የኦሮሞ ህዝብ ከወያኔ በላይ ኦነግ እንደ ገደለው ያወቀ እለት ያ…ኔ ኦነግን ምን ይውጠው ይሆን?

እጅግ ብትጃጃም!! ጦረታ ባትወጣም!! አንቱ እንኳን አልልህም!! ታጋይም አልልህም!! ምክኒያቱም የነጻነት ቁማርተኛ ነህና።ይህን ሃቅ ከአንተ ግድያ በተዓምር ተርፈው የመጡ ታጋዮች በሚገባ ነግረውኛልና። ብቻ ግን በእየ በርሃው ያስረሸንካቸው የኦሮሞ ተወላጆች ደም ማእበል ሆኖ ይብላህ!! አጥንታቸው እሾክ ሆኖ ይውጋህ።ለዳውድ ኢብሳ ነው።

አንድ የአሪሲ ልጅ ከኦነግ አምልጦ አርበኞች ግንቦት 7ን የተቀላቀለ ታጋይ የኦነግን ጭካኔ እንዲህ ሲል ነበር ቁጭት እያንገበገበው ያጫወተኝ፦

“እኔን የሚገርመኝ ኦሮሞን የሚታደገው ማነው? ወያኔ ይገድለዋል !! ነጻ አወጣህ አለሁ ብሎ በስሙ የተደራጀው ኦነግ ይገድለዋል!! ያሠቃየዋል!! ያሳጭደዋል!! ያሳርመዋል!! ያስከስለዋል!! በአጠቃላይ እንደ ባሪያ ቀጥቅጦ ይገዛዋል” ብሎ የተረሸኑ ጓደኞቹን እያሠበ ነው መሰል ቁልቁል አቀረቀረ።

ታጋዩ ቀጠለ “የኦሮሞ ህዝብ ከወያኔ በላይ ኦነግ እንደ ገደለው ያወቀ እለት ያ…ኔ ኦነግን ምን ይውጠው ይሆን?”

እናም አቶ ዳውድ ኢብሳ

ለአንተ እና ለቡድንህ የሚመጥነው ገዳይ!! አስገዳይ!! ጭራቅ!! ደም መጣጭ…የሚሉት ቃላቶች እንጂ አንተ እንደምታቅራራው “ነጻ አውጭ!! አገር ጠባቂ!!” አይደለህም!! “ጅብ በማያውቁት አገር ሂዶ ቆርበት አንጥፉልኝ” ቢይል ማንም ይሰማዋል!!

አቶ ዳውድ ኢብሳና መንጋ ቡድኑ ልብ ሊለው የሚገባው ከተጨማለቀበት ደም ሳይጸዳ ወደ ምርጧ አገራችን የገባሃው በአንድ ክንድህ መሳሪያ አንግተህ በሌላኛው እጅህ ደግሞ ብዕር ጨብጠህ እያታለልክ ልታሸብረን አለመሆኑን አስምርበት!! ታጣቂዎችህ በንጹሃን ላይ እርምጃ ሲወስዱ “ኦነግን” አይወክሉም ትለን አለህ።በእርግጥ የመንግስት ሰዎችም ወንጀልህን እየሸፈኑልህ ይመስላል?

የፌድራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ዘይኑ ጀማል በመግለጫቸው ያሳዩትም ይሄውን ።አቶ ዳውድ ኢብሳ ትጥቃችን አልፈታነም እያለ ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል ግን “ማንነታቸው ያለታወቁ የታጠቁ ሃይሎች” እያሉ ይሸፋፍኗቸዋል።ኮሚሽነር ዘይኑ ማንነታቸውን ማጣራት የፖሊስ ስራ መሆኑን ጭራሽ የረሱት ይመስል?

በእኔ እምነት ግን ድብብቆሹ የትም አያደርሰነም።ኦነግ ከእነ ወንጀሉ ወደ አገር የገባው ታጥቆ እሱ እንደሚለው አገር ሊጠብቅ ሳይሆን መሳሪያውን ጥሎ በጠቅላይ ሚኒስተሩ አገላለጽ “ተፎካካሪ” ሊሆን ነው።ይህ ካልሆነ ኦነግ እሱም የጃጃ ቢሆንም፣ከብጤውና ከአሮየው ስርዓት ሃይላት ጋር ሆኖ አገር ማሸበሩ ይቀጥላል።እንዲያውም ህግና ሥር ዓት ካለ በወንጀል ሊጠየቅ ይገባልየሚል እምነት አለኝ። ደግሞም “መደመር” ለሠላምና ለአንድነት እንጂ አገርን ለማናጋት አይሆንም።አናጊዎች ይቀነሱልን።በእነሱ ምክንያት ነብሠጡሩዎች፣ህጻናት፣ሽማግሌዎች…መገደል፣መፈናቀል…የለባቸውም!!

ሃቁ ኦነግ እንኳን ዛሬ ትላንት በዚያ…ድቅድቅ ጨለማ ለኦሮሞ ህዝብ የፈየደው ነገር የለም። ግማሽ ምእተ-አመት መሳሪያ አንግቦ ለነጻነት ታገለኩ ቢልም የነጻነቱ ቋት አልሞላለት ብሎ ኳትኗል።

ይልቁንስ በፕሮፖጋንዳው ተሰልበውና እውነት መስሏቸው ህይወታቸውን ገብረው ለህዝባቸው የነፃነትን ጮራ ለመፈንጠቅ የተቀላቀሉትን ታጋዮች ቅርጥፍ አደርጎ በልቷል።እነ ጀነራል ከማል ገልቹ፣ እነ ኮሎነል አበበ ገረሱ ሻቢያ ባይደርስላቸው ኖሮ እንደ ወገኖቻቸው በኤርትራ በርሃ ተረሽነው፣በአሸዋ ተዳፍነው ቀርተው እንደነበር እራሱ ኮሎኔል አበበ ገረሱ አጫውቶኛል። እናም ትላንትም ገዳይ ነበራችሁ።ለታጋዮቻችሁ እንኳን ምህረት የሌላችሁ ጨካኝ መሆናችሁን ጠንቅቀን እናውቃለን።

አሁን ጦረታ የማያውቀውንና ግትሩን ዳውድ ኢብሳን ልተወውና ወደለውጥ ሃይሉ ፊቴን አዙሬ ጥያቄ ልሰንዝር፦ በተለይ ለአቶ ለማ መገርሳ፣ ለዶ/ር አቢይ

1. ኦነግ ወደ አገር የገባው ከእነ ትጥቁ ነውን?
2.የኦሮሚያ ክልልን ማነው የሚያስተዳድረው? ኦሮምያ ላይ ከኦነግ ጋር የጋራ መንግስት ተመስርቷልን?
3.አቶ ዳውድ ትጥቅ አንፈታም ያለው ማንን ተማምኖ ነው?

ዓምደማሪያም ዕዝራ

1 COMMENT

  1. You are not Oromo, never cared for Oromos that used to be killed and maimed for generations now, never raised your voice or pen when 100 thousands were slaughtered by TPLF, evicted in millions, etc etc. Now you want to warn us Oromos against the OLF?!!! Do you think all are more dumb than you?? Or are you having day time nightmare ?? All that happens in Oromia. Why are you so terrified??

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.