ማመልከቻ ለፅልመት ሀይሎች! ….በቲም ለማ , አቢይ, ታከለ ኡማ ዘመቻ ለከፈታችሁ የፅልመት ሀይሎችና አዳናቂዎች – በያላችሁበት

አባዊርቱ
በተለይ ለተአሚነት ይበቃ ዘንድ ሽገርን የመሰለ ኢትዮጵያዊ ሚድያን ቁንፅል ይዛችሁ ዘጭ ዘጭ ለምትሉ የፖለቲካ ሱቅበደረቴዎች : እድሜ ያላስተማራችሁ ወይም ትምህርት ያልገራችሁ ምድረሱቅበደረቴዎች ምንድነው የምትፈልጉት ከኢትዮጵያ? ሚሊዮኖች ወጣቶች የስራ እድል ባጡበት አገር ስራ ፍለጋ ነው ወይስ ለናንተ ኢጎ ሲባል ባተሌ የሆኑት ወጣት መሪዎች እነለማና ታከለ መብጠልጠል አለባቸው? የለየላቸው  የፅልመት ሀይሎችስ ብዙ ቀርቶባቸው ነው የሚጮሁት:: የጀሌዎችና የናንተው መወራጨት ነው በጅጉ ያሳሳሰበኝ:: የአቶ ዳውድ ትእቢት ይደንቃል:: የሌሎችም መወራጨት እጅግ ልብ ይሰብራል:: ትንሽ ህዝቡ ይታዘበናል አይባልም? ጉድፈላባችሁ እንግዲህ:: ከግራ ኦዴፓ ከቀኝ አዴፓ ከመሀል አውላላ ሜዳ:: ከመሀል እናንተ እርቃናችሁን ቀራችሁሳ:: ምንስ ታረጉ:: የታሰበውን ቁማር ሁሉ እነ ቆፍጣናው ለማ በፎርፌ በሉባችሁ:: እንግዲህ መቀበል የግድ ይላል:: የኢትዮጵያ አምላክ ሲፈርድ አያዳላም አሉ:: ኦሮሞና አማራ እሳትና ጭድ መሆናቸው ቀረና ጋራና ሸንተረር ሆኑባችሁ:: እንግዲህ እንዴት ትወጡት ይህን አቀበት? ኦነግን የመሰለ አገራዊ ይቅርና ክልላዊ ራእይ የሌለው ጉድ  ያ ሁሉ ክብር ተሰጥቶት በአጀብ እና በሆታ እንዳልገባ ዛሬን ላይ ቆሞ እንዲህ አይነት ለፅልመት ሀይሎች ጆሮ ክላሲካል ሙዚቃ ሲያሰማ ማየቴና ማዳመጤ እጅጉን አሳዝኖኛል:: ይህ ሁሉ መቼስ በግዳይ እንዳልገባ ልቦናው ቢያውቅም የገባእለት የወጣው እልፍ ወጣት ልቡን እንዳሸፈቱትና በትእቢት እንደወጠሩት መገመት አያዳግትም:: ቄሮ እንዲያ አምሮበት በፍቅር እነዳውድን እንዲቀበል የነቲም ለማና አቢይ እጅ እንደሌለው አይነት መቁጠሩ እጅግ ያሳፍራል:: የዶር ብርሃኑም አላስፈላጊ ስላቅ ብሎም የወረደ መወረፍ ለግንቦቴዎች ምንም ያተረፈላቸው የለም::  ከትዝብት በቀር:: የአዴፓና ኦዴፓ መጠንከር ለታደለውና አገራዊ ራእይ ላለው የየብሄር  ፖለቲካ  ነባራዊ ሀቁን ዋጥ አርጎ የዜግነት ፓለቲካውን በአግባቡ ማስተናገድ ሲቻል የክረምት ላይ የጉልት ገብያ  ቅርምት ይመስል ገብያተኛን ለመቀራመት አስነዋሪ ስራዎችን መስራት ያሳፍራል:: አይታወቅ ከመሰላችሁ ተሳስታችሁዋል:: እየታዘብን ነው::
አንዳንድ የአይምሮ ደሀዎች  ደሞ ታከለ ኡማ ለደሀ ወገኖቻችን ቤት ማደሉ ያውም መረጃው በህዝብ እየታየ ለኦሮሞ ወገኖቹ ካስባለ እሰየው:: ምነው አርከበ እንዲያ የኦሮሞ ልጆችን ሲያሳድድና ገበሬዎችን ሲያፈናቅል ትንፍሽ አላላችሁ? ማፈሪያ ሁላ!! እየመረራችሁም ቢሆን እንቆቆውን ተጋቱት:: ምን ታመጣላችሁ እንግዲህ ከተራ መረጃ ከራቀው አሉባልታ በቀር??! አንድ ታከለ ብዙ እየለወጠ ነው በጥቂት ወራት እናንተ 27 አመታት የቦጠቦጣችሁትን ከተማ:: እንግዲህ ለውጡ ላይቀለበስ እየተመመ ነው:: ነገሩ ጅቦቹ ይጮሀሉ የነ አባጆቢር ፈረሶች እየጋለቡ ነው ወደፊት:: የናንተው ግመሎች የነሱን ሰንጋፈረሶች አይመጥኑም ብዬ እሰጋለሁ:: አንዳንዶችማ ፋናን ዋቢ እያረጉ ሀሜቱን ይዘውታል:: የ “ሽገርንም ” ፅዱ ውሀ  ከፀበል እየቀላቀሉ  ያጠጡን የሚመስላቸው ጅሎች ፀበልን ከጨቀየ ኩሬውሀ መለያ መነፅር እንዳደረግን  እንኩዋ አለማወቃቸው ያስደምመናል:: እንዲህ ነው ነገሩ: ተረዱት:
ሀ) የነአቢይ ፈረሰኞች  ተራማጅ ቲም ወደፊት እንጂ እንደ ፅልመት ግመሎች ወደሁዋላ  አይሸናም!
ለ) በወጣቶቹ ታከለና ዳግማዊት ቲም የተጀመረው የሸገር ላይ መልካም ስራ ይቀጥላል:: አትሊስት እስከምርጫው
ሐ) የኦነግ ጎማ ዳግም ላይነሳ እስከወዲያኛው ተንፍሷል:: አላስፈላጊ አቴንሺን ፍለጋው ግን ፈገግ  ያረጋል
መ) ግንቦቴዋች ግራ ሳትጋቡ በሰላም የተሰጣችሁን እድል ተጠቀሙ:: ለሀሳብ ፍልሰትና ለአዲሲቱዋ ኢትዮጵያ ብዙ ይጠበቅባችሁዋልና:: ሳስበው ለመምረጥና መመረጥ ግን ገና ናችሁ
ለመንግስት ጥብቅ ማሳሰቢያ!
የውጭ ዜግነት ወስደው ከውጭ ለተመለሱት ተፎካካሪዎች የ 5 አመት የዜግነት ነዋሪነት ሳያገኙ ለምርጫ ይሁን ለቅርጫ ብቃት ስለሌላቸው ይህን ባስቸኩዋይ ህግ አርቁባቸው:: በአሜሪካም ቢሆን ዜጋ ካልተሆነ ይህ አይፈቀድም:: አለመታደል ሆኖ አልበለፀግንም እንጂ ስርአት አለን መቼስ:: ምናልባት ምርጫ አጥተው ተገፍተው የሄዱት እየተለዩ ዜግነት ይሰጣቸው ለዚያውም የድሮውን አሽቀንጥረው ከጣሉ ከተረጋገጠ በሁዋላ::  በኢትዮጵያ ቢላዋና በፈረንጅ ሴንጢ እኩል ድፎዳቦ  አይቆረስምና::  ቢላው ለድፎ ሴንጢው ለኬኩ ነውና:: ወይ ከድፎው ወይ ከኬኩ:: ይህው ነው:: ሌላውና ሳልጠቅስ የማላልፈው የዶር አቢይ አደባባይ ያውም ኮለኔል ሆነው ተራ ጎበዝአለቃ ይመስል ፑሻፕ ለእይታም ይሁን ለፍጆታ አልተመቸኝም:: በጭራሽ! ይህ ወታደራዊ ዲሲፕሊን ከባድ ጥሰት ነው:: የተደረገው ስህተት ሳያንስ የሳቸው የጋንታ መሪ ይመስል የተቃቅፎ ፎቶ ይሁንየአደባባይ ፑሻፕ በጭራሽ ላይደገም በቤተመንግስት የሆነውን የፕሮቶኮል ክፍል መዋጥ ሲገባውና በደፈናው አሳማኝ መረጃ ለህዝብ መቅረብ ሲኖርበት ስህተትን በስህተት አይመለስም:: መንግስታችን እንደመሪዎቻችን ጎልማሳ ስለሆነ በድንጋጤ አልፈነዋል:: የነዛ ወታደሮች መሪዎቻቸው ግን በደንብ ይፈተሹ:: አቢይም ከገለፃው ይቆጠቡ:: እምብዛም ቅንነት ለበግም አልበጀ እንዲሉ::
ሰላም!
አባዊርቱ ነኝ: አባቦራም (እስከፈረሴ)

1 COMMENT

  1. ማንን እየተቆጡ እንደሆነ አላወኩም :: ተገቢ ሆኖ ይሆናል የሰጠው::
    ነገር ግን ቤት ቦታ ለምን ለኦሮሞ ተስጠ ሳይሆን የሚያስስበኝ መሪ በቀየርን ቁጥር በመወገን አድልዎ መቼ ነው የምናቆመው ነው:: ትግሬ በየኤርፓርቱ ማየት አንገሽግሾኝ 27 ዓመት ሙሉ አሁን ደግሞ ኦሮሞ በማየት ልንገሸገሽ እየተዘጋጀሁ ነው:: የጉራጌ ሊስትሮን በወላሞ/ከንባታ ከተካን ሩቅ አይደለም በደሳለኝ ግዜ::
    ስንኮንን የነበረውን ስርአት መልሰን እምንደግመው ከሆነ ምን ዋጋ አለው? በተለይ በኦሮሞው መሪያችን ዐብይ ብዙ ተስፋና ምኞት አለን:: ዐብይ የወለድ ቅናሽም ሳይስጠው አይቀርም ከአረቦቹጋ አብሽር ብሎ እና የቡርካ ለባሹን ቁጥርም ጨምሯል:: ህዝቡ በፍቅር ቢደነዝዝ እንአድንዴ ህዝብ ምን ይለኛል ቢልም ጥሩ ነው:: እግረ መንገዱን የማያስቅ ቀልድ ፑሻፕ ባይሞክር ጥሩ ነው የወያኔ ኮርኔል እንደነበር ባያስታውስን::

    We need to cut the ethnic based an employment vicious cycle!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.