ባል እንዳጋጣሚ ጎግል ማፕን ሲያስስ ሚስቱን ከሌላ ወንድ ጋር በማየቱ ሊፈታት በቅቷል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 02፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጎግል ማፕ የመልካምድር አቀማመጥን በምስል የሚያሳይ የቴክኖሎጂ ውጤት ሲሆን፥ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል የሳተላይት ምስሎችን እንዲሁም “ስትሪት ቪው” ወይንም ሰዎች የፈለጉትን ቦታ ጥርት ባለ መልኩ እንዲያሳያቸው በሚጠይቁበት ወቅት የጠየቁትን ምስል እንደሚያቀርብ ይታወቃል፡፡

በፔሩ የሚገኝ አንድ ግለሰብም ወደ በይነ መረቡ በማቅናት የተለያዩ አካባቢዎችን ምስል በሚቃኝበት ወቅት በስትሪት ቪው የባለቤቱን የሚመስል ምስል ይመለከታል፡፡

በኃላም ጥርጣሬውን የሚያጎላ አንድ ነገር ይመለከታል፤ እርሱም የጸጉሯ አሰራር ከሚስቱ ጋር ተመሳሳይ መሆኑ ነው፡፡

በመጨረሻም ልብሷን ጨምሮ የተለያዩ ነገሮችን ከተመለከተ በኃላ ሚስቱ መሆኗን ደረሰበት ሆኖም ጉልበቷ ላይ ጭንቅላቱን አሳርፎ ከንፈሩን የምትስመው ግለሰብ ሌላ ሰው ሆኖ አገኘው፡፡

በዚህ ጊዜ ታዲያ ሚስቱ የትዳር ቃልኪዳኗን እንዳልጠበቀች አወቀ፤ የተመለከተውንም ፎቶግራፍ ለማህበራዊ ሚዲያ አጋራ፡፡

ይህንንም ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶችን ተቀብሏል፤ አንዳንዶቹ እርሱን የሚያጽናኑ ሲሆኑ፥ ሌሎቹ ደግሞ ባለቤቱን የሚዘልፉ ነበሩ፡፡

ጎግል ፎቶውን ያነሳው ከአምስት ዓመታት በፊት ቢሆንም የተደበቀው ጉድ ግን ጊዜውን ጠብቆ ለመውጣት በቅቷል፡፡

ባልም ምንም እንኳ ከአምስት ዓመታት በፊት የተፈጸመ ድርጊት ዘግይቶ የተመለከተው ቢሆንም ሁኔታው ተቀባይነት የለውም በማለት ሚስቱን ፈቷል፡፡

በጎግል ስትሪት ቪው ምስሎች ብዙ ጊዜ ተመሳሳይ ድርጊቶችን ሲፈጽሙ የተያዙ በርካቶች መሆናቸውን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

ምንጭ፦ኦዲቲይ

በአብርሃም ፈቀደ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.