ዜጎች ከዓለም አቀፍ የሽብር ድርጅቶች የሚጠብቅ የፀረ ሽብር ህግ ያስፈልጋል – ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ ዜጎቿን ከዓለም አቀፍ የሽብር ድርጅቶች የሚጠብቅ የፀረ ሽብር ህግ እንደሚያስፈልጋት የተለያዩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስታወቁ።

ዜጎች ከዓለም አቀፍ የሽብር ድርጅቶች የሚጠብቅ የፀረ ሽብር ህግ ያስፈልጋል – ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች 1ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የመኢአድ፣ የኢዴፓ እና የገዳ ስርዓት አራማጅ ፓርቲ መሪዎች በስራ ላይ ያለው የፀረ ሽብር ህግ በመርህም ሆነ በአፈጻጸም በርካታ ክፍተቶች ያሉበት ነው ብለዋል።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ እና ተፎካካሪ ፓርቲዎች በፀረ ሽብር ህጉ ዙርያ በመምከር ላይ ይገኛል፡፡

በውይይቱ ላይም የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህግ ምሁር የሆኑት ዶክተር ወንደሰን ደምሴ በመድረኩ ላይ በህጉ ይዘት ዙሪያ ጥናታቸውን አቅርበዋል፡፡

የህግ ምሁሩ የኢትዮጵያ የጸረ ሽብር ህግ ስለሽብር ጥልቅ ትርጉም የለውም የትርጓሜ ክፍተትም ይታይበታል ብለዋል፡፡

በጥቅሉ በመድረኩ የተለያዩ የጸረ ሽብር ህጉ አንቀጾች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በዚህም አንቀጽ ሦስት ላይ የእንግሊዘኛው ትርጉም አሻሚና ለሌላ ትርጉም ይጋብዛል ተብሏል፡፡

ማቀድ፣ ማሴር፣ ማነሳሳት እና ሌሎቹንም ወንጀል አድርጎ የሚደነግገው አንቀጽ አራትም በውይይቱ የአዋጁ ክፍተት ሆነው ከተነሱት መካከል ይገኛበታል፡፡

የተጠርጣሪዎችን መረጃ በተመለከተ የሚዳስሰው አንቀጽ 14 ለብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የተጠርጣሪዎችን መረጃ የመጥለፍ ህጋዊ መብት የሰጠ ሲሆን ይህም የፍትህ ስርዓቱን የሚቃረን መሆኑ በመድረኩ ተነስቷል፡፡

እንዲሁም በጸረ ሽብር ህጉ አንቀጽ 19 የተጠቀሰው ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ዜጎች እንዲያዙ የሚደነግገው አንቀጽም ክፍተት እንዳለበት ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም በጸረ ሽብር ህጉ የሰሚ ሰሚ ማስረጃዎች ተቀባይነት ማግኘታቸው የአዋጁ ክፍተቶች ናቸው ተብለው ከተጠቀሱት መካከል ናቸው፡፡

መድረኩ በህጉ ህልውና ዙሪያ የተያዩ አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን አንዳንዶች በአዲስ ህግ መተካት እንዳለበት ሲያነሱ ሌሎች ደግሞ መሻሻል ያለባቸው አንቀጾች ተስተካክለው መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡

 

በፋሲካው ታደሰ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.