የኢህአደግ  ስራ አስፈጻሚ  የኤርትራ የአልርጀርስ  የኮሚሽኑ ውሳኔ  እፈጽማለሁ ማለታቸው (አስገደ ገብረስላሴ)

ከ29 /09 /2010 ዓ  ም

ኣስገደ ገብረስላሴ

የኢህአደግ   ስራ አስፈጻሚ  የኤርትራ የአልርጀርስ  የኮሚሽኑ ውሳኔ  እፈጽማለሁ ከማለታቸው ለኢትዮጱያ ህዝቦች   አስተያየት ቢሰበስቡ ነሮው ከሀገራችን ሊሂቃን ገንቢ  ሀሳብ ያገኙ ነበር ። አሁን የወሰናችሁት  ወሳኔ ትልቅ ታሪካዊ የክዳት ስህተት እንደፈጸማችሁ ደግሞ ከወዲሁ  ከህዝቡ እያገኛችሁት ያላችሁት ግብረ መልስ እየተመለከታችሁት ያላችሁት ይመስለኛል ።

ደክቶር አብይ ይህ  የኃላ እሳት (Bak fayer) የሚፈጥር  የውሳነ አጀንዳ ይዘህ  ከመቀረብህ አስቀድመህ የህዝብ የልብ ትርታ የሚለኩ አስተያዬት ብትሰበስብ ኖሮ ፣ይህ በህዝብ ቤት ለቤት ገብቶ  ያለው የእሳት ቃጠሎ ፈጥሮ ያለው ሁኔታ በቀላሉ ትቆጣጠረው ነበር ።አሁን ግን ደጋፊህ ከአጅህ እያመለጥህ ነው ። ይህ ተግባር ደግሞ ከመለስና ጓዶቹ የወረስከው  ይመስላል ።  የመለስና ጓዶቹ ውድቀት የነበረው የመላው ህዝባችን በተለይ የሊሂቃን አስተያየት አለመቀበልና መናናቅ ነው ።
ሌላው ይህ ወሳነ  ከማስወሰንክ   በፊት ከሱኡዲ  ጉብኝት ተያይዞ በአረብ  ኢማራት አሁን ሎሌ ልትሆንላቸው ከሚፈልጉ የአለማችን ፈላጭ ቆራጭ  አካላት  ጋር ሌሎች ሰዎች  አግኝተውህ  መመሪያ እንደሰጡህም አስቀድመው  እያፈተለኩ   እየተናፈሱ ሰንብተዋል በመሆኑ  ይህ እርምጃ መውሰድህ  በግብታውነት ተነድተህ   ለኢትዮጱያ ለህዝብ  መክዳት  የነበረህን ተስፋ አጨልሞታል ። በእኔ እምነት ህዝብ  ህዝቦች የቀይባህር ድርሻቸው ሊያገኙ ፣የሀገራችን የኢኮኖሚ የጸጥታና የድህንነታቸው  መብታቸው ሊጠበቅላቸው   ካንተ የሚጠብቁት  ነገር ነበር ።በአንጻሩ ይህ አስደንጋጭ ውሳነ መስማታቸው አች አገር ቡቁ መሪ ለማግኜት  ያልታደለች መሆናን ያሳያል በማለት ተስፋ ቆርጠዋል  ። እኔም አንተ ባሳያሀቸው  ስትሞክራቸው የሰነበትክ  የለውጥ እርምጃዎች ከሚደግፉ አንድ ነበርኩ ። ግን ይሁን ያገር ጉዳይ ነውና ይህ ሀሳብ እስከአልቀየራችሁትተቃውሞዬ ቀጣይ ነው።

ከላይ የተጠቀሰ የህዝብ ፍላጎት ካላሟላቹ እና ውሳኒያቹ ከማስፈጸማችሁ በፊት ቆም ብላችሁ አስባችሁ የውሳኒያችሁ ማስተካከያ እርምጃ ካለወሰዳችሁ  ማህበረሰባችን  መውሰድ የሚገባቸው እርምጃ ጊዜ ሳይፈጁ አስፈላጊ የሚሉት እርመጃ መስራት ይገባቸዋል  ይህ ፣
1** የሀገራችን ሚስቴሮች ምክርቤት ፣ የህዝብ ተወካዮች ያገራችን ፓርላማ  ካሁን በፊት የምተወስናቸው የነበርክ  በጠ /ምኒስቴሮችና በአፈጉባኤዎች  የሚቀርብል አጀንዳ አጅህ አውጣ ስትባል እጅህ እያወጣህ ቡዙ ስህተት ፈጽምሀል  ።አሁን ያለፈ አልፈዋል  የዚህ የአብይ ቡዱን ግብታዊ ውሳነ ልትቃወም የህዝበ ተወካይነት  በቆራጥነት ስራ ።ይህ የኢህአደግ ስራ አስፈጻሚ በግብታውነት የተወሰነ ማጸደቅ የለበትም ።ይህ ጥቁር ታሪክ በችላ ተመልክታች የምታልፉት ከሆነ  ታሪካችሁ  ለዘልአለም ብልሽው ይሆናል ።
2** የሀገራችን የጸጥታ ሀይሎች በተለይ በየግንባሩ ያላችሁት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ይህ አገር እና ህዝብ የከዳ  ውሳነ  ሲመጣባችሁ በቀጥታ ሊታያችሁ የሚገባ በዬ  ምሽጋችሁ የምትመለከቱት የጓዳችሁ መቃብል በማስታወስ የነዚህ አገርና ህዝብ ከሀዲዎች ትእዛዝ አትቀበሉ ። ይህ ደግሞ ከሞቶ መሪ እስከ እዝ ሀላፊዎች ይመለከታል ።
3**ሌላ ማህበረሰብ በተለይ ሙሁራን ጊዜ ሳትፈጁ የተቃውሞ ድምጻችሁ ብትገፉበት ሙሁራዊ ግዳጃችሁ ብትወጡ ለህዝባችን ጥቅምና ሞራል ይጠቅማል ።
4** የድሮ ታጋዮች ነበር ፣ጥሮቶኞች ፣ወ ዘ ተ ለዚሁ የተሳሳተ ውሳነ በመኮነን ድምጻችሁ ታሰሙ ዘንዳ ጥሬን አቀርባለሁ ።
5 **የከበርከው  የኢትዮጱያ ህዝብ በተለይ በቅርበት የምትገኜው የትግራይ የአፋር ህዝብ ይህ የተባላሸ ውሳኔ በመኮነን የተቃውሞ ድምጽ ማሰማት  ብቻ ሳይሆን ነፍጥህ ይዘህ ትጥቅህን አስጥመህ ተዘጋጅ ።
6** የሀገራችን ወጣቶች ወደ አደባባይ ወጥታችሁ የተቃውሞ ድምጻችሁን አሰሙ ።
7** በዲያስፖራ ያላችሁ ወገኖች በመሉ ይህ የደኩተር አብይ ቡዱን ግብታዊ ውሳኔ በመቃወም አደባባይ ውጡ 8 በሀገር ውስጥ እና በውጭ የምትገኙ የተፎካካሪ ፓርት መሪዎች ፣አባላት  ደጋፊዎች ይህን ከዳተኛ ውሳኔ በመቃወም ተቃውሞ ማሰማት ፣በስተጀርባቹ ያለው አባል ደጋፊያችሁ በማሰለፍ  የተቃውሞ  እንቅስቃሴ ሙሩት ።
9 በሀገር ውስጥና በዲያስፖራው የምትገኙ ሚዲያዎች የህዘብን የተቃውሞ ድምጽ በማስተጋባት በሙያችሁ የዜግነታችሁ  ሚናችሁን ተጫወቱ ።
10** የሀገራችን ነጋዴዎች ፣ባለሀብቶች  የሀገራች ህዘቦች የባህር በራችን ባለቤትነታችን መብት ተረጋግጦ አገራች ትልቅ የገበያ ቀጠና ትሆን ዘንዳ ከደኩተር አብይ የለውጥ ምልክት እያዬን ነበር ።ይህ ግን ደኩተሩ ረጅም ሳይራመድ በመበርከክ በኢትዮጱያ ሉአላሏውነት ላይ መጠፎ ታሪካዊ ስህተት እየፈጸመ ይታያል ፣ይህም ደኩተር አብይ መሰሎቹን የኢህአደግ ስራ አስፈጻሚ ቡዱን ሰብሰቦ ለሀገራችንና ህዝባችን የሚጎዳን ውሳኔ ወስኗል አሰወስናል ፣አሁንም  የፓርቲው ቡዱን ወሳኔ እንዲመረቅለት ለምኒስቲሮች ምክርቤት (ካቤኔ ) ለፓርላማ ህዝብ ተወካየች በቅርቡ  አስመርቆ ወደ ተግባር ለማውረድ ፣የጌቶቹ ጉዳይ ለማስፈጸም ሊሯሯጥ ከአዋጁ ማስተጋበቱ ከወዲሁ እያዬን ነው ። በመሆኑም የንግዱ ማህበረሰብና የባለሀብቶች ተጽእኖ የማሳደር ሚናችሁ ትልቅ ስለሆነ ለዚህ  ቡዱን የወደቀ ውሳኔ ለመቃወም አደባባይ ወጥተን ደምጻችን እናሰማ ።
ይቀጥላል
ከአስገደ ገብረስላሴ ፣
መቀለ
30  / 09 ./2010

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.