ከ70 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወገኖች ያለቁበት የባድመ ከተማ ባድማ ሆነች! (ጌታቸው ሺፈራው)

~ ትህነግና ሻዕቢያ እስኪጠግቡ ድረስ ኢትዮጵያን ዘረፉ፣ ኢትዮጵያውያንን ገረፉ። ጥጋብ ስትመጣ ኢትዮጵያን እየቦጨቁ መነካከስ ጀመሩ።

~ ኢትዮጵያውያን የባድመ ጦርነትን ያህል የተሞኙበት ጊዜ ያለ አይመስለኝም። ሁለቱ ጥጋበኞች ኢትዮጵያውያንን ያሻቸውን ካደረጉ በኋላ ሲጣሉ ትህነግ/ህወሓት ኢትዮጵያውያንን በስስ ጎናቸው ገባ። ዳር ድንበር ተደፈረ ብሎ ለፈፈ። ዳርድንበር ማስጠበቅ የለመደ ሕዝብ ጠላቱ ትህነግን አምኖ ወደ ጠላት ሰፈር ጎረፈ! ሻዕቢያና ትህነግ ወደሚባሉ ሁለት ጅቦች ቀጠና!

~ ዳር ድንበር ተደፈረ ብሎ የለፈፈው ትህነግ/ህወሓት ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር ሆኖ ኢትዮጵያን ሊበትን እንደነበር ተረሳ። ገንጣይ፣ አስገንጣይ እንደነበር ተዘነጋ። ኢትዮጵያውያን በስስ ጎናቸው ዳር ድንበር ተደፈረ ብለው ዘመቱ። ድሃው ገበሬ ከሻዕቢያና ትህነግ የተረፈውን ሀብቱን ለጦርነቱ አበረከተ። ከትህነግና ሻዕቢያ ጭፍጨፈ የተረፉ ወጣቶች ወደ ጦርነት ተመሙ። ዳርድንበር እያስጠበቁ እያለ ጊዜአሸንፏቸው የወደቁና ጠላት ተብለው ከጦር ሰራዊቱ የተባረሩ የድሮው ጦር አባላት ቁስላቸውን ረስተው ከትህነግ አዛዦች ስር ሆነው ህይወታቸውን ሰጡ።

~ ሻዕቢያና ትህነግ ከጋምቤላ እስከ ኦጋዴን፣ ከወልቃይት እስከ ቦረና ያለውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ተባብረው እንዳልዘረፉ፣ ይህን በጋራ የዘረፉት ሕዝብ ባድመ የሚባል ድነጋያማ ቦታ “የእኔ ነው የእኔ ነው” ብለው አጫረሱት!

~ ያ ሁሉ ሕዝብ ካለቀ በኋላ፣ ያ ሁሉ ንብረት ከወደመ በኋላ ትህነግ ህዝብን በቀሰቀሰበት ህብረ ዜማ ስልጣኑን አጠናከረ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆ ብሎ በወጋው ሻዕቢያ ስም በርካታ የአማራ፣ ኦሮሞ፣ የጉራጌ፣ …ወጣቶች እስር ቤት ገቡ። ሻዕቢያን የወጉ ወጣቶች ከሻዕቢያ ጋር ተባብረው፣ ከኤርትራ ሰልጥነው ኢትዮጵያን ሊወጉ ነው ተብለው ሁለት አስርት አመታትን የስቃይ ጥግ አዩ

~ “ባድመ የኢትዮጵያ ነው” እያለ ወጣት ያስጨረሰው ትህነግ ጉምቱ ፖለቲከኞች ከጦርነቱም በኋለ “በኤርትራ አትምጡብን፣ ስለ አሰብ አትጠይቁ” እያሉ ህዝብን ዘለፉ! ኢትዮጵያውያንን የሚፈልጉት ሲጣሉ ብቻ ነው። ሲጨንቃቸው ብቻ ነው።

~ ትግራይና ኤርትራ ድንበር ስላለው ባድመ ስንጨነቅ እነሱ የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን፣ የአርሶ አደሩን መሬት ለሳውዲና ለራሳቸው ተከፋፈሉት። የዋህ ሕዝብ ስለ ባድመ እያሰበ ባድማውን ተነጠቀ

~ ዳር ድንበርን ማስጠበቅ የለመደ ህዝብ፣ ሉዓለዊነትን ማስከበር ግዴታው የሆነን ሕዝብ በስስ ጎኑ ገብተው ልጁን ካስገደሉ በኋላ፣ ስለ ሞተው ልጁ፣ ስለባድመ እያሰበም ተወልዶ ያደገበትን ባድማ ቀምተው አባረሩት። ያቀናውን ቀየ፣ የለመደውን ባድመ ነጥቀው ስለ ባድመ እንዲያስብ አደረጉት። መዳፉን ቅንድቡ ላይ አድርጎ ሩቅ ያለውን ባድመን ሲያይ የቆመበትን ባድማውን ዘረፉት፣ ሀብት ንብረቱን ዘርፈው ባድመን ለማስመለስ የሞተው ልጁ ወደሄደበት ቀየ አሸሹ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ባድማ ተራቁጦ፣ ባድመን መሰል ድንጋያማ ቦታዎች እንደምናያቸው ሆኑ!

~ የኢትዮጵያ ሕዝብ የባድመን ያህል የተሞኘበት ጉዳይ ያለ አይመስለኝም። ባድመ ከአራጁ ጋር አብሮ የተሰለፈበት ጦርነት ነው።

~ ጋምቤላ ላይ አምርተው ለውጭ ሀገር የሚሸጡት 75 በመቶ የትህነግ ባለሀብቶች በሆኑበት ተወልዶ ካደገበት ጋምቤማ ተዘርፎና ተገርፎ የሚባረር ህዝብ ባድመ ምኑ ነው? ሀገርህ አይደለም ተብሎ ከቤንሸንጉል ሀብት ንብረቱን ብቻ ሳይሆን ህይወቱን እያጣ ያለ ሕዝብ ባድመ ምኑ ነው? ወልቃይት ላይ አማርኛ ትንፍሽ ማለት አትችልም እየተባለ የሚገረፍ ሕዝብ ትህነግና ሻዕቢያ የሚዋሰኑት አለት ምኑ ነው? ኦሮሚያ ውስጥ መኖር አትችልም እየተባለ የሚፈናቀል ሕዝብ፣ ባድመ ላይ ወጣቱን ከፊታቸው አድርገው ያስፈጁት ጀኔራሎች የሚፈነጩበት ሶማሊ ክልል የአንተ ሀገር አይደለም ተብሎ የተፈናቀለ ሕዝብ የሻዕቢያና የትህነግ ወሰን ምኑ ነው? ከባድማው፣ ከቀየው ለመኖር ዋስትና ያላገኘ ሕዝብ፣ ባድማውን ጥሎ ባድመ የዘመረው መጠየሚያ መሆኑን በአይኑ ያየ ሕዝብ በድመ ምኑ ነው? ባድመ ዘምቶና ቆስሎ፣ ወንድሙ ሞቶበት ያሰበውን አለማግኘቱ አልበቃ ብሎ ከባድማው ተፍኖ መኖርያውን ጠባብና አሰቃቂ እስር እንዲሆን የተደረገ ወጣት ያ ፈረፈር ሄደ መጣ ምን ይፈይድለታል? ባድማው ያልተከበረለት ሕዝብ፣ ለም ባድማውን በገዥዎቹ የተነጠቀ ሕዝብ ድንጋያማው ባድመ ምን ይሰራለታል?

1 COMMENT

  1. When peace prevails between the two people , especially Eritrea and Tigray, you start to cry like a baby baboon. Are you expecting the two people to be in conflict for ever and then to take power as usual when they become week Mr. loser!!! As the Ethiopian government has announced its unconditional accept of the Algiers agreement, and its unconditional implementation, I would like to congratulate the people of Eritrea and Ethiopia (Tigrayans) on this Historic day ! The Ethiopian government should start implementing its decision immediately ! Once the Final and Binding Decision is implemented, the Eritrean government should do its part and work for peace in Ethiopia.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.