆን 15 በመቶው በኢትዩጵያ መንግስት የሚሸፈን ነው፡፡ በዚህም የዕዳ ጫና የተነሳ በ2010ዓ/ም ሁሉም የመንግሥት ተቆማት በተለይም እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድና ኢትዮቴሎኮም የመሳሰሉት የልማት ድርጅቶች የአጭር ጊዜ ብድሮችን ከመበደር እንዲቆጠቡ ማስጠንቀቂያ ተስጥቶቸዋል፡፡ በዚህም የአገሪቱ የብድር ዕዳ ጫና ቀስ በቀስ እያደገ በመምጣቱ ሳቢያ፣ እንዲሁም አበዳሪዎችን እምነትም ላለማጣት ጭምር መንግሥት በአጭር ጊዜ የሚከፈሉ ብድሮችን በማቆረጥ በብድር ዕዳ ክፍያ ላይ ማተኮሩን መርጦል፡፡

{4} የባህር ማዶ ልማት ትብብር (ODA፡ Official Development Assistance) ከ1991 እኤአ እስከ 2012 እኤአ ለህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት አርባ ቢሊዩን ዶላር የልማት እርዳታ ሰጥተዋል፡፡ በአለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ በአማካኝ በአመት ሁለት ቢሊዩን ዶላር እርዳታ ሃገሪቱ እንዳገኘች ያስረዳል፡፡ የባህር ማዶ ልማት ትብብር እርዳታ ከ2008 እስከ 2015እኤአ ያለውን ብቻ ብናይ ከ3 እስከ4 ቢሊዩን ዶላር ሃገራችን የልማት እርዳታ አግጥታለች፡፡ በኦዲኤ ዋና ዋናዎቹ እርዳታ አድራጊ መንግስቶችና ተቆማት አሜሪካ መንግሥት፣ የእንግሊዝ መንግሥት፣ የአውሮፓ ህብረት ኢንስቲቲዉሽኖች፣ ኢንተርናሽናል ዲቨሎፕመንት አሲስታንስና ግሎባል ፈንድ ናቸው፡፡  የህወሓት/ ኢህአዴግ ፋሽስታዊ መንግሥት ለሦስተኛ ጊዜ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ› እንዲያነሳ ጫና እንዲደረግበት የዲያስፖራው የትግል እንቅስቃሴ በነዚህ አገሮችና ድርጅቶች ላይ ማነጣጠር ይኖርበታል፡፡ ወያኔ የተነቃነቀ በትረ ሥልጣኑን ዴሞክራሲን በማፈን፣ ስብዓዊ መብቶችን በማፈን፣ ህገ-መንግስቱን በመጣስ የኢትዮጵያ ህዝብን አፍኖ በመግዛት ላይ መሆኑን በሠላማዊ ሠልፍ መግለፅ አስፈላጊ ነው፡፡ የህወሓት መንግሥትን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ› የወያኔ አንባገነን ስርዓት መገለጫ በመሆኑ የባህር ማዶ ልማት ትብብር አጋር አገራቶች  ድጋፍ ይቀንሳል ብሎም ይቆማል፡፡

{5} በኢትዮጵያ ከውጭ የተላከ ገንዘብ/ የውጭ ሐዋላ መቀነስ፣  ከ2000 እስከ 2015እኤአ በ2000 እኤአ 53 ሚሊዩን ዶለር  የነበረው እያደገ መሄዱን  የብሄራዊ ባንክ ገዥ ይፋ አድርረው ነበር፡፡ በግምት አንድ ሚሊዩን ከሚሆኑት ባህር ማዶ ሃገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሰደተኛች በ2012 እኤአ 2.4 ቢሊዩን ዶለር ከውጭ ሐዋላ ወደ ሀገር ውስጥ እንደገባ የብሄራዊ ባንክ ገልፆል፡፡ በዚህም  መሠረት ከባህር ማዶ ከሚኖሩ ኢትዬጵያውያን ወደ ሃገር ውስጥ የተላከ ገንዘብ የዓለም ባንክ ባወጣው መረጃ፣ ከሠንጠረዡ ላይ መመልከት እንደሚቻለው ዝቅተኛ ከውጭ ሐዋላ የተገኘው ገቢ በ2001 እኤአ 18 ሚሊዩን ዶለር የነበረ ሲሆን ከፍተኛ 3 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር በ2013እኤአ እድረት እንዳሳየ መረዳት ይቻላል፡፡ እንዲሁም በ2015 እኤአ 4 ቢሊዩን ዶላር ወደ ሃገር ቤት ገንዘብ ልከዋል፡፡ በዚህም መሠረት በውጭ የሚኖሩ ኢትዬጵያውያን ወገናቸውን በመርዳትና በማስተዳደር የሲሶ መንግስትነት ድርሻ በመወጣት ላይ ይገኛሉ ሰለዚህም በሀገራቸው ጉዳይ ከማንም በላይ ሊያገባቸውና ድምፃቸውም ሊሰማ ይገባቸዋል፡፡

የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!!!የአየር ኃይል አብራሪዎች የሆኑት መቶ አለቃ ኃይሉ ገብሬ፣ ማስረሻ ሰጤ፣ ዳንኤል ግርማ፣ አንተነህ ታደሰ እንዲሁም አበበ ወንድም አገኝ፣ ፍቅረማርያም አስማማው፣ የኦነግ፣ ግንቦት ሰባት፣ የኦብነግ እና የአረና የፖለቲከኛ እስረኞች ይፈቱ፡፡

 

ያለ ኢኮኖሚ ነፃነት የፖለቲካ ነፃ ነት የለም!!!

የሙስናው ቀይ መሥመር ተጣሰ፣ ህግ የለም ፍትህ የለም!!

የህግ ልዕልና በኢትዮጵያ ይስፈን!!!

የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!!!

‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ››

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.